Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 21, 2014

በሐድያና ስልጢ ሀገረ ስብከት ጎረጎራ ወረዳ ውቅሮ ፋለታ ቀበሌ የደብረ ምጥማቅ ቡሻና በዓታ ለማርያም ገዳም ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. የከተራ ዕለት መነሻው ባልተወቀ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ተቃጠለ

ሰበር ዜና ! በሐድያና ስልጢ ሀገረ ስብከት ጎረጎራ ወረዳ ውቅሮ ፋለታ ቀበሌ የደብረ ምጥማቅ ቡሻና በዓታ ለማርያም ገዳም ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. የከተራ ዕለት መነሻው ባልተወቀ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ቢኒያም መንቻሮ ገለጹ፡፡  11 እንግዲህ ጨለማን ተገን አድርጎ ለመጣ ጠላት እኛ ምን እንላለን? ሁሉን አዋቂው ጌታ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ ከማለት በስተቀር።ነገርግን በዚህም አለ በዚያ የወያኔ የስራ ፍሬ ውጤት ለመሆኑ ጥርጥር የለንም።ግድ የለም የጊዜ ጉዳይ ነው ሁሉም የዘራውን ያጭዳል። በእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ እንደማይጓደል እናምናለን።
11



 በሐድያና ስልጢ ሀገረ ስብከት ጎረጎራ ወረዳ ውቅሮ ፋለታ ቀበሌ የደብረ ምጥማቅ ቡሻና በዓታ ለማርያም ገዳም ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. የከተራ ዕለት መነሻው ባልተወቀ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ቢኒያም መንቻሮ ገለጹ፡፡ ሥራ አስኪያጁ በሰጡን መረጃም የከተራ ዕለት የበዐታ ለማርያም ታቦት ወደ ጥምቀተ ባሕር ከወረደ በኋላ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ መቃጠሉን ገልጸው ቤተ ክርስቲያኑ ንዋያተ ቅዱሳቱን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ብለዋል፡፡ በካዝና ውሰጥ የነበረው የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽላት ካዝናው በእሳቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመለብለቡ ምክንያት መክፈት እንዳልተቻለና መቃጠልና አለመቃጠሉን እንዳልተረጋገጠ ያስታወቁት ሥራ አስኪያጁ፤ ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቅ የቃጠሎውን መንስኤ ለማጥራት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የቡሻና በዐታ ለማርያም ገዳም ከዚህ በፊት ሥዕለ አድኅኖ በዛፎች ላይ ታይቶበት በነበረ ቦታ መቃኞ ተሰርቶለት ሐምሌ 2001 ዓ.ም. ቅዳሴ ቤቱ እንደተከበረ ይታወቃል፡፡

Monday, January 20, 2014

“ነፃነታችንን መልሱልን!?” ከተመስገን ደሳለኝ


dd
የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ‹መዝገበ ቃላት› ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ ‹አራምደዋለሁ› ከሚለው ግራ-ዘመሙ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብያኔ አንፃር የሚተነተን በመሆኑ፣ የየትኛውም ተቋም ነፃ ሆኖ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ረዣዥም እጆቹን ደጋግሞ እየጫነ ሲጨፈልቅና ሲያስጨፈልቅ ለመኖሩ በርካታ ማሳዎችን ማቅረብ ይቻላል… ይሁንና ከብዙዎቹ መሀል ለጊዜው የእምነት ተቋማት የነፃነት ወሰን እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለውን ተጠየቅ በተለይም ከሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች (ክርስትና እና እስልምና) አንፃር ተራ በተራ ከፈተሽን በኋላ ተቋማቱን ከእንዲህ አይነቱ ወደ ቅርቃር ከሚገፋ ፈተና የሚታደጋቸውን ብቸኛ የመውጫ መንገድ ለማስታወስ እሞክራለሁ፡፡
‹‹እስልምናን መቆጣጠር››
ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ገዥው ፓርቲ እስልምናን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር እቅዱን ዳር ለማድረስ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ የአልማሰው ሥር እንዳልነበር ጥቂት የማይባሉ ምልክቶችን አይተናል፡፡ ለምሳሌነትም የቅርቡ በተለምዶ ‹‹የአወሊያ ንቅናቄ›› ተብሎ የሚጠቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ በቂ ይመስለኛል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ (ንቅናቄ) ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ የወጣው፣ መንግስት የእምነት ተቋሙን በማያፈናፍን መልኩ ለመቆጣጠር በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ፊት-አውራሪነት ያለአንዳች ይሉኝታ (የብዙሃኑን የእምነቱ
ተከታዮች ይሁንታ ሳያገኝ) ‹‹አህባሽ›› የተሰኘ አስተምህሮ በድፍረት ለመጫን ከሞከረባቸው ጊዜያት አንስቶ ባደረጋቸው ተከታታይ ጣልቃ-ገብነቶች ሳቢያ ነው ወደሚል ድምዳሜ ከሚያደርሱን ምክንያቶች ዋነኛው ሆኖ ይነሳል፡፡ ለመንደርደሪያነት ያህልም የተቃውሞውን ጅማሮ በአዲስ መስመር በጨረፍታ እንዳስሰው፡፡
…ለንቅናቄው መነሾ የሆነው በወቅቱ የመጅሊሱ የአመራር አባል የነበሩት ጀማል መሀመድ፣ ለእምነቱ ብቸኛ የሆነውን ሚሲዮናዊ አወሊያ ትምህርት ቤትን በተመለከተ ታሕሳስ 21 ቀን 2004 ዓ.ም ላይ የላኩት ደብዳቤ ነው፤ የደብዳቤው ጭብጥም በርካታ የመስጂድ ኢማሞች፣ መምህራን እና የአረብኛ ተማሪዎች መባረራቸውን የሚያረዳ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡
የመጅሊስ አመራርን ‹ፖለቲካዊ ክንድ› ፈርጣማነት በሚያሳብቅ መልኩ የተሰናዳው ይህ ደብዳቤ የቀሰቀሰው ቁጣ፣ ሕዝበ-ሙስሊሙ ለዓመታት አምቆት የነበረውን ብሶት ሊያፈነዳና በርካታ የመብት ጥያቄዎቹን እንዲያነሳ መግፍኤ ይሆናል ብሎ አስቀድሞ የገመተ ያለ አይመስለኝም፤ የሆነው ግን ይህ ነበር፡፡ የእምነት ነፃነት እንዲከበር ሶስት መሰረታዊ ጭብጦችን የያዙት ጥያቄዎችም፡- ‹‹የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንምና ወርደው አዲስ ምርጫ ይካሄድ››፣ ‹‹አህባሽን በምእመኑ ጫንቃ ላይ በግዴታ ለመጫን የሚደረገው ሙኩራ ይቁም›› እና ‹‹አወሊያ ከመጅሊስ ወጥቶ በገለልተኛ ቦርድ ይተዳደር›› በሚል ስር የሚጠቃለሉ ናቸው፡፡ የኋላ ኋላም በአገዛዙ ‹‹እስላማዊ መንግስት በሽብር ተግባር ለመመስረት›› ወደሚል ተምኔታዊ ውንጀላ የተቀየሩት እነዚሁ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡
በርግጥ ‹‹አህባሽ››ን ተከልሎ የመጣው መንግስታዊ ጫና ዋነኛ ዓላማው (ከአንዳንድ የምዕራብ ሀገራት ፍላጎት ባሻገር) አስተምህሮውን ተገን አድርጎ ምእመኑን እርስ በርስ በመከፋፈል፣ የተቋሙን ነፃነት በቀላሉ ለመጋፋት የሚያስችለውን መደላድል መፍጠር ነው፡፡ ይሁንና ስልቱ ምንም እንኳ ከሃሳቡ ተጋፊዎች አንጻር አነስተኛ ቢሆንም፣ መንገድ ጠራጊ ደጋፊዎች ሊያስገኝለት መቻሉን መካድ ግን መሬት ካለው እውነታ ጋር እንደ መላተም ይቆጠራል፤ ምክንያቱም የመጅሊሱ አመራር ሙሉ በሙሉ ከአገዛዙ ጎን በመቆም አጀንዳው ቅቡል እንደሆነ ለማስመሰል የማይናቅ አስተዋጽኦ አድርጓልና፡፡
ይህም ሆኖ አብዛኛው የእምነቱ ተከታይ በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ ተቃውሞ በተነሳበት እዛው አወሊያ ግቢ ተሰባስቦ፣ ከሰባት መቶ ሺህ በላይ የውክልና ፊርማ በማሰባሰብ፣ አስራ ሰባት አባላት ያሉት አንድ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አዋቅሮ ሲያበቃ ከላይ የተጠቀሰውን ሕገ-መንግስታዊ የመብት መከበር ጥያቄውን መልክ አስይዞ መታገሉ ብዙም አላዳገተውም፡፡ እነሆም በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ሕዝበ-ሙስሊሙን ከጎኑ በማሰለፍ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ እስከተከበረው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ድረስ በየመስጊዶቹ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለጥያቄዎቹ ሁነኛ መልስ ይሰጠው ዘንድ ከፍተኛ የተቃውሞ ትግል አድርጓል፤ በተጨማሪም የኮሚቴው አባላት ከተመረጡ ከስምንት ወራት በኋላ (ሐምሌ 10/2004 ዓ.ም) በግፍ መታሰራቸው ሳያንበረክከውና ሳይከፋፍለው፤ ይከተለው ከነበረው ሰላማዊ መንገድ ውልፍት ሳይል ለተራዘመ ጊዜያት መቀጠሉ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የታሪክ ገፅ ላይ አዲስ አሻራውን ለማሳረፈ ያስቻለው ይመስለኛል፡፡
አህአዴግአዊ ‹ህቡዕ መዳፍ›…
አገዛዙ በግልፅ የሚታየውን መጅሊስ፣ በማይታይ ስውር ‹መዳፉ› ልጓም ጨብጦ እየጋለበ በኃይማኖታዊ ተቋሙ ላይ በስፋት ጣልቃመግባቱን የምንረዳው ‹‹መፍትሄ አፈላላጊ›› ተብለው የተመረጡትን የኮሚቴውን አባላት አንድ በአንድ ለቅሞ ወህኒ ቤት ከወረወረ በኋላ፣ የከሰሰበትን የመወንጀያ ጭብጥ እና እንዲከላከሉ የወሰነበትን የማስረጃዎች ይዘት ስንመረምር ነው፡፡
በርግጥ ሁሉም የተከሰሱት በፀረ-ሽብር ሕጉ ሲሆን፣ ከውሳኔው በኋላም አንዳንድ አንቀጾች ከመሻሻላቸው በቀር ምንም የረባ ለውጥ አልታየም፡፡ ይሁንና መንግስት ገና ከመነሻው (ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ) በኮሚቴው አባላት ላይ የተለያዩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞች›ን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በማስተላለፍ የወንጀለኛነት ብያኔ እና የማጠልሸት ቅስቀሳ አድርጎባቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላም (ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም) ‹‹ጥፋቶች›› ያላቸውን አራት ጭብጦች በመዘርዘር መደበኛ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ የክሱ ይዘትም ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ተጠቃሎ ሊቀርብ ይችላል፡-
‹‹…‹መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ› በሚል እርስ በእርስ ተመራርጠው ሲያበቁ ከጥር 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሁሌ በየሳምንቱ አርብ ለፀሎት አወሊያ መስጊድ ለሚሰበሰበው ሕዝብ የሽብር ዓላማቸውን ለማራመድ በአዲስ አበባ እና በክልሎች ባዘጋጁት የሰደቃ እና የአንድነት ዝግጅቶች ለሚጠሩት ሕዝብ፣ በማሕበራዊ ድህረ-ገፆች፣ ለዚሁ ትግበራ በተቋቋሙት የተለያዩ ኃይማኖታዊ መገናኛ ብዙሀን፣ በመፃህፍት፣ በበራሪ ፅሁፎችና ዘጋቢ ፊልሞች አማካኝነት… የመጨረሻ ግባቸው የሆነውን እስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሙስሊሙ ሕዝብ ቁጥር ከ80 በመቶ በላይ ነው በማለት ለሽብር ተግባር ቀስቅሰዋል፤ አነሳስተዋል፡፡››
ጉዳዩንም በዝግ ችሎት ሲመለከት የነበረው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከአንድ ወር በፊት (ታሕሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም) የሰጠው ውሳኔ በሶስት የተከፈለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የመጀመሪያው አቡበከር መሀመድ፣ አህመዲ ጀበል፣ ያሲን ኑር እና ካሚል ሸምሱን ጨምሮ አስራ አራት ሰዎች ያሉበት ሲሆን፣ ከተከሰሱበት የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)(ለ) እና 38(1) መካከል፣ በአንቀጽ 32(1)(ሀ) እንዲከላከሉ ተወስኗል፤ በተጨማሪም ‹‹በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(2)(4)(6) እና አንቀጽ 4 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ›› ከሚለው ደግሞ አንቀጽ 3 ቀርቶ በአንቀጽ 4 ተመሳሳይ የተከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ሁለተኛው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸውን ጨምሮ አራት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ እነርሱም ከእነ አቡበክር ክስ ጋር የተጠቀሰባቸው የወንጀለኛ መቅጫ አንቀጾች ሁሉም ውድቅ ሆነው በፀረ-ሽብርተኝነትሕጉ አንቀፅ 7(1) ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡ ሶስተኛው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ባለቤት ወ/ሮ ሀቢብ መሀመድ እና ሁለት የበጎ አድራጎት ድርጅትን ጨምሮ አስራ ሁለት ተከሳሾች ያሉበት ሲሆን፣ የተላለፈው ውሳኔም በነፃ መሰናበታቸውን የሚገልፅ ነው፡፡
‹‹ማስረጃ›› ፍለጋ…
ከክሱ ጀርባ ረጅሙ የመንግስት እጅ መኖሩን የሚያመላክተው ‹‹ጥፋተኛ›› በተባሉት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ‹‹ማስረጃ›› ነው፡፡ እንዲያ ስርዓቱን በኃይል አፈራርሰውና ሌሎች ኃይማኖታዊ ተቋማትን ጨፍልቀው ‹‹እስላማዊ መንግስት›› ሊመሰርቱ ወጥነው ሲንቀሳቀሱ እጅ ከፈንጅ ለመያዛቸው በበቂ ሁኔታ ያስረዱልናል ብለው የጠቀሷቸው ‹‹ማስረጃዎች›› በጠቅላላ የሚከተሉት ናቸው፡- ‹ሁሉም ታሳሪዎች ለፖሊስ ሰጡ የተባለው የእምነት-ክህደት ቃል፣ ዓቃቢ-ሕግ ሰብስቦ ያቀረባቸው የሰው ምስክሮች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ላፕቶፖች፣ ሲዲዎች፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ጭልፋና የወጥ-ድስቶች…›፤ በቃ! በአናቱም ‹‹የሙስሊሙ ቁጥር ከሀገሪቱ ሕዝብ ሰማኒያ በመቶውን ይይዛል ብለዋል›› የሚለው ክስ ተራ አሉባልታ መሆኑን ለማስረገጥ፣ ራሳቸው የኮሚቴው አባላት መጋቢት 2004 ዓ.ም ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ከፃፉት ደብዳቤ ውስጥ የሚከተለውን አንቀጽ ብቻ መጥቀሱ በቂ ነው፡-
‹‹…እንደሚታወቀው የሃገሪቱን ሰላሳ ሶስት በመቶ የሚሆነውን የሕብረተሰብ ክፍል የሚወክለው የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ም/ቤት (መጅሊስ) ተገቢው ሕጋዊ ሰውነት የለውም…››
እናሳ! ዓቃቢ-ሕግጋኑ 80 በመቶን ከየት አምጥተው ይሆን? …በርግጥ አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹መረጃ እንጂ ማስረጃ የለንም›› እንዲል ገዥው ፓርቲ በእነዚህ የ‹‹ሽብር›› ማስፈፀሚያ ቁሳቁሶች ነው መንበረ-መንግስቱን ከመገልበጥም ሆነ ሀገሪቱን ከኃይማኖታዊ ስርዓት ለጥቂት ታድጌያታለሁና ወንዶች በጭብጨባ፣ ሴቶች በእልልታ አመስግኑኝ የሚለው፡፡ የክሱን ልብ-ወለድነት በአመክንዮ ለማስረዳት ከ‹‹ማስረጃዎቹ›› ውስጥ ሁለት ጉዳዮችን ብቻ መምዘዙ ይበቃናል፡፡ ተከሳሾቹ ለፖሊስበምን ሁኔታ ቃላቸውን እንደሰጡ እና የአንድ ምስክር እማኝነትን (ምንም እንኳ ችሎቱ በዝግ የተካሄደ በመሆኑ የሁሉንም የሀሰትመስካሪነት ሙሉ ለሙሉ ማጋለጥ ባይቻልም፣ ዳኞቹ ራሳቸው ባሳለፉት ውሳኔ ላይ የተጠቀሰው የአንድ የምስክር ቃል ይህንን መከራከሪያ ያስረግጥልናል)
የመርማሪዎቹ ‹‹ችሎታ››…
የጥፋተኝነታቸው ማሳያ የሆነው የኮሚቴው አባላት ለፖሊስ የሰጡት ቃል ተብሎ በሰነድነት የቀረበው በድምሩ 413 ገፅ ሲሆን፤ ይህ ምርመራም በምን መልኩ እንደተካሄደ በቅርቡ ታሳሪዎቹ በተለያዩ ሚዲያዎች ባሰራጩት ደብዳቤ ላይ የፍትሕ ስርዓቱን ገመና እና በዚች አገር ሰብዓዊ መብቶች ምን ያህል ዋጋ እንዳጡ ልብ የሚሰብሩና በድንጋጤ ዓቅል የሚያስቱ መከራዎቻቸውን ጭምር በመዘርዘር ነግረውናል፡፡ በደብዳቤው ላይ ዓቃቢ-ሕግ ክስ መመስረቻ ያደረገውን ቃላቸውን ፖሊሶቹ ፈልፍለው የደረሱበት የመርማሪነት
‹‹ጥበብ››ን እንዲህ በማለት ነበር የገለፁት፡-
‹‹…በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ ደርሶብናል፡፡ ከአስራ አራት ሰዓታት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን እስኪላጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና አይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን እስከሚላጥ ገልብጦ በመግረፍ፣ ቀንና ማታ አሰቃቂ በሆነ ምርመራ እና በድብደባ ብዛት እንቅልፍ በመንሳት፣ ፂማችንን በመንጨትና እንድንላጭ በማስገደድ፣ ከአቅም በላይ የሆነ ስፖርት በግድ በማሰራት፣ ብልት በመግረፍ፣ ‹ልጅህን እንገድለዋለን! ሚስትህን አስረን በፊትህ ቶርች እናደርጋታለን! ብልትህ ላይ የውሃ ሃይላንድ በማንጠልጠል መሀን እናደርግሀለን!› እያሉ በማስፈራራት ከፍተኛ የሆነ እንግልትና ስቃይ አድርሰውብናል፡፡ …በክረምት ቀርቶ በበጋ እንኳ ቅዝቃዜው በማይቻለው ‹ሳይቤሪያ› ተብሎ በሚጠራው ጨለማ ክፍል አጉረውናል፡፡ መቋቋም የሚያዳግተውን የማሳቃያ ስሌታቸውን በመጠቀም ያላሰብነውንና ያልሰራነውን ‹እመኑ! ተናገሩ! ፈርሙ!› ብለው አስገድደውናል፡፡››
ወደድንም ጠላንም የሀገራችን እውነተኛ ገፅታ ይሄ ነው፡፡ በአናቱም ታሳሪዎቹ የደረሰባቸውን ግፍና መከራ የሚያረጋግጡልን ገፊ-ምክንያቶች፣ የመጀመሪያው ከዚህ ቀደም የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት እና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ድርጅቶች ማዕከላዊን በተመለከተ ያወጧቸው ሪፖርቶች ሲሆን፤ ሁለተኛው ታሳሪዎቹ ራሳቸው ይህንኑ የጭካኔ ተግባር በዝርዝር ጠቅሰው በመርማሪ ፖሊሶቹ ላይ በፍርድ ቤት ክስ መስርተው የነበረ መሆኑ ነው፤ ሶስተኛው ደግሞ መንግስት ‹ጅሃዳዊ ሀረካት› በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ‹ዶክመንተሪ
ፊልም› በድጋሚ እኩለ ሌሊት ላይ በተላለፈበት ወቅት የማዕከላዊ መርማሪዎች የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆነውን አቡበከር መሀመድን እጁን በሰንሰለት የፊጥኝ አስረው ሰብዓዊነቱን በሚያንቋሽሽና መንፈሱን በሚያሸማቅቅ ሁናቴ ቃሉን ሲቀበሉ በቴሌቪዥን መስኮት መመልከታችን ነው፡፡
የዓቃቢ-ሕግ ምስክር ሲባል…
ለዚህ ሙግት ማሳያ የማደርገው ከዓቃቢ-ሕግ ምስክሮች መሀል አንዱ የሰጠውን የምስክርነት ቃል ነው፤ ይህ ግለሰብ በ21ኛ ተከሳሽ ሼኽ ጣሂር አብዱልቃዲር መኖሪያ ቤት ሽጉጥ ከነጥይቱን ጨምሮ የተለያዩ ማስረጃዎች በብርበራ ሲገኝ መመልከቱን በችሎቱ ፊት በፈጣሪው ስም ምሎ ተናግሯል፤ የሚገርመው ነገር ግን ይህ አይደለም፤ ዳኞቹ በሰጡት ውሳኔ ላይ እንደሚከተለው ማለታቸውን መስማታችን እንጂ፡-
‹‹እነዚህ ማስረጃዎች (ሽጉጡም ጨምር) አልቀረቡም፤ ዓ/ሕግም በማስረጃ ዝርዝርና በሰነድነት አልጠቀሳቸውም፤ ሌላ ማስረጃም አልቀረበም፡፡››
እንግዲህ በዝምታ ተገርሞ ከማለፍ በቀር ‹ታዲያ ምስክሩ ከየት አምጥቶ ነው ስለመሳሪያው የዘባረቀው?› የሚል ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፤ ቢቀርብም አጥጋቢ መልስ አይገኝለትም፤ ለምን ቢሉ ሀገሪቱ ኢትዮጵያ ነቻ!! ያውም ኢህአዴግ በብረት መዳፉ ጨፍልቆ የሚገዛት ምስኪን ሀገር፡፡ …መቼም ይህ ተጨባጭ እውነታ እንዲህ ገሀድ መውጣቱ በዚህ ፀያፍ ተግባር ውስጥ የቀጥታ ተሳትፎ ያልነበራቸውን የገዥው ፓርቲ አመራርንም ሆነ አባላትን ጭምር የአትንኩኝ ባይነት ንዴት ይቀሰቅስ እንደሆነ እንጂ፣ ስለሕገመንግስት፣ ሕሊና፣ ሕዝብና አገር በድፍረት መናገር (ጥብቅና መቆም) የሚችሉበት ሞራል ይኖራቸዋል ብሎ ማሰብ ተላላነት ነው (በነገራችን ላይ የሀገሬ የፍትሕ ደጆች እንዲህ የዘቀጡ መሆናቸው ሲጋለጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በድህረ-ምርጫ 97ም የፈጠራ ማስረጃዎች እና ሓሳዊ ምስክሮች ምን ያህል ነግሰውበት እንደነበረ ታይቷል፡፡ የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› እና የአንተነህ ሙሉጌታ ‹‹የተዋረደው ፍርድ ቤት›› መፃህፍት ሂደቱን በቦታው የነበርን እስኪመስለን ድረስ በውብ ቋንቋ ከሽነው በዝርዝር ተርከውልናል)
ከቤተ-ክህነት ጀርባ…
በርግጥ ከቤተ-ክህነት ‹የእምነት ነፃነት ይከበር!› ጥያቄ ጋር በቀጥታ ተያይዞ ለአስከፊው የቃሊቲ ማጎሪያ የተዳረጉ መንፈሳውያን መሪዎች እስካሁን የሉም፡፡ ይህ ግን የአገዛዙ ‹እርኩስ መንፈስ› በደጆቿ ዙሪያ አልረበበም እንደማለት አይደለም፡፡ ፓትሪያርክን አባርሮ ሌላ መሾም፣ እነአቦይ ስብሃትን የመሳሰሉ የፓርቲው አንጋፋ መሪዎች በአደባባይ ‹‹አንድም ከመንግስት ነፃ የሆነ ጳጳስ የለም!›› ከማለት አልፈው፣ ‹‹ነፃ የሆነ ጳጳስ ካለ እሸልመዋለሁ›› እስከሚለው ተሳልቋቸው ድረስ ያሉ ማረጋገጫዎች የሚያሳዩት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ነውና፡፡ በተለይም በያዝነው ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ወራት ውስጥ ብቻ በቤተ-ክህነቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የገባውን ስውር እጅ እና የእምነቱን የአስተምህሮ መንገድ፣ ከኑፋቄው በመለየትም ሆነ በተለያዩ መንፈሳዊ ተግባሮቹ ስመ-ገናና የሆነውን ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› ላይ የተሸረበውን መንግስታዊ ተንኮል ‹‹ቀጣዩ የኢህአዴግ ዒላማ ማህበረ ቅዱስን ይሆን?›› እና ‹‹ኢህአዴግና የኃይማኖት ነፃነት›› በሚሉ ፅሁፎች እዚሁ መፅሄት ላይ ቀደም ሲል በስፋት ስላወሳናቸው ዛሬ መድገሙ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ይሁንና ጣልቃ ገብነቱን የሚያመላክቱ ሁለት አዳዲስ ማሳያዎችን የአጀንዳውን ተጠይቅ ለማጠናከር እጠቅሳቸዋለሁ፡፡
ወረራ-ሲኖዶስ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢህአዴግ ለ‹‹አውራ ፓርቲ››ነቱ ዋስትና የእምነት ተቋማትንም በ‹መንፈሳዊ ክንፍ›ነት ከጎኑ የማሰለፍ ግዴታ ውስጥ የከተተው ይመስል፣ ከፍተኛ ባጀት መድቦና ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡ ባሳለፍነው ወርሃ ጥቅምት መደበኛው የሲኖዶሱ ጉባኤ በተደረገበት ወቅት፣ ለመጪው ግንቦት አጠናቅቀው እንዲያዘጋጁ ኃላፊነት ለሰጣቸው አራት አባላቱ ያስተላለፈው ውሳኔ፡- ‹‹ዘጠኝ እጩ ጳጳሳትን መልምላችሁ አቅርቡ!›› የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ከቤተ-ክህነት ምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ፣ መንግስት የፊታችን ግንቦት ወር በሚደረገው ጉባኤ ላይ ሹመታቸው ፀድቆ በቀጥታ የሲኖዶሱ አባል መሆን በሚችሉት ዘጠኙ ጳጳሳት ምልመላ ላይ ረዥም እጁን እየከተተ መሆኑን ነው፡፡
እንደሚታወሰው ነባሩ የቤተ-ክህነት የጳጳሳት የአመራረጥ መስፈርት የሚከተሉት ናቸው፡- ‹‹በምንኩስና የኖረ (ትዳርም ልጅም ያሌለው)፣ መንፈሳዊውንም ሆነ ዓለማዊው ትምህርቱን በሚገባ ያጠናቀቀ፣ ከአንድ በላይ ቋንቋ መናገር የሚችል፣ እውነትና ሀሰትን የማይናገር፣ አስካሪ መጠጥ የማይጠጣ፣ እድሜው ሃምሳ ዓመት የደረሰ፣ በሚያገለግለበት ቦታ ምስጉን መሆኑ የተረጋገጠ…፡፡›› ይሁንና ጀግናው ኢህአዴግ ደግሞ የፖለቲካ ታማኝነትን በተጨማሪነት ለመክተት ‹አክራሪ ያልሆነ› እና ‹ልማታዊ የሆነ› በሚሉ ሁለት
መስፈርቶች ሸፋፍኖ በለመደው ስውር እጁ ተፅእኖ በማድረግ በሲኖዶሱ ውስጥ ያለውን ጉልበት ለማጠናከር እየሞከረ እንደሆነ ማረጋገጤ ለተጠየቁ እንደ አንድ ማሳያ ሊወሰድ ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡
የለውጡ አንድምታ…
ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ሆነው በሲኖዶሱ የተሾሙት አቡነ እስጢፋኖስ፣ በአቡነ ቴውፍሎስ ዘመን ፀድቆ ይሰራበት የነበረውን ‹ቃለ-አዋዲ› ለማሻሻል ይሁን ለመሻር ባይታወቅም አዲስ ጥናት አጥንቶ እንዲያቀርብላቸው ኃላፊነቱን ለማህበረ ቅዱሳን ይሰጣሉ፡፡ ማህበሩም በአጭር ጊዜ ውስጥ ‹‹የአዲስ አበባ የሀገረ-ስብከት የአደረጃጀትና አሰራር ለውጥ ጥናት›› በሚል ርዕስ የቤት ስራውን አጠናቅቆ ያቀርባል፡፡
ነገር ግን የመዋቅርንና የአሰራር ለውጥን ጨምሮ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓት እንደተካተተበት የተነገረው የጥናቱ ረቂቅ መሰናዳቱን ተከትሎ ገና ከአሁኑ ከአንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎች ዘንድ ከባድ ተቃውሞ እየደረሰበት ነው፡፡ እንደ ምንጮቼ መረጃ ሁናቴው በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት ሀገረ-ስብከቱንም ሆነ የደብር አስተዳዳሪዎችን መከፋፈሉ አይቀሬ ነው፡፡
ይህንን ጉዳይ እዚህ ጋ ያነሳሁት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ያሳያል በሚል ነው፡፡ ይኸውም የጥናቱ ይዘት በወሬ ደረጃ በመናፈሱ ብቻ ‹‹መተግበር የለበትም!›› የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ያሉ አንዳንድ ጳጳሳት እና የደብር አስተዳዳሪዎች ‹‹መንግስት ከጎናችን ስለሆነ፣ ከእርሱ ጋር እንነጋገርበታለን››፣ ‹‹ይህ ህግ መፅደቅ የለበትም፣ አለበለዚያ ሪፖርት ለምናቀርብለት አካል ሪፖርት እናደርጋለን››፣ ‹‹አርፋችሁ ብትቀመጡ ይሻላችኋል››፣ ‹‹እርሶንም (አቡነ እስጢፋኖስን) ከሥልጣንዎት እናወርዶታለን››… እና መሰል ማስፈራሪያዎችን አቡኑ ቢሮ ድረስ በመሄድ መናገራቸው ነው፡፡
በጥቅሉ እነዚህ ሁነቶች ስርዓቱ በቤተ-ክህነት የውስጥ አስተዳደር ምን ያህል ጠልቆ እጁን እንደሰደደ ያስረግጡልኛል ብዬ አምናለሁ፡፡
‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ወዴት ተሰወረ?
ባሳለፍነው ሳምንት ሁለተኛ ዓመቱን የደፈነው የሕዝበ-ሙስሊሙ ‹‹የእምነት ነፃነት ይከበር!›› ጥያቄ፣ በተለይም ‹‹መፍትሄ አፈላላጊ›› ተብለው የተመረጡት የኮሚቴ አባላት ለእስር ከተዳረጉ በኋላ የተቃውሞ ንቅናቄው ሲመራ የቆየው ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› የሚል መርህ ባነገቡ አስተባባሪዎች እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ፍፁም ሰላማዊውን እና ሕጋዊውን መንገድ በመከተል የጁምዐን ሶላት እየጠበቁ የኮሚቴው አባላት በአስቸኳይ ከተጣሉበት የስቃይ ጎረኖ እንዲወጡና ያነሷቸው የመብት ጥያቄዎችም ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ
እንዲመለሱ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎችም የሀገሪቱ ከተሞች ያስተባበረው የተቃውሞ ድምፅ ዛሬ በቦታው የለም፡፡ በግልባጩ መስጊዶቹ በከባድ ፀጥታ የተመቱ መስለዋል፡፡
ከማሕበራዊ ሚዲያዎች እስከ የእጅ ስልክ መልዕክት መለዋወጫዎች፤ ከበራሪ ወረቀቶች እስከ ፍትህ ሬዲዮ ድረስ ያሉ የመረጃ ማስተላለፊያ ዘዴዎችን እጅግ በሰለጠነ መንገድ ይጠቀም የነበረው የ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› ተቃውሞ፣ በዘንድሮው የዒድ በዓል ወቅት በእምነቱ ተከታዮች ላይ መንግስት ከወሰደው መጠን የለሽ የጭካኔ እርምጃ በኋላ ዳግም አልተከሰተም፡፡ ይሁንና ምንም እንኳ በበዓሉ ዋዜማ አስተባባሪዎቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለጊዜው ለማቋረጥ መወሰናቸውን ቢያሳውቁም፣ በስርዓቱ የአመራር አባላት ዘንድ ያለው አተያይ ግን ተቃውሞውን በኃይል መቆጣጠር እንደተቻለ ነው፡፡ በርግጥም ይህ አይነቱ የተሳሳተ መደምደሚያ ይመስለኛል የኮሚቴው አባላትን ውሃ በማይቋጥር ክስ ‹‹ጥፋተኛ›› ብሎ እንዲከላከሉ እስከመወሰን ድረስ የልብ-ልብ የሰጠው፡፡
የሆነው ሆኖ አገዛዙ የእስልምና እምነት ተከታዮችን በአህባሽ እና ሓሳዊ ሰባኪያን ከፋፍሎ ለማዳከም ያደረገው ሙከራ ቢከሽፍም፣ ዛሬም የተነሱት ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎች መልስ ካለማግኘታቸውም በላይ፣ በእነዛ ፈታኝ ጊዜያት ሚሊዮኖችን ወክለው በድፍረት ከፊት መስመር የተሰለፉት ንፅሃን የኮሚቴው አባላት በእስር እየማቀቁና ለተለመደው የፖለቲካ ፍርደ-ገምድል ውሳኔ እያመቻቿቸው ስለመሆኑ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› አስተባባሪዎች ይዘነጉታል ተብሎ አይገመትም፡፡ በአናቱም ይህ ሁናቴ እንደ ልጅነት ዘመን፣ የሚታሰረው ታስሮ፣ የሚገደለው ተገድሎ፣ የሚሰደደው ተሰዶ… ሲያበቃ ‹ዳቦ ተቆረሰ፣ ዕቃቃው ፈረሰ› ተብሎ በየፊናችን የምንበታተንበት አይነት ጨዋታ አለመሆኑን ማስታወሱ አግባብ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
የመውጫው መንገድ
ኢህአዴግ ያለፉትን ሃያ ሁለት የሰቆቃ ዓመታት በስሁቱ የ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› ርዕዮተ-ዓለም ብያኔ ሀገሪቱንና ሕዝቧን ለአስከፊ ድህነት፣ ለመራራ ጭቆና ዳርጓል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ባነበረው መከፋፈልና አለመተማመን የሥልጣን ዕድሜውን ያለስጋት ማራዘሙ ተሳክቶለታል፡፡ ጥያቄውም ከዚህ የሚነሳ ቢሆንም፣ ምላሹ በቅርቦቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ከታየው የሙስሊሙ ሰላማዊ የትግል ስልት ጋር የሚተሳሰር ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ማንኛውም የመብት ጥሰት የሚያሳስበው ዜጋ ይህን ክቡድ መንፈስ ከመቀላቀል የተሻለ አመራጭ የለውምና (በነገራችን ላይ የኮሚቴው አባላት በቀጠሮ ከሚቀርቡበት የፊታችን ጥር 22 ቀን ጀምሮ ችሎቱ ለታዳሚ ክፍት በመሆኑ ያለአንዳች የኃይማኖት ልዩነት ወደ ፍርድ ቤት በመትመም ከጎናቸው ታላቅ የሕዝብ ደጀን መኖሩን ማሳየቱ መንፈሳቸውን ለማበርታት መልካም አጋጣሚ ነው)
በጥቅሉ ሰማያዊ ነፃነታቸው በፖለቲካ ጉልበት እየተናደ የመጣው የሁለቱ ኃይማኖት ልሂቃንና ተከታዮች ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጎንዮሽ መተያየታቸውን ገርቶ፣ የብሔር ልዩነትን አዘልሎ በአንድ አውድ ሊያሰባስባቸው የሚችል ገፊ-ምክንያት አላቸው፡፡ እናም ስርዓቱ እርስ በእርስ በጥርጣሬና በስጋት እንዲተያዩ ለማድረግ በተንሸዋረረ የ‹‹መቻቻል›› ፕሮፓጋንዳ ስም እየዘረጋው ያለውን የረቀቀ ወጥመድ በመሻገር፣ የአደባባይ ተቃውሞዎችን በጋራ በማስተባበር የማያቋርጥ ጫና ፈጥረው ለቤተ-አምልኮዎቻቸው ‹‹ነፃነታችንን መልሱልን!?›› አንገብጋቢ ጥያቄ መፍትሄ ማስገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ከግብ ለማድረስ በተለይም ከ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ውጤታም እንቅስቃሴ ጥቂት ገፆችን በመገንጠል ሰፊ መዋቅር ያለው ‹‹ማሕበረ ቅዱሳን›› ደጋግሞ ቢከልሰው ካለፈ ቁጭት ራሱን መታደግ የሚችልበትን የመውጫ ቀዳዳ ማግኘቱ ብዙ አያለፋውም፡፡
በመጨረሻም ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ከታሳሪዎቹ የኮሚቴው አባላት መካከል አንዱ የሆነው ካሚል ሸምሱ ሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ.ምእንደ ተናገረው ጠቅሶ በማሕበራዊ ድህረ-ገፆች ያሰራጨውን መልዕክት የርዕሰ-ጉዳያችን መደምደሚ ይሆን ዘንድ ወደደሁ፡-
‹‹የዚህች ሀገር ሰላም ፀጥታ ነው፤ ዲሞክራሲን ማስፈን የሚቻለው፤ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የሚቻለው በጋራ ነው፤ እኛም የእዛው አካል ስንሆን ነው፤ የአንዱ መብት ተከብሮ የሌላው ተጥሶ ሊሆን አይችልም! አንደኛው የሕገ-መንግስት ክፍል ተከብሮ ሌላኛው ተደፍጥጦ ሊሆን አይችልም! ሰላምን ነው የምንዘምረው! ለሰላም ነው የምንታገለው! ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ እንሄድበታለን!››

Sunday, January 19, 2014

‹‹አባቴ ለምን እንደተገደለና እጄ በምን ምክንያት እንዴቆረጥ እንደተፈረደብኝ አላውቅም እናም ፍትህ እንዳገኝ እርዱኝ››

  Look at the kid her hand is cut wounded by the the Ethiopian government soldier in Gonder. Her name is Silenat masresha her father is also killed by the dictator government of Ethiopia. On the contrary the girl next to this victm is called blen ,Child of the Minstry of Foreign Affairs of the same regim. She is happy and rather her father , the Minster post her wishes for the Ethiopian foot ball team.”My daughter, Blen, asked me to post on facebook her very best wishes for our Walya. “All the best Walya” from Blen……..How ever the vulnerable daugher of the deceased Silenat has not any one to ask why her father is died and why they shot her……….
1546464_10152194782224743_271819834_n
ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ልጅ ከብሌን አጠገብ ያለችውን የስምንት አመት ታዳጊ ደግሞ ተመልከቷት ፡፡ቴድሮስ በውጪ ጉዳይነት የሚወክሉት መንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ስለእናት ማስረሻ ወላጅ አባቷን ‹‹አባዬን››በግፍ ተነጥቃለች፡፡በመኝታዋ አልጋዋ ላይ እንዳለች የመታት ጥይትም ቀኝ እጇን ቆርጦ ወስዶታል፡፡
ብሌን ሙሉ ፈገግታዋ በፊቷ ላይ ይነበባል በአንጻሩ ስለእናት ፊት ላይ ፈገግታን መፍጠር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ……..
የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ና የተገዳዩ ገበሬ ልጅ ምኞት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ልጅ ብሌን እንደምትመለከቷት በቀለም አሸብርቃ በቻን 2014 የአፍሪካ ዋኝጫ እተካፈለ ለሚገኘው ቡድናችን መልካም ምኞቷን ገልጻለች፡፡አባትም ፎቶዋን በገጻቸው በመለጠፍ ምኞቷን አድርሰዋል፡፡ My daughter, Blen, asked me to post on facebook her very best wishes for our Walya. “All the best Walya” from Blen.በማለት ከብሌን አጠገብ ያለችውን የስምንት አመት ታዳጊ ደግሞ ተመልከቷት ፡፡ቴድሮስ በውጪ ጉዳይነት የሚወክሉት መንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ስለእናት ማስረሻ ወላጅ አባቷን ‹‹አባዬን››በግፍ ተነጥቃለች፡፡በመኝታዋ አልጋዋ ላይ እንዳለች የመታት ጥይትም ቀኝ እጇን ቆርጦ ወስዶታል፡፡ ብሌን ሙሉ ፈገግታዋ በፊቷ ላይ ይነበባል በአንጻሩ ስለእናት ፊት ላይ ፈገግታን መፍጠር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ለአቤቱታ አዲስ አበባ በመጣች ወቅት አግኝቼያት ለመገንዘብ ተረድቻለሁ፡፡ ክቡር ዶክተር ሆይ ስለእናት ፎቶዋን በፌስቡክ እንዲለጥፉላት አትጠይቅዎትም እርሷ ስለዋሊያዎቹ የምታውቀውም ምንም ነገር የለም ግን በልጅ አንደበት ‹‹አባቴ ለምን እንደተገደለና እጄ በምን ምክንያት እንዴቆረጥ እንደተፈረደብኝ አላውቅም እናም ፍትህ እንዳገኝ እርዱኝ››ትለዎታለች፡፡

Friday, January 17, 2014

ጀርመንና የውጭ ዜጎች ጉዳይ- German prefer skilled migrants

ጀርመንና የውጭ ዜጎች ጉዳይ

ጀርመን ውስጥ የውጭ ዜጎች ጉዳይ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚነሳ ሁሌም የሚያነጋግር ርዕስ ነው ። በአንድ ወገን የውጭ ዜጎች መበራከት ማህበራዊ ኑሮአችንን አዛብቶ ለችግር ይዳርገናል ሲሉ
Symbolbild syrische Asylbewerber in Deutschland
የሚከራከሩ ጀርመናውያን ሲኖሩ በሌላ ወገን ደግሞ ቁጥራቸው አንሷልና ከፍ ሊል ይገባል የሚሉም አሉም ። ሌሎች ደግሞ የመጡትንም እንኳን በደንብ ማስተናገድ አልተቻለም ሲሉ ይወቅሳሉ ። እነዚህን የመሳሰሉ አከራካሪ አቋሞች ቢኖሩም በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ውስጥ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ተጨባጩ ሁኔታ ከዚህ የተለየ ነው ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ አለው
Source DW

Why Poverty? Ethiopia and Niger are the first 3 poorest countries in the world

This article is about level of poverty in the world. According to the study shown below The first poor countries are african countries. Ethiopia is the second poor country in the world next to Niger. Why  we are regarded as the poorest nation despte the Ethiopian government falsifies this fact pretending We are growing well........Also other African countries leaders hide their corruption aganst the poor farmers through ther monopoly medias, monopoly economies owned by the Government family. Rather THe funny African presidents say We are poor by the Neo colonial practice of Western World which is false.


Governments are just Legalized Mafia all around the world, and the IGNORANCE OF PEOPLE is the foundation they stand on we are brainwashed by media and society to believe that our only worry and purpose in life is to "get a job! get a job!", but no one thinks about the big picture. And no one cares really, it's how we were programmed to think all our lives

Corporate farms always push corporate crops like sugar and rice which are the number one cause of diabetes which is joined by highblood pressure and kidney failure. The individual family should have land to grow their own food and sell the remaining for a profit. Corporations are the cause of poverty.



Here is the list any way .....then attend the Documentry film why Africans are poor.Image

Documentary: Why Poverty


From refugee to leader: an Ethiopian woman shows the way in Kenya

              


© UNHCR/S.Camia
Alemnish Tefera Abebe smiles as she stands on the balcony of her brightly coloured building complex in Ruiru, which is located on the edge of Nairobi. The area is home to hundreds of refugees from Ethiopia.
RUIRU, Kenya, January 16 (UNHCR) On the outskirts of Nairobi, Alemnish Tefera Abebe sits in her living room, curtains drawn to block out the invasive midday heat. The cool darkness contrasts with bright yellow cushion covers that adorn her sofa and chairs. "I sell them for a living," she says, to support herself and her 13-year old daughter, Gloria.
Alem is one of 500 refugees from Ethiopia who have settled in Ruiru, a dormitory town just three kilometres outside the Kenyan capital. It is at once a bustling industrial area and home to lush green coffee plantations. Just off a major highway, swarms of people kick up dust from red dirt roads. Stalls and shops are alive with colour, as men push carts, selling chickens trapped in cages.
In Ruiru, Alem is a well-known and beloved figure. "She has the trust of the whole community," says Ojuni Ojulu, who serves with her on the Ethiopian refugee community council. "When mothers give birth, she's always there, making sure they get to the hospital. She's also a leader at the church she attends."
Alem is more modest when she speaks about her presence in others' lives. "We are always together," is all she says.
This is Alem's life now, full of connections and meaning. But she's made many sacrifices and survived much trauma to get here.
In 2004, Ruiru and her daughter fled the violence raging between her tribe, the Anuaks, and the Ethiopian army. The fighting left hundreds of people dead, mostly men and boys, in the western region of Gambela.
Witnesses say women were being beaten and raped; hundreds of homes were being burned to the ground. The conflict prompted thousands of Anuaks to leave Ethiopia for neighbouring countries, such as Sudan and Kenya.
Alem was faced with a difficult decision  either leave behind everyone and everything that she had ever known or stay and face the risk of violence, rape and even being killed. At first she says, she "stayed with the hope that things would get better. But they kept getting worse," she says through an interpreter.
She took her daughter and escaped to Nairobi, even leaving behind her husband, who did not want to accompany them.
She plunged into life in her adopted community, forging new, life-restoring bonds. "When there were arrivals from Ethiopia, especially women," Ojuni says, "she would offer her home as a place to stay, before they moved on to the refugee camp."
As she offered her home and her time, her fellow refugees could see her commitment to others. They responded by electing her to the nine-member community council, which presents the needs of Ruiru's Ethiopian community to UNHCR and other organizations.
Alem is the representative for both finance and women. "I meet with others up to three times each week, listening to their concerns and discussing possible solutions," she says. "I love women and I will always stand up for them, to make sure they get the services they deserve."
Her contributions are applauded by UNHCR. "Women leaders like Alem make one feel humbled when you understand how much she invests in being a volunteer for the community," says Joanina Karugaba, UNHCR's senior regional advisor for women and children at the Regional Support Hub in Nairobi. "Supporting such women adds to the value of refugee communities being able to reach those most in need. UNHCR and NGOs must invest in women to ensure that they fulfill their potential in contributing to family and society."
Alem wants to see more young girls, especially her daughter, follow her lead, and she emphasizes the importance of learning as the key to lifelong success.
"My strength lies with the hope in my child being someone in the future [because of] education," she says. "That is the driving force I have within myself."
By Shirley Camia in Ruiru, Kenya
source: UNCHR

Thursday, January 16, 2014

በትግራይ ክልል በአጽቢ ወንበርታ በሕዝብ እና በአስተዳዳሪዎች መካከል ጸብ ተነሳ፤ 37 ጊዜ ጥይት ተተኩሷል

 

(አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)
(አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)
አብርሃ ደስታ ከመቀሌ እንደዘገበው ይህ ዜና እየተዘገበ ባለበት ሰዓት (ሓሙስ 08/05/06 ዓም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ) በትግራይ ክልል በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ (ጣብያ ሩባ ፈለግ ቁሸት ሕኔቶ) በህዝብና አስተዳዳሪዎች መካከል (በውኃ አጠቃቀም ምክንያት) በተፈጠረ አለመግባባት ሃይለኛ አምባጓሮ ተፈጥሯል። ፖሊሶች ተኩስ ከፍተዋል። እንደ አብርሃ ዘገባ ከ11:30 እስከ 11:40 ሰዓት ባለግዜ ለሰላሳ ሰባት (37) ግዜ ተተኩሷል።
“ምልሻዎች በተጠቀቅ ይገኛሉ።” ያለው የአብርሃ ዘገባ “የመንግስት የሚድያ ሰዎች ሂደቱ እየቀረፁት ነው። የቆሰለ ውይም የሞተ ሰው ስለሞኖሩ ወይ አለመኖሩ በግርግሩ ምክንያት ለማወቅ አልተቻለም። ተኩሱ እየቀጠለ ነው።” ብሏል።
አብርሃ በፌስቡክ ገጹ ጨምሮም በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ህዝብና አስተዳዳሪዎች መካከል ባጋጠመ ግጭት ፖሊስ ቢተኩስም ችግሩ ከፖሊስ አቅም በላይ በመሆኑ አሁን አስተዳደሩ የመከላከያ ሰራዊትን እርዳታ ጠርቷል። አሁን የመንግስት ምልሻዎች በአካባቢው እየተሰማሩ ይገኛሉ። በግጭቱ የተሳተፈው ኗሪ ህዝብ ከሺ በላይ ይሆናል። እስካሁን ድረስ የኗሪው ህዝብ ተወካዮች የነበሩ አራት ሰዎች የት እንደገቡ አይታወቅም። ፖሊሶች ህዝቡን ለመበተን ሃይል ቢጠቀሙም ህዝቡ ግን አራቱ ተወካዮቹ ካልተለቀቁ ላለመበተን አድማ መቷል። ህዝብ እየተሰባሰበ ነው። (የተኩስ ድምፅ በስልክ አስደምጠውኛል)።
በዚህ ዜና ዙሪያ ዘ-ሐበሻ ዘርዘር ያለ መረጃ ከደረሳት ለማቅረብ ትሞክራለች።


Source :Zehabesha news

Wednesday, January 15, 2014

የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ



የብአዴን አባላት የአፍሪካው ልዑል የተሰኘውን መጽኃፍ በሬዲዩ ፋና መተረኩን ተቃወሙ

ኢሳት ዜና :- በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በመተረክ ላይ ባለው በታጋይ መዝሙር ፈንቴ ተርጓሚኒት  በአቶ ዳንኤል ግዛው ጸኃፊነት የቀረበው መጽሀፍ  በአማራ ህዝብ  ላይ  ጥላቻ እንዲፈጠር እያደረገ ነው በማለት የብአዴን አባላት ተቃውመውታል።
አባላቱ በብር ሸለቆ በመካሄድ ላይ ባለው ስልጠና ላይ  እንደተናገሩት ሬዲዩ ፋና ታሪካዊ ስህተት እየፈጸመ ነው ፡፡ “የህውሃት ድብቅ አላማ እውን እየሆነ ነው” ያሉት ፤ መካከለኛ እና ታዳጊ የብአዴን አመራሮች ፤ ከደቡብ ወንድሞቻችን ጋር ታሪክን በማሳሳት እና በማጥላላት የትውልድ ጠላትነትን አስፍቶ አሁንም የህውሃት የበላይነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው በማለት በጽኑ ተቃውመውታል።
ጥያቄው የቀረበላቸው  የኢህአዴግ የስልጠና ዋና ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ “መፅሃፉ እየተተረከ መሆኑን በፍጽም አላውቅም” ያሉ ሲሆን ፣ ምላሹን አጣርተው እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡ የመጽሃፉ ትረካ ባሰቸኳይ እንዲቆም የጠየቁት አመራሮች ፣ ፋና ራዲዮን መስማት ማቆማቸውንም ለአቶ አዲሱ ተናግረዋል፡፡ የመለያየት ፖለቲካው  መርዛማነት እያሰቃየን ነው ሲሉም አባላቱ አክለዋል፡፡
ከቀናት በሁዋላ ወደ ተለያዩ አካላት  በመደወል መረጃ ያሰባሰቡት አቶ አዲሱ ለገሰ፣ ” ሃይለማርያም እንደፈረመበት እና  ፍቅር እስከ መቃብር ሲል እንዳወደሰው”  በማሾፍ መልክ መናገራቸውንና  ከፋና ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረው ” የመጽሃፉ ትረካ ቢቋረጥ በሬዲዩ ጣቢያው ላይ የሚፈጥረው ችግር ታይቶ ቢያንስ ቢያንስ የአድማጭ አስተያየት ባለመቀበል ልናጠፋው እንሞክራለን” ሲሉ መልስ እንደሰጡዋቸውና ሰልጣኞችን ለማረጋገት እንደሞከሩ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ “መጽኃፉን አንብቤ እከታተለዋለሁ” ያሉት አቶ አዲሱ፣ ስህተቱ መፈፀም የለበትም ሲሉ አክለዋል፡
“ስህተቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሁቱና ቱትሲ አይነት ግጭት የሚፈጥር ነው” ያሉት አባላቱ፣ ከደቡብ ወንድሞቻችን ጋር የሚፈፀም ቅራኔን አንፈልገውም” ሲሉ ለአቶ አዲሱ ገልጸውላቸዋል።
ሟቹ ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊና አቶ በረከት ስምኦን መጽሀፉ እንዲታተም ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ ነበር ያሉት ምንጮች፣ ሬዲዮ ፋናም የሩዋንዳውን የራዲዮ ሚሊኮልን ስራ እየሰራ ነው ሲሉ” ተቃውመውታል።
Ethsat.com

Tuesday, January 14, 2014

አንጎላ በሀገሯ የእስልምናን እንቅስቃሴ አገደች ተባለ!

አንጎላ በሀገሯ የእስልምናን እንቅስቃሴ አገደች ተባለ!

በትላንትናው ዕለት የግብጹ የሃይማኖት ሙፍቲ ሻውቂ ዓለም አንጎላ እስልምናን ከሀገሯ እንደሃይማኖት ተቋም ማገዷ በ 1ነጥብ 5 ቢሊዮን ሙስሊም ላይ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ልታውቅ ይገባታል ሲሉ አስጠነቀቁ። ይህም ትልቅ ዋጋ ያስከፍላታል ሲሉ ማስፈራሪያቸውንም አክለዋል።
 ይሁን እንጂ 83% የክርስትና እምነት ተከታይ ያለባት አንጎላ በሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬቷ በኩል በሰጠችው መግለጫ በቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በታች የሆነው የሙስሊም ቁጥር በነጻነት እየኖረ መገኘቱን በመግለጽ የሚታዩት አንዳንድ የእስልምና እንቅስቃሴዎችን ግን በትኩረት እየተከታተሉ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በየቦታው እየሄዱ መስጊድ መገንባት፤ የሃይማኖት ትምህርት ቤት መስራትና እስልምናን ለማስፋፋት የሚደረጉ የእጅ አዙር እንቅስቃሴዎችን ግን መንግሥታቸው በፍጹም እንደማይቀበልና እንደማይታገስ ሳይገልጹ አላለፉም። አንጎላ ከየትኛውም የእስላም ሀገራት ጋር የትብብር ስምምነት ስለሌላት በውስጥ ጉዳያቸው የትኛውም የእስላም ሀገር እጁን እንዳያስገባ አሳስበዋል።
 እስልምና በተስፋፋባቸው የአፍሪካ ሀገራት ሁከት፤ ብጥብጥና ግድያ እየተስፋፋ እያየን ቁጥሩ ምንም ትንሽ ቢሆን በሌላው ያየነው ሁኔታ በሀገራችን እንዲታይ በምንም መልኩ እድል አንሰጥም ያሉት የአንጎላው  የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክተር ያለንን ሰላም ለማስጠበቅ የምንወስዳቸው እርምጃዎች ከሃይማኖት ዲሞክራሲ ጋር በፍጹም አይያያዝም ሲሉ የሃይማኖት ነጻነትን ትጋፋለች በማለት ለሚጮሁ ክፍሎች አስረድተዋል።
ንግግራቸውን በማያያዝም እንደተናገሩት፤ ማንም አንጎላዊ በእምነቱ ሳቢያ በግሉ አይጠየቅም፤ አድልዎም አይደረግበትም።  ነገር ግን ገንዘብና ነጻነት አለኝ ብሎ የትም እየዞረ መስጊድ ለመትከልና ከራሱ አልፎ በሌላው አካባቢ ላይ የማስፋፋት መብት የለውም። በቂ የአምልኮ ስፍራና የእምነቱ መግለጫ ስፍራ እያለው ተጨማሪ የመስፋፋት እንቅስቃሴ ሲደረግ በማግኘታችን አንድ ያልተፈቀደ መስጊድ ዘግተናል፤ አፍረሰናል፤ ይህንንም ቁጥጥር አጥብቀን እንገፋበታለን ሲሉ ጨምረው ገልጸዋል።

amharic.voa

posted by Aseged Tamene

የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃት ማጥፊያ መዳኒት ..........በሮባ ጳዉሎስ

የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃት ማጥፊያ መዳኒት (ሮባ ጳዉሎስ)

ካለመታደል  ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው። በዚህም የተነሳ በሀገራችን ለብሔራዊ ክብርና ነፃነት፡ ለዲሞክራሲ፡ ለማህበራዊ ፍትህ፡ ለሰላምና ለእኩልነት የሚታገሉ ኃይሎች የሰላማዊ ለውጥ በሮች ስለተዘጉባቸው የአ መፅን ጎዳና እንዲከተሉ የሚጋብዝ በር ተቀዶ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ንእዲፈጠር፡ ሕዝቡም አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ አግኝቶ ያለስጋት ለመኖር እንዲችል፡ የዳኝነት ተቋሞች ነፃ ሆነው የሚሠሩበት፡ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲፈጠርና፡ ህዝቡም በህግና ሥርዓት መኖር ላይ እምነት እንዲያድርበት ለማድረግ እንዲቻል፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በኅብረት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም እስከዛሬ የተደረጉት ጥረቶችን ሁሉ በማምከን ወያኔ የሰላምና የእርቅ መሰናከል ከመሆኑም ባሻገር በንፁሃን ዜጎች ደም ሰላምን አጠልሽቶታል። ወያኔ ስለ ሰላምና እርቅ ሊሰማም ሊነጋገርም እማይችልበት የደም ስካር ላይ ደርሷል።
ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ – አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ።  የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።
ሌላ ሌላውን ትተን መሰረታዊ የሆነ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል፣ የፍትህ ስርዕቱ የፍትህ ስርእት መመስልም መሆንም አለበት፣ የነጻው ፕሬስና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዳሴ አንመራለን አየተባለ በመካከለኛው ዘመን አና ከዛ በፊት ከነበረው አንደነበረው በሰይፍ አና በሰደፍ መያዝ የለበትም። አነኚህ ወሳኝ ርምጃዎች በአዝጋሚ ለውጥ ይመጣሉ ብየ አላስብም። የአዝጋሚ ለውጥ ዲስኩር (ፍላጎት ካለ ፍላጎትም) ጭራሽ ወደማይቀልበስ የባርነት ዓለም አና ዘመን የመውሰጃ ከፓለቲካ ዘዴ ሊሆን ይችላል።  ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓለቲካ መሪዎች ዘብጥያ ሲጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፈጠሩትን ዓይነት ጫና መፍጠር ስላልተቻለ አንኳን መሰረታዊ የፕሬስ ነጻነት አና በነጻነት ያለገደብ የመደራጀት መብት የሚከበርበት ፍንጭ ሊገኝ ቀርቶ የታሰሩትን ጋዜጠኞች አና የፓለቲካ መሪዎች ማስፈታት አንኳን አልተቻለም። ጭራሽ መብታቸው ተረግጦ ያላግባብ አስር ቤት የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድረስ “አሸባሪ” አየተባሉ አየተፌዘባቸው ነው ያለው። አቶ ኃይለማርያምም ፌዙን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ አያስተጋቡት ነው።
ከበቀለበት የተጋጋበት አንዲሉ የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” ዜማ ከህወሃት አባላት በእህት ድርጂቶች የፓለቲካ አላዋቂዎች አና መሪዎች ይበልጥ ተዜመ! በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ተሰማ። ችግሩ የለውጥ ጥያቄ ማድበስበሻ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ሊቆይ አይችልም። በውሽት ላይ የተመሰረተ ፐሮፓጋንዳ ስር ሊይዝ አይችልም።አንዴት ይሄን ማየት አቃታቸው?!የሕዝባችን መከራና ሰቆቃ እየከፋ ሄደ።  የተጨቆነዉ ሕዝብ ተነሳስቶ ለመብቱ ሲታገል ጨቋኝ መንግሥታት ለዉጥ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፤ ካለዚያ በተባበረዉ የሕዝብ ኃይል ተንኮታኩተዉ ይወድቃሉ። የታገለዉ ለዉጥ ያመጣል፤ ያልታገለዉ ቁጭ ብሎ በባርነት ሲገዛ ይኖራል፤ ቁጭም ባለበት ይሞታል ማለት ነው። የለዉጥ ባለቤት ሁሌ ሕዝብ መሆን አለበት። ህዝቡ ትግሉን በሚገባ እንዲያቀናጅ የትግል መሪ ይፈልጋል።
ስለዚህ የተቃዋሚ የፖሊቲካ መሪዎች ታላቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። ያገራችንን ጭብጥ ሁኔታ ስንመረምር ግን በሁለቱም በኩል ታላላቅና ተደጋጋሚ ድክመቶች ታይተዋል። አምባገነን መንግሥታት ለዘለዓለም ካልገዛን ሲሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኅብረታቸዉን ማጠናከር ስላልቻሉ የጨቋኝ መንግሥታትን ዘመናት ሲያራዝሙ ቆይተዋል።ወያኔ/ኢሕአደግ ለዘለዓለም ሊገዛ አይችልም፤ ለሁሉም ጊዜ አለዉና።ትግሉ ይበልጥ መፋፋም፡ ይበልጥ መጨስ፡ መጋጋም፡ መንደድ ይጠበቅበታል። ትግሉን ለማፈንና አቅጣጫውን ለማሳት የወያኔ መንጋ እየተሯሯጠ ነው። በውጭ ያለውንም የሕዝብና የድርጅቶችን ተቃውሞ ቢቻለው ለማዳፈን፡ ካልሆነለት ደግሞ ለማዳከም፡ በአሁኑ ወቅት የወያኔ ከፋፋይ ቡድን በየቦታው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ እያየን ነው። ይህ ቡድንም፡ ምሁር ነን፡ አስታራቂ ነን፡ ሽማግሌ ነን ወይም ታጋይ ነን በሚሉ መሰሪዎችም እየተደገፈ ነው። የሕዝብ ክንድ ይላላ፡ ይደክም ዘንድ፡ በከፋፋይ ሴራ የተሰማሩትን ነቅቶ መጠበቅ፡ ትግሉን መከላከል ብቻ ሳይሆን ወያኔ ለባሾችን፡ ሰላዮችን ሳንፈራ እየመነጠርን ማጋለጥ ይኖርብናል። ዘረኛው ቡድንና ጭፍሮቹ የሕዝቡን ትግል ለመከፋፈል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጣሩ ናቸውና። ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ፡  የወያኔን ቡድን ለአንዴም ለሁሌም ለማስወገድ አስፈላጊውን መስዋእ ትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶችን እገዛና አመራር ይጠይቃል። የሕዝብ አሸናፊነት አጠራጣሪ ባይሆንም፡ አሸናፊ ለመሆን ግን መታገል መቅደም እንዳለበት ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ለዚህ መሠረቱ ግን ከራስ ጋር እየታረቁ፡ ከወገን ጋር እየተስማሙ በጋራ ዓላማና ብሔራዊ እጅንዳ ዙሪያ ተሰባስቦ በጋራ መታገል ብቻ ነው።
በዓለም ታላቅ ዝና ያተረፉት የግ/ቀ/ኃ/ሥና በአፍሪቃ አህጉር መሬትን ያንቀጠቀጠዉ የደርግ መንግሥት ቀናቸዉ ሲደርስ እንዴት እንደመነመኑና እንደከሰሙ መዘርዘር አይኖርብኝም፤ በታሪክ ፊት ተቀምጧልና። በሩቁም በእነ አሜሪካ ለረዥም ዓመታት ሲረዱና ሲደገፉ በነበሩት በእነ ሞቡቱ፤ የሻህ ንጉሥ፤ ሆስኒ ሙባረክ፤ ወዘተ ላይ በመጨረሻ የደረሰዉን ዉርደት መገንዘብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉትና በተግባር ግን የጭቆናን ዘመን የሚያራዝሙ በሙሉ ካለፉት ስህተቶች ገና ሊማሩ አልቻሉም፤ ・ድር ቢያብር እንበሳ ያስር・ የተባለዉን ቅዱስ አሳብ ደጋግመዉ መናቃቸዉ ያስተዛዝባል። ቁርጥ ያለ አቋም ያስፈልጋል፤ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ዬትም አያደርስም። ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅሞች በርካሽ መገዛትና አገርን መሸጥ በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል። ቀኑ ሲደርስ ራቆታችንን ወደምድር እነደመጣን ሁሉ ራቆታችንን ወደዚያዉ እነደምንመለስ አንርሳ!!!
ነገርግን በህብረት ለሀገር ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ዘላለማዊ የትዉልድና የሀገር ክብር ነዉ!!!
ከጎልጉል የተወሰደ

ዳር ድንበራቸው ለሱዳን ሊሰጥ መዘጋጀቱን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

ዳር ድንበራቸው ለሱዳን ሊሰጥ መዘጋጀቱን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

DC ethiopian sudan(ዘ-ሐበሻ) 1200 ኪሎ ሜትር የሚገመትን የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ጠዋት በዋሽንግተን ዲሲ የሱዳን ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ።
“የወያኔ መንግስት ሃገርን በመሸጥና በመክዳት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ በመስጠትና ነዋሪዎችንም በማባረር እየፈጸመ ያለው ወንጀል ዝም ሊባል” አይገባም የሚሉት እነዚሁ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሱዳን መንግስት ከዚህ ወንጀል ጋር ተባባሪ እንዳይሆን በተቃውሞ ሰልፋቸው ጠይቀዋል። በሰልፉ ላይ ከተሰሙ መፈክሮች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል።



Source :Zehabesha

wanted officials