Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, October 14, 2015

ሰበር ዜና የወያኔ ሰራዊት ለበተንቸሮ ላይ በግፍ ታረደ!!







ሰበር ዜና
የወያኔ ሰራዊት ለበተንቸሮ ላይ በግፍ ታረደ!!
የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት መንግስትን የገንዘብ ጥማት ለማርካት ሲባል ብቻ ወደ ሶማሌያ የተላከዉ የወያኔ ሰራዊት ከሳምንት በፊት ልዩ ስሙ ለበተንቸሮ ተብሎ በሚጠራዉ ከአሚሶም ወይም ከአፍሪህብረት ተብዬዉ ሰራዊት ክልል ዉጭ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን ከሰራዊቱ መካከል በተማረኩት 3 ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን ላይ አሰቃቂ ግድያ ተፈጸመባቸዉ።
አልሸባብ እየተባለ የሚጠራዉ ቡድንና የወያኔ ቡድን በሚያደርጉት በዚህ ጦርነት ዉስጥ ጭቁኑ የህዝብ ልጅ! የኢትዮጵያ ትዉልድ! እንደበግ እየታረደና በመኪና እየተጎተተ የመኪና ጎማ ስር ተንጋሎ ደሙ እንደ አልባሌ ሲወርድ ማየት ያሳዝናል!! ሲሉ መረጃዉን የላኩልን የኮነሬል የማነ ግ/ማርያም ዉስጥ አዋቂ ምንጫችን ገልጸዋል፤፤
በለበተንቸሮ ተደርጎ በነበረ የማጥቃት እርምጃ ወቅት ኪሳራ የደረሰበት ወያኔ ከተማረኩት ወታደሮች መካከል ሁለቱ አንገታቸዉን ተቀልተዉ ከተገደሉ በኋላ በመኪና እየተጨፈለቁ ለሌሎች ትእይንት የተደረጉ ሲሆን ሌላ አንድ የ24 አመት ምርኮኛ ከነህይወቱ በመኪና እየተጎተተ ስጋዉ እስኪላቀቅና አጥንቱ እስኪደቅ በስቃይ እንዲሞት ሆኗል።
የህዝብና የሐገራችን ጠላት የሆነዉ ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት በየወቅቱና በየጊዜዉ ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ወገኖቻችንን በማስጨረስ የሰራዉን እና እየሰራ ያለዉን ግፍ ለመበቀል መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ከህዝብ አብራክ የወጣህዉ የመከላከያ ሰራዊት ከህዝብ ጎን በመቆም በአንድነት በወያነ ጎጠኛ ቡድን ላይ አፈ ሙዙን እንዲያዞር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!
ወያኔ ይዉደም!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

ጉድሽ ወያኔ

ወገን እማማ ኢትዮጵያ ተርባለች … የድረሱልኝ ጥሪዋንም እያሰማች ነው?!


ወገን እማማ ኢትዮጵያ ተርባለች … የድረሱልኝ ጥሪዋንም እያሰማች ነው?!



የ1966ቱ እና የ77ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት ለወገኖቻችን እንድረስላቸው!

ከፍል- ፪



በዲ/ን ኒቆዲሞስ

በአገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተውን የረሃብ አደጋ አስመልክቶ ከሰሞኑን በመጀመሪያ ክፍል ያስነበብበኳችሁን ጽሑፍ ባወጣሁ ማግሥት አንዲት በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነች ወዳጄ የRFI ድረ-ገጽ ‹‹Sever Drought Threatens Millions of Ethiopia›› በሚል ርዕስ በአገራችን ስለተከሰተው ረሃብ የሚያትት ጽሑፍ በሾሻል ሚዲያ ላከችልኝ፡፡ ይህ የrfi ድረ ገጽ ያስነበበው ጽሑፍ እንደሚያትተው የኤሊኒኖ ክስተት በምሥራቅ አፍሪካና በኤዥያ በሚገኙ አገራት ባስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አገራችን በድርቁ በከፍተኛ ኹኔታ ተጠቂ መሆኗን ዘግቦአል፡፡



ይህ ዘገባም አገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1984-85 በርካታዎች ከቀዬአቸው በተፈናቀሉበትና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ካለቁበት የረሃብ ክስተት ጀምሮ አገሪቱ በምግብ እህል ራስን የመቻል ጥያቄ ውስጥ የወደቀች አገር መሆኗን በመግለጽ፤ የዘንድሮ በዝናም እጥረት ምክንያት የተከሰተው የድርቅም ከምሥራቅ አፋር ክልል እስከ ደቡብ ሶማሊያ ያለውን ሰፊ ቦታ እንደሚሸፍንና ረሃቡ በእነዚህ ቦታዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ማኅበራዊና ሰብአዊ ቀውስ እያደረሰ እንዳለ ይገልጻል፡፡

ይኸው rfi.fr ድረ ገጽ የተባበሩት መንግሥታት ባስነበበው ጽሑፉ ከጥቂት ወራት በፊት ያወጣውን ፬.፭ ሚሊዮን ተረጂዎች ቁጥር በአሁን ሰዓት ድርቁ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክልሎች በመስፋፋቱ የተነሣ ወደ ፰ ሚሊዮን እንዳሻቀበና ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ጠቁሟል፡፡

ይህን በአገራችን የተከሰተውን የረሃብ አደጋ በተመለከተ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ባደረጓቸው ሰፊ ምርምሮችና ጥናቶች የሚታወቁት የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ክርስቶፈር ክላፕሃም ለRFI በሰጡት ጠቅለል ያለ አስተያየት፡- ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት ዐሥር ዓመታት ድርቅን ይህን ተከትሎም ሊከሰት የሚችለውን ረሃብን ለመከላከልና ዜጎቼ በምግብ እህል ራሳቸውን የሚችሉበትን የተሳካ ውጤታማ የሆነ ሥራን ሠርቼያለሁ በሚልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነቱ የረሃብ አደጋ መከሰቱ ነገሩን እንቆቅልሽ ያደርገዋል ሲሉ ነው፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡

The Ethiopian government having established what is generally considered to be quite an efficient system for controlling the effects of drought and malnutrition is probably embarrassed and surprised that such a serious issue has risen, Christopher Clapham, a Professor specialized in the region at Cambridge University, told to rfi. አሳዛኙ እውነታ ደግሞ ይህ የረሃብ አደጋ በቀጣይ ዓመታትም ተባብሶ የሚቀጥል መሆኑን ነው ጥናቶች የሚጠቁሙት፡፡

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የኢትዮጵያ መንግሥት 33 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መድቦ ድርቁ የከፋ አደጋ ባደረሰባቸው የአገሪቱ ክልሎች አፋጣኝ የሆነ የምግብ እህል እርዳታ እያደረገ መሆኑን ቢናገርም የተባበሩት መንግሥታት ከሰሞኑን ባወጣው ዘገባ ግን ለረሃብ የተጋለጡ ወገኖቻችንን ቁጥር መሻቀቡንና እነዚህን ወገኖቻችንንም ለመታደግ ከ237 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ጠቅሶአል፡፡

መንግሥት ዘግይቶም ቢሆን በአገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ ለጋሽ አገራትና ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች እጁን እንዲዘረጉለት የተማጸነ ቢሆንም ድርቁ በአገሪቱ የጋረጠውን የከፋ የረሃብ አደጋና እልቂት በተመለከተ ግን ሰፋ ያለና የተብራራ መረጃ በመስጠት በኩል ጉልህ ችግር እንዳለበት የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መገናኛ ብዙኃን በሰፊው እየተናገሩና እየወቀሱ ነው፡፡

በአገራችን በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱትን የረሃብ አደጋዎች ከወዲሁ አስቀድሞ በመግለጽ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ረገድና በረሃብ የሚያልቁ ወገኖቻችንን ለመታደግና አደጋውን ለመቀነስ መወሰድ ስላለበት አፋጣኝ ዕርምጃዎችን በተመለከተ ትልቅ ችግር እንዳለ ግልጽ ነው፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት ፈጣን ልማትና ዕድገት እያስመዘገብን ነው፣ ሚሊዬነር የሆኑ አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን እያፈራን ነው፣ ረሃብ ካሁን ወዲያ ታሪክ ይሆናል እያለ ባለበት ወቅት እንዲህ ዓይነቱ አንገትን የሚያስደፋ የረሃብ አደጋ መከሰቱ ራሱን በደንብ መፈተሽ እንዳለበት ትልቅ መሳያ ይመስለኛል፡፡

ይኸው የረሃብ አደጋ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን በከተሞችም እየተስፋፋ ያለ መሆኑን መስማት፣ ማወቅ ደግሞ እጅጉን የሚያሰቅቅ ነው፡፡ የፌዴራሉ መንግሥት መቀመጫና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በሚገኙባትና የአፍሪካ ርእሰ መዲና በምትባለው በአዲስ አበባ ሣይቀር ባሉ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሕፃናት በረሃብ የተነሣ በትምህርት ገበታቸው ላይ እያሉ ተዘልልፍለፈው እወደቁ መሆናቸውንና እንዲሁም በኑሮ ውድነት ምክንያት በርካታ ቤተሰቦች በፈረቃ ለመብላት መገደዳቸውን በአገሪቱ የሚገኙ እንደ ሪፖርተር ጋዜጣና ሸገር ራዲዮ በተለያዩ ጊዜያት ዘግበዋል፡፡

በተለይ በብዙዎች ዘንድ አፍቃሪ ኢሕአዴግ፣ እንደው ያሰበውንና የተመኘውን ያህል ሰሚ ጆሮ፣ አስተዋይ ልቦና አላገኘም እንጂ የመንግሥት መልካም መካሪና ዘካሪ እንደሆነ አብዝቶ የሚታማው የሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው እሑድ ዕትሙ ርዕሰ አንቀጹ ላይ፡- ‹‹በድርቅ ለተጎዱትም ሆነ ለከተማ ድኅነት ፈጣን ምላሽ ያስፈልጋል›› በማለት ያስነበበው፣ በአደጋ ማስጠንቀቂያ የታጀበው ርዕሰ አንቀጹ አገሪቱ ያለችበትን እውነታና የተጋረጠባትን የረሃብ አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡

ዘንድሮ በአገራችን የተከሰተውን ድርቅና ይህንም ተከትሎ በአገራችን የተከሰተውን የረሃብ አደጋ በተመለከተ መንግሥትም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተው እየዘገቡት ነው ብሎ ለመናገር አያስደፍርም፡፡ ያው በታሪካችን እንደምናውቀው ሺዎች ከቀዬአቸው ካልተፈናቀሉና ካልሞቱ በስተቀር ‹‹ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም›› እንደሚባለው እየሆነ ያለ ነው የሚመስለው፡፡

ታሪካችን እንደሚነግረን በ፲፱፻፷ዎቹ በአገራችን ሰሜናዊ ክፍል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው ሲፈናቀሉና ለአሰቃቂ ሞት ሲዳረጉ የዘውዱ መንግሥት በክብረ በዓልና በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ነበር ተጠመዶ የነበረው፡፡ እናም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቹን ከቀዬአቸውና ላፈናቀለውና ለአሰቃቂ ሞት ለዳረጋቸው ለነበረው የረሃብ አደጋ ምላሽ የሰጠው ዘግይቶ ነበር፡፡

በወቅቱ ይህ የረሃብ እልቂት እንዴት ወደ አደባባይ ሊወጣ እንደቻለ በሰማኒያዎቹ በሰሜን አሜሪካ ይታተም በነበረው ‹‹ሰምና ወርቅ›› በተባለው ጥናታዊ መጽሔት ‹‹ድርቅና ጠኔ በኢትዮጵያ›› በሚል ጥናታዊ ጽሑፋቸው ውስጥ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እንዲህ ገልጸውት ነበር፡፡ በወቅቱ የረሃቡን መከሰት የሰሙት ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ ዶ/ር አሉላና ለሌሎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ባልደረቦቻቸው በግላቸው ሴስና አውሮፕላን ተከራይተው ረሃቡ የከፋ አደጋ ወዳደረሰበት ወደ አገራችን ሰሜናዊ ክፍል መረጃ ለመሰብሰብ ተጓዙ፡፡

ከወሬ ባለፈ በዓይናቸው ያዩትና ምስክር የሆኑበት የረሃብ አደጋና የወገኖቻቸው አሰቃቂ የሆነ እልቂት እጅጉን ልባቸውን የነካቸው እነዚህ ምሁራን በድርቅ የተጋለጡትን የአገሪቱን ግዛቶች፣ በረሃቡ የተነሣ እጅጉን የተጎዱትን ወገኖቻቸውን በማነጋገር በምስልና በቪዲዮ ያሰባበሰቧቸውን መረጃዎች በፕ/ር መስፍን አማካኝነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እንዲታይ ተደረገ፡፡

ይህን አሰቃቂ የሆነ የወገኖቻቸውን እልቂት፣ የሞት ጥላ ያንዣበባቸውን፣ ቆዳቸው ገርጥቶና አንጀታቸው ተጣብቆ፣ ከሰው መልክና ወዘና የወጡትን ወገኖቻቸውን፣ በእናቶቻቸው ደረት ላይ ተጣብቀው የሟች እናቶቻቸውን ጡት ሲመገምጉ የሚታዩ ሕፃናትን ምሰልና ቪዲዮ የተመለከቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ማኅበረሰብ ወገኖቻችን በረሃብ እያለቁ አንማርም፣ መንግሥት የረሃቡን እልቂት ለለጋሽ አገራትና ለዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ያጋልጥ በሚል ያስነሱት ዓመፅ ቀስ በቀስ ተባብሶ ለዘውዱ ሥርዓት መገርሰስ ምክንያት ሊሆን እንደበቃ እናውቃለን፡፡

ፕ/ሮ ጌታቸው ኃይሌ በዚሁ ጥናታዊ ጽሑፋቸው ላይ እንደሚያትቱት በወቅቱ ረሃቡ በአገሪቱ ላይ ያደረሰውን የከፋ እልቂት ያሰባበሱትን መረጃዎች ለኤምባሲዎችና ለውጭ አገራት በመስጠታቸው ረሃቡ ሊጋለጥ መቻሉንና ከዚሁ የ፷፮ቱ የከፋ የረሃብ እልቂት ጋራ በተያያዘ ስሙ በእጅጉ የሚነሳው ጆንታን ዲምቢልቢም ረሃቡ የከፋ አደጋ ባደረሰበት በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ተገኝቶ መረጃውን በዓለም ሁሉ እንዲናኝ ያደረገው ከነፕሮፌሰር ባገኘው መረጃ በመነሣት እንደሆነ ጠቅሰውታል፡፡

ፕ/ር ጌታቸው በዚሁ ጥናታዊ ጽሑፋቸው መደምደሚያ ላይም፡- ‹‹ኢትዮጵያ ትገብር ፋሲካ ታኅፂባ በደም ውሉዳ፣ ወንዞቿንም በከንቱ ወደ ግብጽ ምድር ሰዳ›› በማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን በፋሲካ በዓል ሌሊት፣ ካህናቱና ሊቃውንቱ ‹‹ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ታኅፂባ በደም ክርስቶስ››፣ ‹‹ምድር በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ታጥባና ነጽታ በሐሤትና በደስታ የፋሲካን በዓል ታድርግ!›› የሚለውን ማኅሌት ‹‹ኢትዮጵያ በአብራኳ ክፋይ በገዛ ልጆቿ ደም ተነክራና ታጥባ፣ ከፈጣሪ የተሰጣትንም የተፈጥሮ ጸጋ ወንዞቿን ሳትጠቀምባቸው እንዲሁ በከንቱ ወደ ምድር ግብጽ ሰዳ በዓለ ፋሲካዋን ታድርግ!›› በማለት አገሪቱ በረሃብ አለንጋ የምትገረፍ፣ ልጆቿ በረሃብ የሚያልቁባት፣ ትውልድ በእርስ በርስ ጦርነት የሚጫረስባት፣ የእልቂት ምድር፣ አኬል-ዳማ መሆኗን እንዲህ አመስጥረውታል፤ ገልጸውታል፡፡

የ፷፮ቱን ረሃብ ተከትሎ ከዐሥር ዓመት በኋላ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተከሰተው ድርቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ሲያፈናቅልና ብዙዎችንም ለሞት ሲዳርግ የደርግ መንግሥት ግን የአብዮቱን ፲ኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እያደረገ፣ ሰማይ ምድሩ ጠቦት ፌሸታ ላይ ነበር፡፡ በተመሳሳይም በዘመነ ኢሕአዴግም በዘንድሮው ዓመት ስለተከሰተው የረሃብ አደጋ ለሕዝቡም ሆነ ለለጋሽ አገራት በቂ የሆነ መረጃ በመስጠት አፋጣኝ የሆነ ዕርምጃ ተወስዷል ብሎ ለመናገር አያስደፍርም፡፡

ለአብነትም መንግሥት በወርኻ ክረምቱ ማብቂያ ላይ ‹‹የዲያስፖራ ቀን›› ብሎ በሰየመው ሳምንት በሺዎች ሚቆጠሩ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሰብስቦ በግብዣ ሲያንበሸብሻቸውና የልማታችን ውጤት ነው በሚል ፌሽታና ፈንጠዝያ ሲያደርግ በአገሪቱ ስለተከሰተው ድርቅና ስለተጋረጠብን ክፉ የረሃብ አደጋ በቅጡ አለመናገሩንና በቂ የሆነ የተብራራ መረጃ አለመስጠቱን ነው ያስተዋልነው፡፡ ወይስ መንግሥት ሆይ የድርቁ፣ የረሃቡ አደጋ ዜና ለመሆን የሚበቃው ሺዎችን ከቀዬአቸው ሲያፈናቅልና ለአሰቃቂ ሞት ሲዳርጋቸው ብቻ ነው ማለት ነው እንዴ …!?

በሌላም በኩል ከጠቅላይ ሚ/ሩ እስከ ታች ባሉ የወረዳ ካድሬና ሹመኛ ድረስ እስኪሰለቸን በነጋ ጠባ የሚነገረን፣ የሚደሰኮረው አገሪቱ አስመዝግበዋለች ስለሚሉት ባለ ኹለት ዲጂት ዕድገትና ፈጣን ልማት ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ዜጋ እንደ ኢትዮጵያዊ የአገራችን ፈጣን ዕድገትና ልማት ሁላችንንም ያስደስተናል፡፡ የሁላችንም ምኞት አገራችን በልጽጋና አድጋ፣ ሕዝባችንም ከስደትና ከጉስቁልና ወጥቶ ማየት ነው፡፡ ግና መንግሥት አገሪቱ አስመዝግበዋለች በማለት ከሚያስተጋባው ፈጣን የሆነ የልማትና የዕድገት ድምፅ ይልቅ የሚሊዮኖች ወጎኖቻችን የዋይታና የሰቆቃ፣ የእልቂትና የመከራ ድምፅ፣ እንባና ጩኸት በምድሪቱ ኹሉ ጎልቶና ደምቆ እያስተጋባ መሆኑን ልብ ሊለው ይገባል፡፡

ኢሕአዴግ ከአጋር ድርጅቶች ጋራ በመሆን ባለፈው ባደረገው ዓመታዊው ስብሰባውና ግምገማው የመልካም አስተዳደር እጦት ድርቅ መመታቱን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ለሥርዓቱ የከፋ አደጋ መሆናቸውን መማመኑንና ይህ አደጋም በአፍጢሙ ሊደፋው ያለ መሆኑን የገለጸበት እውነታ፣ የሙሰኛ ባለሥልጣናቱ ማን አለብኝነትና አምባ ገነንነት፣ ግፍና ዓመፃ፣ የፍትሕ ረሃብና የመልካም አሥተዳደር መታጣቱ ከተጋረጠብን የረሃብ አደጋ ባልተናነሰ ሕዝባችንን ክፉኛ አስጎብጦትና እንደ መርግ ተጭኖት፣ ምድሪቱን በእንባ አጨቅይቶ፣ የዋይታና የሰቆቃ ምድር እያደረጋት ነውና መንግሥት ቆም ብሎ አብዝቶ ሊያስብ፣ ሊጨነቅ ይገባዋል፡፡ አለዚያ አደጋው እጅጉን ሊከፋ እንደሚችል አያጠያይቅም!!

ይቀጥላል፡፡

ሰላም!

በቴፒ አንድ የፖሊስ አባል ሲገደል አምስት ፖሊሶች መታገታቸው ተሰማ

ኢሳት ዜና :-ለአመት የዘለቀው የቴፒ ግጭት በአካባቢው ለሰፈረው የፌደራል ፖሊስ እና ለፌደራል ባለስልጣናት እንቆቅልሽ ሆነ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ባለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 6 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ሚሊኒየም ጎዳና ላይ ወይም ሚካኤል አካባቢ ካሳሁን የተባለ የከተማው ፖሊስ አባል ተገድሏል። ፖሊሱ በቅርቡ ለከተማው ተመድቦ የመጣ ነበር። እርምጃውን የወሰዱት ራሳቸውን የቴፒ ወጣቶች ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ናቸው።
 ታጣቂዎቹ 5 የፌደራል ፖሊስ አባላትን አግተው ወደ አልታወቀ ስፍራ መውሰዳቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በእስር ላይ የሚገኙ ጓደኞቻቸው ካልተፈቱ ያገቱዋቸውን ፖሊሶች እንደማይለቁ ታጣቂዎቹ አስታውቀዋል። ኢሳት ስለታገቱት ፖሊሶች ከመንግስት በኩል ለማረጋገጥ አልቻለም። ይሁን እንጅ ወጣቶቹ ያገቱዋቸውን ፖሊሶች ፎቶ ግራፍ ለመንግስት ባለስልጣናት መላካቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በአካባቢው ያለው ውጥረት እንዳለ ቢሆንም፣ መንግስት ነዋሪው ህዝብ ለታጣቂዎቹ ድጋፍ ይሰጣል በሚል ፖሊስ ህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ወከባ ቀጥሎበታል። 

የፖሊስን ጫና በመፍራት በርካታ ወጣቶች እየተሰደዱ ነው። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በከተማዋ ሁለት የኢህአዴግ ካድሬዎችና 1 የፖሊስ አባል ሲገደሉ፣ ፖሊሶች ደግሞ አንድ ሰላማዊ ሰው ገድለዋል።

በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ ተረኛ ችሎት የወሰነውን ይግባኝ ሰሚ ሻረው

በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ ተረኛ ችሎት የወሰነውን ይግባኝ ሰሚ ሻረው
᎐የአቃቤ ህግ ይግባኝ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለው ጥቅምት 17/2008 ይወሰናል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ በተረኛ ችሎት ይግባኙ ያስቀርባል ቢባልም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ይህንን ውሳኔ በመሻር ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለውን ለመበየን ለጥቅምት 17/2008 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ዛሬ ጥቅምት 3/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የፓርቲ አመራሮቹ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሽ እና አብሯቸው ይግባኝ የተጠየቀበት አብርሃም ሰለሞን ዛሬ የቃል ክርክር እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ የነበር ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ግን በነሀሴ 15/2007 ዓ.ም ተረኛ ችሎት ይግባኙ ያስቀርባል ያለውን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው አቃቤ ህግ የይግባኝ አቤቱታውን እንደገና እንዲያሰማ አድርጓል፡፡
በመሆኑም አቃቤ ህግ የስር ፍርድ ቤት በአቃቤ ህግ የቀረቡትን የቴክኒክና የሰነድ ማስረጃዎች ይዘት በአግባቡ ሳይመረምር ውሳኔ ስለሰጠብን ውሳኔው አግባብ ስላልሆነ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ እንዲመረምርለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ይህንኑ የይግባኝ አቤቱታ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 17/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል በነጻ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው ተከሳሾች እስካሁን በእስር ላይ የቆዩበት ምክንያት አግባብ ስላልሆነ አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ተከሳሾች ገልጸዋል፡፡ እስካሁን በእስር ላይ ሊቆዩ የቻሉት ተረኛ ችሎቱ በሰጠው እግድ መሆኑ ቢገለጽም፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ግን አቤቱታው እንዲቀርብ ፈቅዷል፡፡ ተረኛ ችሎቱ ነሀሴ 15/2007 ዓ.ም ብይኑን ሲሰጥ ተከሳሾች ችሎት ሳይቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡


አስደንጋጭ ዜና ! ሀብታሙ_አያሌው‬ በጠና ታሞ ዘውዲቱ ሆስፒታል ገባ


በእስር ላይ የሚገኘው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት የነበረው‪#‎ሀብታሙ_አያሌው‬ በጠና ታሞ ዘውዲቱ ሆስፒታል ገብቶዋል ህመሙ ምን እንደሆነና ምን እንደደረሰበት የታወቀ ነገር የለም ሆስፒታል በትላንትናው እለት የገባ ሲሆን እስካሁኗ ሰዓት የተኛበት ክፍል በፖሊስ ተከቦ ማንም ቤተሰብን ጨምሮ ገብቶ እንዲያየው አልተፈቀደም።ማንም የቤተሰብ አበል እንዲያስተመው ወይም እንዲጎበኜውም አልተፈቀደም። ይህ የሚያሳየው አሰቃቂ ድብደባ ተፈጽሞበት ሚስጥር ለመጠበቅ ይሆናል።

Tuesday, October 13, 2015

ረሃቡ ከገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት የመነጨ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገለፀ

ረሃቡ ከገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት የመነጨ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገለፀ
• ‹‹ለችግሮቻችን ምንጭ የሆነውን ስርዓት በቁጥርጠኝነት መታገል አለብን››
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ መስከረም 27/2008 ዓ.ም በፅ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ረሃቡ ከገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት የመነጨ ነው ብሏል፡፡ ፓርቲው ‹‹ረሃቡ የገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት ነው!›› በሚል በሰጠው መግለጫ ‹‹ገዥው ፓርቲ ችግር ቢከሰት እንኳ በአደጋ ጊዜ ለዜጎች የሚበቃ እርዳታ አቀርባለሁ ሲል የነበረ ቢሆንም ለወገኖቻችን ግን የሚደርስላቸው አልተገኘም፡፡›› ሲል ወቅሷል፡፡ ‹‹ለዜጎች ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዳይደርሱላቸው የተፈጠረው ረሃብ የራሱ የፖሊሲ ውድቀት መሆኑን የሚያውቀው ስርዓቱ የዜጎቻችን ስቃይና መከራ ሲሸፋፍን እንደቆየና ከአቅሙ በላይ ሲሆን ችግሩ እንደተከሰተ ቢገልፅም ለዜጎች ተገቢውን እርዳታ በሚያስገኝ መልኩ እርምጃ እየወሰደ አይደለም›› ብሏል መግለጫው፡፡ ለተከሰተው የረሃብ አደጋ ተገቢው ትኩረት መነፈጉም ገዥው ፓርቲ እመራዋለሁ ለሚለው ህዝብ ደንታ ቢስነቱን የሚያረጋግጥ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ፓርቲው በመግለጫው ‹‹ረሃቡ፣ ርዛቱ፣ ድህነቱ፣ ስደቱ፣ ስራ አጥነቱ፣ የኑሮ ውድነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዜጎችን በብርቱ እየተፈታተኑ በሚገኝበት ወቅት ገዥው ፓርቲና በስሩ ያሉ ድርጅቶች ተመሰረትንበት የሚሉትን ጊዜ ለወራት በቅንጦት በማክበር በብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ከኢትዮጵያውያን ጉሮሮ ነጥቆ ድግስ ሲደግስና አሸሸ ገዳሜ ሲል በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል፡፡›› ብሏል፡፡ ለተከሰተው ረሃብ ኢህአዴግ ለይስሙላ ቆሜለታለሁ የሚለውን አርሶ አደርና አርብቶ አደርን ህይወት ለማሻሻል የረባ ስራ እንዳልሰራ አረጋግጧል ያለው መግለጫው ግብርናው ኢኮኖሚውን ይመራል ቢልም እስካሁን ግን በየአመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የረሃብ ሰለባ እንደሆነ መቀጠሉን ገልፆአል፡፡ መሬት የመንግስት ነው በሚል ሽፋን አርሶ አደሩን ከቀየው እያፈናቀለ ለስርዓቱና ደጋፊዎችና ለባዕዳን መሬትን እየሸጠ አርሶ አደሩን ለረሃብ ተጋላጭ አድርጎታል ሲልም ለርሃቡ ምክንያት የኢህአዴግን የፖሊሱ ውድቀት እንደሆነ ገልፆአል፡፡
ገዥው ፓርቲ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቀው ሰማያዊ ፓርቲ ስለ ችግሩ ለኢትዮጵያውያንና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚያስረዳ ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ በረሃብ ለተጠቁት ዜጎች መፍትሄ እንዲፈለግም ጠይቋል፡፡ ስርዓቱ ደካማና ኃላፊነት የጎደለው እንደሆነ የገለፀው ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያውያንና የዓለም ማህረሰብ ማህበረሰቡ ከተጎጅዎቹ ጎን እንዲቆሙ ጠይቋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያውያን መከራ የመነጨው ከገዥው ፓርቲ የተሳሳተ ፖሊሲ፣ የአፈፃፀም ብቃት ችግርና ለኢትዮጵያውያንም ባለው ግድ የለሽነት በመሆኑ ለችግሮቻችን ምንጭ የሆነ ስርዓት በቁጥርጠኝነት መታገል አለብን›› ሲልም ለህዝብ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ለብይን ተቀጥረው የነበሩት ጦማሪያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ



በተጠረጠሩበት የሽብርተኝነት ድርጊት ወንጀል ለብይን ለመስከረም 27 ቀን 2008 ዓ.ም. ተቀጥረው የነበሩት ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ አቤል ዋበላና በፈቃዱ ኃይሉ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡
zonee

ጦማሪያኑ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበት ምክንያት ደግሞ በዕለቱ በሌላ ሥራ ምክንያት ይሁን ወይም በሌላ ጉዳይ ባይታወቅም፣ ለብይን የቀጠሯቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዳኞች እንደሌሉ ተነግሯቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

ብይኑ በዕለቱ እንደሚሰጥ የገመቱ የጦማሪያኑ ቤተሰቦች፣ ጓደኞቻቸውና ጋዜጠኞች በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ የተገኙ ቢሆንም፣ የፍርድ ቤቱ ሠራተኞች ‹‹ዳኞች ስለሌሉ እንዳይመጡ መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ለማረሚያ ቤቱ ተደውሎ ተነግሮታል›› በማለታቸው ለመከታተል የሄዱ ታዳሚዎች ተመልሰዋል፡፡

የጦማሪያኑ ጠበቆች ግን በሁኔታው ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ፍርድ ቤቱ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማስታወቂያ መለጠፍና ጉዳዩን የሚከታተሉ እንዲረዱ ማድረግ ሲገባው፣ ምንም ሳይል መሄዱ አግባብ አለመሆኑንና ታይቶም እንደማይታወቅ ገልጸዋል፡፡

ጦማሪያኑ እንዲከላከሉ ወይም መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ የሚሰናበቱበት ብይን ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች በሙሉ ከመስከረም 26 ቀን እስከ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. አዳማ ሥልጠና ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

Monday, October 12, 2015

በሶማሊያ የተጎዱ ኢትዮጵያዊያን የሰላም አስከባሪዎች በኬንያ ሆስፒታል ተረስተዋል

በሶማሊያ የተጎዱ ኢትዮጵያዊያን የሰላም አስከባሪዎች በኬንያ ሆስፒታል ተረስተዋል 
--አስታማሚ ባለማግኘታቸው ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል
--115 ዶላር ብቻ ሲከፈላቸው መቆየታቸውንም ይናገራሉ
(በዛብህና በየነ እውነተኛ ስማቸው ለዚህ ጽሁፍ ሲባል ተለውጧል) ሁለቱም በሐያዎቹ አጋማሽ የዕድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ፤አገራቸውን በወታደርነት ለማገልገል ቅጥር የፈጸሙት ከዛሬ ስድስትና አራት አመታት በፊት ነው፡፡የትውልድ አካባቢያቸው የነበሩትን ዲላና ሆሳህናን ለቅቀው በተለያዩ ግዳጆች አገራቸውን እንደተመኙት ሲያገለግሉ ቆይተው የዛሬ አንድ አመት አካባቢ የተባበሩት መንግስታትን የሰላም አስከባሪ ሐይል በመቀላቀል በሽብርተኛው አልሻባብ ወደ ምትታመሰው ሶማሊያ አቅንተዋል፡፡
በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተግባራቸውን እየፈጸሙ በነበረበት አንድ መጥፎ ቀን በዛብህ በተተኮሰበት ሁለት ጥይት ሆዱ አካባቢ ተመትቷል፡፡ራሱን በህይወት ያገኘው ግን በሌላኛዋ ጎረቤት አገር ኬንያ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ነበር፡፡በየነ የተቀበሩ ፈንጂዎችን የመፈተሸ ግዳጅ ተሰጥቶት የያዘው የፈንጂ መጠቆሚያ መሳሪያና የተቀበረው ፈንጂ በመሳሳባቸው በተፈጠረ ፍንዳታ ሁለት እግሩንና የአንድ እጁን አንድ ጣት ለማጣት ተገድዷል የአንድ አይኑ የማየት አቅምም ክፉኛ መጎዳቱን ይናገራል፡፡
በዛብህና በየነ አደጋውን ካስተናገዱ በኋላ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲተኙ በመደረጋቸው ለመተዋወቅ በቅተዋል፡፡በየነ የተሰጠው ዊልቼይር ላይ ተቀምጦ በዛብህ መጽሐፍ ቅዱስ እያነበበለት ልጎበኛቸው በሄድኩበት ሰዓት አግኝቻቸዋለሁ፡፡ሰው የተራቡት ሁለቱ የአገሬ ልጆች የቅርብ የቤተሰቡን አካል እንዳገኘ ሰው እቅፍ አድርገውኝ ስመውኛል፡፡
‹‹የቋንቋ ችግር አለብን፣ካለንበት ሆስፒታል ሰዎች ጋር መግባባት አልቻልንም››፡፡በየነ እንባ አቅርሮ ይናገራል ‹‹እርሱን አጠገቤ ማግኘት ባልችል ኖሮ እንዴት አድርጌ ሁኔታውን እንደምለምደው አላውቅም፡፡ፈንጂው በፈነዳበት ወቅት አንድ እግሬ ተቆርጦ ሲቃጠል ተመልክቼው ነበር፡፡ አንደኛው እግሬ ቢቆስልም ሊድን ይችል እንደነበር አምናለሁ፡፡ነገር ግን እዚህ ከመጣሁ በኋላ ቆረጡት፡፡ለምን እንደቆረጡት እንኳን እስካሁን ለእኔ ግልጽ አይደለም››ብሏል ፡፡
ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ በኋላ ዲላና ሆሳህና ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለመገናኘት ቢያስቡም በየነ በፈንጂው አደጋ ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልኩ በመጥፋቷና የበዛብህ ደግሞ ለብልሽት በመጋለጧ ምንም ማድረግ ሳይችሉ መቅረታቸውን በሐዘን ተውጠው ይናገራሉ፡፡
‹‹የተባበሩት መንግስታትን ተልእኮ ተቀብላችሁ የዘመታችሁ በመሆናችሁ እንዴት እንዲህ ያሉ ጥቃቅን ነገሮችን እንኳን ሊያሟሉላችሁ አይችሉም ?›› በአግራሞት ተሞልቼ የወረወርኩት ጥያቄ ነበር፡፡
‹‹ወደ ሆስፒታሉ እንደመጣን አንድ ኮሎኔል የእኛን ሁኔታ እንደሚከታተል ተነግሮን የነበረ ቢሆንም ሰውዬው የሚመጣው በጣም እየዘገየ ነው፡፡የሚያደርግልን ምንም የተለየ ነገር የለም፣ እነርሱ ከህክምናችን ውጪ የሚያደርጉልን ምንም የለም››፡፡ለጥያቄዬ የሰጡኝ ምላሽ ነበር፡፡
ከሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች አጠገብ አንድ እግሩን በአደጋ ያጣ ጎልማሳ ኬንያዊ ተኝቷል፡፡በዛብህ ጣቱን ወደ ኬንያዊው እየቀሰረ ‹‹እባክህ ስለእኛ ሆነህ ይህንን ኬንያዊ አመስግንልን ፤ የእርሱ ቤተሰቦች ሊጠይቁት ሲመጡ አትክልት፣ምግብና ወተት ሁልግዜም ያመጡልናል››አለኝ፡፡
ወታደሮቹ በሆስፒታሉ ከሚያገኙት የህክምና፣የምግብና የአልጋ አገልግሎት ውጪ ምንም አይነት እርዳታ አያገኙም፡፡በየነ ሁለት እግሮቹን በማጣቱ መጸዳጃ ቤት የሚወስደው፣አልጋው ላይ የሚያወጣውና የሚያወርደው ረዳት ያስፈልገዋል፡፡በአሁኑ ወቅት ይህንን አገልግሎት እየሰጠው የሚገኘው በሁለት የሆዱ ክፍሎች ላይ ቀዶ ጥገና ያደረገውና ቁስሉ ያልደረቀለት በዛብህ ነው፡፡
‹‹በየነ በጣም ሰው ያስፈልገዋል፡፡እኔ ደግሞ እንደምታየኝ ቀዶ ጥገና ያደረግኩት በቅርቡ ነው፡፡ግን እርሱ ከእኔ በሚብስ ሁኔታ ውስጥ ስለሚገኝና ከእኔ ውጪ ሊረዳው የሚችል ሰው ባለመኖሩ እያመመኝም ቢሆን እረዳዋለሁ››ብሎኛል፡፡
በየነ አሁን ከሁሉም በላይ አገሩ መግባትን ናፍቋል፡፡‹‹በዚህ ሁኔታ መቀጠል ስለማልችል ወደ አገሬ እንዲወስዱኝ እፈልጋለሁ ቢያንስ ቤተሰቦቼ አጠገቤ ሆነው ሊያስታምሙኝ ይችላሉ››ይላል፡፡
ሁለቱ ወታደሮች በሶማሊያ ቆይታቸው በወር 115 የአሜሪካ ዶላር አበል እየተባለ ሲከፈላቸው መቆየታቸውን ይናገራሉ፡፡በየነ በፈንጂው ወዲያውኑ በተቆረጠው እግሩ ባጠለቀው ሱሪ ኪስ ውስጥ የተቀበለውን ዶላር አስቀምጦ እንደነበር በማስታወስ ፈገግ ይላል፡፡
ወታደሮቹ ምንም እንኳን ስለሚገኙበት ሆስፒታል የህክምና አሰጣጥ ባያማርሩም መረሳታቸው ግን ያበሳጫቸዋል፡፡ከአገራችን አልፈን ለአህጉሪቱ ችግር መፍትሄ ለመስጠት በተሰማራንበት ግዳጅ ጉዳት አስተናግደን የምንፈልጋቸውን ጥቃቅን ነገሮች ሊያሟልልን የሚችል ረዳት ከአጠገባችን ማጣታችን ቅስማችንን ሰብሮታል ይላሉ፡፡
በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ግዳጅን በመወጣት ላይ የሚገኙ 5000 ያህል ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡በኬንያ በተለይም በዋና ከተማይቱ ናይሮቢ የምትገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጉዳተኞቹ ወደሚገኙበት ሆስፒታል በማምራት እንድትጎበኟቸው ትጠየቃላችሁ፡፡

Human rights award for Helawit, daughter of man being held on death row in Ethiopia

Human rights award for Helawit, daughter of man being held on death row in Ethiopia
እንኳን ደስ ያለሽ ህላዊት አንዳርጋቸው ጽጌ በእስር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የ16 አመቷ ህላዊት አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ አባቷ የዲሞክራሲ ተጋድሎ በፃፈችው ጽሁፍ የሒውማን ራይትስ አዋርድ ተሸላሚ ሆነች ።

Helawit with Menabe and Yilak and her mother, Yemi
Helawit with Menabe and Yilak and her mother, Yemi. Below: Helawit at the award ceremony with Shami Chakra­barti, director of Liberty
Helawit at the award ceremony with Shami Chakra­barti, director of Liberty
Published: 9 October, 2015
by KOOS COUVÉE
THE daughter of a British man held on death row in Ethiopia has been lauded with a human rights award for a play she wrote with her friends about her father’s plight.
Helawit Hailemariam, 16, from Clerkenwell, was awarded the Christine Jackson Young Person Award by the charity Liberty in recognition of her ongoing battle for the release of her father, the Ethiopian-born democracy activist Andargachew Tsege, 60.
Liberty honoured a number of activists, young campaigners, artists and lawyers who champion “fundamental freedoms” at its annual Human Rights Awards last month.
“We need help for our campaign to get my father back,” Helawit, who is studying for her A-levels at City and Islington College in Angel, said. “I really did not expect to to win the award. It defin­itely helps our campaign, it makes my father’s story more real and it validates it.”
In June, Ask, a new play by Islington Community Theatre starring Helawit and five of her friends marked the anniversary of her father’s kidnapping on the command of the Ethiopian government while he was travelling through Yemen last year. He was on his way to Eritrea to attend an opposition conference.
Helawit said she wants to go on tour with the play too, in the hope this will put pressurise on the UK government to press the Ethiopians to release Mr Tsege. “I want the British government to listen and do much more. They haven’t done very much at all,” she added.
Ask will be performed at Hugh Myddelton primary school – which is attended by Helawit’s sib­lings Menabe and Yilak, both 8 – in the near future.
Until recently the Ethiopian authorities refused to tell his family where Mr Tsege, 60, was being held. But last month the UK ambassador met him at Kaliti jail, a notorious state prison located just south of the capital Addis Abbaba, commonly referred to as a gulag.
The family has not been allowed any contact. There is also no sign Ethiopia is following any kind of legal process.
Helawit's mother Yemi, 45, has been campaigning tirelessly for her partner's release. This week she wrote to foreign secretary Phillip Hammond to express her anger after Britain’s most senior Foreign Office official said human rights are no longer a “top priority” for the government, adding the Conservatives’ “prosperity agenda” was now “further up the list”.
“We are the human face of this policy,” she wrote.
Islington North MP Jeremy Corbyn, who has campaigned for Mr Tsege's release, said he would continue to do so “with the same vigour” now he is Labour leader.
“The release of Andy Tsege should be a political priority as his ongoing safety is a real concern,” he said.
“I have been working to secure the release of Mr Tsege for some time and I have given a firm commitment to his family that I will continue to press for his release now that I am leader of the opposition, with the same vigour.
“I am working closely with [human rights charity] Reprieve to this end and it is long overdue that the Prime Minister intervenes to help secure Andy's release as soon as possible".   
A petition calling on the Prime Minister to intervene with the Ethiopian government and demand the safe return of Mr Tsege has been signed by more than 127,000 people. It can be signed here. 
https://you.38degrees.org.uk/petitions/please-save-our-father-from-execution-in-ethiopia

የ16 አመቷ ህላዊት ስለ አባቷ አንዳርጋቸው ጽጌ የዲሞክራሲ ተጋድሎ በፃፈችው ጽሁፍ የሒውማን ራይትስ አዋርድ ተሸላሚ ሆነች ።

Human rights award for Helawit, daughter of man being held on death row in Ethiopia
እንኳን ደስ ያለሽ ህላዊት አንዳርጋቸው ጽጌ
 በእስር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ  አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ   የ16 አመቷ ህላዊት  ስለ አባቷ የዲሞክራሲ ተጋድሎ በፃፈችው ጽሁፍ የሒውማን ራይትስ አዋርድ ተሸላሚ ሆነች ።

Helawit with Menabe and Yilak and her mother, Yemi
Helawit with Menabe and Yilak and her mother, Yemi. Below: Helawit at the award ceremony with Shami Chakra­barti, director of Liberty
Helawit at the award ceremony with Shami Chakra­barti, director of Liberty
Published: 9 October, 2015
by KOOS COUVÉE
THE daughter of a British man held on death row in Ethiopia has been lauded with a human rights award for a play she wrote with her friends about her father’s plight.
Helawit Hailemariam, 16, from Clerkenwell, was awarded the Christine Jackson Young Person Award by the charity Liberty in recognition of her ongoing battle for the release of her father, the Ethiopian-born democracy activist Andargachew Tsege, 60.
Liberty honoured a number of activists, young campaigners, artists and lawyers who champion “fundamental freedoms” at its annual Human Rights Awards last month.
“We need help for our campaign to get my father back,” Helawit, who is studying for her A-levels at City and Islington College in Angel, said. “I really did not expect to to win the award. It defin­itely helps our campaign, it makes my father’s story more real and it validates it.”
In June, Ask, a new play by Islington Community Theatre starring Helawit and five of her friends marked the anniversary of her father’s kidnapping on the command of the Ethiopian government while he was travelling through Yemen last year. He was on his way to Eritrea to attend an opposition conference.
Helawit said she wants to go on tour with the play too, in the hope this will put pressurise on the UK government to press the Ethiopians to release Mr Tsege. “I want the British government to listen and do much more. They haven’t done very much at all,” she added.
Ask will be performed at Hugh Myddelton primary school – which is attended by Helawit’s sib­lings Menabe and Yilak, both 8 – in the near future.
Until recently the Ethiopian authorities refused to tell his family where Mr Tsege, 60, was being held. But last month the UK ambassador met him at Kaliti jail, a notorious state prison located just south of the capital Addis Abbaba, commonly referred to as a gulag.
The family has not been allowed any contact. There is also no sign Ethiopia is following any kind of legal process.
Helawit's mother Yemi, 45, has been campaigning tirelessly for her partner's release. This week she wrote to foreign secretary Phillip Hammond to express her anger after Britain’s most senior Foreign Office official said human rights are no longer a “top priority” for the government, adding the Conservatives’ “prosperity agenda” was now “further up the list”.
“We are the human face of this policy,” she wrote.
Islington North MP Jeremy Corbyn, who has campaigned for Mr Tsege's release, said he would continue to do so “with the same vigour” now he is Labour leader.
“The release of Andy Tsege should be a political priority as his ongoing safety is a real concern,” he said.
“I have been working to secure the release of Mr Tsege for some time and I have given a firm commitment to his family that I will continue to press for his release now that I am leader of the opposition, with the same vigour.
“I am working closely with [human rights charity] Reprieve to this end and it is long overdue that the Prime Minister intervenes to help secure Andy's release as soon as possible".   
A petition calling on the Prime Minister to intervene with the Ethiopian government and demand the safe return of Mr Tsege has been signed by more than 127,000 people. It can be signed here. 
https://you.38degrees.org.uk/petitions/please-save-our-father-from-execution-in-ethiopia

ተመስገን ደሳለኝ በግፍ ከታሰረ አንድ አመት ሞላው! Bro. Temesgen Just one year in jail





ከአቻምየለህ ታምሩ

ፈላጭ ቆራጭ አምባገነኖች ባሉበት ሁሉ የጀግና ማደሪያው እስር ቤት ነው። ተመስገን ደሳለኝም የአዕምሮው የበላይነት በቀሰቀሰው ፍርሀት ሳቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስትነት በተሰየመው ሽፍታ ቡድን በግፍ ከታሰረ ይሄው አንድ አመት ሞላው። በመሰረቱ የወያኔ ፖለቲካ የጀግኖች የአዕምሮ የበላይነት የቀሰቀሰው ፍርሀትና ጥላቻ ነው። በመንግስትነት የተሰየሙት እነዚህ ሽፍቶች የአዕምሮ የበላይነት ያለውን ሰው ሁሉ መታሰቢያው ከምድር እንዲጠፋና በዓለም እንዳይኖር በማድረግ ድምፅ ያልነበረው ህዝብ ድምጹ እንዲጠፋ በማድረግ ከብርሃን ወደ ጨለማ ይመልሱታል። ለወያኔዎች ፖለቲካ ማለት ከተቻለ ሁሉን ወደ ዞምቢነት መቀየር፤ካልተቻለ ደግሞ አሳዶ ማሳደድ ነው፤ ምክንያቱም እነሱ የእድገት ተስፋቸውን ያቆራኙት የአዕምሮ የበላይነት ካላቸው ሰዎች ውድቀት ጋር ነውና!

ስለ ተመስገን ደሳለኝ ስጽፍ ውዬ ስጽፍ ባድር ተመስገንን በሚገባው መጠን የገለጽሁት መስሎ አይሰማኝም። ተመስገንን ሳስበው ሁልጊዜ አስቀድሞ ወደ ህሊናየ የመሚጣው ግን እንደ ሰው ተፈጥሮ፣ እንደ ሰው ማሰብና እንደ ሰው መኖር ያልተሳነው የዘመናችን ጀግና መሆኑ፤በቁሳዊ አለም ውስጥ እየኖረ በጎ ሰውነቱ ግን ሞልቶ የተትረፈረፈ አይበገሬና ቆስቋሽ ብዕረኛቱ ነው።

እንደ አንድ አገር ወዳድ ዜጋ ተሜ ለአገሩ የሚጠበቅበትን በማድረጉና ለህሊናው ተገዢ በመሆኑ ያልተደሰቱበት ዞምቢዎቹ ወያኔዎች በግፍ ዘብጥያ አውርደውት ሰቆቃ እየፈጸሙበት የጭካኔያቸው ማርኪያ ማድረጋቸው ሳይበቃ፤ እነሱ በየእለቱ በሚፈጽሙበት ጭካኔ እየተደሰቱ በፍቅር የሚሳሱለት አሮጌ እናቱ ግን በወር አንዴ እንኳ አይኑን አይተውት የልጅ ናፍቆታቸውን እንዳይወጡ አርቀው ማሰራቸው ሳያንስ በደካማ ጉልበታቸው ክህመም ጋር እየታገሉ የልጅ ነገር ሆኖባቸው በታሰረበት የዝዋይ እስር ቤት ሊጠይቁት ሲሄዱ እንኳ እንዳይጠይቁት በመከልክል ሁለት ትውልድ ሰዎችን የደም እንባ እያስለቀሱ ይገኛሉ።

ተመስገን ደሳለኝን በቅርብ የማውቀው ወንድሜ ነው፤ እንደ ጽሁፉ አንባቢም አብሮት እንደሰራም ሰው የማደንቀው ጎልማሳ ነው። ተሜ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን አሰልፎ «ተራሮችን በነፍጥ እንዳንቀጠቀጠ» የሚደሰኩረውን የወያኔ ቡድን ብቻውን በብዕሩ ያንቀጠቀጠ የዘመናችን ትንታግ ጋዜጠኛ ነው። ተመስገን ደሳለኝ ከምርጫ 97 በኋላ በተፈጠረው የለውጥ ስሜት መጨናገፍ ሳቢያ «ተስፋ ቆርጦ አንድ ላይ ከመቆም፡ ይሻላል በተስፋ ሲጓዙ መክረም» የሚል መንፈስ በሰላማዊ ትግሉ ጎራ እንዲያንሰራራ ታላቅ ስራ የሰራ የህዝብ ልጅ ነው ብዬ አምናለሁ።

ተመስገን ደሳላኝ ዘርፈ ብዙ ስብዕና የተላበሰ የቀለም ቀንዲል ነው። ተመስገንን በወዳጅነት ለመጎዳኘት ለቀረበው ሰው፡ እሱ ግንኙነቱን ወደ ወንድማዊ/ እህታዊ መተሳሰር ለውጦት ያገኘዋል። እኔ ግን ከተሜ ወንድማዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊና ሞያዊ በረከትም የተቋደስሁ ሰው ነኝ። ይህንንም እሱ ያሳትማት በነበረች መጽሄት ለመጀመሪያ ጊዜ ባሳተምሁት ጽሁፌ ገልጨዋለሁ። ተሜን አንድ ሰው አዲሳባ ለሆነ ጉዳይ ማግኘት ፈልጎ ለቀጠረውም ሆነ በእንግድነት ሊጎበኝ ወጣ ባለባቸው ያገራችን ክፍሎች ሁሉ፤ በእግድነት የሚያስተናግደውን ሰው እንግዳ ያደርገውና ራሱን እንግዳ ተቀባይ አድርጎ የሚያስተናግድ ሰው ነው። ከዚህም አልፎ ተመስገን፣ ሌሎች ጓደኞቹም እንደሚመሰክሩለት፣ እጁን ዘርሮ የማይታክትና የማይነጥፍ ምንጭ ነው።

ተመስገን ከዘመን ተጋሪዎቹ አልፎ በመሄድ፣ በተባ ብዕሩ፣ ባዲስ አቀራረብ፣ የፖለቲካና የሲቪል ነጻነት ሐሳቦችን ለወገኖቹ ኢትዮጵያውያን ለማሳወቅ የተጋ፣ ሌት ተቀን ታግሎ ያገሩ ልጆች የመንፈስ ግዛታቸውን ለማስፋት የጣረ ምርጥ ሰው ነው። እንደ ተሳለ ካራ በምታበራው ብዕሩ ሀሳብ አፍልቆ የወቅቱን አስገባሪ ቡድን ድብቅ ድርጊት ባደባባይ ለህብረተሰባችን እያጋለጠ ለኋላ ቀር ገዢዎቻችን የእግር እሳት፣ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ የንቃተ ህሊና መብራት የሆነ የእናት አገሩ የስለት ልጅ ነው።

ለተሜ ፖላቲካ በእውቀት የተሻሉ ሰዎች ህዝብን ለማገልገል ያስተሳሰብና የተግባር ፉክክር የሚያደርጉበት እንጂ ልክበር፣ ልሰር፣ ልግደል፣ ልበድል፣ ባይ ልቦናን ድል ሳያደርግ ዳግማዊ ሚኒልክ ቤተ መንግስትን መቆጣጠር ስላልሆነ፤ የመንግስትነት ጠባይ ሳያሳይ 24 ዓመታትን አገባድዶ 25ተኛውን የግፍ ዘመን ለማክበር ተፍ ተፍ እያለ ያለውን ቡድንም ፣ «መለስ ሆይ፡―ክልምኖም ይስምዑኒ» እያለ አደብ እንዲገዛ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል።

ፍርሀትና ጥላቻ ሆደ ጠባብ እንዲሆን ያደረገውን ይህን በመንግስትነት የተሰየመ የባሪያ አሳዳሪዎች ቡድን፤ ከሩብ ክፍለ ዘመን የመንግስትነት ቆይታ በኋላም በዕውቀትና በጥበብ ከፍ ያለ አእምሮ ያላቸውን ሰዎች እያሳደደ፣ ከሰውነት ጠባይ ወጥተው ሲሰሩ ያገኛቸው ይመስል የሃጢያት ክስ እየደረደረ፣ እልቆ መሳፍርት ምርጦችን አሳጥቶ ዛሬ ራቁታችንን አቁሞን ይገኛል።

የተሜ የሀጢያት ክስ ሲገለጥ እንደ ሌሎች የህሊና እስረኞች ሁሉ «ጥፋቶቹ» ተመሳሳዮች ናቸው። ከጥፋቶቹ መካከል እንደ ገዢው ቡድን የተወለዱበትን አካባቢና የተዛመዳቸውን ብቻ አገሬና ወገኖቼ ብሎ አለመለየቱ፤ በሰፊው አስተያየት ገምቶ የሰውን ዘር ሁሉ እንደ ወንድም ባለማስተዋል ወገኔ ዘሬ ባለማለቱ፤ልቦናውንና አእምሮውን በጥበብና በስልጣኔ ያለሰለሰ ሰው ሆኖ መገኘቱ፤ አገሩን በጠባቡ ክልላዊ ጠረፍ ወስኖ ሰው ያለበትንና ተሰርቶ የሚታደርበትን ሁሉ አገሬ ነው በማለቱ የተነሳ እና ሌሎች ዝባዝንኪ ሰበቦችም ተደርድረውበታል።

እውነቱ ግን ተመስገን፡ ሁሌ በሚጽፋቸው ጽሁፎቹ ለጆሮ የሚቀርቡ ጉዳዮችን እያነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ ከገዢዎቹ ተላቆ በህሊናው መሪነት የገዛ ራሱ አስተዳዳሪ ወደሚሆንበት ምድረ ርስት ለማድረስ የታተረ ጀግና ነው። ይህ ጠቢብ ባሁኑ ወቅት ያለው አገዛዝ እጅግ አጥቦት ካለው የህይወት መስክ ኢትዮጵያውያን ወጥተው፡ እውቀት ከሚያስገኘው የነጻነት ሰፊ ሜዳ ገብተው እንደልባቸው ተዝናንተው እንዲራመዱ፡ ብርቱ የሆነ የሰለጠነ ትግል እንደሚያስፈልግ በመምከሩ እንደ ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ በጨለማ እስር ሆኖ በተፈጸመበት ግፍ ምክንያት ጀርባው አብጦ፤ግራ ጆሮው ሙሉ ለሙሉ መስማት አቁሞ ስለእኛ እጅግ ብዙ መስዕዋትነትን እየከፈለ ይገኛል። በዘመነኞች ተዓብዮ እንዲህ የህዝብ ልጆች ስቃይና ግፍ ሞልቶ ሲፈስ ሰሚ ቢጠፋም መጪው ትውልድ ይፋረድበት ዘንድ የነተሜን ስቃይና ግፍ የኢትዮጵያ አፈርና ቅጠል ሰምቶ በታሪክ መዝገብነት ቀርጾ አስቀምጦታል።

ተሜ የዘመናችን አቤ ጉበኛ ነው። በችሎታው ስለሚመካ፣ ስለሚጽፈው ጽሁፍ ብዙ አይጨነቅም፤ ለሱ እንደማንኛውም ነገር የሚሰራው ስራ ለህትመት ሲበቃ ብዙ አንባቢን ያነጋግራል። ተመስገን፡ የብእር ትሩፋትን፡ እንደ ቅኔ መምህሩ ስብረ አብ፡ ሁለት ቤት ቅኔ፡ እንዲነበብ አድርጎ ያስተዋወቀ ታላቅ ብእረኛ ነው። ተሜ በteam work የሚያምን፣ ፈገግታ የማይለየው፣ ሞያውን የሚያከብር፣ በስሩ አብረውት የሚሰሩትን የሞያ ጓደኞቹን ችሎታ የማይጋፋ፡ይልቁንም የሚያከብር፣አድናቆትና ምስጋናውን ያላንዳች ስስት የሚቸር፣ መታበይና ትክሻን መስበቅ የማያውቅ፣ መስሪያ ቢሮውና መኖሪያ ቤቱ ሳይቀር ለሁሉም ክፍት የሆኑ፣ በህትመት መገናኛ ብዙሀን አዲስ አሰራር ፈር የቀደደ የህዝብ ድምጽ ነው። ይህንን አንደበት እስር ቤት ቆልፎ እንዲሰቃይ ማድረግ የሚያም ትልቅ አገራዊ ጉዳት ቢሆንም ቅሉ፤ የእርሱ መታሰርና መሰቃየት ለሀገሩ የሚገባውን ሰርቶ ነውና እኛ ያልታሰርነውና ከእስር ያመለጥነው እርም አንልም! ተሜ ሆይ ተመልሰን የምንገናኝበት ቀን ግን ሩቅ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። 

እስከዚያው ባለህበት ሰላም ሁን!

Sudan, S Sudan border demarcation mechanism meets in Addis Ababa ,when ETH-Sudan boarder dispute


Meetings of Sudanese and South Sudanese officials are ongoing in Addis Ababa under the auspices of the African Union Border Program. The meetings are about implementation of the 2012 Cooperation Agreement between the two countries.

The AU Commissioner for Peace and Security, Ismail Chergui met South Sudan’s Minister of Information and Broadcasting, Michael Makuei Lueth and State Minister at the Sudanese Presidency Al-Rashid Haroun in Addis Ababa.

The two Sudans still have disputes over areas that include Abyei, 14-Mile area, Joudat Al-Fakhar, Jebel al-Megenis, Kaka, and Kafia Kingi enclave (Hofrat al-Nihas).

In a statement, the AU commissioner stressed the importance of building on the current momentum between the two countries in order to give more impetus to peace efforts in the region.

Chergui further said the positive atmosphere at the meeting and the cooperation between the two parties with the AU commissioner including the commitment of their respective governments will push for the demarcation of the common borders between both countries.







wanted officials