Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 25, 2016

“ግማሹ መሬቱን… ሌላው ማንነቱን በወያኔ ሲነጠቅ!!” – ከአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማኅበራት ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ


australia ethiopians
በኢማማምአ የተሰጠ መግለጫ!!
እ.ኤ.አ 21/07/2016
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እነ ከተማ ይፍሩና እውቁ ደራሲ አዲስ ዓለማየሁ ከዚያ ዘመን ትውልድ ራሳቸውን እጅግ በጣም ተራማጆች አድርገው ይቆጥሩ ስለነበር በወቅቱ በምሥራቁ አውሮፓ የተራማጅነት ምልክት ተደርጋ የምትቆጠረውን ቀይ
ባጅ (ምልክት) በእግራ የደረት ኪሳቸው ላይ ይሰኩ እንደነበር የዚያ ትውልድ መጻጽፎች በዋቢነት የሚጠቀሱ ሲሆን እንዲሁም በዓለማችን የተለያዩ ጠንፍ ላይ የሚገኙት እነ ቸጉቤራና ሆቺሚን የኢትዮጵያን የአምስት ዓመት የአርበኝነት የነፃነት የሽምቅ ውጊያ ስልትን ለነፃነት ትግላቸው በያሉበት በዋቢነት መጠቀሙ እንዳለ ሆኖ የቸጉቤራ ለሰው ልጆች እኩልነት ሲል (በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ቅኝት ለማለት ነው) የወጣ የወረደባቸው ጋራ ቁልቁለቶችና የዘመራቸው የእኩልነት መዝሙሮች እንደ ሰደድ እሳት በአዲሱ ትውልድ ሕሊና ውስጥ በመቀጣጠላቸው በሂደት በ1960ቹ አጋማሽ አካባቢ በነ አዲስ ዓለማየሁ እግር የተተካው ኢትዮጵያዊው ወጣቱ ምሁርና በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች እጅግ በጣም ቀልብ የሚስቡ
ብሔራዊ መፈክሮችን አንግበው ለአብነት ያህል “መሬት ላራሹ፣ ሕብረተሰባዊነትና እኩልነት፣ ሕዝባዊ መንግሥት፣ ወ.ዘ.ተ” የመሳሰሉትን በግልጽና በድፍረት በአደባባይ ያስተጋቡ ነበር::


ሞተ የተባለው ታጋይ ተስፋሁን አለምነህ ኤርትራ በወታደራዊ ስልጠና መቆየቱንና ችግር እንዳላገኘው ገለጸ

ታጋይ ተስፋሁን አለምነህ ኤርትራ በወታደራዊ ስልጠና መቆየቱንና ችግር እንዳላገኘው ገለጸ

 ተስፋሁን ሞተም ሆነ ሌላ ስለኔ የተባለውን አልሰማሁም።ኤርትራ ከገባሁ ጀምሮ ችግር አላገኘኝም እንቅፋትም መቶኝ አያውቅም  ስራ ላይ ነበርኩ ስልጠና ላይየተለያየ ግዳጅ ላይ ነበርኩ።ምንም አልሰማሁም። በአገር ቤት ያለውን አሁን በጎንደር ያለውን ግን እሰማለሁ እንከታተላለን። … > ታጋይ ተስፋሁን አለምነህ የቀድሞየመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ስለሱ በኤርትራ ሞቷል ወይ ታስሯል ስለሚባለው ኤርትራ ደውለን በቀጠሮ ሰሞኑን ባነጋገርነው ወቅት ከተናገረው ሙሉውን ያዳምጡ


Sunday, July 24, 2016

German police: Munich shooter planned crime for a year


German police: Munich shooter planned crime for a year

German police say the teenager who killed nine people during a shooting rampage in Munich had been planning the attack for more than a year. Investigators also said the perpetrator bought his weapon over the internet.



The 18-year-old gunman behind the shooting spree at a Munich shopping center "had been preparing for a year," Bavarian police chief Robert Heimberger told a press conference Sunday.

Heimberger said the German-Iranian teen, identified only as David S., visited the site of a 2009 school shooting in the southwest German town of Winnenden and took photographs. He added that material found at the shooter's home showed he had likely obtained his Glock 17 pistol illegally through the internet's "dark net" market, and was an avid player of first-person shooter video games like "Counter-Strike."


Robert Heimberger (L) and Thomas Steinkraus-Koch address journalists in Munich

Mourners have laid flowers and candles at the Olympia shopping center where David S. fatally shot nine people on Friday night before turning the gun on himself.

On Sunday, authorities raised the number of injured people from two dozen to 35.

Most of the dead were teenagers, and six had a non-German background, police said. Prosecutor Thomas Steinkraus-Koch told journalists on Sunday that investigators had concluded the gunman had chosen his victims randomly and did not appear to be motivated by a political ideology.

"It is not the case that he deliberately selected" the people who he shot, he said. He also revealed that the teenager had spent two months in a closed psychiatric ward in 2015 and received treatment for social phobias and anxiety.


People gather to mourn and lay flower tributes near Munich's Olympia shopping center

Officials have ruled out any connection to extremist group "Islamic State," which has claimed responsibility for recent attacks in Paris and Belgium. However, they have pointed to an "obvious link" between Friday's killings and the massacre of 77 people by white supremacist Anders Behring Breivik in Norway in 2011.

Breivik's attack took place five years to the day before the Munich shooting. Bavaria's interior minister said a copy of Breivik's manifesto had been discovered on the 18-year-old's computer.

አሳሳና አዳባ በህዝብ ተቃውሞ እየተናጡ ነው – ተቃዋሚዎች የአላሙዲ አጥሮችን ለመንገድ መዝጊያ እየተጠቀሙበት ነው


adaba adabs asasa 2 asasa asasa.jpg2
 ምዕራብ አርሲ አሳሳና አዶላ በህዝብ ተቃውሞ ውጥረት ውስጥ እንዳሉና አካባቢውም በአጋዚ ሰራዊት ቢወረረርም ሕዝቡ የተለለያዩ ነገሮችን በየአደባባዩ በማንደድ በአጋዚዎች ላይ መንገድ በመዝጋት ላይ እንደሚገኝ የሚደርሱን መረጃዎች ጠቁመዋል::
እንደ መረጃዎች ከሆነ በም ዕራብ አርሲ አሳሳ ከተማ ከሕዝብ ተቀምቶ ለአላሙዲ የተሰጠው መሬት የታጠረበትን አጥር ሕዝብ ነቃቅሎ መንገድ እየዘጋበትና እያቃጠለበት እንደሚገኝ የዜና ምንጮች አስታወቀዋል::
በተመሳሳይም በአዳባ ከተማ እንዲሁም የመንግስት እርሻዎች የታጠሩበት አጥሮች እየተገነጣጠሉ አጋዚ ወደ ከተማው እንዳይገባ በ እሳት እየተቀጣጠለና ለመንገድ መዝጊያነት እንዲውል መደረጉ ታውቋል:: በድንጋይ እና በሚቀጣጠል እሳት መንገዶች በመዘጋጋታቸው በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት የመኪና እንቅስቃሴ በአካባቢው እንደሌለ ተረጋግጧል::
ምዕራብ አርሲ በዶዶላ; በአሳሳና በአዳባ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ነው:: ህዝቡም ጮክ ብሎ ተቃውሞውን በመንግስት ላይ በመግለጽ ላይ ይገኛል::



Saturday, July 23, 2016

የጎንደር ዜናና ብአዴን – ግርማ ካሳ

13669846_228558014204928_6547288386076616196_nዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ጎንደር ላይ ሲካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደሚቀጥለው ሳምንት ማለት ወደ ሐምሌ 25 ቀን 2008 ዓ.ም እንደተዘዋወረ መረጃዎች እየወጡ ነው። ከጥቂት ቀናት በፊት የአገር ሽማግሌዎች ከክልሉ አስተዳደር ጋር ባደረጉት ዉይይት፣ አስተዳደሩ ለ10 ቀን ሰልፉ እንዲራዘም መጠየቃቸው ይታወሳል።
ለሰላም ሲባል የክልሉ አስተዳደር ጥያቄን በማክበር እና በጎንደር ዙሪያና በሌሎች የአገራችን አካባቢዎች የሚኖሩ ወደ ጎንደር ከተማ እንዲመጡ ሁኔታዎችንም ለማመቻቸት ሲባል እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
በተያያዘ ዜና በብአዴን ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ መከፋፈል እንዳለም ይነገራል። ታማኝ ምንጮዎቸ በመግለጽ አንድ ታዋቂ የፖለቲክ አክቲቪስት እንደ ጦምረው ብኢዲን ክሦስት ተክፍሏል ።
የመጀመሪያው ክፍል የክልሉ አስተዳዳሪ የሆኑት እነ ገዱ አንዳርጋቸው ያሉብት፣ አብዛኛው የብአዴን አባላት የደገፉት፣ “የአማራ ው ህዝብ ተወካዮች እስክሆን ድረስ የሕህት የበላይነት ይብቃ” የሚል አለመካከት ያላቸው ሲሆን፣ ይህ ቡድን ክፍተኛ የህዝብ ደጋፍ ያለው ቡድን ነው። አቶ ገዱን ጨምሮ፣ የተወሰኑ የፖሊት ቢሮ አባላት ያሉበት ሲሆን፣ ከግማሽ በላይ የሆኑ የማክላዊ ኮሚቴ አባላትን ያካተተ ነው። መካክለኛው እና ዝቅተኛ የሆኑ የብአዴን አመራሮችና አባላት በብዛት ማለት ይቻላል የሚደገፉት ቡድን ነው። ከአንድ አመት በፊት በባህር ዳር ብአዴን ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ” እነርሱ ባለ ፎቅ እና ሎተሪ ሻጭ” በሚል የጉባኤው አባላት በሕወሃት ላይ እየደጋገሙ ምሬታቸውን ሲገልጹ እንደነበረም የሚታወስ ነው።
ሁለተኛው ቡድን እነ ብናልፍ አንዱለምን ያካተተ የመሀል ስፋሪ ቡድን ነው። የተወስኑ ስዎችን የያዘ ስልጣን ናፋቂ ቡድን፣ ግን በሚደረገው የዉስጥ ትግል አሽናፊው ማን እንደሆነ እየተጠባብቀ ያለ ቡድን።
ሶስተኛው በአለምነህ መኮነን፣ ደመቀ መኮንን …ያሉበት የወያኔ አሽክርነት የሚደግፉ ነባር አመራሮች ያካተተው ቡድን ነው። ይህ ቡድን በሕወሃት አዝማችነትና ትእዛዝ የሚንቀሳቀስ እንደሆነ ይነገርለታል።
አቶ ደምቀ ተቀዳሚ ም/ጠሚኒስቴር ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የየአማራው ክልል ከፍተኛ ትንቅንቅ ከሕወሃት ጋር እያደረገ ባለበት ወቅት፣ ህወሃቶች በሚቆጣጠሩት ሜዲያ ህዝቡ እያስፈራሩና እየሰደቡ ባለበት ወቅት ዝምታን የመረጡ ደካማ አመራር ናቸው።
አቶ አለምነህ መኮንን ከፍተኛ የሕወሃት ጥበቃ የሚደረግላቸው የክልል /ፕሬዘዳንት የሆኑ ሰው ናቸው። የአማራውን ክልል ህዝብ ” ምንም ሳይኖረው የሚመጻደቅ፣ በእግሩ የሚሄድ ልፋጫም የሆነ” በማለት መሳደባቸው፣ ያንንም ተከትሎ ድፍን የባህር ዳር ሕዝብ ወጥቶ ሰዉዬዉን ማወገዙ ይታወቃል። ሆኖም የሕወሃት ጋሻ ጃግሬ በመሆናቸው ያን ያህል በሕዝብ የተጠሉ ሰዉዬውም ቢሆኑም፣ አሁንም በስልጣናቸው ላይ ናቸው። ህወሃቶች በተለያዩ ጊዜ ግምገማ እያሉ አቶ ገዱን በማንሳት አቶ አለመንሀን የክልሉ አስተዳዳሪ ለማድረግ ብዙ የሞከሩ ቢሆንም እስከአሁን ግን ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
ይህ በብአዴን ዉስጥ የሚደረገው የዉስጣዊ ትግል በሕዝቡና በሕወሃት መካከል የሚደረግ የተዘዋዋሪ ትግል ነው። (proxy) የህዝብ ድጋፍ ያለው የነገዱ አንዳርጋቸው ቡድን ወይስ የህወሃቱ አሽከር የነ አለምነህ መኮንን ቡድን አይሎ ይወጣል?? ወሳኙ ሕዝብ ነው።
ህዝብ እንቅሳሴዉን አጠናክሮ ከቀጠለ የሕወሃት ተጽኖና ሃይል ካነሰ የተሻለ ዉጤት ይመጣል። ግን ህዝብ ከተዘናጋ፣ ህወሃት በዘዴና በጥበበ እያሰራ፣ እየገደለ በገንዘብ እየደለለ ህዝብን መከፋፈል ከቻለ ግን የሕወሃት የግፋ አገዛዝ በባሰ ሁኔታ ይቀጥላል።
ሊሰመርበት የሚገባ ተቃዉሞው ከጎንደር ዌወደ ጀግናው የባህር ዳር፣ የደንረ ብርሃኑ፣ የደብረ ማርቆስ፣ የወሎ…ህዝብ መሸጋገር አለበት።

Friday, July 22, 2016

Deutsche Welle DW reports Ethnic clashes against the government in Gonder Ethiopia






At least 10 people have been killed in Gonder northern Ethiopia in clashes as locals with security forces. The government blames Eritrea for the unrest but residents cite disputes over land and ethnicity.
Ethiopia’s government spokesperson Getachew Reda has accused arch-enemy Eritrea for the unrest




According to several reports, the unrest in Gonder began earlier this week when armed police entered the city to arrest members of the “Wolkayit committee” who had been protesting against the government’s decision to merge the Wolkayit community and its land into the neighboring Tigray Regional State. The Ethiopian government spokesperson Getachew Reda on Friday accused the members of kidnapping, murder and being in possesion of arms with an intent of staging terrorist attacks. He also rejected any notion that the clashes was being spearheaded by the Amhara community.

“What happened is that there were individuals suspected of engaging in crime. So to arrest those individuals the Federal Police moved into this area,” Negusu Tilahun, Head of Communication Affairs with the Amhara Regional Government told DW.

“As result there was a clash between residents and the police. There was also an exchange of gunfire which resulted in the deaths of federal police officers and civilians as well. Besides that, there were also damages to property. The government and the public are now working together to bring the town back to its normal situation,” Tilahun said.

Ethiopian government officials have blamed opposition groups based in Eritrea for the unrest in Gonder. However, residents say ethnic tensions are the real reason behind the skirmishes.
6,000 Ethiopian Jews live in Gonder awaiting relocation to Israel



Over the last two decades, the Welkait community has been fighting to become part of Amhara saying it identifies more with the Amharas than Tigrayans.

One local resident who spoke to DW on condition of anonymity said the government should stop labeling civilians as terrorists. “That is a very cheap political propaganda. Every freedom fighter is linked to Eritrea or terrorism,” the resident said.

He accused the government media of ommitting to mention that those who were detained were committee members of the Welkait community. “The more the government labels them as terrorists or bandits, rather than responding to the real question, the more things will get worse,” he added.

The Welkait region was under Gonder province until it was handed over to Tigray State in 1991 by the current EPRDF government. The Amharas and Tigrayans had previously lived peacefully side by side but analysts blame the ethnic-federalism system which introduced ethnic ownership of lands for triggering the current dispute.

The US has issued a temporary travel advisory on Gonder and warned its citizens and those travelling to the city to be cautious. US citizens have also been advised to avoid large crowds and the ongoing protests.

The clashes also forced Israel to evacuate a group of 23 young Israeli volunteers from Gonder. The city has about 6,000 Ethiopian Jews who are waiting to be flown to Israel. The Israeli Foreign Ministry said the Ethiopian Jews were not in any immediate danger.

http://www.dw.com/en/ethiopia-riots-in-gonder-claim-casualties/a-19403372

ትግሬ ሁሉ ወያኔ አለመሆኑን ያሳዩን – አብርሃም ታዬ


በየድርጅቱ ፥በየሰራዊቱ ፥በየህዋሱ ጠርናፊው ህወሃት ብቻ ሲሆን አንድ ቀን በቃኝ የማይሉ ይመስላችኋል? እስቲ አስቡት ከስልሳ የጦር ጄነራሎች 57 ትግሬ፥ ብሎም የቴሌ እና ሌሎች ሲቪክ መስሪያ ቤቶች ጠርናፊ አለቃ ትግሬ ሲሆን አይሰቀጥጣችሁም?  ንግዱንማ ሙሉ በሙሉ  በድፍረት ተቆጣጥራሁታል።debark car

የእናንተ ቤት እየተመረጠ ሲቃጠል፥ የእናንተ ድርጅት እየተነጠለ ጉዳት ሲደርስበት፥ የሰላም ባሳችሁ በየወቅቱ  ሲቃጠል ምንም አይሰማችሁም ትግሬ ወያኔዎች? ኢትዮጵያ ውስጥ ግርግር በተነሳ ቁጥር ለምን የሁሉም ጣት እኛ ላይ ያነጣጥራል ብላቹ ለምን አትገመግሙም። ምርጫ ዘጠና ስባትን ተከትሎ በተነሳው ነውጥ ሆነ የአሁኑ የጎንደር ህዝብ ጥያቄ ላይ የትግሬ  ሆቴል እና ንብረት ኢላማ መሆናቸው ሌላውም ሲነሳ ያንገበግባችኋል።መጽሃፍ እንደሚል በእርጥቡ እንዲህ ከሆነማ በደረቁ እንዴት እንደምትነዱ አስቡት። ዘላለም ስለማትነግሱ የለውጥ አብዮቱ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ለመግባት ገና ግማሽ ሃገር ሲቀረው ሙሉ በሙሉ የዘረኝነት ጄኖሳይድ ሰለባ እንደምትሆኑ ግልጽ ነው። ከኢትዮጵያ ህዝብ  አምስት ከመቶ የማይሞላ የቁጥራችሁን ማነስን የባሰ የሚገዳደር ዕልቂት ተጋርጦባችኋል።በየጊዜው ቂም የያዘባቹ  ከዘጠና ፐርሰንት በላይ  የሚሆን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የግፍ ጽዋው ሲሞላ ይበቀላችኋል። ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በሰላም በፍቅር በመከባበር ለመኖር የሚያስችል የእርቅ ድልድይ  መፍጠር ካለባቹ ጊዜው አሁን ነው።
የተገላቢጦሽ  እናንተ ግን  የአናሳ አምባገነን (minority dictatorship )ነታቹ ብሶባችኋል።ከናዚ ጀርመን  የበለጠ የሚዘገንን ሰይጣናዊ በሆነው ዘረኝነት ታውራቹ ዛሬም  አማራ እና ኦሮሞን በማናቆር  በዳኝነት  ስልጣን ለመክረም የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ይልቁንም ተጋሩ የተሰኘው ማህበራችሁ ሳይቀር ያባሳጨው የወደመው ንብረት እንጂ ከሁለቱም ወገን የተቀጠፈው የሰው ህይወት አይደለም በመግለጫቹ  እንዳሳሰባችሁት።
በአገዛዙ ተማረው ተሰደው  በግፈኛው  አይሲስ እና በሜዲትራንያን ባህር ያለቁት ኢትዮጵያውያን   መሆናቸውን የአለም ሚዲያዎች እየዘገቡት እየነገሯችሁ  ዜግነታቸውን ሳናጣራ እንደርስላቸውም በማለታችሁ ስንቶች መንግስት የሌላቸው አስከሬን ሆኑ? ለህወሃቱ ዘፋኝ ኢያሱ በርሄ ወይም ለመለስ ዜናዊ በድን ግን መንገድ ተዘግቶ ከሁለት ሳምንት በላይ ብሄራዊ የ ሃዘን ቀን ታውጆ ነበር። እነዚህ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሊወክሉ የሚችሉ  ከመቶ በላይ የወገኖች  ደም ከዘረኛው መለስ ዜናዊ ወይ ካንዱ  ዘረኝነትን ሊተክል ከተሰዋ ትግራዋይ ደም በብዙ እጥፍ መከበር ነበረበት።  በጋምቤላ የአኙዋክና የኑዌርን ጎሳ በማጋጨት ለፈጸማችሁት የዘር ጅምላ ጭፍጨፋ የብዙ ሺ ሰዎች  ፍርድ ሳታገኙ የሩዋንዳን ሁቱ እና ቱት ሲን  ኢንተርሃሞይ ዕልቂት ትዘክራላቹ። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላልች ማለት ህወሃት ናት። ጀኖሳይድ ዋች የተባለ ድርጅት እንደዘገበው ኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ ሁሉም አይነት  ድርጊት በዘር ከመከፋፈል classification እስከ ጅምላ ጭፍጨፋ ያሉት ሰባት እርከኖች ተፈጽሞብናል። “Genocide Watch considers Ethiopia to have already reached Stage 7 of the 8 stages of, genocidal massacres, against many of its peoples, including the Anuak, Ogadeni, Oromo, and Omo tribes.”
በደኖ በሃረር በቁማቸው ለተቀበሩት የአማራ ወገኖች እልቂት መንስኤ መፍትሄ ሳታበጁ ከሃያ አምስት  አመት በላይ ተጎልታቹ በፌደራሊዝም ስም ትነግዳላችሁ።
አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ብሎ ህወሃት እንደተነሳ ሁሉ አማራው እናንተ ላይ የአጸፋ እርምጃ ቢወስድ አይደንቅም። ሆን ተብሎ በሰሜን ጎንደር ያሉ ሴቶች እንዳይወልዱ የሚያመክን መርፌ ለምን ተወጉ? ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ እንዳረጋገጠው የአማራ ህዝብ ብዛት መሆን ካለበት በሶስት ሚሊዮን ያነሰው በዘመናዊ ጀኖሳይድ ሂሳብ ብትገድሉ ኣይደል እንዴ? በጀቱን ለመቀነስ?
በታሪክ ድንበሩ ከተከዜ ወንዝ  አልፎ ያማያውቀውን የትግራይ ክልል ከሱዳን ጋር ለማዋሰን ስትሉ ብሎም በአፋርም በወሎም በኩል ያልነበራችሁን ይዞታ የመውረር አባዜ ግጭት የፈጠራችሁት እናንተ አይደላችሁ እንዴ? በጎንደር ወልቃት ጠገዴ  አማራነት ላይ ያልነበረ ማንነት ባትፈጥሩ ኖሮ ይኼ ሁሉ  ቀውስ ባልመጣ ነበር።
ለመሆኑ የትኛው የኦሮሚያ ክልል ወይ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ነው በህወሃት ከተሰጠው ሃላፊነት ውጭ ራስ ገዝ የሆነው?  ለጠቅላይ ሚንስትር አማካሪ በትግሬው  መለስ ጊዜ ሳይኖር ከደቡብ ለመጣው ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆን ግን አራት አማካሪ በአናቱ ማስቀመጥ ስድብ አይሆንም? ተጠቅላይ ምኒስትርነቱን ለማጉላት ለዛውም አለቆቹ ሁሉ ትግሬ። እራሳቹ  እንደምትናገሩት ኦሮሞዎችን የምታስፈራሩበት የምትገለገሉበት ድርጅት  ኦህዴዶች ልባቸው ቢፋቅ ኦነግ ናቸው። በቅርቡ ግምገማቹ   ስጋታችሁን እንደገለጻችሁት  የአማራው ብአዴን ወይ የደቡቡ አሻንጉሊት ድርጅት  ደኢህዴን ውስጥ ግንቦት ሰባቶች  አሉ። እነዚህ ህወሃትን ያዘሉ አንቀልባ ድርጅቶች ማዘል ደክሞአቸው በቃ ሲሉ ማንም የሚያዝንላቹ የለም።  እስካሁንም ያላችሁት በነዚህ ተላላኪ ካድሬዎች ብቻ ነው። አንዳንድ የኦህዴድ፥ የብአዴን ወይም የደቡብ ህዝብ ደኢህዴን  አመራሮች ከአለቃቸው ህወሃት የበለጠ ዘረኝነቱንስ ሲያስፈጽሙ ወገናቸው ላይ የመጨከናቸውን ያህል ትግሬ ሆኖ ህወሃትን ጨክኖ አንቅሮ የሚተፋ አርአያ ሰብ ያስፈልጋል።
ኢፈርት በተባለ የህወሃት ክንዳቹ  የሃገሪቱ ሃብትን ስትቀራመቱ ያልመሰላችሁን ከገበያ ስታባርሩ ከርማችሁ  በቅርቡ የሆላንድ ካር(Holland car ) ድርጅትን  ከአዲስ አበባ በቀይ ካርድ አባራችሁ  የፈረንሳዩ ፔጆ መኪና በመስፍን ኢንደስትሪያል ስር እንዲመረት ፋብሪካውን መቀሌ ላይ ገነባችሁ። ትግራይ ልትለማ ሌላው የሚደማ ለምንድነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ቲቪ  ከፍተን ስናይ ማስታወቂያው ሁሉ ሲሚንቶ፣ መድሃኒት ፋብሪካ፥ ምግብ እና የተለያዩ ሸቀጦች ወዘተ የተገነቡት ወይ አድራሻቸው ትግራይ ላይ ነው። ብቻውን የበላ ብቻውን እንደሚሞት ማን በነገራችሁ? የሃገሪቱ ሃብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለሁሉም ተደራሽ ይሁን የሚል እንዴት አንድ ቅን አሳቢ ከመሃላችሁ ይጥፋ?
ለኮሎኔል አታክልቲ ገብረሚካኤል  ልጅ ህክምና ከኢፌዲሪ የብረታብረት ኮርፖሬሽን ኤጀንሲ 14 ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች  ሶስት ሚሊዮን ብር አዋጥተው ባንኮክ ታይላንድ አሳከሙት። ብቸኛው የህዝብ ልጅ ሃብታሙ አያሌው ግን በከፍተኛ ኪንታሮት ታሞም ከሃገር ወጥቶ እንዳይታከም ተከልክሏል። ኢፍትሃዊነት በየፈርጁ ማለት ይኸ ነው። ህወሃት ማለት ኢፍት ሃዊነት ነው።
በእርግጥ ትግሬ ሁሉ አልፎለታል ወይም ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው ባይባልም ትግሬ ሆኖ ተቃዋሚ የሆነ አስር አይሞሉም። እንዘርዝር ሲባል ወያኔ አስሮ ከሚፈታቸው አብርሃ ደስታ ፤ አሰግድ ገብረስላሴ ወይም በስደት ካሉት ገብረመድህን እና አረጋሽ ይጠቀሳሉ።በቃ። ከነዚህ  ውጭ ሰው የለም እንዴ? ህወሃት እየገነባ ካለው ራሱን አጥፊ ዘረኝነት አንጻር ቅን ትግሬዎች ተሰባስባቹ ትግራይን እናድን የሚል ማህበር ወይ ፓርቲ ብትመሰርቱ ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጉልህ ከሚጠቀስላችሁ የጣልያን ጊዜ ባንዳነታቹ (የመለስ ዜናዊ አባትንም የጣልያን ተላላኪ እንደነበሩ በመጥቀስም) ወይም ወይም ሞላ አስገዶም ትህዴንን  ስለካደ    አይደለም ካሳ የምትከፍሉት። ይልቅ ከትግራይ ማሕጸን ተወልደው መሰዋዕት የሆኑት የራስ አሉላ አጽም ብሎም ለጣልያን ያደሩ መስለው ለአጼ ምኒልክ መረጃ በማቀበል ለአደዋው ድል  አስተዋጾ ያበረከቱት የባሻ አውአሎም አጽም እንዳይወቅሳችሁ  ነው።ለወያኔ ተብሎ  የተተኮሰ ጥይት ወይ ፍንጣሪ  እናንተንም በማወቅም ይሁን ባለማውቅ   ስለሚመታችሁ አስቡበት።ነግ በኔ በሉ። ለወያኔ የተወረወረ እሳት ትግሬዎችን በሙሉ እንዳያቃጥል መፍትሄውን ራሳቸው አሁኑኑ ይጠቁሙን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ላለመሆኑ በተናጥል ወይ በማህበር  አሳዩን።  ጀግኖች በአንድነት የተዋደቁላትን ሃገር እንዳትፈራርስ ማደረግ  የሁሉም ሃላፊነት ነው።
አብርሃም ታዬ  zeabraham@gmail.com

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ተፈረደባቸው

ኤርትራ ድንበርን በማቁዋረጥ አርበኞች ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ሲያመሩ ተይዘው የሽብር ክስ የቀረበባቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
ተከሳሾ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካሳይ ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስረዳቱ የጥፋተኝነት ፍርድ መስጠቱን 14ኛ ወንጀል ችሎት ገልጹዋል።
ተከሳሾች 141 መከላከያ ምስክሮችን አስመዝግበው እንደነበር አስታውሶ፣ በተከሳሾች በኩል የተመዘገበው ጭብጥ ግን የፈጸሙት ተግባር ወንጀል ነው ወይስ አይደለም በሚል እንዲመሰክሩ በመሆኑና አንድን ተግባር ወንጅል መሆን አለመሆን በህግ እንጂ በምስክር ስለማይረጋገጥ የምስክሮች መሰማት አግባብነት ስለሌለው መታለፉ ተወስቱዋል። 
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለሀምሌ 22/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቱዋል።
ተከሳሾች ጥፋተኛ የተባሉበት የህግ ክፍል የጸረ ሽብር አዋጅ 652/2001 አንቀጽ 7(1) ን መተላለፍ የሚል ነው።
Belay Manaye's photo.

Thursday, July 21, 2016

ሰበር ዜና! ቤታቸው በክረምት የሚፈርስባቸው ወገኖች በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እናደርጋለን አሉ፡፡

ሰሞኑን በቃሊቲ ገብርኤል ወረዳ.07 ቀበሌ10/11-ልዩ ስሙ ጨሬ ሰፈር በመባል የሚታወቀው ኣካባቢ ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ በአፍራሽ ግብረ ሃይል ምልክት ተደርጎባቸው በሁለት ቀን አፍረስው ካልጨረሱ በዶዘር ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው፡፡ በሁኔታው የተቆጡ ነዋሪዎች መንግስት በዜጎቹ የሚፈጽመው ጭካኔ እንግዲህ በቃ,ሞት ተፈርቶ ውርደት መቀበል አንችልም እያሉ ይገኛል፡፡ በዚህ ክረምት የት እንሄዳለን በማለት የተቆጡ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡም እንዳሰብ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ አንድ ነዋሪ ሲናገሩ በቅርቡ ወረገኑ በርካታ ሰዎች ሜዳ ላይ ወደቁ በን/ስ/ላ ቀበሌ01 ቀርሳ ኮንቶማ ማንጎ ከ20 ሺህ በላይ ቤቶች አፈረሱ ሕጻናት አረጋዊያን ያለ መጠለያ በሜዳ ላይ በዚህ ክረምት ለጎርፍና ለጅብ ቀለብ ተሰጥተዋል፡፡ መንግስት የሌለው ሕዝብ መሆናችን በደንብ አይተናል፡፡ እነሱ ከበርሃ አዲስ አበባ በኮንጎ መጥተው ባለ ፎቅ ሲሆኑ እኛ ተወልደን ባደግንበት ምድር እንዴት ቤት እናጣለን? በማለት በቁጭት ይናገራሉ፡፡ ከዚህ መኖር ሞታችን ይመረጣል የሚሉት ሌላው ነዋሪ ከዚህ በላይ ሞት ምን አለ? ሁል ጊዜ ቤታችን አፈረሱት በማለት ማልቀስ አንፈልግም የጎንደር ሕዝብ አሳይቶናል በቃ..ሰልፍ እንወጣለን መንዱን በተቃውሞ ይዘጋል ሲሉ ተናግረዋል፡

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ በኢንተርፖል ተይዞ ወደ አዲስ አበባ መጣ

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው በክሪ ሙሀመድ ሹሬ በኢንተርፖል አማካኝነት ዛሬ ጠዋት ከኩዌት ተይዞ መጥቷል።
ግለሰቡ ከ5 ዓመት በፊት ሙሀመድ አብዱልአዚዝ በሚል ሀሰተኛ ስም ኤጀንሲ እንዳለው በማስመሰል በማታለል በሕገወጥ መንገድ አንዲት ወጣትን ወደ ኩዌት ልኮ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ገልጿል።
ተጠርጣሪው ወደ ኩዌት በሕገወጥ መንገድ የሄደችው ወጣት ከፋተኛ ስቃይ ደርሶባት ህይወቷ አልፎ አስከሬኗ ወደ ሀገር ቤት መጥቶ ሥርዓተ ቀብሯ እንደተፈፀመም ኮሚሽኑ አስታውሷል።
በዚህ ወንጀል ሲፈለግ የነበረው ተጠጣሪ በክሪ መሀመድ ስሙ በኢንተርፖል አባል ሀገራት መበተኑን ተከትሎ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርና በፌዴራል ፖሊስ ኢንተርፖል አማካኝነት ዛሬ ጠዋት ከኩዌት ተይዞ መምጣቱን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የዓለም አቀፍ ድንበር ዘለል ተፈላጊዎች ክትትል ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሻምበል አሰፋ ገልፀዋል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የምርመራ ሥራውን እንደሚቀጥል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ማስታወቁን ኢብኮ ዘግቧል።

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከህዝቡ ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ ነው ተባለ

የኮሚቴ አባላቱ ለኢሳት እንደገለጹት የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱንም ሆነ በአጠቃላይ የታሰሩትን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ የኮሚቴ አባላትን ጉዳይ የሚከታተሉ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ኮሎኔሉ ወደ ትግራይ ተላልፈው እንደማይሰጡ እንዲሁም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ኮሎኔሉና ሌሎችም የኮሚቴ አባላት ለሽማግሌዎች ተመልሰው እንደሚሰጡ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር። ኮሎኔሉ ራሳቸው ሽማግሌዎች በተስማሙት መሰረት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ መጠየቃቸውን የተናገሩት የኮሚቴ አባላቱ፣ አሁን ግን ኮሎኔሉ ጎንደር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሃምሌ 22 ቀን 2008 ዓም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ የሚል መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
ሽማግሌዎቹ ዛሬ ከኮሎኔሉ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ በወልቃይት ጠገዴና በጎንደር ህዝብ ላይ ጉዳት ያደረሱትን በህግ ለመክሰስ፣ ታፍነው የተወሰዱ የኮሚቴው አባላት ለሽማግሌዎቹ ተመልሰው እንዲሰጡ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ኮሎኔል ዘውዱ ከፍተኛ ጀብዱ መፈጸማቸውን የሚያወሱት የኮሚቴው አባላት፣ ኮሎኔሉ በሰላም ከተኙበት ለማፈን ሙከራ ያደረገው የህወሃት የሽፍታና ተላላኪ ቡድን እርሳቸውን ለመክሰስ ምንም የሞራልም የህግ ልእልናም ስለሌለው የጎንደርም፣ የአማራም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ሃይል ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማድረግ አለበት ይላሉ። ስምምነቱ ኮሎኔሉንና የኮሚቴ አባላቱን መልሶ ለሽማግሌዎች ለማስረከብ በመሆኑ ስምምነቱ መፈጸም አለበት ብለዋል
በበየዳ፣ በዳንሻ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩት ህዝባዊ ተቃውሞች ከመልካም አስተዳደርና ገዢው ፓርቲ ከሚከተለው የዘረኝነት ፖሊሲ ጋር እንደሚያያዝ የኮሚቴው አባሉ ተናግረዋል። 

Wednesday, July 20, 2016

በያቤሎ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ

በያቤሎ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ
ሐምሌ ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ሃምሌ 13 ቀን 2008 ዓም የከተማው ህዝብ በነቂስ በመውጣት ተቃውሞ ሲያካሂድ ውሎአል።
ተቃውሞውን የጀመሩት ተማሪዎች ሲሆኑ፣ የከተማውም ህዝብ ተቀላቆሎአቸዋል። ከጥንት ጀምሮ የሞያሌ ወረዳ በቦረና ዞን ይተዳደር እንደነበር እየታወቀ፣ በየትኛውም ቦታ ባልታዬ ሁኔታ ወረዳው በሁለት ክልላዊ መንግስት ሲተዳደር መቆየቱ አግባብ ባለመሆኑ ወደ ቦረና ዞን እንድትመለስ የሚል ጥያቄ ቀርቧል።
ሰልፈኞቹ “ ባልተማሩ ሰዎች አንተዳደርም፣ በያቤሎ አካባቢ ዩኒቨርስቲ ይሰራልን፣ ፍትህ ይከበር፣ እውነተኛ የዳኝነት ውሳኔ ወስኑ፣ ነገሌ ወደ ቦረና ዞን ይከለልልን፣ ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብታችን ይከበር፣ ይህ መንግስት መብታችንን ሊያከብር አልቻለም” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
በመጨረሻ የአገር ሽማግሌዎች ከባለስልጣናት ጋር እንዲነጋገሩ ከተደረገ በሁዋላ ባለስልጣናቱ፣ ጥያቄያችሁን ለመመለስ የአንድ ሳምንት ጊዜ ስጡን በማለት ህዝቡን አረጋግተው ተቃውሞው በቀጠሮ እንዲተላለፍ አድርገዋል።
ሞያሌ ከተማ ላለፉት 25 አመታት በሶማሊ እና በኦሮምያ ክልሎች በጋራ ሲተዳደር ቆይቷል። በከተማዋ ተደጋጋሚ ግጭቶች ሲካሄዱ ቆይቷል። በዚህ ሳምንት በምእራብ ሃረርጌ በአሰቦት ፣ ሂርና እና ምስራቅ ሃረርጌ እንዲሁም በምእራብ ሸዋ በጀልዱ አካባቢዎች ተቃውሞች ተካሂደዋል።

wanted officials