Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 8, 2017

አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ታወቀ


የቀድሞው የብአዴን ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው የአካባቢው የደህንነት ሃላፊ ሆነው የቆዩት አቶ አያሌው መንገሻ ይፋ አደረጉ።
አቶ አዲሱ ለገሰ በይፋ የፓፒረስ ሆቴል ባለቤት በመሆን ከሚታወቁትና አሁን በሕይወት ከሌሉት አቶ ጠብቀው ባሌ ጋር የንግድ ግንኙነት የጀመሩት የሽግግር መንግስቱ ጊዜ የባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ምርቶችን እንዲያከፋፍሉ ያለጨረታ በመስጠት እንደነበር የደህንነት አባሉ ገልጸዋል።
አቶ ጠብቀው ባሌ ከአቶ አዲሱ ለገሰ ጋር የተገናኙት በወቅቱ ስልጣን የያዙት የሕወሃት መራሹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለፋብሪካው ሰራተኞች የሚከፍሉት ደሞዝ ሲያጡ እኚሁ ነጋዴ ደሞዝ በመክፈላቸው ነበር።
በሙስናና በአራጣ ማበደር ተይዘው እየተመረመሩ ያሉት የአዲስ ቪው ኢንተርናሽነሰል ሆቴል ባለቤት አቶ አብይ " ሆቴሉ የኔ ሳይሆን የአቶ አዲሱ ለገሰ ነው" በማለት አጋለጡ፣ 

የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት በመባል የሚታወቁት አቶ ሐብተስላሴ ታፈሰ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ



የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት በመባል የሚታወቁት አቶ ሐብተስላሴ ታፈሰ በ90 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
ለረጅም አመታት የኢትዮጵያ ቱሪዝም መለያ ምልክት የሆነውን “የ13 ወር ጸጋ ፈጣሪ” የሆኑት አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ ህይወታቸው ያለፈው በባልቻ ሆስፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት የሚባሉት አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ በቱሪዝም ኮሚሽነርነትና የቱሪዝም አስጎብኝ በመሆን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶችን በማስተዋወቅ የዜግነት ግዴታቸውን ተወጥተዋል።
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ)እንዲመዘገቡና እውቅና እንዲያገኙ አድርገዋል።
ለኢትዮጵያ የቱሪዝም እድገት ላደረጉት አስተዋጽኦ በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የእውቅና ሽልማት አግኝተዋል።
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ በኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት ሞት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ወዳጆቻቸውና ለኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ይመኛል።Bildergebnis für አቶ ሐብተስላሴ ታፈሰ

Monday, August 7, 2017

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም በየክልሉ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቶት የተሰማራው ኮማንድ ፖስት ስራውን እንደሚቀጥል በፓርላማው ይፋ ሆኗል።


ከመስከረም 28/2009 ጀምሮ ላለፉት 10 ወራት ተግባራዊ ሆኖ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዛሬ መነሳቱ ተገለጸ።
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም በየክልሉ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቶት የተሰማራው ኮማንድ ፖስት ስራውን እንደሚቀጥል በፓርላማው ይፋ ሆኗል።
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ ተብሎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስራውን የጀመረው ኮማንድ ፖስት አለመፍረሱ አነጋጋሪ ሆኗል።
ይህም መንግስት ከኢንቨስትመንትና ከቱሪዝም ጋር በተያያዘ የገጠመውን ቀውስ ለመሻገር ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እይታ ሲባል ብቻ በቃል የተነሳ በድርጊት የቀጠለ እንደሆነም ታምኖበታል።
ሰኔ 30/2009 እረፍት በወጣውና በመስከረም 2010 መጨረሻ መመለስ የሚጠበቅበት ፓርላማ ድንገት አስቸኳይ ስብሰባ መጠራቱ የተሰማው በሳምንቱ መጀመሪያ ነበር።
ፓርላማው መጠራቱን ባለፈው ረቡእ ማረጋገጫ የሰጡት የፓርላማው የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ጸዳለ ረጋሳ ለምን እንደተጠራ እንደማያውቁ መናገራቸው ይታወሳል።
ፓርላማው ዛሬ አርብ ሐምሌ 28/2009 የጠራው አስቸኳይ ስብሰባ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ለመምከር እንዲሁም የተጓደሉ የካቢኔ አባላትን ለመተካትና በሌብነት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ያለምከሰስ መብት ለማንሳት እንደሆነም ታውቋል።
በዚህም መሰረት የእስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሴክሬቲሪያት አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ባቀረቡት ሪፖርት መሰረትም ፓርላማው አስቸኳይ ግዜ አዋጁን እንዳነሳ ተዘግቧል።
አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ሪፖርታቸውን ባቀረቡበት ወቅት ለአዋጁ መነሻ የሆኑ ችግሮች በአንዳንድ አካባቢዎች መቀጠላቸውን አረጋግጠዋል።
ሆኖም በመደበኛው የህግ አግባብ ለማስተናገድ ሲባል አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ለፓርላማው ገልጸዋል።
ችግሮቹ የቀጠሉባቸውን አካባቢዎች ግን ይፋ አላደረጉም።
ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዳነሳ ቢገልጽም በአዋጁ መሰረት የተቋቋመውና በክልሎች በበላይነት ጸጥታውን የሚቆጣጠርው ኮማንድ ፖስት እንዳልፈረሰ ታውቋል።
ይህ ሃይል ከክልል ሃይሎች ጋር ጸጥታውን እንዲቆጣጠር መወሰኑም ተመልክቷል።
ኮማንድ ፖስቱ ባልፈረሰበት ሁኔታ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ ለማለት ያስቸግራል የሚሉት የፖለቲካ ተንታኞች አላማው በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም ዘርፍ የተከሰተው ችግር ያባባሰውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመሻገር ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፍጆታ ሲባል በቃል የተነሳ በድርጊት የቀጠለ ሲሉ ይገልጹታል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ አሁንም ወደ 8 ሺ ሰዎች በወህኒ ቤት እንደሚገኙ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ለፓርላማው ባቀረቡት ሪፖርት አመልክተዋል።
በኦሮሚያ ክልል 4 ሺ 136 ሰዎች በወህኒ ሆነው ክስ ሲመሰረትባቸው፣ በአማራ ክልል ደግሞ 1 ሺ 166 እንዲሁም በአዲስ አበባ 547 ሰዎች እስር ቤት ሆነው ክስ ተመስርቶባቸዋል።
በአጠቃላይ 7 ሺ 737 ሰዎች በወህኒ እንደሚገኙም አረጋግጠዋል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከኦሮሚያ፣ከአማራ፣ደከቡብ ክልሎችና ከአዲስ አበባ ውጭ የታሰረ እንዳለም ተመልክቷል።
በአማራ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታስረው በወህኒ ቤት ከሚገኙት ውስጥ በአርቲስት ፋሲል ደሞዝ ዘፈን ጨፍራኋል በሚል የታሰሩ ወጣቶች ይገኙበታል።
ህዳር 21/2009 በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 05 ልዩ ስሙ ማሬ ተመስገን አረቄ ቤት ውስጥ የፋሲል ደሞዝን ሒድልኝ የሚለውን ዘፈን በሞባይል ስልካቸው ከፍተው ጨፍረዋል በሚል ተይዘው የታሰሩትና የተከሰሱት እንዳልክ ስራውቀና፣ ተመስገን ሞገስና ሰለሞን ግርማ የተባሉ የ17 የ18ና የ20 አመት ወጣቶች መሆናቸውን ከአቃቢ ህግ የክስ መዝገብ ለማወቅ ተችሏል።

Arrest of Ethiopian army general suspected of embezzling 8 Million USD


ESAT News 
State and ruling party media reported the arrest of a general in connection with the embezzlement of 8 million USD from a government sugar project.
Brigadier General Ephrem Bange, an Oromo, and three others were arrested on Tuesday and brought to a court in Addis Ababa today. It was not immediately clear what connection the General has with the Omo Kuraz Sugar Project or if he held any official position with the project.
The charges read at the court indicate that the General and his accomplice who are still at large have pocketed 8 million dollars.
Also brought to court today were former head of the Tendaho Sugar Project, Yoseph Begashaw for misappropriation of 3.6 mill. dollars and head of procurement with the Ethiopian Roads Construction Corporation, Kassahun Kachi for siphoning off 1.1 mill. USD.
The arrest of the General followed a similar arrest of over 40 technocrats and business people in the last two weeks. Critics however say that the crackdown against corruption had avoided the big culprits in the higher echelons of the TPLF who have allegedly squandered billions of dollars from sugar and other development projects. Birgadier General Kinfe Dagnew of the Metals and Engineering Corporation and Abay Tsehaye, one of the founders of TPLF and a man with great power of influence are two names frequently mentioned allegedly squandering millions of dollars.
Last week, authorities released the names of 40 people whom they say have misused millions of dollars in procurement, contract awards and sale of lands among others. The suspects include former and current executives of the Addis Ababa as well as the Ethiopian Roads Authority, Tendaho Sugar Factory, Metehara Sugar Factory and the Ministry of Finance and Economic Cooperation.

U.S. announces $169 million aid to Ethiopia, Kenya drought victims




(AP Photo/Mulugeta Ayene)
The Trump administration announced more than $169 million in humanitarian assistance to Ethiopia and Kenya to support people affected by prolonged severe drought.
Ethiopian regime officials have been saying that they would use available local resources and funds meant for development projects if the international community did not step in to help the drought affected people. Officials were also playing down the severity of the drought crises and the widespread cholera epidemic, especially in the Somali region of Ethiopia.
The additional funding, including nearly $137 million in Ethiopia and nearly $33 million in Kenya, brings the total U.S. humanitarian contribution in Ethiopia and Kenya to more than $458 million in Fiscal Year 2017, the USAID Press Office said in a press release.
The USAID said in Ethiopia, the new assistance includes a contribution of more than 111,000 metric tons of relief food aid for approximately three million people. “An estimated 7.8 million people require urgent humanitarian assistance throughout Ethiopia, where the USAID-funded Famine Early Warning Systems Network (FEWS NET) signals that, without immediate and sustained assistance, food insecurity could reach catastrophic levels for some families in the worst-affected areas,” the humanitarian agency said in a release.
“This additional aid comes at a critical moment. In addition to severe hunger, acute watery diarrhea is spreading in drought-affected regions, which presents a deadly triple threat of hunger, malnutrition, and dehydration, in addition to the displacement of affected populations.”
The U.S., one of the largest donors to Ethiopia and Kenya, also called other humanitarian donors, to address the growing needs of people affected by the drought.

Sunday, August 6, 2017

በላሊበላ ከተማ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ቀጥሏል!!

በላሊበላ ከተማ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ቀጥሏል!!
በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በዘፈቀደ የተጣለብንን ግብር አንከፍልም በማለት ዕለተ ዓርብ ሐምሌ 28 /2009 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የጀመረው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ሐምሌ 29 /2009ዓ.ም በከተማው ያሉ ሱቆች እና መደብሮች በመዝጋት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ በላሊበላ ከተማ የሚገኘው የቅዳሜ ገበያ በዙሪያ አካባቢው ከመጡ ያልሰሙ ገበያተኞች ውጭ ጭር ብሎ ውሏል። በገበያው የበርበሬ ተራ፣ የልብስ ተራ ፣ የሸቀጣ ሸቀጦች ተራ ነጋዴወች አይታዩባቸውም። የአካባቢው የህወሓት ካድሬወች የሀገር ሽማግሌ በመምረጥ ቤት ለቤት እየዞሩ የሀገር ገፅታ ግንባታ ታበላሻላችሁ ክፈቱ እያሉ ቢያስገድዱም ሁሉም በስራ ማቆም አድማው በመፅናት አልከፍትም ብለዋል።
በላሊበላ ከተማ በሮሃ ላልይበላ ውቅር አበያተክርስቲያናት ከፍተኛ የውጭ ሀገር እና የሀገር ውስጥ ጎብኝወች የሚጎርፉ ሲሆን ከአምናው የወያኔ ስርዓትን ካሽመደመደው ህዝባዊ እምቢተኝነት እና ህዝባዊ አመፅ ወዲህ የቱሪስቶች ፍሰት በጣም የቀዛቀዘ እንደሆነ ታውቋል።
በተያያዘ መረጃ በዘፈቀደ በካድሬወች የተጣለብንን የግብር ውሳኔ አንከፍልም በማለት ከላሊበላ ከተማ በ30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ብልባላ ከተማ የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ ከሳምንት በፊት የጀመሩት የስራ መቆም አድማ እንደቀጠለ ይገኛል። የአካባቢው ካድሬወች ነጋዴወቹን ስራ እንዲጀምሩ ቢያግባቡም ግብር አንከፍልም በማለት መሳሪያቸውን ወልውለው እንደተቀመጡ ታውቋል።
ግብር ለህወሓት ወያኔ አንከፍልም !!
No automatic alt text available.No automatic alt text available.

የሎንደን አትሌቲክስ ኢትዮጵያውያን ውደድር መተላለፊያ ሰአቶች





የአባባ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ

የአንጋፋው የኪነጥበብ ሰው የአቶ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በኢትዮጵያ የኪነጥበብ መድረክ ውስጥ የቆዩትና በኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለይም በልጆች ፕሮግራም እጅግ ታዋቂ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሳህሉ በ93 አመታቸው ባለፈው እሁድ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
የአንጋፋው የኪነጥበብ ሰው የአቶ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ሲፈጸም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቻቸውና ወዳጆቻቸው እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
አቶ ተስፋዬ ሳህሉ በተዋናይነት፣በግጥምና ዜማ ጸሃፊነት እንዲሁም በድምጻዊነት በኪነጥበብ ዘርፍ ውስጥ ማገልገላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።
የዛሬ 11 አመት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተባረሩትና ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ በዚሁ ተቋም ለ42 አመታት ያገለገሉት አቶ ተስፋዬ ሳህሉ ሰኔ 20 ቀን 1916 በቀድሞው መጠሪያው በባሌ ክፍለ ሀገር ልዩ ስሙ ኮዶ በተባለ ስፍራ መወለዳቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።
ከአባታቸው ከአቶ ኤጀርሳ በዳኔና ከእናታቸው ወይዘሮ ዮንዢ ወርቅ በለጠ የተወለዱት አባባ ተስፋዬ በኪነጥበብ መስክ እንዲሁም በልጆች ፕሮግራም ላደረጉት አስተዋጽኦ ከቀድሞው ንጉስ አጼ ሃይለስላሴ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልመዋል።
በ1950ዎቹ በኮሪያ ዘመቻ በሙያቸው ላደረጉት አስተዋጽኦና በዘመቻው ተሳታፊ በመሆናቸውም የሃምሳ አለቅነት ማእረግ እንደተበረከተላቸው በቀብር ስነስርአታቸው ላይ የተነበበው የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።
በሙያቸው ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ከኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም ከአለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች ያገኙት አቶ ተስፋዬ ሳህሉ የ2 ልጆች አባት ነበሩ።5 የልጅ ልጆችንም አይተዋል።
እኚህን አንጋፋ፣ ባለሙያና ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ረቡእ ከቀትር በኋላ 9 ሰአት ላይ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።Image may contain: 1 person, smiling

በአንድ ወጣት 9 ልጆቻቸው የተደፈሩባቸው ወላጆች ፍትህ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ

በአንድ ወጣት ልጆቻቸው የተደፈሩባቸው ወላጆች ፍትህ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ

 በአንድ ወጣት ልጆቻቸው የተደፈሩባቸው ወላጆች ፍትህ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ።
በአዲስ አበባ ጉለሌ አባዲና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ6 እስከ 8 አመት የሚሆናቸውን ዘጠኝ ህጻናት ወንዶችን የደፈረው ወጣት በእስር ላይ ቢሆንም እስካሁን ግን ፍትህ እንዳላገኙ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
የተደፈሩት ህጻናት ለከፍተኛ የጤናና የስነልቦና ችግር ተዳርገዋል።
ሽንትና አይነምድራቸውን መቆጣጠር አልቻሉም።ወላጆቻቸው እንደሚሉት ህጻናቱን የደፈረው ወጣት ወላጅ አባት እያስፈራሯቸው ነው።
በልጆቻቸው ላይ ከደረሰው አደጋ በተጨማሪ የአካባቢው ማህበረሰብ እያገለላቸው እንደሆነም ገልጸዋል።የሕጻናቱ ወላጆች የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ለሰማው አስደንጋጭ ነው።ከኢትዮጵያዊ ባህልና ስነምግባር አንጻር ጉዳዩ ለብዙዎች አስፈሪ ሊሆን ይችላል።በጉለሌ አካባቢ ልዩ ቦታው አባዲና የተፈጸመው ወንጀል ህጻናቱን ለከፍተኛ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ለእንግልትና ስቃይ ዳርጓል።
ከምንም በላይ ደግሞ ለተፈጸመባቸው በደል ፍትህ የማጣቱ ጉዳይ ለወላጆቻቸው ተጨማሪ በደል ሆኗል።
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆነው ወጣት የአካባቢው ሕጻናትን በተለያዩ ጊዜያት ደፍሯቸዋል።ይህን ደግም ወላጆቻቸው አላወቁም።ህጻናቱም አልተናገሩም።ከስድስት እስከ ዘጠኝ አመት የሚሆናቸውን እነዚህን የአንድ አካባቢ ህጻናት ወንዶችን እይስፈራራ ድርጊቱን እንደሚፈጽም ነው የተረጋገጠው።የአንዱ ልጅ እናት ለኢሳት እንደተናገሩት ልጃቸው የተፈጸመበትን ድርጊት ያወቁት ከቆየ በኋላ ነው።
በጤንነቱ ላይ ችግር ተፈጥሮ ሽንትና አይነ ምድሩን መቆጣጠር ሲያቅተው ችግሩ ሌላ ነገር እንጂ ይህ ይፈጸማል የሚል ነገር አስበውም እያውቁም ነበር።
የአንደኛው ሕጻን ወላጅ እናት እንደሚሉት በልጃቸው ላይ የደረሰው እሳቸው እጅ ከፍንጅ ከያዙ በኋላ ጉዳዩ በአካባቢው ህዝብ ጆሮ ደረሰ።
ሌሎች ተመሳሳይ ጥቃት የተፈጸመባቸው ተገኙና ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆነ።በፖሊስ ዘንድም ታወቀ።
የዛሬ አመት አካባቢ ዘጠኙን ሕጻናት በተለያዩ ጊዜያት ደፍሯል የተባለው ወጣት በቁጥጥር ስር ዋለ።
ነገር ግን ፍትህ እስከዛሬ ሊገኝ ባለመቻሉ ወላጆች የፍትህ ያለህ ጥሪያቸውን ማሰማት ጀመሩ።
የከፋው ደግሞ የእነዚህን ሕጻናት ወላጆች ቤታቸው ድረስ በመሄድ ልጄን አሳሰራችሁብኝ እያሉ እያስፈራሩ እስከ ምደብደብና የአካል ጉዳት ያደረሱት የደፋሪው ወላጅ አባት ጉዳይ ነው።
ገንዘብ ስላላቸው ያንን ተመክተው በየቤታቸው እየመጡ ያስፈራሩናል ይደበድቡናል።የሚል ክስ ከተጎጂ ህጻናቱ ወላጆች ይሰማል።እኚሁ የተከሳሽ አባት የአንዱ ሕጻን እናት ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል።
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህጻናቱ መደፈራቸውን በህክምና ማስረጃ ቢረጋገጥም ጉዳዩን ለፍርድ ለማቅረብ ሳይቻል ከአንድ አመት በላይ መቆየቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
ህጻናቱ ለከፍተኛ የጤንነት ችግር በመዳረጋቸው አቅመ ደካማ የሆኑት ወላጆቻቸው ማሳከም አልቻሉም።
ችግሩ የስነ ልቦና ጉዳትም በማስከተሉ ወላጆቻቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸው ታውቋል።እናት የልጆቻቸውን ጉዳት ይናገራሉ።
ወጣት ኢዩኤልና ወጣት ረቂቅ ከሌሎች ጋር በመሆን ፍትህ የሚያገኙበትን ህጻናቱም ህክምና አግኝተው የሚፈወሱበትን እርዳታ ፍለጋ በበጎ ፈቃደኝነት እየሰሩ ናቸው።
የልጆቹ ስቃይ ቃላት ከሚገልጸው በላይ ሆኖባቸዋል።ፍትህ ማጣት ግን ሌላው ጉዳት እንደሆነባቸው ነው የሚናገሩት።
ጉዳዩ በመንግስት በኩል ችላ የተባለበት ምክንያት አልታወቀም።የህጻናቱ ወላጆች ስጋት ላይ ናቸው።የኢትዮጵያ ህዝብን ድጋፍ ይሻሉ።

በባህርዳር ከ50 በላይ ወጣቶች የተጨፈጨፉበትን ቀን ለማሰብ ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ

በባህርዳር ከ50 በላይ ወጣቶች የተጨፈጨፉበትን ቀን ለማሰብ ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 28/2009) በአንድ ቀን ብቻ በህወሃት አጋዚያን ከ50 በላይ ወጣቶች የተጨፈጨፉበትን ቀን በሀዘን ለማስታወስ በባህር ዳር ነሐሴ 1/2009 ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ።
የወጣቶቹን 1ኛ አመት ጅምላ ግድያ በሀዘን ለማስታወስ ከቤት ያለመውጣት አድማውን ለሰኞ የጠራው የባህርዳር ወጣቶች አስተባባሪ ኮሚቴ በሚል በህቡእ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው።
በሕወሃት አጋዝያን ጭካኔ ኮብል በተባለ አካባቢ በአንድ ስፍራና ሰአት የተረፈረፉትን ወጣቶች ለማስታወስ የጎንደር ከተማ ህዝብም ከቤት ባለመውጣት የሐዘኑ ተካፋይ እንዲሆን ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል።
ባለፈው አመት በዚህ ወቅት በአማራ ክልል በወልቃይት የማንነት ጥያቄ መነሻነት መላው የባህርዳር ሕዝብ በደባባይ በመውጣት ያስተጋባው ሰላማዊ ጥያቄ ምላሹ በጥይት መደብደብ ነበር። የጎንደር ከተማ ህዝብ በቀነኒሳ ወይም የተቃውሞ ችቦውን ከለኮሰ በኋላ ባህርዳሮችም አጋርነታቸውን ወዲያውኑ ነበር ያሳዩት። የአማራ ህዝብ የመብት ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጉዳይ መሆኑንም አሳይተዋል። እንኳን የወልቃይት እንኳን የጎንደርና የአከባቢው ነዋሪ የኦሮሞ ህዝብ ደምም ደሜ ነው ሲሉም ነበር። መስዋእትነት የከፈሉት ነሃሴ 1/2008 አ ም ያለፈው አመት የመብት ጥያቄን በሰላማዊ ሰልፍ በነቂስ ወጥተው ያስተጋቡ ወጣቶች በጅምላ ተረፍርፈዋል። በጅምላ ታስረው መከራና ስቃይን ተቀብለዋል።
የባህርዳር ህዝብ በነቂስ ወጥቶ አደባባዩን በመሙላት አገዛዙን በሰላም ሲያወግዝ ውሏል። ሰላም የማይወደው የህውሃት አገዛዝ ግን አባይ ማዶ ኮብል በተባለ ቦታ በኮንዶሚኒየም ቤት ላይ ቀድሞ እንዲያደፍጡ ቢያደርጋቸውም አነጣጥሮ አልሞ ተኳሾች በአንድ ስሜት ውስጥ ብቻ ከ50 በላይ ወጣቶች ተረፍርፈዋል። እነዚህን ወጣቶች የገደሉት የአገዛዙ ታጣቂዎች ግን አንዳቸውም እስካሁን ላይረዱ አልቀረቡም። ይልቁንስ ሰላማዊ ተቃውሞ ያነሱ ከ15ሺህ የሚበልጡ ወጣቶች በብርሸለቆ ማጎሪያ ተጋዘው ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፤ አይደገምም በሚልም በግዴታ እንዲምሉ ተደርገዋል። አሁንም እስር ቤት የሚገኙ በርካታ ናቸው። እነዚያ በግፍ የወደቁ 50ወጣቶች ደማቸው በከንቱ ፈሶ አይቀርም ይላሉ የብህር ዳር ወጣቶች። ወንድምና እህቶቻችን አንረሳቸውም ሲሉ ለከተማዋ ህዝብ ቀኑን በሃዘን ለማሰብ ከቤት ያለመውጣት አድማ ከሰኞ ነሐሴ 1/2009 አ ም ይፋዊ ጥሪ አድርገዋል። በዚሁ አድማም የንግድ መደብሮች እንዲዘጉ፣ በጎዳና ላይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይደረግና በከተማዋ ጸጥታ በማስፈን ፍጹም የሆነ ሐዘናችንን በሰላማዊ መንገድ እንገልጻለን ብለዋል። ወጣጦችና ልጆቻቸው የተጨፈጨፉባቸው ወላጆችም የሐዘን ካባ ለብሰው አይቀሩም ለነጻነት የሚደረገው ትግል ይቀጥላል ነው ያሉት ወጣቶቹ። እናም ይህን ጥሪ ለመላው ህዝብ አድርሱልን ሲሉ የባህርዳር ወጣቶች አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ለኢሳት በላኩት መግለጫ አመልክተዋል። የጎንደር ህዝብም ሆነ የአከባቢው ህብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት በአድማው ባለመሳተፍ በባህርዳር ለተገደሉ 50 ወጣቶች ሃዘኑን በመግለጥ እንዲተባበር ጥሪ አድርገዋል። መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ጨምሮ የኦሮሞ ማህብረሰብ ለነጻነቱና ለመብቱ በጋራ የሚያደርገውን ትግል እንደሚደግፍም ገልጸዋል። በአንድ ሰአት፣ በአንድ ቦታ፣ ቀድመው ባደፈጡ አጋዚያን አልሞ ተኳሾች 50 ወጣቶች በአንድ ጊዜ የተፈረጀበት ቀን ነሐሴ 1/2008 አ የባህር ዳር ወጣቶች ሰማእታት ቀን።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በባህርዳር ከተማ የንግድ ተቋማትን ለማዝጋት ጥረት ሲያደርጉ ነበር የተባሉ 5 ግለሰቦች መያዛቸውን የከተማዋ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ገልጿል።
የከተማዋ የጸጥታ መዋቅር 5 ግለሰቦችን ይዟል ቢባልም የተያዙት ሰዎች ማንነት ስምና አድራሻ ባለመገለጹ ሆን ተብሎ ሰኞ ነሐሴ 1 በግፍ የተጋደሉትን የባህርዳር 50 ወጣቶች ለማስታወስ የተጠራውን አድማ በማስፈራራት ጥሪውን ለማኮላሸት የተቀናበረ ዜና መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል።
አምስቱ ወጣቶች ከተያዙ በኋላ በተመሳሳይ የተሰማሩትን ግለሰቦች መረጃ ሰምተዋል በሚልም የህዝቡን ቤት ለመዋል የተጠራ አድማ በማስፈራራት ለማስቀረት አገዛዙ እየተፍጨረጨረ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በባህርዳር ከተማ የሚገኙ አባላቱን የትግራይ ልማት ማህበር ጠርቶ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና አድማውን ለማስቀረት የመረጃ ስራ እንዲሰሩ በስብሰባ ተነግሯቸዋል።
ነሐሴ 1/2008 ባለፈው አመት በባህርዳር ከተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ በአንድ ስሜት ውስጥ የተገደሉትን 50 ወጣቶች ለማስታወስ ኢሳት ከግድያው ጀርባ የነበረውን ስራ የሚያጋልጥ ሪፖርታዥ የሚያቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የተባበሩት መንግስታት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ተደረጉ


ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የተባበሩት መንግስታት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ተደረጉ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 27/2009) በኢትዮጵያ ከሴቶች ወሊድ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ አገልግሎት የሰጡት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የተባበሩት መንግስታት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ተደረጉ።
ሽልማቱ የተሰጠው የተባበሩት መንግስታትን እሴቶች በበጎ ላስተዋወቁ አውስትራላውያን እውቅና በሚሰጠው ተቋም አማካኝነት ነው።
ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የሕይወት ዘመናቸውን በኢትዮጵያ ለፌስቱላ የተጋለጡ 50ሺ ሴቶችን በመታደግ አገልግሎት የሰጡ አውስትራሊያዊ ሀኪም ናቸው
ዶክተር ሐምሊን እድሜ ልካቸውን ከባለቤታቸው ጋር በመሆን በፌስቱላ የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያንን በመርዳት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ አንጋፋ ሀኪም ናቸው።
ባለቤታቸው ዶክተር ሀምሊንም በተመሳሳይ ሁኔታ ከጎናቸው በመቆም ለኢትዮጵያ ሴቶች ጤና የበኩላቸውን ሲያደርጉ ኖረዋል።–በልጅነታቸው በመውለዳቸው ሳቢያ ለፌስቱላ ህመም የተዳረጉ ሴቶችን በማከምና በማገዝ
ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በኢትዮጵያ የፌስቱላን በሽታ የማስወገድ ሕልም አላቸው።
እስካሁን በነበራው አገልግሎታቸውም 50 ሺ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከፌስቱላ በሽታ ታድገዋል።
እናም ይህን አገልግሎታቸውን የተገነዘበው የተባበሩት መንግስታት የአውስትራሊያ ማህበር የተባለው ተቋም የ2017 የሕይወት ዘመን ተሸላሚ አድርጎ መርጧቸዋል።
ተቋሙ ለፍትህ፣ ለሰላምና በዝቅተኛ ደረጃ ላሉ የማህበረሰብ አባላት ለሰሩ አውስትራላውያን እውቅና በመስጠት ተሸላሚ ያደርጋል።
በዚሁ መሰረት ላለፉት 60 አመታት በኢትዮጵያ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ለፌስቱላ በሽታ የተጋለጡ ሴቶችን በማከምና እገዛ በማድረግ አገልግሎት ለሰጡት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን ሽልማቱን አብርክቶላቸዋል።
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በያዝነው ወር መጨረሻ ለሽልማት የበቁት ዶክተር ሐምሊን ኑሯቸው በኢትዮጵያ በመሆኑ በተወካያቸው አማካኝነት የእውቅና ስነ ስርአቱ እንደተዘጋጀላቸው ተገልጿል።
ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታል ገንብተው በአለም ደረጃ ከፍተኝ እውቅና ያለው በጎ አገልግሎታቸውን አሁንም በ93 አመት እድሜያቸው እየሰጡ ይገኛሉ።
Bildergebnis für dr. Katrin hamlin UN winner

ዩትዩየብ ቻናል "#ይለፈኝ" የተሰኘውን አዲስ #የፋሲል ደመወዝን ዘፈን አልለቅም ማለቱ ታወቀ

ሰበር ዜና
#Hope የተባለ ዩትዩየብ ቻናል "#ይለፈኝ" የተሰኘውን አዲስ #የፋሲል ደመወዝን ዘፈን አልለቅም ማለቱ ታወቀ
የውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት ከሆነ ፋሲል ደመወዝ ከሆፕ ጋር ውል ወስዶ አዲስ ነጠላ ዘፈኑን በዩቱዩብ ቻናሉ እንዲለቅለት ሲጠባበቅ ቆይቷል።እናም ዘፈኑን ለህዝብ እንዲያደርስለት ሲጠየቅ ነገ ዛሬ እያለ ሳምንታትን ካስጠበቀው በኋላ #ለእሁድ ለህዝብ ሊያደርስ ተስማምተው ነበር።
ሆኖም ይህ ለቃሉ የማይታመን እና የኪነ ጥብበን ምንነት ያልተረዳ ነጋዴ በርካታ ቀናትን ማስጠበቁ ሳይበቃው ዛሬ ደግሞ "ዘፈኑ ከፖለቲካ ጋር የሚያያዝ ይመስላል" የሚል የማይረባ ምክንያት በመቀረብ ዘፈኑን መልቀቅ እንደማይፈልግ ታወቋል።ዘፈኑ ግን እንደማንኛውም ዘፋኝ እና የኪነ ጥበብ ሰው #የኑሮ_ውጣ_ወረድንየሚዳስስ እንጅ ፖለቲካን እንደማይነካ ከግጥሙ ተረድተናል።
በዚህ ጉዳይ ፋሲል ደመወዝ ያለው ነገር ባይኖርም ጉዳዩን በቅርቡ ያሉ ሰዎች ለሌላ አቀናባሪ ለማስተላለፍ እና በአጭር ጊዜ ለአድማጭ ለማደረስ እየሰሩ ነው ተብልሏ።
ሁላችንም ፕፍፋይል ፎቷችን በዚህ ፎቶ በመቀየር ከፋሲል ጋር መሆናችን ለአርቲስቱ እናሳየው።

wanted officials