Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, July 14, 2018

በግብጽ በሰው አካል ንግድ ላይ ተሰማርተው ተገኝተዋል ባላቸው 37 ግለሰቦች ላይ የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተሰማ


 የግብጽ ፍርድ ቤት በሰው አካል ንግድ ላይ ተሰማርተው ተገኝተዋል ባላቸው 37 ግለሰቦች ላይ የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተሰማ።
በሃገሪቱ የሚታተም አንድ ጋዜጣ ለንባብ እንዳበቃው የካይሮ ፍርድ ቤት በወንጀሉ ተሳትፈዋል ባላቸው ግለሰቦች ላይ ከ 7- 15 አመት ቅጣት ማስተላለፉን አስነብቧል።
ከተከሳሾቹ መካከል በህገወጥ የአካል ዝውውሩ ላይ የጤና ባለሙያዎችም እንደሚገኙበት ታውቋል።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ግብጻውያን በህገወጥ መንገድ አካላቸውን በመሸጥ ገንዘብ እንደሚያገኙም ጋዜጣው አስነብቧል።

ሰማያዊ ፓርቲ ከአርበኞች_ግንቦት7ጋር አብሮ ከመስራት እስከ ውህደት ድረስ ለመስራት ፈቃደኛ ነው

ሰማያዊ ፓርቲ በተለይ በሕብረብሔራዊ አስተሳሰብና በሰላማዊ ትግል የሚታገሉ ድርጅቶች ጋር አብሮ ከመስራት ጀምሮ እስከ መዋሃድ የሚደርስ እርምጃ ለማከናወን ፈቃደኛ እንደሆነ ከዚህ ቀደም በስራ አስፈጻሚና በምክር ቤት ደረጃ በተሰጡ ተደጋጋሚ መግለጫዎች ላይ አቋሙን ግልጽ አድርጓል፡፡ አሁንም #ከአርበኞች_ግንቦት7ጋር አብሮ ከመስራት እስከ ውህደት ድረስ ለመስራት ፓርቲያችን ፈቃደኛ በመሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት አመራሮች ጋር በመገናኘት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ፡-
1ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና ተቋማትን ነጻና ገለልተኛ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ህዝብ እና ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሚመራው መንግስት ጋርመነጋገር በሚቻልበት መንገድ ላይ፤
2ኛ. ሁሉም በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ የተለያዩ ድርጅቶች ሰራዊቶቻቸውን ሳይበትኑ ሃገርን መጥቀም የሚችሉ ዜጎች የሚሆኑበትን እና እንደፍላጎታቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል ሆነው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ፤
3ኛ. የዜጎች ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በእኩልነትና በተቋም ታግዞ ማስከበር የሚችል፣ የህዝብን አብሮ የመኖርና የመተማመን መንፈስ የሚያጎለብት እና ከጎረቤት አገራት ጋር በመተሳሰብ በጉርብትና መንፈስ ሊያኖረን የሚችል የዜጎች ተሳትፎ በነጻነት የሚያሳትፍ ህገ መንግስት ተዘጋጅቶ እውን በሚሆንበት ሁኔታ ላይ በዋነኝነት እንዲወያይ የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ወስኗል፡፡ via Yidnekachew Kebede

ልብወለድ የሚመስለው የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ገድል !!

ልብወለድ የሚመስለው የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ገድል !!
* * * * *
ለሀገራችን ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈው ታላቅ ገድል ከፈፀሙ በርካታ ጀግኖች መሀል አንዱ ነው፡፡ በፈፀመው ወደር የሌለው ጀግንነት ሊታወስ የሚገባ የሀገር ኩራት። ነገር ግን ጀግንነቱ በወጉ ያልተነገረለት፡፡
ጀግናው ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ዘላለማዊ ኩራት ከሆኑ ድንቅና ብርቅዬ ተዋጊዎች መሃል በጀግንነቱ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡ ፡
.
በ1944 ዓም የተወለደው ይህ ብርቅዬ ጀግና ታላቅ ገድል ከፈፀመባቸው የውጊያ ውሎዎቹ መሃል የሐምሌ 27 ቀን 1969 ዓ.ምህረቱ ይቀድማል፡፡ በዚያ ወቅት ትምክህተኛው የዚያድ ባሬ መንግስት በምስራቅ ኢትዮጵያ ግዙፍ ወታደራዊ ወረራ ይፈፅሞ ነበር፡፡ ይህንን ወረራ ለመመከት ከተሰማሩት የአየር ኃይል (አሜሪካ ሰራሽ ኤፍ 5 ኢ) ተዋጊ ጀቶች መሃል አንዱን የያዘው ይህ ጀግና ነበር።
እናም በኦጋዴን ሐረዋ፣ አይሻ፣ በእነኖ ሜጢ እና በሌሎችም ቦታዎች የሮኬት ናዳ በማውረድ ወራሪውን የሶማሊያ ጦር ባለበት እንዲገታ ከማድረግ ባሻገር፣ 8 የጠላት ታንኮችን ከእነምድብተኛው ረመረመ፡፡ ይህንን ታላቅ ጀግንነት ባስመዘገበ በ10 ሰዓት ልዩነት እንደገና ወደ ምስራቅ ጦር ግንባር በመብረር የኢትዮጵያን አየር ኃይል ብቃት ያስመሰከረም ነው፡-
ይህ ጀግና።ገድሉ ይቀጥላል፡-…..
.
ጥቅምት 7 ቀን 1970 ዓም፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በጅጅጋ ካራማራ ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ ይገኛል፡፡ ያኔ እሱ ከላይ ከሰማይ በሚያወረደው ቦንብ የሶማሊያን ወራሪ ጦር ብትንትኑን ማውጣት ተያያዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ከጠላት ወገን በተተኮሰ አየር ቃወሚያ የሚያበረው ኤፍ 5 ኢ ተዋጊጀት ተመታ፡፡ ይኼኔ እሱ በዥንጥላ ወርዶ ህይወቱን ማትረፍ ነበረበት፡፡ ነገርግን የሚያበረውንም ጀት ጭምር እንጂ የራሱን ህይወት ብቻ ማትረፍ አልፈቀደም፡፡ እናም የሚያበረውን ጀት በቆራጥነት እየቀዘፈ ወደ ቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ገስግሶ በሰላም አረፈ፡፡ የተመታውም ጀት ተጠግኖ እንደገና ለግዳጅ ተሰማራ፡፡
.
ሐምሌ 30 ቀን 1969 ዓ.ም በነገሌ ቦረና ግንባር የተሰማራውን የሶማሊያ ጦር የቦንብ ናዳ በማውረድ ጠላትን ብትንትኑን ማውጣቱን ቀጠለ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ሁለት የሶማሊያ ጦር ጀቶችን በአየር ላይ አጋይቶ ጣለ፡፡ የሚገርመው አንዱን የሶማሊያ ጦር ጀት ያጋየው ሶማሊያ ግዛት ውስጥ ዘልቆ ገብቶ መሆኑ ነው፡፡
አሁንም የጀግናው ገድል ይቀጥላል፡-
.
ጥቅምት ወር 1970 ዓ.ም፡- የሶማሊያ ጦር ጀቶች ድሬደዋ ከተማ ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ ይኼኔ ለጥቃቱ የአፀፋ መልስ እንዲሰጡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተዋጊዎች ታዘዙ፡፡ ከታዘዙት ተዋጊዎች መሃል አንዱ ይህ ጀግና ነበር፡፡እናም ጀቱን እየቀዘፈ የአየር ላይ ትርዒት ጭምር በማሳየት ጀግናው ገድሉን ቀጠለ፡፡ እናም የሶማሊያን ሚግ 21ተዋጊ ጀት ከነአብራሪው በአየርላይ አጋይቶ በሰላም ወደ ቢሾፍቱ ተመለሰ፡፡ እነሆ ይህ ጀግና እንዲህ ያለ አኩሪ ገድል የፈፀመ ነው፡፡
ማነው?
.
ይህ ጀግና ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ይባላል፡፡ (በነገራችን ላይ ኮሎኔል በዛብህ፤የፕር በየነ ጴጥሮስ ወንድም ነው፡፡)ከላይ የጠቀስነውን ጀግንነት በፈፀመ ጊዜ የሻለቅነት ወታደራዊ ማዕረግ ነው የነበረው፡፡ የሆነ ሆኖ የጀግናችንን አኩሪገድል መተረካችንን እንቀጥል፡፡
.
ሕዳር 3 ቀን 1970 ዓ.ም፡፡የሶማሊያ ተዋጊ አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ጥቃት ፈፅመው ተመለሱ፡፡ ይኼኔ ሁለት የኢትዮጵያ ተዋጊዎች (ሻለቃ በዛብህ ጴጥሮስ እና ኮሎኔል ለገሰ ተፈራ) ተከትለዋቸው ገሰገሱ፡- እስከ ሞቃዲሾ ድረስ፡፡ የሶማሊያ አውሮፕላኖች ሞቃድሾ አየር ማረፊያ ደርሰው ለማረፍ ዝቅ ሲሉ፤ ጀግኖቹ ሻለቃ በዛብህና ኮሎኔል ለገሰ ተፈራ እዚያው ደፍቀው አጋዩአቸው፡፡ እናም በሰላም (እየሸለሉ) ወደ ቢሾፍቱ ተመለሱ፡፡ ይህ የጀግኖቻችን ተግባር ለሶማሊያውያን ዘላለማዊ ውርደት ያከናነነበ እንደ ነበር ታሪክ ይመሰክራል፡፡
.
የጀግናው በዛብህ ጴጥሮስ ገድል ይቀጥላል፡-
ታህሳስ 13 ቀን 1970 ዓም በዛብህ፤ ቶጎ ውጫሌ በሚባል ቦታ ላይ የሚገኝን የሶማሊያ ጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት እና መካናይዝድ ክፍለ ጦር መምሪያ በቦንብ እያጋየ ሳለ ከጠላት ወገን በተተኮሰበት አየር መቃወሚያ ጥይትየሚያበረው አውሮፕላን ሞተር ክፍል ተመታበት፡፡በዛብህ ጴጥሮስ አውሮፕላኑ ክፉኛ ቢመታም አልተደናገጠም፡፡ የተመታውን
አውሮፕላን መልሶ ደብረዘይት ለማሳረፍ ታላቅ ጥረት አደረገ፡፡
ሆኖም ጥረቱ አልተሳካም የአውሮፕላኑ ነዳጅ አለቀበት፡፡ በዚህ የተነሳ ቢሾፍቱ እና ሞጆ መሃል በሚገኝ ገላጣ ሜዳ ላይ አውሮፕላኑን አሳርፎ ድርብ ጀግንነቱን አስመሰከረ፡፡ጀግናው በዛብህ ጴጥሮስ፤ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር ተፈሪ በር በተባለ የጦር መንደር ላይ የሚገኘውን (በጥር ወር 1970) የከባድ መሳራያ ግምጃ ቤት እና የጠላት ጦርም ድባቅ መታ፡፡ በዚህ ወቅት 5 የጠላት ታንኮችን ከነምድብተኛቸው ደመሰሰ፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም ከጠላት በተተኮሰ ፀረ አውሮፕላን ጥይት ተመቶ የሚያበረው አውሮፕላን በእሳት ተያያዘ፡፡ ጀግናው ይህም ጥቃት አላሸበረውም፡፡ እሳቱን በመከላከያ በማጥፋት ወደመጣበት ተመለሰ፡፡ አሁን ግን ቢሾፍተቱ መድረስ አልቻለም፡፡
አውሮፕላኑን ድሬደዋ አየርማረፊያ አሳረፈው፡፡አውሮፕላኑም ተጠግኖ እንደገና ለግዳጅ በቃ፡፡ይህ ጀግና ፤ ከሚያዝያ ወር 1970 ጀምሮ ኤርትራ ወደ ሚገኘው 2ኛው አየር ምድብ እንዲዛወር ተደረገ፡፡ ሻለቃ በዛብህ ጴጥሮስ የሶማሊያን ወረራ ለመቀልበስ ከሐምሌ ወር 1969 እስከ የካቲት ወር 1970 በተደረገ የመከላከልም ሆነ የማጥቃት
ውጊያ 191 ጊዜ ወደ ጠላት ወረዳ በርሯል፡፡
በዚህ የላቀ እና ታላቅ ሀገራዊ ተጋድሎ ላበረከተው አስተዋፅኦ በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት
መስከረም 3 ቀን 1972 ዓ.ም “የላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይ” ሸልሞታል፡፡
.
እዚህ ላይ ሻለቃ በዛብህ ጴጥሮስ ህዳር 21 ቀን 1972 ዓም ለንባብ በበቃው “ታጠቅ” የተሰኘ የሰራዊቱ ጋዜጣ ላይ ከሰጠው ቃለምልልስ የሚከተለውን መጥቀስ ይገባል፡፡ እነሆ፡-
“… እኛ ብንሞት ሌላ ሰው ይተካናል፤ መተኪያ የሌላት ሀገር ከሞተች ግን ተተኪው ትውልድ ስለሚሞት ዋጋ አይኖረውም፡፡ የሀገርን ሉአላዊነት በአስተማማኝነት መጠበቅ ቆራጥነት እና ልበ ሙሉነት ይጠይቃል፡፡ እኛ በሕይወት ቆመን እያየን ጠላት አንዲት ስንዝር መሬት ቆርሶ መሄድ ቀርቶ በአንድ እግሩ እንኳ ሊቆምባት አይችልም፡፡ ከሀገር ወዲያ ሌላ መኖሪያ ዋሻ ስለሌለ በሃገርና በነፃነት ጉዳይ ምንም ቀልድ ሊኖር አይችልም፡፡…”
.
ይህ ጀግናችን የተናገረውን ካለማወላወል በተግባር የፈፀመ ብርቅዬ ልጅ ነው፡፡ ከሶማሊያ ወረራ በኋላ ወደ ኤርትራ ዘምቶ እስከ 1977 ድረስ ግዳጁን በአግባቡ የተወጣ አርበኛ ነው፡፡ በ1977 ዓም ግን ከሻዕቢያ ጋር በናቅፋ ግንባር እየተዋጋ ሳለ አውሮፕላኑ ተመታ፡፡ አሁን ግን ወደ ተነሳበት ቦታ መመለስ አልቻለም፤በሻዕቢያ እጅ ወደቀ ጀግናችን እስረኛ ሆነ፡፡
በ1983 ዓም ከእስር ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀልም ችሎ ነበር፡፡ከሰባት ዓመት በኋላ በ1990 ዓም የኢህአዴግ ወዳጅ የነበረው ሻዕቢያ ጠላት ሆኖ መጣ ተባለ፡፡ ባድመን ወረረም ተባለ የሦሥት ወንዶች እና የሁለት ሴቶች አባት የሆነው ኮሎኔል በዛብህ የሀገሩን ክብር ለማስመለስ እና ሻዕቢያን ለመደምሰስ ዳግም ዘመተ፡፡
እንደ ልማዱ ተዋጊ አውሮፕላኑን እየሰገረ የሻዕቢያን ጦር አከርካሪ መሰባበሩን ቀጠለ፡፡ግንቦት 5 ቀን 1990 ዓም ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ወደ ኤርትራ ምድር ዘልቀው ከገቡ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተዋጊዎች አንዱነበር፡፡ የሚያበረውን አውሮፕላን ዝቅ፤….እጅግ ዝቅ….. አድርጎ የሻዕቢያን ጦር “አፈር ድሜ እያስጋጠ “ ሳለ ተመታ፤ እንደገና በሻዕቢያ እጅ ወደቀ፡፡ የሻዕቢያ እስረኛ ሆነ፡፡
እነሆ ይህ የሀገር ፈርጥ፤ ይህ ብርቅዬ ጀግናችን እስካሁን በሕይወት ይኑር አይኑር በይፋ የታወቀ ወይም የተነገረ ነገር የለም፡፡ “አውራምባታይምስ” ድረ ገፅ ኦክቶበር 16፤2013 ከሕውሐት መሪ ስብሃት ነጋ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ጀግናችን ሳይገደል እንዳልቀረ ጠቁሟል፡፡
ያሳዝናል፡፡ እንዲያም ተባለ እንዲህ ጀግናችን በልባችን ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል፡፡ እኛ ገድሉን እንዘክራለን፡፡ በታሪካችን ውስጥ ከፍ ከፍ እያደረግን እናወሳዋለን፡፡ የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ታሪክ እና ገድል ከመቃብር በላይ ነውና....
.
.
ምንጭ፡- (የአናብስት ምድር – መጽሀፍ) Wossen Ayehu አሳጥሮ እንዳቀረበው።

Friday, July 13, 2018

የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው፡፡


(ኢሳት ዲሲ–ሃምሌ 5/2010)
ዩኒቨርሲቲው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው እና ለመሃመድ አህመድ ቆጴ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥም ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት መረጃ ሰጥቷል፡፡
ሃሮማያ ዪኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ከመጀመሪያ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ 7900 በላይ ተማሪዎች ሐምሌ 07/2010 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ ታዉቋል፡፡
በዕለቱም ለርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው እና ለመሃመድ አህመድ ቆጴ የክብር ዶክትሬት ይሰጣቸዋል፡፡
የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ለአማራ ክልል ርእሰመስተዳድር አቶ ገዱ አንድአርጋቸው የክብር ዶክትሬት ለመስጠት የወሰነው በኢትዮጵያ እየተደረገ ባለው የለውጥ እንቅስቃሴ እያደርጉ ላለው አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ነው።
መሃመድ አህመድ ቆጴ የመጀመሪያው የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ሆነው በሃረር ከተማ ይሰሩ እንደነበረም ከዩኒቨርሲቲው ካገኘነው መረጃ አረጋግጠናል፡፡
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት ለሁለት ሰዎች ብቻ ነው የክብር ዶክትሬት የሰጠዉ፡፡
በማሽላ ላይ ታዋቂ ተመራማሪ እና የምግብ እና የእርሻ ድርጅት/FAO/ አማካሪው ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ እና የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ  በዩኒቨርሲቲው የእስካሁን ታሪክ የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸዉ ናቸው፡፡
በቅርቡም የጅማ ዩንቨርስቲ ለኦሮሚያው ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል።

Thursday, July 12, 2018

አብዲ ኢሌ የፓርላማ አባሉን አሰሩ



( ኢሳት ዜና ሃምሌ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ) ትናንት በክልሉ ለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት የቀድሞውን የደህንነት ሚኒስትር ተጠያቂ ያደረጉት የሶማሌው ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኢሌ፣ አቶ ጌታቸውን በተመለከተ ከአጀንዳ ውጭ በፓርላማ መናገራቸውን በመንቀፍ ለአፈ ጉባኤውና ለሶማሊ ክልል አመራሮች ደብዳቤ የጻፉትን አቶ አብዲ ዴሬን “የጌታቸው ደጋፊ” በሚል ዛሬ አስረዋቸዋል።
የፓርላማ አባሉ አቶ አብዲ ዴሬን በደብዳቤያቸው “የስብሰባው አጀንዳ ከጸደቀ በኋላ ም/ቤቱ ካፀደቀው አጀንዳ ውጪ በሆነ ጉዳይ ሁለት ሰዓት ሙሉ እንድናዳምጥ ተገደናል ብለዋል።
ም/ቤቱ ቀኑን ሙሉ ዶ/ር አቢይ አህመድ ያስተላለፉትን የይቅርታ መልእክትና የክልሉ አመራር አካላት አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተ ያላቸውን ፍራቻ ነው እንድናዳምጥ የተደረግነው ያሉት አቶ አብዲ ዲሬን፣ “ዶ/ር አቢይ ባስተላለፉት የይቅርታ መልእክት ላይ አቶ ጌታቸውን አልተካተቱም ወይ?” ሲሉ ጠይቀዋል።
“ይህን ልጠይቅ የቻልኩበት ዋንኛ ምክንያት እኔን እስከገባኝ ድረስ የይቅርታ መልዕክቱ እኛንም ጨምሮ በአጠቃላይ ለሁሉም ሰው የተላለፈ መልዕክት ስለመሰለኝ ነው”ያሉት የምክር ቤቱ አባል፣ በዚህ ረገድ ም/ቤቱ ለክልሉ ህዝብ እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ከመወያየት ይልቅ ቀኑን ሙሉ ስለ አንድ ከስራ ኃላፊነቱ ስለተነሳ ግለሰብ ላይ ግዜያችንን ማጥፋታችን ከምክር ቤቱ ደንብ ውጪ ከመሆኑም በተጨማሪ የም/ቤቱን ክብር የሚነካ ጉዳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡” ብለዋል።
በዚህ የቅሬታ ደብዳቤ የተቆጡት አቶ አብዲ ኢሌም “የኦጋዴንን ማእከላዊ እስር ቤት ዘግተው መስኪድ እንደሚያደርጉት የገቡት ቃል አንድም ቀን ሳያድር የምክር ቤቱን አባል አስራዋቸዋል
ትናንት “ጌታቸው አሰፋ ጣልቃ እየገባ አላሰራኝ አለ” እያሉ የተናዘዙት አቶ አብዲ፣ ከእርሳቸው ጀርባ ሆነው በክልሉ ህዝብ ላይ ጥፋት ሲያደርሱ ስለነበሩት የመከላከያ ጄኔራሎች ምንም የተናገሩት ነገር የለም።Image may contain: 1 person, sitting

Eritrea withdraws troops from border with former foe Ethiopia

Eritrea has withdrawn its troops from the heavily militarised border with Ethiopia as a "gesture of reconciliation", the pro-government Eritrean Press agency has said.
"It is imperative for all those who care about the long-term stability and economic viability of the region to do everything they can to help the two countries move beyond the senseless war that wrought so much suffering on both people," the agency said.
Asmara has yet to comment on the report but the move appears to be consistent with recent developments and the restoration of diplomatic ties between the two countries.
On July 9, Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed arrived in Eritrea's capital Asmara to sign a landmark agreement with President Isaias Afwerki, formally ending the "state of war" between their nations.
A week later, Isaias visited Ethiopia to re-open Eritrea's embassy in Addis Ababa.
The newly appointed reformist Abiy first initiated the peace overtures and restoration of relations in April.
Ethiopia and Eritrea expelled each others' envoys at the start of the 1998-2000 border war, which killed about 80,000 people.
Once a province of Ethiopia, Eritrea seceded in 1993 after a long independence struggle. A dispute over the demarcation of their shared border triggered the later conflict.
The Horn of Africa nations remained at loggerheads since Ethiopia rejected a United Nations ruling and refused to cede to Eritrea land along the countries' border following the 1998-2000 war. 
On Wednesday, Ethiopia's national carrier made its first landing in Asmara after a two-decade military standoff. 

የኤርትራው መሪ ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ መንግስት አስታወቀ

Image may contain: 4 people, people smiling, outdoor

የኤርትራው መሪ ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ መንግስት አስታወቀ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት ቅዳሜ የሚገቡት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባና በሃዋሳ የስራ ጉብኝት ያካሂዳሉ። የሁለቱ አገራት መሪዎች በሚሊኒየም አዳራሽ ተገኝተው የሁለቱን አገራት ሰላም እንደሚያበስሩ ሃላፊው ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሃዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዶ/ር አብይ አህመድ ኤርትራን በጎበኙ በሳምንታቸው የኤርትራው መሪ ኢትዮጵያን በይፋ መጎብኘታቸው ሁለቱ አገራት ሰላም በማውረድ በጋራ ለማስራት ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል። ባለፉት 20 አመታት በነበረው ሁኔታ ሁለቱም አገራት መጎዳታቸውን ያመኑበትና የጠፋውን ጊዜ ለመካስ እሩጫ መጀመራቸውን የሚያሳይ ነው በማለት ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።

Wednesday, July 11, 2018

ለአ/አበባ ሀ/ስብከት ችግሮች አጣሪ ኮሚቴ ሰብሳቢው፣ ከሀገረ ስብከቱ ገቢ እንዲከፈላቸው የታዘዘው 50ሺሕ ብር እያነጋገረ ነው



pat megabe kahinat haile ze collusion
  • መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም፣የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ናቸው፤
  • ለኮንዶሚኒየም ግዥ የተበደሩትን መክፈል ስላቃታቸው ርዳታ ተፈቀደላቸው፤
  • ገንዘቡ የሚከፈላቸው ከሀገረ ስብከቱ ገቢ ላይ ሲኾን፣ማጣራቱ ግን አላለቀም
  • ለምን ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ አይከፈልም?በምንስ አግባብ ሊፈቀድላቸው ቻለ?
†††
  • ሌሎች ሊቃውንትና ሠራተኞችስ በተመሳሳይ ቢጠይቁ ይፈቀድላቸዋል ወይ?
  • ኮንዶሚኒየም ከገዙ፣የተከራዩትን የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ቪላስ ያስረክባሉ ወይ?
  • ልዩ ሀ/ስብከት ካልተነሣ የፓትርያርኩ የጓሮ ሽንኩርት መኾኑን ይቀጥላል፤”
  • “የመዋቅር ለውጥ እንጅ፣የ4 ወይም የ44 ጳጳሳት ምደባ አይታገደውም!”
†††
ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፣ በቤተ ክርስቲያኒቷ ሕግ ፊት እኩል የመታየት፤ በዘር፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በሀብት ወይም በሌሎች ከሚፈጸም አድሎአዊ አሠራር የመጠበቅ መብት እንዳለው ተደንግጓል፡፡ ኾኖም ሕግ መደንገጉ ብቻ፣ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ግንባር ቀደም ኾና የምትቆመውን ቤተ ክርስቲያናችንን፣ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ከመነቀፍና ከመተቸት አላዳናትም፡፡መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ ሌብነትን መከላከል፣ ዘረኝነትን መዋጋት አለመቻሉ፤ በሚሰጠውም ምክር የማስተካከያ እርምት ለማድረግ በጎ ፈቃድ አለመታየቱ፣ በቁጥር አንድ ከፈጠራቸው ክፍተቶች አንዱ፣የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደኾነ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ደረጃ ሳይቀር ታምኖበታል፡፡
የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የኾነው አዲስ አበባ፣ ለችግሩ በዋና ማሳያነት ሲጠቀስ፣ 253 አገልጋዮች ከሌብነትና ጠባብነት መስፋፋት ጋራ ተያይዞ በሚፈጸም አድልዎ ከሥራ እንደተፈናቀሉና እንደታገዱ በምልኣተ ጉባኤው ላይ ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በሕዝብና በመንግሥት አካላት ዘንድ፣ አገልጋይ ለመቅጠርም ኾነ ለማዛወር፣ እንደየሥራው ዘርፍና ምድብ ለቦታው ለመስማት በሚዘገንን መልኩሊቃውንትን በማጉላላትና ገንዘብ በመቀበል ቤተ ክርስቲያኗን በሚያሳዝን መልኩ ያስተናግዳል እየተባለ ይተቻል፤ ችግሮቹ ዕለት ተዕለት ከመባባሳቸውና መፍትሔ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣ የቤተ ክርስቲያን ሀብት የኾኑ የአብነት መምህራን የባለጸጋ ቤት ዘበኛ/ጥበቃ ኾነዋል፤”ብሏል – በምልዓተ ጉባኤው ላይ ለመነሻ የቀረበውና ወቅታዊ ችግሮችን የሚዳስሰው ጥናት፡፡
እነኝህን ችግሮች በምርመራ አጣርቶ ሪፖርት እንዲያቀርብ፣ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ባለፈው ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. አምስት አባላት ያሉበት ኮሚቴ የሠየሙ ሲኾን፣ ሰብሳቢው ደግሞ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የካህናት አስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊ መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም ናቸው፡፡ ኮሚቴው በተቋቋመበት የፓትርያርኩ ደብዳቤ መሠረት፣“የሀገረ ስብከቱን የአስተዳደር ችግር፣ የሙስና ተግባርና ሌሎችንም የአሠራር ጥሰቶች” በተበዳዮች አቤቱታና የማስረጃ ሰነዶች እያጣራ ሰንብቷል፡፡ ኾኖም፣ የምርመራ ሪፖርቱን አጠናቅሮ እንዲያቀርብ የተቀጠረበት ከአራትና አምስት ያልበለጡ ቀናት በቀሩበት ዛሬ፣ የኮሚቴው ሰብሳቢ መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም፣ ከሀገረ ስብከቱ እንዲወስዱ የተቀፈደላቸው የ50ሺሕ ብር ርዳታ በከፍተኛ ደረጃ እያነጋገረ ይገኛል፡፡
pat megabe kahinat haile letter - Copy
መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ርዳታውን የጠየቁት፣የኮንዶሚኒየም ቤት ሲገዙ ከግለሰብ የተበደሩትን ገንዘብ ለመክፈል“ከአቅሜ በላይ ስለኾነብኝ ነው፤” በሚል ነው፡፡ ቋሚ ሲኖዶስ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ 50ሺሕ ብር ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲሰጣቸው መወሰኑንና በውሳኔውም መሠረት፣ከሀገረ ስብከቱ ገቢ ላይ ገንዘቡ ወጪ ኾኖ እንዲከፈል ትእዛዝ ተላልፏል፡፡
መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የመምሪያ ሓላፊነት ደረጃ ያሉ ቢኾንም፣ ከአምስት ዓመት በፊት በጡረታ መሰናበታቸውንና በአሁኑ ወቅት በኮንትራት ውል መቀጠላቸውን የጠቀሱ አስተያየት ሰጭዎች፣“እንደ ቋሚ ሠራተኛ እንዴት ብድግ ተደርጎ ይሰጣቸዋል?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ የመኖርያ ቤት ችግር፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱም የሀገረ ስብከቱም ብዙ ሠራተኞች ችግር እንደመኾኑ፣ “ቋሚ ሲኖዶሱ ተመሳሳይ ጥያቄ በእኩልነት ያስተናግዳል ወይ?” ለሚለው ጥያቄአቸው ምላሽ ይሻሉ፡፡
በቀድሞው መንግሥት የተወረሱ ቤቶችንና ይዞታዎችን ለማስመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት የሚታወቁት መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ፣ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት በአነስተኛ ክፍያ በተከራዩት ቪላ ቤት ነው እየኖሩ የሚገኙት፡፡ ለኮንዶሚኒየም ግዥ ዕዳ መክፈያ ርዳታ መጠየቃቸው በራሱ ባይነቀፍም፣ተመሳሳይ ጥያቄ ያላቸውና ለቤተ ክርስቲያን የደከሙ ሊቃውንትስ ምን ያህል ታይተዋል? ወደገዙት ኮንዶሚኒየም ቤት ገብተው የተከራዩትን ቪላ ያስረክባሉ ወይስ እንደተለመደው የተከራይ አከራይ ኾነው መብላታቸውን ይቀጥላሉ? የሚልም ጥያቄ አላቸው፣ አስተያየት ሰጭዎቹ፡፡
Debramarkos faithfuls petition
ከሁሉ በላይ አነጋጋሪ የኾነው ግን፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የኮንትራት ሠራተኛ እስከኾኑ ድረስ የገንዘብ ርዳታው ለምን ከዚያው እንዲሰጣቸው አልተደረገም? የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የርዳታ ድርጅት ነው ወይ የምእመናንን ገንዘብ እያነሡ የሚሰጡት? የሚል ነው፡፡ የሀገረ ስብከቱን የሙስና ተግባራትና የአሠራር ጥሰት የሚያጣራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኾነው እያለና የማጣራቱ ውጤት ተጠናቆ ውጤቱ ባልታወቀበት ኹኔታ አግባብነት ይኖረዋል ወይ?“በማጣራት ሒደት የተገኙ ማስረጃዎችን መደራደሪያ እያደረጉ የቤተ ክርስቲያኒቱን መብቶችና ጥቆሞች አሳልፈው የሚሰጡ፣ ከተበዳዩ ይልቅ ዘራፊውን ነጻ የሚያወጡ ሐሰተኛ ሪፖርቶችን ማቅረብ በተለመደበት ኹኔታ፣አድርባይነት ለሚጫናቸው መጋቤ ካህናቱ፣ ለ“አጣሪነታቸው” ውለታ የተከፈለ እንዳይኾን እንሰጋለን?” ይላሉ፡፡
በቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ ውሳኔ እንደኾነ ቢገለጽም፣ ቋሚ ሲኖዶሱ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የተዘረዘሩ ተግባራትና ሓላፊነቶቹን ማስጠበቅ እንዳልቻለ፣ ረዳት ሊቀ ጳጳሱ በፓትርያርኩ አሻፈረኝ ባይነት በስሙ ከተመደቡበት “የሐሰት የሹመት ደብዳቤ” በላይ ማሳያ የለም፡፡በምልዓተ ጉባኤውም ባይኾን ቋሚ ሲኖዶሱ በወጉ ተወያይቶ የያዘውና የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ፓራፍ ያደረጉበት ቃለ ጉባኤና ደብዳቤ ሳይኖር፣ብፁዕ ዶ/ር አባ ኀይለ ማርያም፣ በቅዱስ ሲኖዶስ እንደተመደቡ ተደርጎ በአቀባበል መርሐ ግብሩ ላይ የተነበበው ደብዳቤ፣ ፍጹም ሐሰትና የለየለት ፓትርያርካዊ እብሪት ነው፡፡
ከዚህ በመነሣት፣ በልዩ ሀገረ ስብከት ሽፋን ፓትርያርኩ እንዳሻቸው ከሚወስኑበት የአዲስ አበባ ገቢ፣ ችግሩን እያጣሩ ለሚገኙት ለመጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም አላግባብ እንዲሰጥ የታዘዘው የ50ሺሕ ብር የገንዘብ ርዳታ፣በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነ ነው፤ ቢባል ማንን ያሳምናል? ለአዲሱ ሥራ አስኪያጅስ፣ እንዲህ ዐይነትና መሰል ትእዛዛት ፈተና አይኾኑባቸውም ወይ?
sealite mih2010d
በሌብነትና ጎሠኝነት የሚገለጽ አድሏዊነትና የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚያምሰው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ መድኅኑ የኾነውንና ከ96 በመቶ በላይ ሊቃውንትን፣ ካህናትን፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ድጋፍ ያረጋገጠውን የመዋቅር፣ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥእስካልተገበረ ድረስ፣ በልዩ ሀገረ ስብከት ሽፋን፣ የፓትርያርኩ የጓሮ ሽንኩርት መኾኑን ይቀጥላል!
ሌላ ሌላውን ትተን፣ ከመደበኛ ደመወዛቸው ውጭ በየወሩ በሀገረ ስብከቱ የደመወዝ መክፈያ መዝገብ ተካትተው የዚያኑ ያህል ይወስዳሉ መባሉ ሳይበቃ፣ለነዳያን በረከት እንዲናኙ” በሚል በየወሩ 150ሺሕ ብር እንደሚወጣ የሀገረ ስብከቱና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች እየተቹበት ያለ የባጀ ወግ ነው፡፡ እናም ሀገረ ስብከቱ፣ ከሰው ኃይሉና ፋይናንሳዊ ሀብቱ አኳያ፣በስትራተጅያዊ ተቋማዊ የአመራር ለውጥ ራሱን ችሎ እንዲመራ ከማድረግ ውጭ፣ስንኳን በረዳት ሊቀ ጳጳስ ቀርቶ በአራትም ኾነ በ44 ሊቃነ ጳጳሳት መመራቱ ከቶውኑም አይታደገውም!!

በቅርቡ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነት ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ



 የህወሃት የደቡብ ክንፍ ቀኝ እጅ ተደርገው የሚቆጠሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከግርብና እና የእንስሳት ሃብት ሚኒስትር ቦታቸው ለቀው በአምባሳደርነት ተሹመዋል። የግለሰቡ ከማእከላዊ ስልጣን መልቀቅ ህወሃት በደቡብ ክልል ያላትን ስልጣን እንደሚያሳጣት ዘጋቢያችን ገልጿል።
ከሽፈራው ሽጉጤ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማም አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል። አለማየሁ ተገኑ፣ እሸቱ ደሴ፣ አዛናው ታደሰ፣ ዮናስ ዮሴፍ፣ ያለው አባተ እና አብዱልፈታ አብዱላሂም እንዲሁ አምባሰደር ሆነው ተሹመዋል። የቀድመው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የነበሩት አቶ ያለው አባተም እንዲሁ የህወሃት ቀኝ እጅ መሆናቸውን እርሳቸውን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች ይገልጻሉ።
Image may contain: 1 person, closeup

ሐምሌ 5,2009 ጀምሮ በነበረው ህዝባዊ ሰልፍ በህወሓት አጋዚ ወታደር የተገደሉ የነጻነት ፋና ወጊዎቻችን









ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትና በውል አድራሻቸው ያልታወቁ እህት ወንድሞቻችን ሐምሌ 5 ጀምሮ በነበረው ህዝባዊ ሰልፍ በህወሓት አጋዚ ወታደር የተገደሉ የነጻነት ፋና ወጊዎቻችን ናቸው።
ስመማቸውም እንደሚከተለው ነው:-


1. ይሻል ከበደ=> ጎንደር
2. ሲሳይ ታከለ=> ጎንደር
3. አበበ ገረመው =>ባህር ዳር
4. ተፈሪ ባዬ=>ባህር ዳር
5. እድሜዓለም ዘውዱ=>ባህር ዳር
6. አደራጀው ደሳለኝ=>ባህር ዳር (ዩኒቨርሲቲ)
7.ይበልጣል=>ደብረ ታቦር
8. ግዛቸው ከተማ=>ጎንደር
9. አዳነ አየነው=>ጎንደር
10.ማንደፍሮአስረስ =>ባህር ዳር
11. ቁምላቸው ቃሉ =>ባህር ዳር
12. አወቀ ጥበቡ=>ፍኖተ ሰላም
13. ሲሳይ ከበደ=>ጎንደር
14. ሰጠኝ=>ጎንደር (የወልቃይት ተወላጅ)
15. እቴነሽ ሽፈራው=>ም/ጎጃም፣ ጂጋ
16. እንዳለው መኮነን=>ጎንድር፣ ጋይንት
17. እሸቴ =>ባህር ዳር (ቀበሌ 16)
18. ሰለሞን አስቻለ=>ባህር ዳር
19. ሙሉቀን ተፈራ=>ባህር ዳር
20. አደራጀው ኃይሉ =>ባህር ዳር
21. አስማማው በየነ=>ባህር ዳር
22. ታዘበው ጫኔ=>ባህር ዳር
23. አስራት ካሳሁን=>ባህር ዳር
24. የሺዋስ ወርቁ=>ባህር ዳር
25. ብርሃን አቡሃይ=>ባህር ዳር
26. ሽመልስ ታየ=>ባህር ዳር
27. አዛናው ማሙ=>ባህር ዳር
28. ሲሳይ አማረ=>ባህር ዳር
29. ሞላልኝ አታላይ=>ባህር ዳር
30. መሳፍንት=/ጎንደር፣ እስቴ
31. እንግዳው ዘሩ=>ባህር ዳር
32. ዝናው ተሰማ=>ባህር ዳር
33. ሞገስ ሞላ=>ባህር ዳር
34. ሞላልኝ ታደሰ=>ባህር ዳር
35. ይታያል ካሴ =>ባህር ዳር
36. እሸቴ ብርቁ=>ባህር ዳር
37.ሞገስ =>ባህር ዳር
38. ገረመው አበባው=/ባህር ዳር
39. ማህሌት=>ባህር ዳር
40. ተስፋየ ብርሃኑ =>ባህር ዳር
41.ፈንታሁን=>ባህር ዳር
42. ሰጠኝ ካሴ=>ባህር ዳር
43. ባበይ ግርማ=>ባህር ዳር
44. አለበል ዓይናለም=>ደብረ ማርቆስ
45. አብዮት ዘሪሁን=>ባህር ዳር
46. አበጀ ተዘራ =>ወረታ
47. ደሞዜ ዘለቀ=>ወረታ
48. አለበል ሀይማኖት=>ባህር ዳር
49. እስቲበል አስረስ=>አዴት
50. ዓይናዲስ ለዓለም=>ደብረወርቅ
51. ሽመልስ ወንድሙ=>ቡሬ
52. ታደሰ ዘመኑ=>አዴት
53. ሀብታሙ ታምራት=>ባህር ዳር
54. ይበልጣል እውነቱ=>ባ/ዳር፣ ጭስ አባይ
55. ይህነው ሽመልስ=>ደብረታቦር
56. በለጠ ካሴ=>ደብረታቦር
57. አዳነ እንየው=>ጎንደር፣ ቀበሌ 16
58. አለማየሁ ይበልጣል=>ዳንግላ
59. ያየህ በላቸው=>ዳንግላ
60. በረከት አለማየሁ=>ዳንግላ
61. ተመስገን=>ዳንግላ
62. ቅዱስ ሀብቴ =>ባህር ዳር
63. ፍስሃ ጥላሁን =>ባህር ዳር
64. ሰለሞን ጥበቡ=>ቻግኒ
65. እስቲበል አስረስ =>አዴት
66. ዘሪሁን ገደብዬ=>ጎንደር
67. ሲሳይ ባብል=>ጎንደር
68. ባየሁ ጎንደር=>ጎንደር
69. በለጡ መሃመድ=>አዘዞ፣ ጎንደር
70. እንጀራ ባዬ => አዘዞ፣ ጎንደር
71. ወንድም=>ጎንደር
72. ግርማቸው ከተማ=>ላይ አርማጭሆ
73. ሊሻን ከበደ =>አይባ
74. መሌ አይምባ=> አይባ
75. አዛነው ደሴ =>አርማጭሆ
76. አራገው መለስ =>አርማጭሆ
77. ሰጠኝ አድማሱ=>ደልጊ
78. ታረቀኝ ተሾመ=> ደልጊ
79. ሄኖክ አታሎ=>ደልጊ
80. ደሴ ደረሰ=>ሻውራ
81. ግርማቸው ሞገስ=> ሻውራ
82. ወርቁ ጠቁሳ=> ሻውራ
83. ማማዬ አንጋው=>ዳንሻ
84. ፈንታ አህመድ=>ዳንሻ
85. ክንፌ ቸኮል=>በአከር
86. ሲሳይ ታከለ=>አርማጭሆ
87. ማዕረግ ብርሃን=>ደብረታቦር
88. መምህር ተስፋየ ብርሃን=>ደብረታቦር ቀበሌ 01
89. ይበልጣል ደሴ=>ደብረታቦርቀበሌ 01
90. አራጋው መለሰ =>አርማጭሆ
91. አዳነ አያሌው=>አርማጭሆ
92. አያናው ደሴ =>አርማጭሆ
93. ትርፌ አጣናው =>አርማጭሆ
94. መምህር ብርሃኑ አየለ=>ሰሜን ሸዋ፣ ማጀቴ
95. አብራራው አለማየሁ=>ደ/ጎንደር፣ ስማዳ
96. ተመስገን ሲሳይ=> ደ/ጎንደር፣ ስማዳ
97. ጋሻው ሲራጅ=> ደ/ጎንደር፣ ስማዳ
98. ፈንታ ሞገስ=>ደ/ጎንደር፣ ስማዳ
99. ታደለ ያየህ =>ም/ጎጃም፣
100 ፡ በለጠ አማረ….ወረታ ጎንደር
101፡ አቶ ምክሩ ጢስ አባይ
102፡ ልዑል ነጋሽ----ባህረዳረ/ጎንደር
103፡ጣም ያለዉ ዘመነ---ዕስቴ ደ.ጎንደር
104: ጌታቸዉ አበራ----ጎንደር/ጠዳ

Ethiopian Splited Orthodox synods to meet for reconciliation, unification


by Engidu Woldie
ESAT News (July 13, 2018)
Abuna Merkorios
One of the activities on the sidelines of Prime Minister Abiy Ahmed’s visit to the United States is the meeting between the exiled synod of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church and the synod in Addis Ababa.
Three archbishops representing each sides will meet in Washington, DC, next week to iron out their differences and perhaps unify the two synods.
A statement released today by the exiled synod says it has been making great efforts to resolve differences peacefully and in line with the dogma of the church.
Abuna Merkorios, the Patriarch of the exiled synod, is the fourth Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church, anointed in 1988. But when the current ruling party, the EPRDF, took control of the government in 1991, he was forced into exile. According to the wikileaks cables, the then Prime Minister, Tamrat Layne, admitted that he had signed an order to remove Abuna Merkorios from the Patriarchate and appoint Abune Paulos, creating division within the Church.
Abuna Paulos died in 2012 and was replaced by Abuna Mathias, who is now the Patriarch in Addis Ababa.
In exile in the U.S., Abuna Merkorios formed his Patriarchate and had his own followers.
Several attempts to unite the two synods were to no avail. The church has remained divided for over a quarter century, mainly due to the interference of the ruling EPRDF in the affairs of the church.
Sources say the new Prime Minister is determined to unite the two synods. He would like to see the two merge before the conclusion of his visit to the United States at the end of this month.

በደብረማርቆስ አቶ በረከት ስምኦን ታይተዋል በሚል ጉዳት የጎዛምን ሆቴል ደረሰበት

የጎዛምን ሆቴል ባለቤት ለሕዝብና ለሃገር እጨነቃለሁ አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በደብረማርቆስ አቶ በረከት ስምኦን ታይተዋል በሚል ጉዳት የደረሰበት የጎዛምን ሆቴል ባለቤት ከንብረታቸው ይልቅ ለሕዝብና ለሃገር እንደሚጨነቁ ገለጹ።
የሆቴሉ ባለቤት ዶክተር ምንውየለት ሞሴ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ሆቴሉን በትውልድ አካባቢውያቸው የገነቡት ሕዝቡ እንዲጠቀምና ሀገርን ለማሳደግ ነው።
ከ40 አመታት በላይ በውጭ ሀገር የኖሩትና በተለያዩ የስራ ሃላፊነት ላይ የቆዩት ዶክተር ምንውየለት ሞሴ ሕዝቡ በኢትዮጵያ ፍትህ እስኪሰፍንና እኩልነት እስኪረጋገጥ ድረስ ትግሉን መቀጠል አለበት ብለዋል።
ለዶክተር አብይ አህመድ የሚሰጠው ድጋፍም መቀጠል እንደሚኖርበትም ነው የገለጹት።
በጎዛምን ሆቴል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስም ኣአሁንም የምጨነቀው ለሃገሬና ለወገኔ በጠቅላላው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ሲሉም ዶክተር ምንውየለት ተናግረዋል።
በአማራ ክልል በደብረማርቆስ ከተማ አቶ በረከት ስምኦን ታይተዋል በሚል የጎዛምን ሆቴልን ጨምሮ ተሽከርካሪዎችና የሆቴሉ ንብረቶች ወድመዋል።ትልቅ ሰው የተባለው ሆቴልም ከቀደመው አገዛዝ ጋር ባለቤቷ የጥቅም ትስስር አላቸው በሚል ጉዳት መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል።
Image may contain: 1 person, standing and outdoor

wanted officials