Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, September 17, 2018

Ethiopia: Suspects in Burayu ethnic attack arraigned before court



Over 200 suspects of ethnic attack perpetrated last weekend outside Ethiopia’s capital Addis Ababa have been arraigned today before the 19th bench of the federal high court.
The defendants were accused of planning and coordinating the attacks in Burayu and other districts in the outskirts of the capital where at least 58 people were killed.
The federal police also presented names of individuals who allegedly used vehicles in transporting the perpetrators and making payments to the alleged participants in the ethnic attack.
Police in Burayu have also arraigned 35 suspects of the attack before a court in the town.
The courts have allowed additional 14 days requested by police to finish its investigations into the deadly attack.
Nearly 400 suspects have been arrested in connection with the weekend attack.
Last weekend saw deadly ethnic violence in west of Addis Ababa, especially in Burayu, where residents and victims told several media outlets that a group used rocks, knives and sticks to attack the Dorzes and other ethnic groups from southern Ethiopia.
Thousands flee their homes to save their lives and are now sheltered in schools.

Sunday, September 16, 2018

Several killed in ‘ethnic motivated’ attacks in Addis Ababa


Partial view of the displaced sheltered in a school
By Engidu Woldie
ESAT News (September 16, 2018)
The last three days have seen bloody and deadly attacks in the outskirts of Ethiopia’s capital Addis Ababa in what residents and social media activists described were ethnic motivated, with an Oromo youth group known as Qeerroo brutally attacking other groups.
ESAT received several gruesome photos of bodies of people covered with blood, not appropriate to share in this post. Messages sent to ESAT also described details of the attacks allegedly perpetrated by the group calling itself Qeerroo, a network of youth led by and taking cues from diaspora Oromo ethno nationalists.
The killings took place as the Qeerroos return home on Saturday to their districts outside the capital after taking part at a welcoming rally in Addis Ababa’s central Meskel Square for leaders of the Oromo Liberation Front (OLF), a group that was in exile for most of its existence.
Deputy Mayor of the capital, Takele Uma, who is an Oromo, said the killings took place as the rally goers return home but denied any links to the Qeerroos. He said several people have sustained injuries and others displaced.
The attacks took place in Burayu, Ashewa Meda, Asko, Anfu and Keta areas in the outskirts of the capital which are administratively with in the Oromo region.
A number of people report seeing several bodies taken into the Paulos Hospital in Addis Ababa.
Reports and photos reaching ESAT show hundreds of people are sheltered in schools and churches to save their lives. Those who escaped from the attacks and spoke to the Ethiopian Television said their houses were set ablaze by the attackers. A man said his life was spared because of a neighbor who spoke the attackers’ language.
Survivors of the attack and some residents of the capital held a flash demonstration at the headquarters of the Ethiopian Television to make their voice heard.
A woman said police were overpowered by the attackers and they could not stop the mayhem.
Asked why the police failed to stop the attacks, police commissioner for the Oromo region, Alemayehu Ejigu told etv that the topography of the areas and inaccessible roads made the work of the police difficult. But a woman who spoke to etv said she actually saw some police officers running away from the attackers.
The commissioner, who denied the attacks were ethnic motivated, could not say how many people were killed in the attack. He however said 70 people have been arrested so far in connection with the attack.
[This story is developing]

Saturday, August 25, 2018

አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ!

አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ!
Image may contain: 1 person
.
እጅግ በጣም ተወዳጁ የአገር ባለውለታ ታማኝ በየነ
ወደ እናት አገሩ ወደ ኢትዮጵያ ከረጅም ዓመት ቆይታ በኋላ ነሐሴ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ይገባል ። ታማኝ በየነ "አንድ ሕዝብ ፣አንድ ኢትዮጵያ " በማለት ባለፉቱ 28 ዓመታት ብሔር ፣ ሐይማኖት ፣ቋንቋ እና ቦታ ሣይገድበው ስለ-ኢትዮጵያዊያን እና ስለ-ሚወዳት እናት ሃገሩ ኢትዮጵያ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል 
ሙሉ ጊዜውን የሰጠ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ ነው። ስለ-ታማኝ ይህ ከላይ የተገለጸው መልካም ተግባር ከውቅያኖስ በማንኪያ እንደመጨለፍ የሚቆጠር እንጂ የእርሱን በጎ ተግባር ሙሉ በሙሉ የሚገልጽ አይደለም ። ይህ ሀቅ እንዳለ ሆኖ የአርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ወደ እናት ሃገሩ ሲገባ የሚደረገለት አቀባበል በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል
ለረጅም ዓመታት አንድነትን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልን እና መተሳሰብን ሲሰብክ የኖረ፣ አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ የሚል አቋም ያለዉ እና ብሔር ሃይማኖት ሳይለይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የታገለ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ለመቀበል ፤ 1ኛ. ረ/ፕ ነብዩ ባዬ፣ 2ኛ. ሀብታሙብ አዱኛ ፣3ኛ. አርቲስት ዳዊት ይፍሩ ፣ 4ኛ. አቶ ይልማ ይፍሩ ፣ 5ኛ. አርቲስትና ጋዜጠኛ ሠይፉ ፋንታሁን ፣ 6ኛ. አቶ የሺዋስ አስፋ ፣ 7ኛ. ኮሜዲያን ደረጃ ሀይሌ ፣ 8ኛ. ድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ ፣ 9ኛ. አቶ ይድነቃቸው ከበደ ፣ 10ኛ. አቶ ፋአድ ሰማን ፣ 11ኛ. አርቲስት አብርሃም ወልዴ ፣ 12ኛ. ድምፃዊ ታደለ ሮባ፤ የአቀባበሉ ዐብይ የኮሚቴ አባላት መካከል ሲሆኑ፤ ሌሎችም ንዑስ ኮሚቴ አባላት በታላቁ ሰው የአቀባበል ሥነ-ስርዓት ስራዎችን የሚያከናውኑ የኮሚቴ አባላት ተዋቅረው ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ። የአርቲስት ፣ የአክቲቪስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የታማኝ በየነን አቀባበል ለማስተባበር በዋነኛነት ይህ ከላይ የተገለጸው ኮሚቴ ነሐሴ 26 እና 27 በሚከናወነው መርሐ ግብር ላይ በዋነኛነት ስራውን ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነው።
.
(ይድነቃቸው ከበደ)

Image may contain: one or more people, people on stage and people standing


የአግ7 አርበኛ ታጋዩች ትጥቃቸውን አይፈቱም፤ ከነሙሉ ትጥቃቸው ይገባሉ።

ስለ አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ፅኑወች አርበኛ ታጋዩች የመጀመሪያ ዙር ወደ ሀገር ቤት አገባብ እና አቀባበል ሁኔታ በቅንጭቡ ፦
፩ኛ. ከኤርትራ የተለያዩ ካምፕች ከ300 በላይ ታጋይ አርበኞች ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ።
፪ኛ. በአማራ ክልል በ3 የማሰልጠኛ ጣቢያወች የሰለጠኑ ፣ እንዲሁም ንቅናቄው በጎበዝ አለቆች አደራጂቶ አስፈላጊውን የትጥቅ፣ የስንቅ አቅርቦት እያሟላ በተለያዩ አካባቢወች የህወሓትን ቡድን መፈናፈኛ አሳጥተው የነበሩ ከ5ሺ በላይ አርበኛ ታጋዩች ከነሙሉ ትጥቃቸው ይቀላቀላሉ።
፫ኛ. ሁለት ከተሞች ጎንደር እና ባህርዳር የአቀባበል መረሀ ግብሮች ተዘጋጂተዋል በጊዜያዊነት ከክልሉ የለውጥ ሃይል ጋር በመወያየት በተዘጋጀ ስፍራ ይሰፍራሉ። ዘላቂው ካምፕ ሙሉ በሙሉ እስኪዘጋጂ ድረስ።
፬ኛ. ሲገቡ በፀረ ለውጥ ሀይሉ የደህንነት ስጋት እንዳይፈጠር ከሀገር መከላከያ እና ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።
፭ኛ. የአግ7 አርበኛ ታጋዩች ትጥቃቸውን አይፈቱም፤ ከነሙሉ ትጥቃቸው ይገባሉ። ከገቡም በኃላ የእራሳቸው ህጋዊ ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል።ከካምፕ ውጭ ወደ ቤተሰብ ቢያቀኑ እንኳ ትጥቃቸውን ይዘው መሄድ ይችላሉ።
፮ኛ. በነፃነት ትግሉ በእስር ፣ በአካል መጉደል ፣ በቤተሰብ መበተን ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ለተጋለጡ አርበኛ ታጋዩች የንቅናቄው አባላት ለአመታት የሚቆይ በሚፈልጉት የሙያ መስክ ብቁ የሚያደርግ እና የሚያቋቁም ትልቅ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ስራ ተግብቷል።
፯ኛ. በመላ ሀገሪቱ ለአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ አባሎቹ ወደ ካምፕ የሚገቡ ከ6 በላይ ካምፕች ቦታ መረጣና ወታደራዊ ጥናት እየተካሄደባቸው ይገኛል።4ቱ ወይም 5ቱ በአማራ ክልል ይሆናሉ።
በፅኑ ኢትዮጵያዊነት ከህብረ ብሄራዊው የአርበኞች ግንቦት 7 ሃይል ጋር ወደ ፊት !!
ኢትዮጵያን እና ህዝቧን እግዚአብሔር ይባርክ ይቀድስም!!

Friday, August 24, 2018

Ethiopian lady looted and deposited billions in a bank in Germany





በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የሚታሙት ፤ የመብራት ሀይል ሹመታቸውን ተከትሎ ቢሊዮኖችን በጀርመን ባንኮች ያከማቹት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ከሀላፊነታቸው ተነሱ።

የፋይላችን መረጃ የአሜሪካ ባለስልጣን የነበሩትን ያማማቶን ዋቢ አድርጎ እንደሚጠቁመው ከደሃው የኢትዮጲያ ህዝብ ላይ የተዘረፈው ብር በአንደኛ ደረጃ የሚገኘው በጀርመን ሀገር እንደሆነ ....... ከሚታወቁት ቱባ-ቱባ የህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት በላይ ኤልክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ዋና ሃላፊ የሆነችዋ ሴትዮ $180,000,000 ዶላር በውጪ ሀገር ባንክ ማስቀመጧ ሁሉም አስገርሟል፡፡ ይህቺ ጀማሪ ባለስልጣን 180 ሚሊዮን ዶላር ከዘረፈች ነባሮቹ ምን ያህል እንደሚዘርፉ መገመት ይቻላል፡፡


ሡዳን ጌታቸው አሰፋን አሳልፋ ላለመስጠት እያንገራገረች ነው



ሡዳን ጌታቸው አሰፋን አሳልፋ ላለመስጠት እያንገራገረች መሆኑን እጅግ የታመነ የሊክድ ኒውስ ምንጮቻችን አሳውቀውናል፡፡




ጌታቸው አሰፋ አገር እየቆረሰ ጉርብትና ባፈራው ወዳጅነት ሱዳኖች አሳልፎ ላለመስጠት እያንገራገሩ ነው። ለኢትዮጲያ መንግስት ተላልፎ እንዲሰጥ መንግስት በከፍተኛ ንግግር ላይ ነው፡፡
የሱዳን መንግስትና ወያኔ በአንድ በኩል የኢትዮያ መንግስት በሌላ ሆነው ስጥ፣ አልስጥም የጦፈ ክርክር ላይ ናቸው። አሁን ላይ ሱዳኖች አሳልፈው እንደሚሰጡ ቃል እየገቡ ነው።

አፈትላኪ ዜናዎች ጌታቸው አሰፋን መፈርጠጡን በግምባር ቀደምትነት ያረጋገጠች ሲሆን አንዳንድ ተልካሻዎች ጌታቸው አሰፋ አዲስ አበባ ነው ብለው የሚያወሩት ፍፁም ሀሰት መሆኑን ልናረጋግጥና
እንኳን አዲሳባ ሊመጣ ከስልጣኑ እንደተነሳ ኦፊሱን ቆልፎ ነው ተደብቆ ወደ መቀሌ የሸሸው።

ከወራት ቆይታ በኋላ በቅርቡ ወደ ሱዳን መሸሹን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በቅርቡም ሴክሬታሪው እቃ ይዛ ወደ መቀሌ ልታመልጥ ስትል ተይዛለች በነገራችን ላይ ብዙ ጉድ አለ እንዲወጣ የሀገሬ ህዝብ እንዲያውቀው እየታገልኩ ነው፡፡ ጌታቸው እንደውቅያኖስ የሰፋ ግፍ አገራችን ላይ ሲፈጽም የነበረ ነው ጠብቁ እንዳንድ ነገሮች ይኖራሉ..!!አባኮስትር በላይ

ፍትህ የጌታቸው አሰፋ ሰለባ ለሆነችው አገራችን!
Image may contain: 1 person, text

ሰበር ዜና : አቶ በረከት ስምዖን እና ታደሰ ጥንቅሹ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሜቴ ታገዱ::

ሰበር ዜና :
አቶ በረከት ስምዖን እና ታደሰ ጥንቅሹ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሜቴ ታገዱ::
Image may contain: 2 people, people sitting

ሶማሊ ላንድ ሲያመልጡ የነበሩ ሁለት የኢትዮጵያ ባልስልጣናትን ይዛ አሰረች።


ሶማሊ ላንድ ሲያመልጡ የነበሩ ሁለት የ ኢትዮጵያ ባልስልጣናትን ይዛ አሰረች።
 ሀልቤግ የተሰኘው የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ የሶማሊላንድ የደህንነት ባለስልጣናት ሀርጌሳ ውሰጥ ነው ሁለት የአብዲ ኢሌይ የካቢኔ አባላትን ይዘው ያሰሩት።
የታሰሩት ባለስልጣናት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የነበሩት ኢብራሂም አድም ማሃድ እና የፍትህ ቢሮ ሃላፊው አብዲልማጅድ አህመድ ጃማ ናቸው።
ባለስልጣናቱ የተያዙት፤የክልሉ ርእስ መስተዳድር አቶ አብዲ ኢሌይ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ከጅጅጋ ሲያመልጡ ነው። ሹመኞቹ ከጅግጅጋ ውድ ሶማሊ ላንድ መዲና ወደ ሀርጌሳ በማቅናት ላለፈው ሳምንት እዚያው መቆየታቸው ታወቆአል።
የሶማሊላንድ የኢሚግሬሽንና የደህንነት ዲፓርትመንት ሀላፊ ታይፕ ኦስማን ለሀልቤግ የዜና አገልግሎት ሲናገሩ ባለስልጣናቱ በኢልጋ አውሮፕላን ማረፊያ በህገ ወጥ መንገድ በመግባታቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
የባለስልጣናቱ አላማ ወደ ሞቃዲሾ ለመሄድ እንደነበር የጠቀሱት ሚሰተር ኦስማን፤ ሆኖም ሁለቱም ምንም አይነት ህጋዊ የጉዞ ሰነድ እንደሌላቸው አመልክተዋል።No automatic alt text available.

ጀርመን ውስጥ 1.6 ሚሊዮን ክፍት የስራ ቦታዎች አሉ

አዲሱ የጀርመን የፍልሰት ጉዳይ ረቂቅ ህግ 

በአዲሱ ህግ  ጀርመን ውስጥ በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ገብተው መሥራት የሚያስችሏቸው መስፈርቶች ተቀምጠዋል። የትምህርት ደረጃ፣ እድሜ፣ የቋንቋ ችሎታ፣ የተጨበጠ የሥራ እድል እና ኑሮን በራስ የመምራት አቅም ጀርመን ለሥራ የሚመጡ የውጭ ዜጎች የሚመረጡባቸው መስፈርቶች ናቸው።
    
አውዲዮውን ያዳምጡ።11:14

አዲሱ የጀርመን የፍልሰት ጉዳይ ረቂቅ ህግ

የሰለጠነ የሰው ኃይል ከውጭ ወደ ጀርመን በቀላሉ እንዲገባ ያስችላል የተባለው አዲሱ የጀርመን የፈላስያን ጉዳይ ህግ ዕውን ሊሆን የተቃረበ ይመስላል። ጀርመን ውስጥ በአንዳንድ የሞያ መስኮች በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት አለ። በተለይ የመሀንዲሶች፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሙያተኞች እና የጤና ባለሞያዎች እጥረት ከፍተኛ ነው።  የኤኮኖሚ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት  እንዳስቀመጠው 1.6 ሚሊዮን ክፍት የስራ ቦታዎች አሉ። በተለያዩ የሙያ መስኮች የሚታየውን ጉድለት ለመሙላት በመፍትሄነት ከሚቀርቡት ውስጥ ከውጭ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማስገባት አንዱ ነው። ይህም ከ20 ዓመታት በላይ ሲያነጋግር ሲያከራክር እና ሲያወዛግብ የቆየ ጉዳይ ነው። ከአከራካሪዎቹ ጉዳዮች ውስጥ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል ከውጭ ይግባ ፣የለም ጀርመን ያሉ ስራ አጦችን ችግሩ ባየለባቸው ዘርፎች በማሰልጠን ለመተካት ጥረት ይደረግ የሚሉ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል። ከዚሁ ጋርም የሀገሪቱ የፍልሰት ጉዳይ ህግ የውጭ ዜጎችን በተለይም በልዩ ክህሎታቸው የሚፈለጉትን ባለሞያዎች የሚማርክ አለመሆኑ ችግሩ እንዳይፈታ እንቅፋት ሆኖ መዝለቁ ነው የሚነገረው። የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በሙያቸው የሚፈለጉ የውጭ ዜጎች በቀላሉ ጀርመን ገብተው እንዲሰሩ ያስችላል የተባለ  አዲስ ህግ በቅርቡ አርቅቋል። የጀርመን ሥራ ሚኒስቴር እና የኤኮኖሚ ሚኒስቴር የተስማሙበት ይህ
Deutschland ausländische Experten (picture-alliance/dpa)
ረቂቅ ከአንድ ሳምንት በኋላ ለጀርመን ካቢኔ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ረቂቅ ህግ እንደሚጠቁመው የችግሩ መንስኤ በሀገሪቱ ሥራ አጥነት መቀነሱ እና ከወጣቱ ይልቅ በእድሜ የገፋው ህዝብ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ነው። በዚህ የተነሳም የጀርመን ኩባንያዎች የሰው ኃይል እጥረት ባለባቸው የስራ መስኮች ሙያተኞችን ለማግኘት ለሌሎች የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ዜጎች የበለጠውን እድል ሲሰጡ ቢቆዩም የሚፈልጉትን ሙያተኛ ማግኘት አለመቻላቸው በረቂቁ ተገልጿል። እናም ጀርመን ከአውሮጳ ህብረት ውጭ ከሦስተኛው ዓለም ሀገራት በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ሙያተኞችን ማስገባት የግድ ይላታል በረቂቁ እንደሰፈረው። ሀገሪቱ የዛሬ 3 ዓመት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን  ስትቀበል  የሞያተኞች እጥረት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ይቀንሳል የሚል ግምት ነበር። ሆኖም በጀርመኑ የኤኮኖሚ ትብብር እና የልማት ድርጅት የፍልሰት ጉዳዮች ተመራማሪ ቶማስ ሊቢሽ እንደሚሉት ይህ ተስፋ እንደተደረገው መፍትሄ ሊሆን አልቻለም። ሊቢሽ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ስደተኞች በብዛት መግባታቸው ጥቅም ነበረው። ግን ያኔ ወደ ጀርመን የገባው ስደተኛ ግን እዚህ ያለውን የሥራ ገበያ የሚመጥን አልነበረም።
« ስደተኞች መግባታቸው በተወሰነ ደረጃ ረድቷል። ሆኖም አብዛኛዎቹ ክህሎታቸው ዝቅተኛ ነው። ለምሳሌ በኢንዱስትሪው እና በጤና ዘርፍ ሙያተኞች የሆኑ ሰዎች ይመጣሉ። ሆኖም
Deutschland ausländische Experten (picture-alliance/dpa)
ለሥራው የሚፈልገው አቅም የሌላቸው  ወይም የሥራ ገበያው የማይፈልጋቸው ናቸው። ከ2 ከ3 ዓመት በፉት የገቡት ስደተኞች ተስፋ እእንዳደረግነው ሆነው አላገኘናቸውም።»
በአዲሱ ህግ  ጀርመን ውስጥ በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ገብተው መሥራት የሚያስችሏቸው መስፈርቶች ተቀምጠዋል። የትምህርት ደረጃ፣ እድሜ፣ የቋንቋ ችሎታ፣ የተጨበጠ የሥራ እድል እና ኑሮን በራስ የመምራት አቅም ጀርመን ለሥራ የሚመጡ የውጭ ዜጎች የሚመረጡባቸው መስፈርቶች ናቸው። የውጭ ዜጎች ለነዚህ መስፈርቶች የተቀመጠውን ነጥብ ካሟሉ ጀርመን መግባት ይፈቀድላቸዋል። የፖለቲካ ሳይንስ እና የህግ ምሁሩ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ  ከከዚህ ቀደሞቹ መመዘኛዎች ተፈላጊ ሙያተኞችን የሚስቡ አልነበሩም ይላሉ። በዚህ የተነሳም ችግሩን መፍታት አለመቻሉን ያስረዳሉ። ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ጋር እያነጻጸሩ ስለ አዲሱ ረቂቅ ህግ በሰጡት አስተያየት  በውስጡ የተቀመጡት መስፈርቶች የውጭ ዜጎችን መማረክ መቻላቸው ያጠራጥራል ይላሉ ዶክተር ለማ ።
ጀርመን የውጭ ዜጎችን ለሥራ እየመለመለች ወደ ሀገርዋ ማስገባት የጀመረችው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ነው። ያኔ የሀገሪቱ ኩባንያዎች ሠራተኞች በእጅጉ ያስፈልጓቸው ነበር። በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር በ1950 ዎቹ እና 60ዎቹ በጦርነቱ የወደመውን መልሶ ለመገንባት የሚያስፈልግ የሰው ኃይል በርካሽ ጉልበት ጀርመን ገባ።  በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች ከኢጣልያ፣ ከግሪክ እና ከቱርክ  «እንግዳ ሠራተኞች» እየተባሉ መጥተው በሀገሪቱ የኤኮኖሚ ተዐምር ማምጣት ተቻለ። ከዚያን ወዲህ የውጭ ዜጎችን የሚመለከተው የጀርመን ህግ እንዳወዛገበ
Symbolbild Flüchtlinge als Fachkräfte (picture-alliance/dpa/S. Hoppe)
ነው። ለሥራ የመጡ የውጭ ዜጎች ሥራቸው ሲያበቃ ወደ ሀገራቸው ከመመለስ ይልቅ በተለያዩ ምክንያቶች ጀርመን መቅረታቸው ከሚያወዛግቡት ጉዳዮች  አንዱ ሆኖ ዘልቋል። በነዚህ ውዝግቦች መንስኤ የፌደራል መንግሥቱ በጎርጎሮሳዊው 1973 የውጭ ዜጎችን ለሥራ መመልመልን አስቁሞ ነበር። በ2000 ዓም መንግሥትን ይመራ የነበረው የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ ይህን እገዳ አንስቶ በተለይ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በምህጻሩ የአይ.ቲ ባለሞያዎች በአሜሪካኑ ግሪን ካርድ አምሳያ ጀርመን እንዲገቡ ተደረጓል። ከዚያን ጊዜ አንስቶም የፖለቲካው ትኩረት በሥራ ወደ ጀርመን የሚገቡ ስደተኞች እና አጠቃላዪ የፍልሰት ጉዳይ ሆነ። ጀርመንን አሁን የሚመራው የእህትማማቾቹ የክርስቲያን ዴሞክራት ህብረት እና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲዎች እንዲሁም የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ ተጣማሪ መንግሥት በዚህ ዓመት በየካቲት ወር ሲመሰረት አንድ የፍልሰት ጉዳይ  ህግ ለማውጣት ተስማምቶ ነበር ። በዚሁ መሠረት የተዘጋጀው አዲሱ ሰነድ በጀርመን ምጣኔ ሀብት በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር በአግባቡ እና በግልጽ አሰራር መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ ተጠቅሷል። ከዚህ ቀደም የተቀመጡ አንዳንድ ገደቦችን ማንሳት አስፈላጊ እንደሆነ ይገልጻል። ለዓመታት ለዘለቀው ችግር መፍትሄ ያስገኛሉ የተባሉ ሌሎች ህጎችም ወጥተው ነበር። አሁን ሌላ አዲስ ህግ ያስፈለገው የፍልሰት ጉዳዮች ተመራማሪው ሊቢሽ እንደሚያስረዱት የቀደሙት መሻሻል ስላለባቸው ነው።
«ከህዝብ ቁጥር ጋር በተያያዘ ምክንያት ከፍተኛ ለውጥ መጥቷል። በሚቀጥለው ዓመት ብዙ ሰዎች በጡረታ ይሰናበታሉ። እነርሱን የሚተካ በቂ ወጣት የለም። ስለዚህ ከቀድሞው የበለጠ የሠራተኛ ኃይል ያስፈልገናል። እነዚህ ማሻሻያዎች ስለሚያስፈልጉን ጥሩ እና የፍልሰተኞች ጉዳይ ህግ ያስፈልገናል።»
Symbolbild Industriearbeiter (picture-alliance/PhotoAlto)
በእስከዛሬው ህግ በማንኛውም ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሀገር ውስጥ አመላካቾች ነበር። ሠራተኞችም ከውጭ የሚገባ የሰው ኃይል ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ በሆነባቸው ሥራዎች ብቻ ነበር የሚፈለጉት ። የሚገቡትም ሥራ ካገኙ በኋላ ነበር ይሁን እና  የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ SPD አሁን ይህን የሚቀይር ሃሳብ ይዞ ነው የቀረበው። ወደፊት የውጭ ዜጎች ሥራ ሳያገኙም ለሥራ ፍለጋ ጀርመን መምጣት ይችላሉ። ሥራ መፈለጊያ የ6 ወራት ጊዜ ይሰጣቸዋል ተብሏል። በዶክተር ለማ እምነት ይህም የውጭ ዜጋ ሞያተኞች ጀርመን ለሥራ ፍለጋ እንዲመጡ የሚያበረታታ አይመስላቸውም። በአሁኑ ጊዜ ጀርመን በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሞያዎች እጥረት ብቻ አይደለም ያለባት። መካከለኛ በሚባል ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግርም ሰንጎ ይዟታል። የነርሶች፣ የበሽተኛ ተንከባካቢዎች፣ የመዋዕለ ህጻናት ረዳቶች ከእጅ ሞያ ዘርፍ ደግሞ ፣የኤሌክትሪክ ባለሞያዎች እና የአናጢዎች አጥረት አለ ። በእነዚህና በመሳሰሉት ዘርፎች ሙያተኞችን ከሦስተኛው ዓለምም ጭምር ለማስገባት የሚደረገው ሙከራ የሁሉንም ፖለቲከኞች ይሁንታ አላገኘም። ቀኝ ጽንፈኛው አማራጭ ለጀርመን የተባለው ፓርቲ  ረቂቁ  ለፍልሰት የተከፈተ የጓሮ በር ነው ሲል ይቃወማል። ከሁሉ በተለየ የግራዎቹ ፓርቲ ይህን መሰሉ አሠራር በሌሎች ሀገራት የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ይፈጥራል ሲል ስጋቱን ይገልጻል። አሠሪዎች ግን የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት እድገት እንዳይደናቀፍ ችግሩን መፍታት ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ አይደለም ሲሉ አጥብቀው ይከራከራሉ። 
ኂሩት መለሰ 
ነጋሽ መሐመድ

Tuesday, August 21, 2018

ኢሳት-የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ በመግባት በሰላማዊ መንገድ ትግሉ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ ደረሱ


 የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ።
በፕሬዝዳንቱ የሚመራው የልኡካን ቡድን ወደ አማራ ክልል እንደሚመጣ የአማራ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው።
በአስመራ ቆይታ ያደረገው የአማራ ክልል የልኡካን ቡድን ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አመራሮች ጋር መወያቱ ታውቋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል የሚያደርጉት ጉብኝት መቼና በምን ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር እንደሚሆን ግን በዝርዝር አልተገለጸም።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 አመት በኋላ ወደ ሞቃዲሾ በረራ ሊጀምር ነው ተብሏል።
የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደገለጹት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አማራ ክልል በመምጣት ጉብኝት እንዲያደርጉ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
የሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትህ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ እና የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ልዩ አማካሪ ከሆኑት ከአቶ የማነ ገብረአብ ጋር ውይይት መደረጉን የጠቀሱት አቶ ንጉሱ ጥላሁን በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ አማራ ክልል እንዲመጣ መስማማታቸውን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ መቼና በምን ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩር ግን ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
አቶ ኢሳያስ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ለ20 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት በአዲስ መልክ ከተጀመረ ወዲህ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ የአማራ ክልሉ ለሁለተኛ ጊዜ ሆኖ ይመዘገባል።
የአማራ ክልል ልዩ የልዑካን ቡድንም ወደ ኤርትራ በቅርቡ እንደሚያመራ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገልጸዋል።
አቶ ንጉሱ ሰሞኑን የክልላቸውን መንግስት ወክለው አንድ የልዑካን ቡድን በመምራት አስመራ ቆይታ ማድረጋቸው መዘገቡ ይታወሳል።
በዚህን ወቅት በኤርትራ ብረት አንስቶ እየታገለ ከሚገኘው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ጋር መወያያቱ ተገልጿል።
ንቅናቄው ወደ ሀገር ቤት በመግባት በሰላማዊ መንገድ ትግሉ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ መደረሱንም አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታውቀዋል።
በኤርትራ ቆይታ ወቅት ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ምክክር መደረጉን የጠቀሱት አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት መደረጉም ተመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ በረራ ሊጀመር መሆኑ ተገልጿል።
ወደ ሞቃዲሾ የሚደረገው በረራ ከ41 ዓመታት በኋላ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሳምንት ሶስት ጊዜ እንደሚደረግም ለማወቅ ተችሏል።
ከሶማሊያ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት በጅቡቲና በናይሮቢ ሲደረግ የነበረውን በረራ የሚያስቀረው የሞቃዲሾው አዲሱ መስመር መቼ እንደሚጀመር ግን የተገለጸ ነገር የለም።

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቅ ዙሪያ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ሚና ጉልህ ድርሻ እንደነበረው የንቅናቄው ዋና ጸሀፊ ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ገለጹ።


በኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቅ ዙሪያ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ሚና ጉልህ ድርሻ እንደነበረው የንቅናቄው ዋና ጸሀፊ ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ገለጹ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ) አቶ አንዳርጋቸው ይህን የገለሱት በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገ ታላቅ ስብሰባ ላይ የኤርትራ መንግስት የነጻነት ትግሉን በማገዝ በኩል ላደረገው ድጋፍና ውለታ ምስጋና ባቀረቡበት ጊዜ ነው።
አንዳንድ ወገኖች ኤርትራና ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በኋላ ወደ እርቅ የመጡት በውጭ ኃይሎች ተጽዕኖ እንደሆነ መላምት ሢሰነዝሩ ቢደመጡም፤ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ግን ሀገራቱ ወደ እርቅና ፍቅር የመጡት ያለ አንድም የውጭ ኃይላት ሸምጋይ እንደሆነ አስረግጠው ተናግረዋል።
ይልቁንም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በዚህ ረገድ ገንቢ ሚና መጫዎቱን የጠቀሱት አቶ አንዳርጋቸው፣”ንቅናቄያችን በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በኤርትራ መንግስት አመኔታን ያተረፈ ነው” ብለዋል።
በርካታ የንቅናቄው ደጋፊዎች በታደሙበት በዲሲው ስብሰባ ታጋይ አንዳርጋቸው የተለያዩ ሽልማቶች የተበረከቱላቸው ሲሆን፣ ዝግጅቱ ላይ ለጨረታ የቀረበውን የገዛኸኝ ነብሮብን ምስል የባልቲሞር ወጣቶች አሸንፈዋል።
አቶ አንዳርጋቸው ቀደም ሲል በሌላ ከተማ በተሰናዳ ተመሣሳይ መድረክ በእስር ቤት ሳሉ የተወሰዱባቸውን የመጽሀፍ ረቂቅ ሶፍት ኮፒ ዶክተር አብይ አሕመድ እንደላኩላቸው፣ በየመን ሰንዓ ሲታገቱ የተወሰደውንም 4 ሺህ ዶላር እንደመለሱላቸው በማውሳት፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የተለዬ ክብርና አድናቆት እንዳላቸው መግለጻቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ቅናቄ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ኢየሩሳሌም ሆቴል የተሳካስብሰባ አድርጓል።
የፋኖ፣ የቄሮ እና የዘርማ ተወካዮችን ጨምሮ ከየክፍለ ከተማው የተውጣጡ በርካታ ወጣቶች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡትን የንቅናቄውን አመራሮች በልዩ ድምቀት መቀበል በሚቻልበት ሁኔታ እና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ሰፊ ውይይት መካሄዱ ታውቋል።

Monday, August 20, 2018

ኢሳት ዜና : ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከስልጣን ከተነሱ አሜሪካ የኢኮኖሚ አደጋ ያጋጥማታል አሉ


ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከስልጣን ከተነሱ አሜሪካ የኢኮኖሚ አደጋ ያጋጥማታል አሉ
 ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እርሳቸውን ከስልጣን ለማንሳት ሙከራ የሚደረግ ከሆነ የአገሪቱ ኢኮኖሚ አደጋ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። ፕሬዚዳንቱ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለሁለት ሴቶች ገንዘብ መክፈላቸውንም የቀድሞው ጠበቃቸውና ጉዳይ አስፈጻሚያቸው ሚካኤል ኮኸን ካጋለጡ በሁዋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ በጠበቃቸው አማካኝነት የከፈሉት ገንዘብ ከሁለቱ ሴቶች ጋር ከፈጸሙት ወሲብ ጋር የሚገናኝ ሲሆን፣ ይህ ይፋ እንዳይሆንባቸውም የአፍ ማዘጊያ ገንዘብ እንዲከፈል ማዘዛቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።
ከፍተኛ የህግ ፈተና የገጠማቸው ፕሬዚዳንቱ ፣ ከስልጣን እንዲወርዱ ግፊት እየመጣባቸው ሲሆን፣ እርሳቸው ግን ከስልጣን የሚወርዱ ከሆነ በአገሪቱ ላይ ከፍተና የኢኮኖሚ ቀውስ እንዲመከሰት በማስጠንቀቅ ስልጣናቸውን ለማቆየት እየታገሉ ነው።
ዋነኛ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው የሆኑት የዲሞክራቲክ ፓርቲክ ፓርቲ ፖለቲከኞች ከመጪው ህዳር ወር አጋማሽ ምርጫ ወዲህ ፣ ፕሬዚዳንቱን የመክሰስ ፍላጎት እንደሌላቸው እየተዘገበ ነው። ፕሬዚዳንት ትራምም ብቸኛ ተስፋቸው የፓርልማና የህግ መወሰኛ ምክር ቤቶችን ተቆጣጥረው የያዙት የረብሊካኖች ሲሆኑ፣ እነዚህን ሁለት የስልጣን ቦታዎች በዲሞክራቶች ላለመነጠቅ ከፍተኛ ቀስቀሳ እያደረጉ ነው።
ከምርጫው ማግስት ዲሞክራቶች በሁለቱም የምክር ቤት ወንበሮች አብላጫ ድምጽ የሚያገኙ ከሆነ፣ ትራምፕን ከስልጣን ለማንሳት ከፍተኛ እድል ይኖራል። ከፍተኛ የሪፐብሊካን ድጋፍ ያላቸው ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ማውረድ ቀላል እንደማይሆን ብዙዎች ይስማማሉ።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምርጫው ወቅት ከሩስያ ጋር በማበር ተፎካካሪያቸው ሄላሪ ክሊንተን እንዲሸነፉ አድርገዋል በሚል የተጀመረው ምርመራ እስካሁን አልተጠናቀቀም። በዚህ የምርመራ ውጤት ፕሬዚዳንቱ ጥፋተኛ ከሆኑ፣ የራሳቸው ፓርቲ አባላት ሳይቀሩ ድጋፋቸውን ሊነሱዋቸው የሚችሉበት አጋጣሚ ከፍተኛ ይሆናል ተብሎ ይገመታል።

wanted officials