other links

Sunday, September 13, 2015

አርቲስት ሰብለ ተፈራ በመኪና አደጋ ሕይወቷ አለፈ።ባለቤቷ ታስሮ ይገኛል









አርቲስት ሰብለ ተፈራ በበርካታ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ ተውናለች በተለይም በኤፍቢሲ ሲተላለፍ በነበረው <<ትናናሽ ፀሀዬች>> በተሰኘው የሬድዮ ድራማ የእማማ ጨቤ የተሰኙ ገፅ ባህሪ በመወከል ተጫውታለች።

ቅዳሜ ምሽት በኢቢሲ እየተላለፈ በሚገኘው ቤቶች ድራማ ላይም ትርፌ በሚለውን ገፀባህሪዋ በርካታ ተከታታዮችን አፍርታለች


መስከረም 1/2008 እንደደረሰን መረጃ ከሆነ ሳሪስ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአርቲስቷ ሂወት አልፏል።
ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ አደጋው ከተፈጸመ በኋላ በ እስር ላይ ይገኛል  :: ፖሊስም ስለአደጋው አፈጣጠር ምርመራ እያደገበት ይገኛል::  ነገ ሰኞ በመንበረ ጸባኦት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በሚፈጸመው የባለቤቱ የቀብር ሥነስርዓት ላይ ሞገስ   በፖሊስ ታስሮ እንደሚገኝ የጠቆሙት  ምንጮች ለፖሊስ አደጋው የተፈጸመ ሙዚቃ ለመቀየር ጎንበስ ሲል እንደሆነ ተናግሯል:: አርቲስት ሰብለ ተፈራ እና ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ ይህ የመኪና አደጋ ከመፈጸሙ ከቀናት በፊት በአቡዳቢ እና በዱባይ ለእረፍት (ቫኬሽን) ወጥተው መልካም ጊዜ ማሳለፋቸውን ባለቤቷ በፌስቡክ ገጹ ለጥፎ ነበር::

ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለአድናቂዎቿ መፅናናትን እንመኛለን።










No comments:

Post a Comment