other links

Sunday, March 18, 2018

በጎንደር በነዳጅ እጥረት ባጃጆች ችግር ውስጥ ወድቀዋል

 በስኬት እየተካሄደ ባለው የነዳጅ እቀባ አድማ የተነሳ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የነዳጅ እጥረት ተከስቷል:: በተለይ ቄሮ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ ፋኖ ከመተማ የሚመጡ የነዳጅ ቦቴዎችን ያስቆመ ሲሆን ይህም ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል::
መንግስት የነዳጅ እጥረት በሃገሪቱ እንዳልተከሰተ የነዳጅ ድርጅት ባለስልጣንን አቅርቦ በሚዲያው ሲያስነገር ቢቆይም አርብ ምሽት ለመንግስት ጋዜጠኞች ቃለምልልስ የሰጡት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ በተቃውሞው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት ምክንያት እንደሆነ ማመናቸው አይዘነጋም::
በዚህም መሰረት በጎንደር ትናንትና እና ዛሬ የሕዝብ ማመላለሻ የሆኑት ባጃጆች በየቦታው ተሰልፈው መቆማቸውን ከስፍራው በፎቶ ግራፍ ተደግፎ የደረሰን መረጃ ያሳያል:

No comments:

Post a Comment