other links

Friday, September 9, 2016

በቺካጎ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሕወሓት መንግስት የተገደሉ ወገኖቻቸውን በጸሎትና ሻማ ማብራት አሰቡ


በቺካጎ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሕወሓት መንግስት የተገደሉ ወገኖቻቸውን በጸሎትና ሻማ ማብራት አሰቡ






(ዘ-ሐበሻ) በኢሊኒዮስ ግዛት ቺካጎ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት በትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የተገደሉ ወገኖቻቸውን በአንድ ላይ ተሰባስበው በጸሎት እና በሻማ ማብራት ማሰባቸውን የዘ-ሐበሻ የቺካጎ ወኪል ጋዜጠኛ ዘላለም ገብሬ ዘገበ::

ዛሬ በቺካጎ ከተማ ፎስተር ቢች የተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን ለወገኖቻቸው የሻማ ማብራት እና የጸሎት ፕሮግራም ካደረጉ በኋላ እጃቸውን ወደ ላይ በማጣመር በሃገር ቤት እየተደረገ ያለው ትግል አጋርነታቸውን አሳይተዋል::

በሕወሓት መንግስት የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ቃል የገቡት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ለትግሉ የሚያስፈልገውን ነገር ለማድረግም ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል:: አዲሱን ዓመት በደስታ ሳይሆን ጥቁር በጥቁር በመልበስ በሃዘን እንደሚያሳልፉም አስታውቀዋል::



No comments:

Post a Comment