Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Showing posts with label #Ginbot 7. Show all posts
Showing posts with label #Ginbot 7. Show all posts

Saturday, July 18, 2015

ከደርግ የባሰ ግፍ በጎንደር

ወያኔ/ኢሕአዴግ “ብሶት ነው የወለደኝ” በሚል ደርግን በሚዋጋበት ጊዜ፣ መንገድ አሳልፎ ወደ መሃል አገር እንዲገባ ያደረገው የጎንደር ሕዝብ ነበር። በመላኩ ተፈራና በደርግ መከራን ያየና በመከራ የተማረረ ህዝብ፣ የተሻለ ሊመጣ ይችላል በሚል ነበር ወያኔን አሳልፎ ያስገባው።

ሆኖም ጎንደሬው ከደርግ የባሰ ግፍና መከራ እየደረሰበት ነው። ደርግ ያላደረገው በደል ህዝቡ እየተፈጸመበት ነው። ገበሬው ከምርታማ የጎንደር መሬት በኃይል እየተፈናቀለ ፣ ለአገዛዙ ቅርበት ላላቸው ኢንቨርስትሮች መሬቱ እየሰጠበት ነው። እሰ ሰሊጥ የመሳሰሉት የሚያበቅለው ለምለሙ መሬት በኢንቨርስተሮች ሕግ ወጥና ጸረ-ሕዝብ በሆነ መንገድ እየተወረረ ነው። ይሄን አይነት ዜጎችን ማፈናቀል ደርግ እንኳን ያልፈጸመው ግፍ ነው።
በምእራብ ወያኔ ገበሬዎችን ቀምቶ የጎንደርን መሬት ለሱዳን አሳልፎ እየሰጠ ነው። ይሄንን በደርግ ጊዜ ያልታየ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥም መቆም ሳይሆን አገርን መሸጥ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ሕዝቡ ለመብቱ፣ ለክብሩ፣ ለነጻነቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ እየተደገደል፣ እየታሰረ፣ ክፍተኛ እንግክትና መከራ እየደረሰበት ነው። በኢትዮጵያ በሰለጠነ መልኩ በሰላም ለዉጥ እንዲመጣ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጋዮች ብዙዎቹ ሲሰደዱ፣ ብዙዎቹ ወህኒ ወርደዋል። በአንድነት ፓርቲ ሥር በጎንደር ክፍል ሃግር ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ጀግና ወገኖቻችን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።



1. ኣንጋው ተገኝ (ሰሜን ጎንደር)
2. አባይ ዘዉዱ (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
3. እንግዳው ዋኘው (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
4. በላይነህ ሲሳይ (መተማ ጎንደር
5. አለባቸው ማሞ (መተማ ጎንደር)
6. አለበል ዘለቃ ሃይማኖት አየና ( ውሮታው፣ ደቡብ ጎንደር)
7. ጸጋዬ ገበይየሁ (አርማጭሆ)
8. መምህርት ግዛው ( ሰሜን ጎንደር)
9. አውቀ ብርሃኑ (ጎንደር)
10. ማሩ አሻግሬ ( የአርማጭሆ ተወላጅ፣ የዞኑ የአንድነት አመራር – ቀይ የለበሰው))
11. አለላቸው አታለለኝ ( የሰሜን ጎንደር አንድነት ሰብሳቢ)
12. አስቴር ስዩም ( በጎንደር የምእራብ አርማጮሆ የአንድነት አመራር)

Monday, August 4, 2014

የህወሃት ሽብር መቆም አለበት!

የህወሃት ሽብር መቆም አለበት!


ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለ አሸባሪ ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ መንግስት በመተቸታቸው በግልጽ በመጻፋቸውና በአደባባይ በመናገራቸው ከዚህም አልፎ በጥርጣሬ በተለይም በብሄረሰብ ማንነታቸው እያሳደደ የሚያፍን የሚያሰቃይና የሚገል የሽብር ተቋም ካለ ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ መሬት ላይ ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የተቃውሞ ሃይል በተግባርም ሆነ በአስተሳሰብ ከወያኔ ውጪ አንዳች ሃይል የለም።
አፋኙ የወያኔ ስርአት በተለየም የህዝቡን ሀብትና ንብረት እየዘረፉ የሚቀማጠሉት የህወሃት መሪዎችና ሎሌዎቻቸው የተቃውሞ ድምጽ በሰሙ ቁጥር እንደሚሸበሩና እንቅልፍ አጥተው እንደሚያድሩ ይታወቃል። አፍነውና ዘርፈው ገለው የሚገዙት ህዝብ ግፍ በዛብኝ ብሎ በተናገረ ቁጥር የሚሸበሩት እነሱ ብቻ እንጂ ህዝቡ አይደለም።
በኢትዮጵያ ምድር ያለው አሸባሪ ወያኔ ብቻ መሆኑን ሺ ምሳሌዎችን ጠቅሶ ማስረዳት ይቻላል። ሶስት አመት ሙሉ የሰላም እጃቸውን እየዘረጉ ከልመና ባልተለየ ሁኔታ መብታቸውን የጠየቁና ድምጻችን ይሰማ ያሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማንንም ዜጋ አላሸበሩም። የተገላቢጦሽ እነሱ አሸባሪ ተብለው የግፍ ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል። ጋዜጠኞችና ጦማሪዎቹ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ስለጠየቁ በአደባባይ ስለጻፉ ግፍ ይፈጸምባቸዋል። እነሱ ያሸበሩት ሀገርና ህዝብ የለም። ከመንገድ ላይ ጎትተው እንደ እባብ ቀጥቅጠውና ፈነካክተው በማግስቱ ፍርድ ቤት ያቀረቧት ወየንሸት ሞላ የተባለች ባለ ተስፋ ወጣት የወያኔ አረመኔዎች በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የሚሰሩትን ጭፍጨፋ እግር ጥሏት ከማየትና ከመታዘብ ውጪ ያሸበረችው ሰው፣ ሀገር የለም። በየወህኒ ቤቱ እና አፈና ጣቢያው ታስረው የሚቀጠቀጡት የኦሮሞ ልጆች ለጥያቄያቸው መልስ ሲጠብቁ ከመጨፍጨፍ ያለፈ የፈጸሙት እብሪት የለም። በየክልሉ ቀና ብለህ ባለስልጣን ተናገርክ፣ ጥያቄ ጠየቅክ፣ ባለስልጣን ደፈርክ፣ ተሰብስበህ አየንህ ወዘተ እየተባለ የሚገረፈው እንደ እንስሳ እየተገደለ የሚጣለው ገበሬ የሰራው ወንጀል የለም። አሸባሪም አይደለም! በየቦታው ቦንብ እየቀበረ አፈንድቶ ንጹሃንን ገድሎ ሊያፈነዱ ሲሉ ፈንድቶባቸው ራሳቸውን ገደሉ ብሎ በአደባባይ የሚሳለቀው አሸባሪው ህወሃት እንጂ ንጹሃኑ አይደለም።
የኛ መሪ አንዳርጋቸው ከልጅነት እድሜው ጀምሮ ራሱን ለህዝብ ነጻነት የሰጠ አርበኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም። በተመሳሳይ ውንብድና ከጎረቤት ሀገር ድረስ በአለም አቀፍ የወረበሎች ውንብድና መንገድ ወያኔ እያፈነ የገደላቸው አሮሞዎችና፣ ሱማሌዎች፣ አኙዋኮች፣ አማሮችና ሌሎችም ነጻነት ከመፈለግ ውጪ ያሸበሩት ህዝብና ሀገር የለም።
በኢትዮጵያ ምድር የነጻነት ድምጽና ኮሽታ በሰማ ቁጥር የሚሸበረው ህወሃትና በለሟሎች ብቻ ናቸው። ይህ የነጻነት ድምጽ ደግሞ እየጎላ መሄዱ የማይቀር ነውና ወያኔ ሰፈር ሽብር ይሆናል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወጣት፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ገበሬ እና በየቦታው ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ! አሸባሪህ ወያኔና ወያኔ ብቻ መሆኑን አውቀህ በገዛ ሀገርህ ላይ ነጻነት በተመኘህና በጠየቅህ ጊዜ ሁሉ ለሽብር ጥቃቱ ኢላማ ያደረጉህን ወያኔ ተባብረን ከላያችን ለማውረድ ተነስ! በያለህበት እምቢ በል! ለወያኔ የሚጠቅም የመሰለህን ነገር ሁሉ አታድርግ! አትተባበር! ሸቀጣቸውን አትግዛ! ወያኔዎችን ከማህበራዊ ሂወትህ አግል! የቻልክ ሁሉ ደግሞ የነጻነት አርበኞችን ዛሬ ነገ ሳትል አሁን ተቀላቀል!!! ነጻነታችን ያለው በእጃችን ላይ መሆኑን አትዘንጋ። ግንቦት 7 ሁልጊዜም ከመቼውም ጠንክሮ ከጎንህ ነው።
የወያኔን ሽብር በተባበረ ሃይል እናቁመው!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

wanted officials