Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Showing posts with label ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AEPO‬ ‪#‎UDJ‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Electionboard‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎Ginbot7‬. Show all posts
Showing posts with label ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AEPO‬ ‪#‎UDJ‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Electionboard‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎Ginbot7‬. Show all posts

Thursday, January 7, 2016

በኦሮሚያ ክልል ግድያው እና እስራቱ ቀጥሏል፥ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች እንዲተባበሩም ጥሪ ቀርቧል

በኦሮሚያ ክልል ግድያው እና እስራቱ ቀጥሏል፥ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች እንዲተባበሩም ጥሪ ቀርቧል


ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2008) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት በአዲስ አበባ ዙሪያ ሊተገበር የተዘጋጀውን ማስተር ፕላን በመቃወም ሰላማዊ ተቃውሞ ያሰሙ ዜጎችን መግደሉን፣ መደብደቡንና፣ ማዋከቡን አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። በኦሮሚያ ስላለው ስለወቅታዊ ሁኔታ አጠቃላይ ሁኔታ ዝርዝር እንዲሰጡን የተጠየቁት ዶ/ር መረራ፣ በመንግስት ሃይሎች ዜጎችን የማሰሩ ሄደት አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ተናግረዋል። ባለፈው እሁድ በሃገረማሪያም ይኖር የነበረ አንድ የኦፌኮ አመራርና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመንግስት ሃይሎች ተይዘው እንደታሰሩ ዶ/ር መረራ ለኢሳት ገልጸዋል። የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የተቃውሞው አስተባባሪዎች ናቸው ያላቸውን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ቱፋ እና የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ የነበሩት አቶ ጉርሜሳ አየነውን ማሰሩን መዘገባችን ይታወሳል። በቅርቡም የአቶ በቀለ ነጋአ በቁም እስር እንዲሆኑ እንደተደረገ ታውቋል። አቶ በቀለ ነጋአ በቁም እስር ላይ እያሉ ለሚዲያ ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጡና ወደ ቢሮ ወይም ወደ ፈለጉበት አካባቢ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ እገዳ እንደተጣለባቸው ለማወቅ ተችሏል። እስካሁን ድረስ ከ4ሺ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በማስተር ፕላን ሰበብ እንደታሰሩ ሲታወቅ፣ አሁንም በመላው ኦሮሚያ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩትን ሁሉ እየታደኑ መታሰራቸው ተገልጿል። የታሰሩት የአመራር አባላትም አብዛኞቹ እስካሁን ድረስ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ በጸጥታ ሃይሎች ተከልክለዋል። የኦሮሞ ኮንግሬስ አባላት ከመታሰራቸው ውጪ ምንም አይነት መረጃ ከመንግስትም ሆነ ከሌሎች አካላት ማግኘት እንዳልቻሉ ዶ/ር መረራ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። ዶ/ር መረራ “የኢትዮጵያ መንግስት የፖሊስ ወይም የህግ አካላት ያልሆኑ ከህግ ውጭ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች አሰማርቶ ባለበት ሁኔታ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ አቶ በቀለ ነጋአን ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት ሲል መጫን አይፈልግም” ብለዋል። የደህንነት አካላት በአቶ በቀለ ነጋአ ቤተሰብ ላይ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ማስፈራርያ እንደሰጧቸው መዘገባችን ይታወሳል። አቶ በቀለ ነገአ በራሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ ወስነው መንቀሳቀስ ከፈለጉ መብታቸው እንደሆነም የደህንነት ሰዎች እንደነገሯቸው ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጩት ጹሁፍ አስታውቀው ነበር። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አባላት ቢታሰሩም ፓርቲው ስራውን አጠናክሮ መስራቱን እንደቀጠለ ለኢሳት የገለጹት ዶር መረራ፣ “መንግስት የተወሰኑ አባሎቻችንን ቢያስርብንም፣ አሁን በዋናነት መልሶ የማደራጀት ስራ እየሰራን ነው” ብለዋል። በአዲስ አበባ እስካሁን ድረስ ለምን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳላደረጉ ለተጠየቁት ጥያቄ ዶር መረራ ሲመለሱ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሲፈልግ ህግን፣ ካልፈለገ የራሱን ህግ የሚጠቀም በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎናል ብለዋል። በመሆኑም ኢህአዴግ “አታደርጉም የሚል ውሳኔ ሲሰጥ ህገመንግስትን እየጣሰ፣ እኛ ግን ህግ ያልሆነውን የራሱን ህግ እንድናከብር የሚፈልግ ፓርቲ ነው” ብለዋል። ሆኖም ዶ/ር መረራ ኢህአዴግ ፈቀደ አልፈቀደ ህዝቡ በየክፍለሃገሩ ለሰላማዊ ሰልፍ እየወጣ እንደሆነ አብራርተዋል። ትግሉ አዲስ አበባ ሲደርስ ሰላማዊ ህዝቡ ሰልፍ መውጣቱ አይቀሬ መሆኑን ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል። ዶር መረራ የኢትዮጵያ መንግስት የገባበት መንገድና ግትር አቋሙ እጅግ አደገኛ፣ ማንንም እንደማይጠቅም መሆኑን አስረድተው ወደ እርቅና ሰላም የሚያመጣ መንገድ መከተል እንደሚያስፈልግ መክረዋል። በመቀጠልም የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ በጋራ እንዲታገል ዶ/ር መረራ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ተሰባስበው ህዝቡን በመምራት ለሁላችን የምትሆን ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያን ለመመስረት የሚያስችል አቅጣጫ መቀየስ እንዳለባቸው ጥሪ አስተላልፈዋል። በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተባብሶ መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ። በትናንትናው ዕለት በአዳማ ላይ አንድ ሰው ተገሎ መገኘቱንና፣ ሰሜን ሸዋ አቦቴ አካባቢ ሌላ ሰው ተሰቅሎ እንደተገኘ ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች ያለመክታሉ። በማስተር ፕላን ሰበብ የተነሳው ተቃውሞ በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች እንደገና አገርሽቷል። በምዕራብ ሸዋ በሃረር መስመር ጨለንቆ እና ቆቦ ላይ በትናንትናው ዕለት የታሰሩት ይፈቱ የሚል ተቃውሞ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል።

Saturday, July 18, 2015

ከደርግ የባሰ ግፍ በጎንደር

ወያኔ/ኢሕአዴግ “ብሶት ነው የወለደኝ” በሚል ደርግን በሚዋጋበት ጊዜ፣ መንገድ አሳልፎ ወደ መሃል አገር እንዲገባ ያደረገው የጎንደር ሕዝብ ነበር። በመላኩ ተፈራና በደርግ መከራን ያየና በመከራ የተማረረ ህዝብ፣ የተሻለ ሊመጣ ይችላል በሚል ነበር ወያኔን አሳልፎ ያስገባው።

ሆኖም ጎንደሬው ከደርግ የባሰ ግፍና መከራ እየደረሰበት ነው። ደርግ ያላደረገው በደል ህዝቡ እየተፈጸመበት ነው። ገበሬው ከምርታማ የጎንደር መሬት በኃይል እየተፈናቀለ ፣ ለአገዛዙ ቅርበት ላላቸው ኢንቨርስትሮች መሬቱ እየሰጠበት ነው። እሰ ሰሊጥ የመሳሰሉት የሚያበቅለው ለምለሙ መሬት በኢንቨርስተሮች ሕግ ወጥና ጸረ-ሕዝብ በሆነ መንገድ እየተወረረ ነው። ይሄን አይነት ዜጎችን ማፈናቀል ደርግ እንኳን ያልፈጸመው ግፍ ነው።
በምእራብ ወያኔ ገበሬዎችን ቀምቶ የጎንደርን መሬት ለሱዳን አሳልፎ እየሰጠ ነው። ይሄንን በደርግ ጊዜ ያልታየ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥም መቆም ሳይሆን አገርን መሸጥ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ሕዝቡ ለመብቱ፣ ለክብሩ፣ ለነጻነቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ እየተደገደል፣ እየታሰረ፣ ክፍተኛ እንግክትና መከራ እየደረሰበት ነው። በኢትዮጵያ በሰለጠነ መልኩ በሰላም ለዉጥ እንዲመጣ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጋዮች ብዙዎቹ ሲሰደዱ፣ ብዙዎቹ ወህኒ ወርደዋል። በአንድነት ፓርቲ ሥር በጎንደር ክፍል ሃግር ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ጀግና ወገኖቻችን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።



1. ኣንጋው ተገኝ (ሰሜን ጎንደር)
2. አባይ ዘዉዱ (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
3. እንግዳው ዋኘው (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
4. በላይነህ ሲሳይ (መተማ ጎንደር
5. አለባቸው ማሞ (መተማ ጎንደር)
6. አለበል ዘለቃ ሃይማኖት አየና ( ውሮታው፣ ደቡብ ጎንደር)
7. ጸጋዬ ገበይየሁ (አርማጭሆ)
8. መምህርት ግዛው ( ሰሜን ጎንደር)
9. አውቀ ብርሃኑ (ጎንደር)
10. ማሩ አሻግሬ ( የአርማጭሆ ተወላጅ፣ የዞኑ የአንድነት አመራር – ቀይ የለበሰው))
11. አለላቸው አታለለኝ ( የሰሜን ጎንደር አንድነት ሰብሳቢ)
12. አስቴር ስዩም ( በጎንደር የምእራብ አርማጮሆ የአንድነት አመራር)

Wednesday, August 6, 2014

እንዋሃዳለን ያሉ ፓርቲዎች እና ምርጫ ቦርድ እንዲሁም የውስጥ ሃይሎች እየተጎሻሸሙ ነው።


"የማይበርድ የመንገድ ላይ አመጽ እጠራለሁ ።" መኢአድ - ውህደቱ አሁንም ተራዝሟል።
መኢአድ በምርጫ ቦርድ ላይ ጠንከር ያለ የተቃውሞ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ህዝባዊ ጥሪ ሊሰጥ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ከፍተኛ ድርጅታዊ መዋቅር እንዳለው የሚታወቀው መኢአድ የጎዳና ላይ አመጽ እንደሚጠራ ምርጫ ቦርድን እና የወያኔ መንግስትን አስጠንቅቋል።በቅርቡ እንዋሃዳለን ያሉት አንድነት እና መኢአድ በውስጣቸው ያለው የአባላት መጎሳሰም የገንዘብ ችግር እና ውህደታቸውን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ውስጣዊ ወገኖች እንደተጠበቁ ሆነው ክምርጫ ቦርድ ጋር አዲስ አተካራ መግጠማቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
በመኢአድ እና በአንድነት በኩል አሉ የሚባለው እና በውህደቱ ላይ ተቃውሞ ያላቸው ሃይሎች ወያኔ በአንድነት በኩል አድርጎ መኢአድን ሊውጠው ነው በሚል መነሾ ውህደቱን የሚቃወሙ ሲሆን እንደ ኢንጂነር ግዛቸው እና ዘረቀ ረዲ የመሳሰሉት የወያኔ ደሞዝተኞች የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ ለማልፈስፈስ ከወያኔ ጋር ይሰራሉ በማለት ውህደቱ አንፈልግም የሚሉ ወገኖች ይናገራሉ።
የማይበርድ የጎዳና አመጽ እንደሚጠራ የሚናገረው መኢአድ ምርጫ ቦርድን ውህደቱ ለማደናቀፍ ደፋ ቀና ይላል ሲል ይወነጅላል። ባለፈው ቀናት መግለጫ የሰጡት እና እንዋሃዳለን ያሉት መኢአድ እና አንድነት በገንዘብ ችግር ምክንያት ውህደቱ እንደዘገየ መናገራቸው የሚታወስ ነው።
ምርጫ ቦርድ እና ወያኔ ውህደቱን ለማደናቀፍ የሚያደርጉትን ሴራ ክላቆሙ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ላይ በመሆን እንዲንቀሳቀስና የምርጫ ቦርድንም ሆነ የኢትዮጵያን መንግሥት በሰላማዊ መንገድ እንዲቃወምና ለትግልም እንዲነሳ ሰላማዊ ሰልፍን፣ የመንገድ ላይ አመፅን እና የመሳሰሉትን እርምጃዎች ሁሉ እንዲወስድ እናስተባብራለን ያለው መኢአድ በነገው እለት የተቃውሞ መግለጫ እና የአመጻ ሕዝባዊ ጥሪ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል

wanted officials