Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, October 30, 2019

የባልደራስ፣ የአብን አባላትና የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባለቤት ተፈቱ

የተፈቱት የባልደራስ አባላትImage copyrightFACEBOOK
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት፣ የአብን ፓርቲ አባላት እንዲሁም የብርጋዴል ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባለቤት በዛሬው ዕለት ተፈተዋል
ግለሰቦቹ የተታሰሩት ከሰኔ 15 ግድያ ጋር በተያየያዘ በሽብር ተጠርጥረው ሲሆን አቃቤ ሕግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ቢሰጠውም ክስ ሳይመሰርት መለቀቃቸውን በዛሬው ዕለት ከእስር የተፈቱት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለቢቢሲ በስልክ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) አባላት ጠበቃ የሆኑት አቶ ሔኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ ያሳለፉት ደንበኞቻቸው የተለቀቁት በመታወቂያ ዋስ መሆኑን ተናግረው ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሰረት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታታቸውን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ህዝብ ግንኙነት ከሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል በተጨማሪ የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት አባላት የሆኑት አቶ መርከቡ ኃይሌ፣ ኤሊያስ ገብሩ እንዲሁም አዳም ጂራ መፈታታቸውን አቶ ሔኖክ ገልጸዋል።
በተለምዶ ሶስተኛ የሚባለው አዲስ አበባ ፓሊስ ጣቢያ ለወራት ታስረው የነበሩት አቶ ስንታየሁ እንደሚፈቱ የሰሙት ዛሬ ከሰዓት እንደነበር ተናግረዋል።
"ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ወስዶ ቢመረመርም ያገኘብን መረጃ ስለሌለ በነጻ ተለቀናል" ያሉት አቶ ስንታየሁ " እኛ ሳንሆን እውነት ነው ያሸነፈው" ብለዋል።
አቶ ስንታየሁ አክለውም መጀመሪያም "የህሊና እስረኞች ነበርን በነጻ ተለቅቀናል፤ ዛሬ ተፈታን ብለን ነገ ከትግል የምንሸሽበት መንገድ የለም አሸናፊ ሆነን ነው የወጣነው" ብለዋል።
የእስር ቆይታቸው ፈታኝ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ስንታየሁ በጨለማ ቤት ውስጥ ከሁለት ወር በላይ ማሳለፋቸውን ለቢቢሲ አስረድታዋል።

"መንፈሳችንን ለመስበር ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፤ የሕዝብ ጥያቄ በመያዛችን ከትግል የምናቆምበት ነገር የለም" ሲሉ ከተፈቱ በኋላ ተናግረዋል።
አክለውም "እስር ቤት ውስጥ ሆነን አልተጎዳንም ፤ሕዝቡ እየመጣ እያጽናን ነው የነበረው። በመታሰር ውስጥም አሸንፈናል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ቀጣይ ብዙ ትግል አለ የሚሉት አቶ ስንታየሁ "እኔ ብፈታም ጥያቄያችን አልተፈታም" በማለት የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት የያዘው ጥያቄ መፈታት እንዳለበትም አስረድተዋል።
በሌላ በኩል አስራ አራት የአብን አመራሮችና ደጋፊዎች በዛሬው እለት መፈታታቸውን ጠበቃቸው አቶ አበረ መንግሥቴ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ክስ ካልቀረበ ይፈቱ በሚል ውሳኔ ካገኙት ውስጥ አምስት ሰዎች ለጊዜው እንዳልተፈረመላቸው ጠቅሰው ክስ ይመስረት አይመስረት የሚለው ጉዳይም ግልፅ አይደለም ብለዋል።
የፓርቲው አባላት ከመታወቂያ ጀምሮ፣ አምስት ሺ፣ ሰባት ሺና አስር ሺ ብር ዋስ መፈታታቸውን ጠበቃቸው ጨምረው አስረድተዋል።
የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ቀርበው የአስራ አምስት ቀን የክስ መመስረቻ የተጠየቀባቸው ሲሆን በመጪው አርብም ይጠናቀቃል።
እስከ አርብ ባለው ጊዜም ውስጥ ክስ ካልተመሰረተ የዋስትና መብታቸውንም ማቅረብ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል።
የዋስ መብታቸው ተጠብቆ በዛ አግባብ ነው የተፈቱት ስለ አፈታታቸው ሁኔታም እስካሁን ባለው እንደማይታወቅና ክስ የሚያስመሰርት ሁኔታ ይኑር አይኑር እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች በመጪው ቀናት እንደሚታወቁም ተናግረዋል።
አቶ ክርስቲያንን ጨምሮ ዘጠኝ አባላት እንዳልተፈቱም አቶ አበረ አስረድተዋል።
የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ባለቤት ወ/ሮ ደስታ አሰፋ በዛሬው ዕለት መፈታታቸውንም ጠበቃቸው ነግረውናል።

Wednesday, October 2, 2019

ፌስቡክ 'የላይክ' ቁጥርን ማሳየት ሊያቆም ነው


የፌስቡክ 'ላይክ' ምልክት
Image copyrightGETTY IMAGES
ፌስቡክ ኢንስታግራም ላይ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በእያንዳንዱ የፌስ ቡክ የተጠቃሚዎች መልዕክት ስር የተሰጡ የመውደድ (ላይክ) ቁጥሮችን አለማሳየት ሙከራ እርምጃውን አውስትራሊያ ውስጥ መጀመሩን አስታወቀ።
ከዛሬ አርብ ጀምሮ አውስትራሊያ ውስጥ ያሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በሌሎች መልዕክት ላይ የተሰጡ የላይክ እንዲሁም የሌሎች ምላሽ ቁጥሮችን መመልከት አይችሉም።
አወዛጋቢ የሆነው ይህ ውሳኔ የፌስቡክ ተዛማጅ ማኅበራዊ መድረክ በሆነው ኢንስታግራም ላይ ከሐምሌ ወር ጀምሮ በበርካታ ሃገራት ውስጥ ተግባረዊ ተደርጓል።
ፌስቡክ ለአንድ መልዕክት የሚሰጡ የላይክ ቁጥሮችን ከባለቤቶቹ ውጪ ሌሎች እንዳያዩ የሚያደርገውን እርምጃውን ለመውሰድ የወሰነው በተጠቃሚዎች ላይ የሚደርሰውን ማኅበራዊ ጫና ለመቀነስ በማሰብ ነው ተብሏል።

ኩባንያው እንዳለው የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በራሳቸው መልዕክቶች ስር የሚሰጡ 'የመውደድ' ምላሾችን መመልከት ግን ይችላሉ።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሚያ ጋርሊክ ለአውስትራሊያ አሶሺየትድ ፕሬስ እንዳሉት "የቁጥርን ነገር ከጉዳዩ ስናወጣ፤ ተጣቃሚው ዋና ትኩረትን በተሰጡ የላይክና የሌሎች ምላሾች ብዛት ላይ ሳይሆን በሚደረጉ ምልልሶችና በቀረቡ መረጃዎች ጥራት ላይ ብቻ ያደርጋል" ብለዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም ድርጅታቸው ይህንን ለውጥ ከማድረጉ በፊት የሥነ አእምሮ ባለሙያዎችንና ማንጓጠጥ እንዲሁም ማስፈራራትን የሚከላከሉ ቡድኖችን ማማከሩን ገልጸዋል።
በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው አንዳንድ ሰዎች ግን በአንድ መልዕክት ላይ የሚታይ የመውደድ አሃዝ ለሚያገኙት ገቢ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ እርምጃውንተቃውመውታል።

wanted officials