Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 30, 2018

Ethiopia passes amnesty law


ESAT News (June 28, 2018)
The Ethiopian Parliament today passed an amnesty law to “pardon” those individuals that the government formerly accused, charged and/or sentenced after alleged crimes such as “attempt to overthrow the government, outrage against the constitution, treason and other political crimes.”
The long awaited law comes after severe criticism against the previous administration, controlled and manipulated by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), that criminalizes dissent and use such laws as the Anti-terrorism Proclamation to target opposition political parties and critical journalists.
Thousands of political activists, members and supporters of opposition parties, critical journalists and citizens with dissenting views have been jailed, tortured and deliberately sentenced to prison terms on trumped up terrorism and other charges by the regime’s kangaroo courts.
Many of those have been released in the last few months after a nationwide protest against the TPLF and international uproar and condemnation of human rights abuses by a security and intelligence controlled by an ethnic party.
The law stipulates that a board would be formed comprised of relevant ministries and government departments to implement the provisions, accept and process appeals for amnesty and present recommendations to the Prime Minister for final decision.
Prime Minister Abiy Ahmed, appointed in April, has oversaw the release of thousands of political prisoners, including leading members of opposition groups and journalists. He is also credited for proposing economic and political reforms in a nation that was ruled with iron fist by ethnic oligarchs.
by Engidu Woldie

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተፈናቀለባት ሃገር ናት ተባለ




(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ሆናለች ሲል የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ገለጸ።
ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር ህዝብ ተስፋ የጣለበት አጋጣሚ እንዳይባክን በሚል ርዕስ ሰመጉ ባወጣው መግለጫ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የዚህ ክልል ተወላጆች አይደላችሁም በሚል ከሚኖሩባቸው አከባቢዎች እየተፈናቀሉ ናቸው ብሏል።
እነዚህ በሐገር ውስጥ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉም ሲል ሰመጉ በመግለጫው አስታውቋል።
አሁን የሚታየው መልካም ጅምር እንዳይቀለበስ ሁሉም የሚመለከተው አካል ሃላፊነቱን እንዲወጣ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ጥሪ አድርጓል።
የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ሰመጉ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መልካም ጅምሮች አድናቆቱን በመግለጽ ይህን ተስፋ የሚቀለብሱ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው በማለት ስጋቱን የገለጸበትን መግለጫ ነው ዛሬ ያወጣው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ወዲህ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች የሰቆቃው ዘመን ወደ ማብቂያ ለመቃረቡ አመላካቾች እንደሆኑ ሰመጉ በጽኑ ያምናል ይላል መግለጫው።
በውጭ ሀገራት ለሚገኙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች ጥሪ ማቅረባቸው ለብሄራዊ ዕርቅ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍትም ነው ብሏል።
ይሁንና ይህን ተስፋ ሰጪ ጅምር ሊያደበዝዙ ወይም ሊቀለብሱ የሚችሉ ሁኔታዎች መታየታቸው ድርጅታችንን በእጁጉ ያሳስበዋል ሲል የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ስጋቱን ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ኑሮአቸውን መስርተው ለዓመታት  ከኖሩበት ቀዬ የዚህ ክልል ተወላጆች አይደላችሁም በሚል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩባቸው አከባቢዎች መፈናቀላቸው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ሰመጉ አያይዞም በእነዚህ ተፈናቃዮች በጊዜያዊነት በተጠለሉባቸው አከባቢዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ተከስቷል ሲል የአደጋውን አሳሳቢነት በመግለጽ ጠቅሷል።
የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች መስሪያ ቤት ኦቻ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት በጉጂና ጌዲኦ መሀል በተነሳው ግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 1ሚሊየን መድረሱን ገልጿል።
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መሀል በተነሳው ግጭትም 1ነጥብ 2 ሚሊየን የሚሆን ህዝብ መፈናቀሉን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተመሳሳይ ግጭቶች የተፈናቀሉትን ሲጨምር ከ2ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያዊ በሀገር ውስጥ መፈናቀሉን ለመረዳት ተችሏል።
የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ዛሬ ባወጣው መግለጫው በሀገር ውስጥ መፈናቀል ከፍተኛ ቁጥር በመያዝ ከሚጠቀሱ የዓለም ሀገራት ኢትዮጵያ አንዱ መሆኗን ገልጿል።
ድርጅቱ በቤንሻንጉል ጉምዝ፡ በጉጂና ጌዲኦ በቄሌም ወለጋ የተፈናቀሉትን ኢትዮጵያውያን በተመለከተ ከቦታዎቹ ያሰባብሰባቸውን በመጥቀስ የመፈናቀሉ አደጋ አዝማሚያው ያሳስባል ብሏል።
በመሆኑም መንግስት አፋጣኝ እርምጃ በመወሰድ የዜጎችን ስቃይና መከራ እንዲያበቃ ያደርግ ዘንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ሰመጉ ጥሪ አድርጓል።
የህግ ተቋማት ገለልተኛ ሆነው በአዲስ መልክ እንዲደራጁ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ቀሪ ሰዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ አፋኝ አዋጆችና ህጎች ማሻሻያ እንዲደረግላቸው፣ ነጻና ገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን እንዲፈጠሩና ያሉትም ከአፈና እንዲላቀቁ፣ በሁለቱም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል እንዲጣሩና ይህን የፈጸሙ የመንግስት አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ በመግለጫው ጠይቋል።

አስቴር በዳኔ ከቤተ-መንግስት ስልጠና ለምን ተባረረች? ክንፉ አሰፋ

ወዲ ብርሃነ “ኮሽ ባለ ቁጥር (በህወሃት) ማሳበብ አስቂኝ ነው” ብሎናል። ልክ እንደ ቦስተን ማራቶን፤ ንጹሃን ዜጎች ላይ ቦንብ ሲወረወር፤ ሌላው ይጨነቃል፤ ኮካ ደግሞ ይስቃል። የቦንብ ፍንዳታ በተሰማ ቁጥር ሕዝብ የነሱን የፈስ ቡክ ገጽ ለመዳሰስ የሚሯሯጠው የተለመደ ፍንጭ ስለሚሰጠው ብቻ መሆኑን እንኳ ገና አልባነነም። የመረጃ ፍንጭ መስጠታቸው ባልከፋ፤ ግና ጉዳዩን ማን መመርመር እንዳለበት ኮካዎች የሚወስኑበት ዘመን፤ እንደ ፈርኦን አሽከሮች የባህር ውሃ ከበላው ወራት አለፉ።
ዘንግተነው ካልሆነ በስተቀር፤ በሟቹ ግዜም፤ “ነገ መርካቶ አካባቢ በአስር ሰዓት ቦንብ ይፈነዳል” እያሉ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ይነግሩን ነበር። የአበሻ ዘር በወቅቱ ያስጨንቀው የነበረው ታዲያ የቦንቡ መፈንዳት ሳይሆን፤ ሊታሰሩ እቅድ የተያዘላቸው “አሸባሪዎች” ጉዳይ ነበር። ፍቅር እንደ ወንጌል እየተሰበከ ባለበት በዛሬ ዘመን ደግሞ የጅቦቹን የልብ ትርታ የሚለካልን ቴርሞ ሜትር የኮካዎቹ ገጽ ሆኗል።
“የቀን ጅቦች” የተሰኘው ነጠላ ስም እንደ ሰደድ እሳት ተለቆ፤ ጅቦቹም ያሻቸውን ሲያደርጉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም ፍቅርን ነው የሚሰብከው። እሳት ጫሪን ከመቅጣት ይልቅ፤ እነሱ የሚጭሩትን እሳት እየዞረ ማጥፋት የለት ስራው ስላደረገ። ይህንን በማድረግ ትእግስቱን ጫፍ ቢያመላክታቸውም እነሱ ግን በንቀት ያዩት ይመስላል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አደረጉ የሚለውን መልካም ዜና ገና ሰምተን ሳንጨርስ የማግለል ፖለቲካ ጉዳይ ተከተለ። ተስፋ አስቆራጭ ዜና!
የአስቴር በዳኔን ከቤተ-መንግስት መባረር ስንሰማ፤ የዚያ ቫይረስ ተሸካሚዎች በኪነጥበብ ስም መስረጋቸውን ያመላክተናል። ክስተቱ ያሳዝናል። ድርጊቱ በየትኛውም መስፈርት ቢለካ፤… የተፈለገው ምክንያት ቢደረደር፤ ስህተት ያለመሆኑን አያስረግጥም።
ማቹ ጠቅላይ ሚንስትር ኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ባናገሩበት ግዜ “ማን ይጠራ፧ ማን ይቅር፧ ማን ምን ይጠይቅ?” ሸፍጥ ሰዓሊ ስዩም አያሌው “ሰራዊትና ሰራዊቶቹ” በሚል ርዕስ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ አስነብቦን ነበር። አቶ መለስ ከሰራዊት ፍቅሬ የወርቅ ብዕር ተሸልመው ነበር። ጋዜጠኞችን በማሰራቸው እና በፕሬስ አፈናቸው። አሁንም እነዚሁ ሰዎች ቆባቸውን ቀይረው አዛዥ ሆነውልናል።
“ግዜው የመደመር ነው፣ ግዜው የምህረት ነው፣ ግዘው የይቅርታ ነው፣ ፍቅር ያሸንፋል።”.. ካልን አንዱን የበኩር ሌላውን ደግሞ የእንጀራ ልጅ የምናደርግበት ምክንያት አይኖርም። “አስቴር በዳኔ ለብቻዋ እውነትን የደፈረች ልጅ ተመርጣ ለምን ከአዳራሹ እንድትወጣ ተደረገ?” የሚለው ጥያቄ ለብዙዎቻችን እንቆቅልሽ ሆኖብናል። ከጅቦቹ ጋር እየተሞዳሞዱ የማስታወቂያ ስራውን ጭምር ጠቅልለው የያዙት ግልገል ጅቦች እያሉ፤ ይህች ልጅ ለምን? “ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” ይል የነበረው፤ ኦነግን ሳይቀር በሁለት እጃቸው ተቀብለው ያስተናገዱ መሪ፤ ሃስዝብን በነጸ የገለጸ ዜጋ ላይ የማግለል ፖለቲካ ይሰራሉ ብለን ለመገመት ይከብደናል። የቀን ጅቦቹ ያሉት ሁሉም ስፍራ ነው።
ዛሬ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት የሚቆረቆር መብዛቱ በጎ ነው። ከነፈሰው የሚነፍሱ ግብዞች፤ ተቆርቋሪዎች እኛ ብቻ ነን ሲሉ ማየት ግን ያምማል።
አንዳንድ ቀላጆች እንደሚሉት አስቴር በዳኔ የጠቅላዩ ስልጠና አያስፈልጋትም፤ እስዋ አስቀድማ ተደምራለች እያሉ የሚነግሩን ቁም ነገር እንደተተበቀ ሆኖ፤ ጉዳዩን ከማድበስበስ ይልቅ ጸሃይ ላይ አውጥቶ ማስጣቱ ትምህርት ይሆን ይሆናል።
የድብቅ ፖለቲካ አይኖርም ተብለናል። ሃገር የምትተዳደረው ገንዘብ እና ጥላቻ ባሰከራቸው ካድሬዎች ሳይሆን በፍቅር እና በህግ እንደሆነም ተነግሮናል። በጠቅላይ ሚንስትሩ የመደመር ራዕይ ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠር፤ ሌሎችን ተስፋ የሚያስቆርጥ፤ ጥላሸት የሚቀቡ ወያላዎች የሚሰሩት ተንኮል እንዳለ ይሸታል።
አርቲስትዋ በቤተ-መንግስት ደብተር እንጂ ድማሚት ይዛ እንዳልገባች እርግጥ ነው። አስቴር ከሌሎች አርቲስቶች የተለየ ሃሳብ እንዳለትም ይታወቃል። የተለየ ሃሳብ ያለው ዜጋ ደግሞ አይደመርም የሚል ደንብ አልወጣም። የአርቲስትዋ ሃሳብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ራዕይ ጋር የሚጻረርም አይደለም።
ከዚህ ቀደም፤ ህወሃት አርባኛ አመቱን ሲያከብር፤ በደደቢት በረሃ ውስጥ ተገኝታ እንደሌሎቹ አላጎበደደችም። ይልቁንም በህወሃት አናት ላይ የሃሳብ ቦንብ አፈንድታ እንደነበር እናስታውሳለን። በዚያ በአስፈሪ ድባብ ውስጥ ማይክ ጨብጣ፤ “እውነትን መናገር እወዳለሁ። … በእርግጥ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም። … እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን?” ብላ ጠየቀች።
“ህዝብ ‘አጎብዳጆች’ ይለናል።” አለች አስቴር በዳኔ። የፖለቲካ አየሩ እንደዛሬው ጸዳ ያለ አልነበረም። የኪነ-ትበብ ሰዎቻችንን መፈተኛ ግዜ ነበር። ከአስቴር ውጭ ጥርስ የሚያስነክስ አይደለም ተራ ጥያቄ እንኳን የጠየቀ አርቲስት አልነበረም። ሁሉም አሞጋሽ ነበር።
አስቴር በአለቆቻቸው ላይ እንደዚያ አይነት የድፍረት ቃል በመናገርዋ አርቲስቶቹ እንዳኮረፏት ሰምተን ተደንቀን ነበር። እነዚያ አሽቃባጮች ዛሬ የፊት ተሰላፊ ሆነው እስዋን ሲገፏት ሰምተን ዝም ልንል እና ልናዝን አይገባም። የደደቢቱ ድፍረትዋ እስካሁን ብዙ አስከፍሏታል። የአሁኑ ድርጊታቸው ደግሞ፤ የቀን ጅቦቹ ሆን ብለው ሞራልዋን ለመጉዳት ስራ እንደጀመሩ ቢያመላክትም፤ ኢትዮጵያ ሕዝብ በሚያከብራት እና በሚመሰክርላት ስለሆነች ልትኮራ ይገባታል። ምክንያቱም የሃቅን መንገድ መረተች እንጂ፤ ያላግባብ ባለሃብት እንደሆኑ አርቲስቶች አጎብድዳ መኖርን አያቅታትም። ለቀን ጅቦች ዘንድሮ የሙስና በር የተዘጋ ይመስላል።
አስቴር ከአዳራሹ እንድትወጣ ተደረገ። ስልጠናው ቀጠለ። ኪነ ጥበብ በኢትዮጵያ ውስጥ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና የንፅፅር ትምህርት ሰጥተዋል ተብሏል። ስልጠናውን የወሰዱት አርቲስቶች በቴሌቭዥን የሰጡዋቸውን ቃላትም ሰምተናል። ራያና ቆቦ!
የዶክተር አብይ ሰዎችን ለስልጠና ሲጠሩ የሰልጣኞችን እውቀት፤ የግንዛቤ እና የትምህርት ደረጃ መጥነው ቢያቀርቡ ይመረጣል። ትምህርቱ እንዲዋሃዳቸው ምንም የእንግሊዝኛ ቃልባይጠቀሙ ደግሞ መልካም ነው። ለምሳሌ እነ ሳሞራን ሲያሰለጥኑ ትምህርቱን ያዘጋጁት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስለነበር ሰዎቹ ገለጸውን ለመረዳት እንደተቸገሩት በግልጽ ይታያል።
የአርቲስት ሰርጸ ፍሬ ሰንበት እና የተዋንያን ሰለሞን ቦጋለን ከስልጠናው በኋላ ተጠይቀው የሰጡትን መልስ ብቻ ሰምቶ አርቲስቶቹ ስልጠናውን እንዳልተከታተሉት መገመት ይቻላል። ሰለሞን ቦጋለ እንዴት መስራት እንደሚገባን አቅጣጫ ጠቋሚ ትምህርት ነበር ሲል። ሰርጸ ግን ከኮሚኒስት ተኮር ጥበብ ነጻ ሆነን መስራት እንደሚገባን … ለምሳሌ ግድብ ሲሰራ ስለ ግድብ ዝፈኑ ከሚል ዕዛ ይልቅ አርቲስቱ በራስ ፈጠራ እንዲመራ የሚል አስተምሮት እንደሆነ ነግሮናል።
ከመጣው ጋር ማሸርገድን አቁሙ ሲሉ ምክር እንደሰጡም ምንጮች ገልሰዋል። በተለይ ድምጻዊ ጌትሽ ማሞ እና ቴዎድሮስ ተሾመን በስም ጠርተው “አብረን አድገናል። ጓደኛ ነን። አሁን ቤተሰብ ነን.. ምናምንም ማለታችሁን አቁሙ ማለታቸውን ቃሊቲ ፕረስ ዘግቧል። እንደ ዶ/ር አብይ ገለጸ ሁሉም የኪነጥበብ ሰው እኩል ነው መታየት ያለበት።
እርግጥ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ስሙን የተሸከመ ሁሉ አርቲስት አይደለም። ከጥበብ ይልቅ ንዋይ ያስቀደመ ሁሉ አርቲስት አይባልም። “ገንዘብን ሳይሆን ጥበብ አስቀድሙ” ይላሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ። እንደዚህ አይነቱ አስተምሮት እንደ አስቴር በዳኔ ላሉ አርቲስቶች አያስፈልጋቸውም።

አርበኛ ታጋይ ሽባባው ጌታሁን ለሀገሩ ማድረግ ያለበትን ሁሉ አድርጎ በመጨረሻ በክብር አረፈ


የአገራችን ፖለቲካ እንዲስተካከል እድሜውን ሙሉ የለፋና የደከመ ፣የኢትዮጵያን ህዝቦች ከጭንቀት ለመገለገል የወጣና የወረደ የያኔው የኢህአፖ የአሁኑ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አርበኛ ታጋይ ሽባባው ጌታሁን ። እራሱን እንደ ሻማ አቅልጦ ለሌሎች ብርሃን ለመሆን በክብርና በኩራት ታሪክ ሰርቶ ያለፈ ጀግና። አርበኛ ታጋይ ሽባባው ሞትን ከአንዴ ሁለት ሶስቴ በተለያዩ ጦር ሜዳዎች ተጋፍጦ አሸንፏል። ይህ ሞትን በተደጋጋሚ የተጋፈጠውና እጅ ላለመስጠት አልያም ከመቃብር በላይ የሚያስጠራ ስራ ሰርቶ ለማለፍ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይለው ሃያል ሰው በመጨረሻ ስዓት የድል ሻማውን ከፍ አድርጎ ሳይጨርስ ከትግል ጓዶቹ በሞት ተለይቶናል። አባታችን ፣ወንድማችን፣ መካሪያችን፣ አስተማሪያችን፣ አለኝታችን ጓድ ሽባባው ጌታሁን ።

አርበኛ ታጋይ ሽባባው ጌታሁን ከአባቱ ከወታደር ጌታሁን ዋዩ እና ከእናቱ ወ/ሮ የሻለም ፈንታ በ1952 ዓ/ም በሰሜን ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ መሆና ጊዮርጊስ በሚባል አካባቢ ተወለደ ። በተወለደበት በአካባቢ ከእኩዮቹ ጋር የልጅነት ጊዜውን አጣጥሞ ሳይጨርስ የ5 ዓመት ልጅ እያለ አባቱ አቶ ጌታሁን ዋዩ ወታደር ቤት በመቀጠራቸው ምክንያት ወደ አዘዞ ከተማ ከአባቱ ጋር መጣ ።እድሜው ለትምህርት ሲደርስ በዛው በአዘዞ ከተማ ትምህርቱን አንድ ብሎ በመጀመር ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ተማረ ከ9-12ኛ ክፍል ትምህርቱን ደግሞ በጎንደር ከተማ በአጼ ፋሲለደስ ትምህርት ቤት ተምሯል ።ይሁን እንጅ የ12ተኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና አልወሰደም በጊዜው የግራው ፖለቲካው ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ስለነበር በህቡዕ በወጣቶች ማህበር ሲንቀሳቀስ ቆይቶ በ1969 ዓ/ም ከኢህአፖ የከተማ መዋቅር ወደ ገጠሩ የኢህአፖ መዋቅር ጎልማሳነቱና ህይወቱ፣ቤተሰቡና ትምህርቱ ሳያሳስቡት በቆራኝነት ጠለምት ወደ ሚገኘው የኢህአፖ ሰራዊት በማምራት ትግሉን ተቀላቀለ ። ከህጻንነት ጊዜው ጀምሮ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ስላደገ የወታደራዊ ህይዎት ብዙም አልከበደው በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ በወታደራዊ መዋቅሩ በምክትል ጋንታ መሪነትና ፣በብሬን ተኳሽነት ተመድቦ ያገለገለ ሲሆን በተጨማሪም በሀይል መሪነት አገልግሏል። በሶስትና አራት ሀይሎች ውስጥም የወታደራዊና የፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን መርቷል። አርበኛ ታጋይ ሽባባው ብዙ ጦር ሜዳዎች ላይ በተዋጊነትና በአዋጊነት ተፋልሟል አፋልሟል፣ አካሉን አጥቷል፣ ጓዶቹን ሰውቷል። አስቸጋሪውን የጣረሞትና የሲቃ በአይኑ አይቷል ኑዛዜአቸውንና አደራቸውን በጀሮው ሰምቶ ተቀብሏል።በ1974 ዓ/ም የኢህአፖ በገጠመው ችግር የመበተን አደጋ ሲያጋጥመው ከፊሉ ወደ ሱዳን ሲሰደድ የተወሰኑት ደግሞ ወደ ኤርትራ በማቅናት ሁለት ወር ግምገማ አድርገው ድርጅቱን ለመታደግ በሞከሩበትና ወደ ቋራ ለዳግም ትግል ሲመለሱ በወቅቱ አርበኛ ታጋይ ሽባባው ቀኝ እጁ ላይ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ አጋጥሞት ስለነበር በጀበሃ አጋዥነት ከሰላ ህክም ላይ ቆይቶ ነበር። ህክምናው ብዙም ለውጥ ስላልታየበት ከአንድ ሳምንት በኋላ ወደ ካርቱም ለከፍተኛ ህክምና እንዲሄድ ተደርጎ ለስምንት ወራት ህክምናውን ሲከታተል ከቆየ በኋላ በ1974 ዓ/ም መጨረሻ ወደ አሜሪካን ሀገር ችጋጎ የመሄድ እድል አግኝቶ ካርቱምን ተሰናብቶ ሄደ።
ጓድ ሽባባው አሜሪካን ሀገር በኖረባቸው 36 ዓመታት በነበረውም ሀገራዊ ስሜትና ተቆርቋሪነት በአሜሪካን ሀገር የኢትዮጵያ ኮሚነቲ ማህበርን በሊቀመንበረነት ለሰባት ተከታታይ አመታት በመመረጥ መርቷል። የማህበሩ አባላትም በሀገራቸው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦና አሻራቸውን እንዲያስቀምጡ በፖለቲካው መድረክ ሲሰራ ቆይቷል ።ኢህአፖን ወደ ነበረበት የትግል ጎዳና ለመመለስ በተደጋጋሚ ሲጥር የነበረው ጓድ ሽባባው እንዳሰበው ስላልሆነለት በመጨረሻ ድርጅቱን ለቅቆ የጓዶችን አላማ ለማሳካት የተሻለ ነው፣ ከግብም ያደርስልኛል ብሎ ያሰበውን አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄን የውጭው ዘርፍን ተቀላቅሎ ሲያገለግል ከቆየ በኋላ በወታደራዊ ዘርፍ ልምዱን ለመካፈል በማሰብ የድርጅቱን የትጥቅ ትግል ተቀላቀለ ።
አርበኛ ታጋይ ሽባባው ጌታሁን የሶስት ልጆች አባትና የቤተሰብ አስተዳዳሪ ነበር ነገር ግን የልጆቹና የቤተሰቡ ሁኔታ ሳያስጨንቀው የተደላደለ የአሜሪካን ሀገር ኑሮውን ጥሎ ኤርትራ በርሃ ገባ ።ለአርበኛ ታጋዩ የትጥቅ ትግልን ለመቀላቀል ምክንያት የሆነው በኢህአፖና በተለያዩ ድርጅቶች ስም ለነጻነትና ዴሞክራሲ ሲሉ አብረውት ተሰልፈው ደማቸውና አጥንታቸው እንዲሁም ምትክ የለላት ህይወታቸውን የሰጡለትን ትግል ፍሬ እንዲያፈራ ለማድረግ በጠመንጃ ሃይል የተገኘን የመንግሥት ሥልጣን የሙጥኝ ብለው የአገራችንና የህዝባችንን ስቃይ ለማራዘም የወሰኑትን ለመፋለም ተገዶ በማረፊያ ዕድሜው መሳሪያ ለማንሳት ከተገደዱት ቅን ዜጎች አንዱ ነው።
ጓድ ሽባባው የብዙ ኢትዮጵያውያን ህይዎት ተገብሮበት ከዚህ ግባ የሚባል ውጤት ያልታየበትን የሀገራችን ፖለቲካ ለማስተካከልና መንገድ ላይ ተሰውተው የቀሩት ጉዶቹ የከንቱ ሞት እንዳልሞቱ የተነሱለትን አላማ ከግብ በማድረስ በሽምግልና እድሜው ፣በጥይት የተጎዳ አካሉ ሳይበግረው፣ በውሃ ጥምና በርሃብ እየደከመና እየዛለ፣በተራራና በቁልቁለት እየወጣና እየወረደ ፣በቀንና በሌሊት ጉዞዎች እየወደቀና እየተነሳ በብዙ ስቃዮች በመፈተን የድርሻውን ሃላፊነት ለመወጣት ወስኖ በ2008ዓ/ም ኤርትራ በርሃ ከሚገኘው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሰራዊት ጋር ለዳግም የትጥቅ ትግል ሲቀላቀል አረአያነቱ ከርሱ ጋር ለነበሩት ጓዶቹ ቀላል አልነበረም።
ጓድ ሽባባው ለወጣቶች የትግል ተሞክሮውን፣ልምዱንና ያለፈባቸውን እልህ እስጨራሽ የፖለቲካና የወታደራዊ ፈተናዎችና መሰናክሎችን ለወጣቶች በማስተማር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ትግሉን አንድ ደረጃ ወደ ፊት ለመግፋት የነበረው ቁርጠኝነት እጅግ የሚደነቅ ነው። በአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የተጋትሮ መምሪያ ውስጥ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሀላፊ በመሆን አዲስ አርበኛ ታጋዮችን በፖለቲካውና በወታደራዊው መስክ ብቁ እንዲሆኑ ሲሰራ ቆይቷል። ለኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲን ፣ነጻነትን፣ፍትህን ፣ እኩልነትን ፣አንድነትን ለማጎናጸፍ የአንድ ሰው እድሜ የሚያክል ጊዜ በትግል ላይ ሲቆይ አንድ ቀን ሳይሰለችና ተስፋ ሳይቆርጥ ከጠለምት እስከ በለሳ ፣ከቋራ እስከ ሱዳን ፣ ከኤሜሪካ እስከ ኤርትራ ቦታዎች በፖለቲካው አለም ታላቅ ስራ ሰርቷል ። በኢህአፖና በአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ውስጥ በሰላማዊና በትጥቅ ትግል ውስጥ ለሀገሩና ለወገኑ ትልቅ ድርሻ አበርክቷል ። አርበኛ ታጋይ ሽባባው ለወጣት አርበኛ ታጋዮች ትልቅ እክብሮት የነበረውና እነሱንም ድርጅቱ በሚፈልጋቸው መንገድ በመቅረጽና በማብቃት ለኢትዮጵያ ህዝብ ጩኽትና መከራ የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ እንዲሁም የያዙት ታሪካዊና ወገናዊ ሀላፊነት እጅግ የሚከብድ እንደሆነና እሱንም በመወጣት ታሪክ የምትመሰክርላችሁ ጀግኖች እንጅ የምትወቅሳችሁ እንዳትሆኑ እያለ እንደ ጉንዳን ሁሌም የሚሰራና የሚያሰራ ፣የሀገር መሰረት ፈር ቀዳጅና የነጻነት ትግሉ ቀንዲል ቆራጥና ጽኑ ጀግና ነው ። አንድን ሰው ይበልጥ ጀግና የሚያስብለው ብቻውን በመታገል ሳይሆን ከጎኑ ብዙ የሱን አይነት ጀግኖችን በማሰለፍ ነውና ጓድ ሽባባውም በእሳት የተፈተኑ እንደ ተሞረደ አልማዝ የሚያብለጨልጩ በርካታ ቁጥር ያላቸው አርበኛ ታጋዮችን ከጎኑ አስልፏል ምንም ቢመጣ ከአላማቸው ንቅንቅ የማይሉ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።
አርበኛ ታጋይ ሽባባው ጌታሁን ለሰው ልጅ የሚሰጠውን የመጨረሻ የህይወት ዋጋ በበርሃ እየሳቀና እየተደሰተ በተወለደ በ58 ዓመቱ በደረሰበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶአል ። የጓዳችን ሞት መሪርና ከባድ ያደረገው እድሜ ልኩን የተነሳለት የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት የማደረግ ፣ዜጎች በሃገራቸው እንደ ዜጋ መቆጠር እንዲችሉ ፣ኢትዮጵያ ከውርደትና ከውድቀት ወጥታ ወደ ነበረችበት የክብር ማማ ተመልሳ ማየትና የመሳሰሉት ሲሆኑ አሁን ትግሉ ጫፍ ደርሶ ነገሮች በተሳካ መልኩ በሚጓዙበት ወቅትና በድል በሚጠናቀቅበት ስዓት ለትንሽ በሞት መቀደሙ ነው ያበሳጨንና ሀዘናችንን መሪር ያደረገው።ይቺ ቀን ለመላው የነጻነት ታጋይና ለአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት የከፋች ናት። ምክንያቱም የወጣት ታጋዮች መምህር፣የዲያስፖራው ኩራትና መሪ የሆነው አርበኛ ታጋይ ሽባባው ጌታሁንን አሳጥታናለች። ጓዳችን ዛሬ ከጎናችን ብትለይም የተነሳህበትን አላማ ከግብ እንደምናደርስ ግን በእርግጠኝነት እንናገራለን ። ነብስህ ፈጣሪ አጸደ በገነት ያኑርልን እያልን የአርበኞች ግንቦት 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለጓድ ሽባባው ጌታሁን ለቤተሰቦቹና ለትግል ጓዶቹ ፣በሀገር ውስጥና በውጭ ላላችሁ ወገኖቻችን መጽናናትን እንመኛለን።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !
አንድነት ሀይል ነው !
የአርበኞች ግንቦት 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

Mystery behind the fire at Grand Anwar Mosque in Addis Ababa, Ethiopia


Mystery behind the fire at Grand Anwar Mosque in Addis Ababa, Ethiopia

ለዶክተር አብይ ከምንቀኝለት ቅኔ የበለጠ የህወሃትን መሰሪነት ለመላው አለም የምናሳብቅበት ወቅት ይሆን



የዚህ ፅሁፍ አላማ ለዶክተር አብይ ከምንቀኝለት ቅኔ የበለጠ የህወሃትን መሰሪነት ለመላው አለም የምናሳብቅበት ወቅት እንዲሆን ለማሳሳብ ነው። ብዙዎች በማርሽ ቀያሪው ዶክተር አብይና ጓዶቹ የሚነገረውን በመስማት ብቻ ለኢህአዴግ ወያኔ እጅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።የትግራይን ክልል ለመገንጠል ወጥኖ የተቆረቆረው ህወሃት ከናዚዘረኛ ባህርዩ አንጻር ብቻ ሳይሆን ሃገር የሚበታትን ህገመንግስት ለምሳሌ አንቀፅ 38 ጋርጦብን እንዴት ከህወሃት ኢህአዴግ ጋር ሰው ስለመደመር ይስማማል። ጨለማ ከብርሃን ጋር ህብረት በፍጹም አይኖረዉም። የምንፈልገው ስር ነቀል ለውጥ ስለመሆኑ በቅድሚያ መነጋገር አያስፈልግም ወይ?ለማለት ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር የተካሄደ ያክል በማስተጋባት እየተሸወዱ ይገኛል።ጉልቻ ተለዋወጠ እንጂ ያው ወጡ ኢህአዴግ ወያኔ አሁንም በስልጣን ላይ እንደሆነ ከመንም በላይ ሰዎች ከኖሩበት ቀዬ መጤ በመባል ሰለመፈናቀላቸው ዜጎች አሁንም ሰለመታሰራቸው ወዘተ ሚዛናዊ ዜና የለም።

ሴቶች እንዳይወልዱ የሚያመክን መርፌ የሚወጉ በእስር ቤት በፍርድርቤት ወዘተ የሚዘገንን ደርጊት የሚፈጽሙ አረመኔ ማፍያዎች በሰው ዘር ፍጅት በጄኖሳይድ ክስ በአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ይቅረቡ እያልን እንዳልጮህን ሰልፍ እንዳልወጣን በአማላይ ንግግር ተማርከን እንዴት ሰው ከሰይጣን ጋር ይደራደራል። ህወሃት እስካለ ድረስ የሚያደርጉት ጥገናዊ ለውጥ ብቻ እንደሆነና የወትሮውን ዘረኝነታቸውን አሸባሪነታቸውን ሳንዘነጋ ብሎም ሳንታክት ለ አለም አቀፉ ህብረተሰብ የምናሳውቅበት ጊዜ ነው።ወያኔም እኛም አለም አቀፉ ማህበረሰብም ባንድላይ ባንድ ጊዜ አንድን ሰው ብቻ ማድነቃችን ተጠቃሚው ህወሃት ብቻ ነው።ሚዛን የሚደፋ ከተባለ ብዙ አመታት ያስቆጠረ አዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር ያልሸፈነው አሁንም የሚደረግ ብዙ የወያኔ ግፍ አለ።

የውሸት ፌደራሊዝም ጦስ /Falseralism :-
ተአምር ከሰማይ የወረደ ያሕል ስናጋንን አገራችን ወደ ከባድ አደጋ እያመራች ነው። ዶክተር አብይ አፍሪካ ወደ አንድነት እያመራች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ የመገነጣጠል የመለያየት ምሳሌ አትሆንም ባሉን በዚህ ወቅት እንኳ ወቅትም ህወሃት ለሃያሰባት አመታት የዘራው ዘረኝነት ምክንያት ግፍ እያጨድን ነው ለምሳሌ ወቅታዊው መፈናቀል ከባሰባቸው ውስጥ:-

– በቤንሻንጉል ጉምዝ በአማራው ላይ አሰቃቂ ግድያና ማፈናቀል እስከ ብልት መስለብ

-በደቡብ ክልል በወንድማማቾቹ በጉራጌና በቀቤና መካከል የተከሰተው ግጭት

-በአፋር ሕዝብና በአማራ ሕዝብ መካከል የተከሰተው ግጭት

– በጌድዎ ሕዝብና በጉጂ ኦሮሞዎች መካከል በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው ግጭት

– በኦሮሞና በሲዳማ ሕዝብ መካከል የሚደረገው ግጭት

– የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይሎች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርጉት ግድያና ማሳደድ

– የኦሕዴድ ካድሬዎች አማራውን እያፈናቀሉ ቤቱን እያቃጠሉ እየገደሉ ማሳደድ አላቆመም።

የዚህ ሁሉ መንስኤ ብሄርና ብሄርን እያጋጨ በዳኝነት ለመቀጠል ተንኮል ጠንስሶ ብሎም አማራ ጠላት ነው መጥፋት አለበት ብሎ የተቆረቆረው ህወሃት የጎሳ ፌደራሊዝም ጦስ ነው።በየትኛውም አለም በቋንቋ ዘርን መስረት ያደረገ ፌደራሊዝም የለም።ስለዚህ የዘረ ፖለቲካን ልንቃወመው ይገባል።No to Racist Federalism ልንለው ይገባል።በወሬ ስላስመረቀነን ብቻ ዶክተር አብይን ና ጋልበን ከማለታችን በላይ በየአለሙ ሚዲያ ልናሳውቃቸው የሚገቡን ህጻኑ አማራ በመሆኑ ብቻ ብልቱ በቤኒሻንጉል መሰለቡ፤የሶማሌ ክልል ወታዶሮች በኦሮሞ ወገናቸውን ላይ የሚፈጽሙት ሬሳ ማስጎተታቸው ፤እንዲሁም በደቡብ ክልል የታየው ሬሳ ማቃጠል ሊለፈፍና ለተጎጆዎች ጠበቃ ሊቆምላቸው ይገባል።

ይህን ጽሁፍ ጨርሼ ልልክ ስል እንኳ ወያኔ የቀበረው የዘረኝነት time bomb ሌላ ቦታ ጊዜዉን ጠብቆ መፈንዳቱ አላቆመም።ዶክተሩ ኤርትራን አስታረቁ በተባለበት ማግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የበርታ ማህበረሰብ ወጣቶች ሰሞኑን ስልጠና በሰጣቸው አባይ ጸሃዬ ተወስወሰው የኦሮሞና አማራ ወገኖችን በቆመጥ በገጀራ እያባረሩ አየገደሉ ይገኛል።የሩዋንዳና ሁቱ ቱትሲ ጭፍጨፋ ምኑን ተለዬ ?ልዩነቱ በአለም አቀፍ ሚዲያ አለመዘገቡ እንጂ እምቦቀቅላ ህጻናትን አናታቸውን በቆሙበት ተርትሩ ብሎ ስልጠና የሰጣቸው አባይ ጸሃዬ እንደሁቱ መሪ በአለም ኣቀፉ ፍርድ ቤት ልክ እንደRuwandan Genocide መዳኘት ያንሰዋል። የቀን ጅቦችን ሊያስር ብቅ ያለው አብይ አህመድ የሩዋንዳዉን የዘር ፍጅት ሊያብስ መሪ ሆኖ ብቅ እንዳለው ፓል ካጋሜ ሙሴ ሊሆነን ከቻለ አርቲስት ማሰልጠኑን ትቶ በቅድሚያ የዘረኝነት ትብታቡን ይበጥስልን።



ወያኔ በአለም አቀፍ ታዋቂው አሸባሪ ድርጅት

የነሱን በአሸባሪነት ለመክሰስ ከሌሎች የውጭ ዜጎች ምስክርነት ካስፈለገም የኢትዮጵያ መንግስት ታክሲ ውስጥ ቦምብ አፈንድቶ በኦነግ እና በኤርትራ ያመካኛል ብለው መረጃውን ለዊኪሊክስ የሰጡትን ያንድ ወቅት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባልደረባ ጥቆማን ማየት በቂ ነው።


Wikileaks Ethiopia Files: Ethiopia Bombs Itself, Blames Eritrea: In a report from 2006 marked “Secret ; Subject: Ethiopia: Recent Bombings Blamed on Oromos Possibly the Work of GOE [Government of Ethiopia]…by: Charge [d’Affairs] Vicki Huddleston”, “An embassy source, as well as clandestine reporting, suggests that the bombing may have in fact been the work of the GoE security forces.” Cable reference id: #06ADDISABABA2708

በመስቀል አደባባይ ላይ የህዝብ ፍቅር ሲፈነዳ ቀንተው ቦንብ ያፈነዱት “ሰው ሲታረቅ ሲፈታ ደማቸው አይን የሚለብሰው” የታሪክ አተላዎች አማካኝነት መሆኑ አይጠራጥርም።።በነኤርትራ ኦነግ ወይ ግንቦት ሰባት እንዳያመካኝ ቀድመው እነሱ ሰላማዊ ያልሆነ ትግል ማቆማቸውን አውጀዋል።የቦምብ ፍንዳታውን ሊያጣራ አሜሪካ ኢትዮጵያ የገባ የአሜሪካው የስለላ ኤጀንሲ FBI በዛዉም አዲስ አበባ በድጋፍ ሰልፍ ስትቀወጥ መቀሌና ጉሙዝ ውስጥ መሽገው ቦምብ ሲያድሉ ለነበሩት እነበረከት ስምዖንን ይመርምርልን።

ከራሳቸው ከወያኔዎች አንደበት በፓርላማ ስብሰባ ላይ ዶክተር አብይ ያለውን እንዳሉት እስረኞችን በማይገባ አያያዝ ያገተው የነሱ የፍትህ ስርዓት ተቋማት ይጠየቁ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በባዶ እጁ ሰልፍ በወጣ ህዝብ ላይ ታንክ ይዞ ለፓርቲ የሚሰራ ፖሊስናወታደራዊ ተቋማት ናቸው አሸባሪዎች ያሉትንም ምስክርነት በመጥቀስ በአለም አቀፉ ወታደራዊ ፍርድቤት ይታዩ።

ህወሃት ከጥንት ጀምሮ በአለም አቀፉ የሽብር መረጃ ቋት/Global Terrorism Database(GTD) ውስጥ በአሸባሪነት ከተፈረጁት ድርጅቶች ውስጥ ስሙ እስካሁን አለ።ኢትዮጵያ ውስጥ በፈጸማቸው በምስሉ ከተጠቀሱት 10 በላይ የማፍያ ድርጊቶች እንዲሁም ለሃያሰባት አመት ሙሉ ለሰራው ወንጀል እንደ እነ አልቃኢዳ/Al Qaeida: IS ወዘተ በምዕራባውያኑ ዘንድ እንደ አሸባሪነትእንዲወገዝ ግፊት ግፊት ማድረግ ከኛ ይጠበቃል።በየሚዲያዎቻቸው በማስተጋባት። ዶክተር አብይ”አሸባሪ ግለሰብ የለም አሸባሪ ድርጅት ግን መጠየቅ አለበት” ባለውም መሰረት ዘረኛና አሸባሪ ድርጅት ህወሃት ከምድረገጽ መጥፋት አለበት።እነአሜሪካ አፍጋኒስታን ቶራቦራ ተራራ ውስጥ ተደብቆ የነበረውን ኦሳማ ቢንላደንን ለመግደል እንደደከሙት ያህል ሀገር መምራት ደረጃ ላይ የደረሰን አሸባሪ ስብስብ ወያኔህወሃትን በቀላሉ ማደን አያቅታቸውም።



ኢሰብአዊነት በወያኔ ማጎሪያ ቤት:- ቀንደኛ የለውጥ አራማጁ የዶክተር አብይ የፕሬስ ነጻነትን አስጀምራለው ያሉትን ተከትሎ ድንገተኛ ሀቀኝነት በኢቲቪ ቀርቦ ነበር።የኢቲቪ ጋዜጠኞች ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት አቅንተው የታራሚውን ብሶትና ታራሚ የሚሰቃይበትን የጨለማ እስር ቤት ቀርፆ አስተላልፏል፡ጥያቄው አዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር በሚነግሩን ተስፋ ብቻ የግድያው የአፈናው እስር ቤት ውስጥ ታራሚዎች ስለሚፈጸምባቸው ዘገባ በኢቲቪ ሳይቀር የቀረበውን ዘግናኝ ድርጊት ችላ ብለነዋል። ራሳቸውን ያጋለጡበትን ዘገባ ሆነ የቀን ጅብነታቸውን ይፋ እያደረገ የመጣውን የለውጥ ሃይል አዎ እኛም 27 አመት ሁሉ ስንቃወም የነበረው ይሄው ነው ብሎ ለውጪው አለም ማሳውቅ አሁንስ ምን ይከለክለናል።

ስለለማ ቲም ከምናወራው ከምንጽፈው የበለጠ የህወሃትን መሰሪነት አውሬነት ዘረኝነት አሸባሪነት በየድጋፍ ስልፉ ሳይቀር ማስተጋባት ጥቅሙ ለኛው ነው። አደራዳሪዎቻችን ወይም ሃያል አገራት ህወሃት ለሽግግር መንግስት ለስር ነቀል ለውጥ የሚገፋፉት አብይን ከምንክበው በላይ ህወሃት በአሁኑ ወቅትም ቢሆን አሸባሪነቱን እንዳልተወ ስናሳስባቸው ነው።ካለበለዚያ ጥገናዊ ለውጡን ተቀበሉ ይሉናል። የፈለገ ቅን ቢመስልም አዲሱ ጠቅላይ ምንስትር አብይ አህመድ እንደ ሟቹ መለስ ዜናዊ ትግራይን ወርቃማ ህዝብ ብሎ አውጆ ሌላውን ንቋል; የሙስና ንግስት የሆነችውን አዜብ መስፍንን ሿሟል::የህወህትን ጄነራል ሳሞራን ቢሽርም የተካው ሰዓረ ያው ስለሆነ ምንም ለውጥ እንዳልሆነ መላው ኢትዮጵያውያን ብሎም መላው አለም ሊያውቀው እና ልናሳውቅ ይገባል::በሌሎች ግፊት ራሳቸውን ማጋለጥ የጀመሩ አመራሮች ፤ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው የሚለቁ ካድሬ ሹመኞች የመኖራቸውን ያህል አሁንም ቢሆን የደደቢት ምሩቃን ለሃገር ክህደታቸው ይቅርታ ሲሉ አይታይም።ለድርድር ኢትዮጵያ የገቡ የሚገቡ ውጭ ሃገር የነበሩ ተቃዋሚዎችስ ዋስትናቸው ምንድነው።በድርድሩ ካልተስማሙ ዘው ብሎ አንደገቡ ዘው ብለው እስር ቤት አንደማይዳርጓቸው ዋስትናው ምንድን ነው። የዶክተር አብይ የድጋፍ ሰልፍ ላይ እንደተወረወረው ቦንብ አይነት ሰለባ ቢያደርጓቸውስ። ሰው እንዴት ከ አራጁ ጋር ይውላል።በግሌ ሁሉም ኢትዮጵያ ያገባኛል የሚሉ አካላት ቢወያዩ ህወሃትን አግልለው መሆን አለበት። ወቅቱ የመደመር መሆኑ እውን እንዲሆን የመገነጣጠል ህገመንግሰት ያነገበው ህወሃት ሱሱን ስሙን መቀየር አለበት።በጥባጩ የጫካ ህግ እያለ የዲሞክራሲን ውሃ መጠጣት አይቻልም።ስለዚህ የደደቢቱ ህወሃት በቅድሚያ ይስተካከል።
አብርሃም ዘሪሁን ታዬ

Tuesday, June 26, 2018

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አፋር ክልል አዳራሹ በካድሬ ብቻ ተሞልቶ ስለጠበቃቸው አኩርፈው የተዘጋጀውንም ምሳ ሳይበሉ መመለሳቸው ተሰማ። በአፋር ብዙ ምሁራንና ወጣቶች ታሰሩ። ባንክና ሆቴሎች የመሳሰሉትም ተዘግተዋል


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ሕዝባዊ ውይይት አደርገዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን መምጣት ተከትሎ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የሆነው የአፋር ሕዝብ ዴሞክራሲያ ፓርቲ (አ.ብ.ዴ.ፓ.) የፓርቲውን አባላትና ደጋፊዎችን ከተለያዩ ከተሞች በማምጣት አስተዳደራዊ ቅሬታዎች እንዳይሰሙ አድርጓል።
በክልሉ የተንሰራፋውን ሌብነት፣ የዘመድ አዝማድ አሰራር፣ ኋላቀርነትና የህወሃትን ጣልቃ ገብነት ያጋልጣሉ የተባሉ ግለሰቦች ላይም አካላዊ ጉዳቶች ተፈጽሞባቸዋል። ቁጥራቸው ከሰማኒያ በላይ የሚሆኑ ወጣቶችና የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንም ካለ ፍትሕ ታስረዋል። ወጣቶችን በመደገፍ የምትታወቀውና የከተማው ፖሊስ ሰራዊት አባል የሆነችው ሳዲያ አህመድ በድብደባ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ አንድዋ መሆኗን የአፋር ሰብዓዊ መብት ታጋይ ወጣት አካድር ኢብራሂም ገልጸዋል።
የአፋር ክልል፣በኢትዮጵያ ኋላቀር ክልል ተብለው ከማእከላዊ መንግስት ተጨማሪ በጀት ከሚመደብላቸው ክልሎች አንዱ ቢሆንም፣ የክልሉ ነዋሪዎች አሁንም የልማቱ ተጠቃሚዎች መሆን አልቻሉም።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ለተገኙት ተሰብሳቢዎች ባሰሙት ንግግር “የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ላይ የሚፈጠሩ ዘርፈ-ብዙ ችግሮችን ለመፍታት በአንድነት ከጎናችን ሆናችሁ ጥንካሬ እንደምትጨሩረልን አንጠራጠርም። ምክንያቱም አንድም ቀን ለኢትዮጵያ ፍቅርን ለባንዲራ ፍቅርን አሳንሳችሁ አታውቁምና!” በማለት የአፋር ህዝብ ለኢትዮጵያዊነት ምስረታ ላበረከቱት አስተዋጾ አመስግነዋል። ወደፊትም የተለመደው አጋርነታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ክቡር ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ የጀመሩትን የመደመር መርሃ ግብራቸውን ለማስቀጠል ዘበዛሬው ዕለት ወደ አፋር ክልል አቅንተዋል። በዚያም የክልሉ ባለሥልጣናት ለጠቅላዩ አቀባበል አድርገዋል። ነገር ግን ለጠቅላያችን የተደረገው አቀባባል በሌሎች ክልሎች ከተደረገው አቀባበል ጋር እንኳን ሊቀራረብ ጭራሽ አይጠቀስም ይላሉ የመረጃ ምንጮቼ።
በአፋር ተቃውሞ ከተጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል። አፋሮቹ እንደሚሉት ከሆነ የህውሓት እስትንፏሷ ያለው ወልቃይት ሳይሆን አፋር ነው ነው የሚሉት። በአፋር ጨውና ጥጥን ጨምሮ የተፈጥሮ ሃብቱንና ኢኮኖሚውን ጭምር የተቆጠጠሩት ህውሓቶች በመሆናቸው ሀገሬው የበዪ ተመልካች ሆነዋል ነው የሚሉት። እናም ዛሬ የከተማው ህዝብ ወደ አዳራሹ በመሄድ ብሶቱን ለመናገር ገና ከጠዋቱ ነበር ጉዞ የጀመረው።
ዶር ዐቢይ ከመምጣቱ ቀደም ባሉት ሳምንታት አፋሮችን የሚያስቆጣ ተግባር በክልሉ መሪ ፓርቲ አብዴፓ/ኢህአዴግ መፈጸሙ ለዛሬው ህዝባዊ ቁጣ እንደዳረጋቸውም ይነገራል። በአፋሮች ዘንድ እንደ እንደ ጀግና የሚቆጠር ረሺድ የሚባል የአፋር ተወላጅ ነበር። ይህ ሰው እጅግ የተማረ ስለሆነ ለሆዱ ሳይሆን ለህሊናው መኖር የጀመረ ሰው እንደሆነ ይነገርለታል። የህውሓቶቹ በክልሉ ውስጥ የሚፈጽሙት ህገወጥ ተግባራት በሙሉ ነገረሥራቸው ሁሉ አይጥመውም፣ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሳይፈራ ይቃወማቸዋል፣ ቢቸግራቸው ገንዘብ ሲያገኝ ይተንይሆናል በማለት የወረዳ ፋይናንስ ኃላፊ አድርገው ይሾሙታል። እሱ ግን አሻፈረኝ በማለት ሰመራ ዩንቨርስቲ የሰው ሃብት ተቀጥሮ በመሥራት ተቃውሞውን ቀጠለበት። በዚህ ሁኔታ እያለ ነው እንግዲህ የዐቢይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ባለፈው ሳምንት አካባቢ ተጠልፎ የተሰወረው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ታድያ አዲሱን መንግሥት ተከትሎ የአፋር ህዝብ ልል እንደሌሎቹ ከተሞች ህዝብ ለዶር ዐቢይ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ ቢወጣ የክልሉ አቃጣሪ ፓርቲ በመሳሪያ ኃይል ሰልፈኛውን እንደበተነ ይነገራል።
አፋሮቹ ተስፋ ሳይቆርጡ እንደገና ሰኔ 16 ጠሚዶኮ ዐቢይን ለመደገፍና አስጠቅቶናል፣ አስዘርፎናል፣ ድኃም እንድንሆን አስደርጎናል የሚሉትን የህውሓት ተለጣፊውን አብዴፓን እንቃወማለን በማለት ሰልፍ ወጡ። የክልሉ መንግሥትና ፓርቲውም አቶ ረሺድን እኛ አላሰርነውም የት እንዳለም አናውቅም በማለት ለህዝቡ ምላሽ ሰጡ። ጉዳዩም ከዶር ዐቢይ ጆሮ ደርሰ። እናም ለዚህ ነበር የአፋር ህዝብ ወደ አዳራሽ እንዳይገባም፣ ጥያቄም እንዳያቀርብ የተከለከለው።
ጠዋት ላይ አሁን የአፋር ወጣቶች ዐቢይን ማግኘት እንፈልጋለን። ለእሱ የምንነግራቸው ምስጢሮች አሉን በማለት ነበር ወደ አዳራሹ የተመሙት። ነገር ግን እዚያ ሲደርሱ አብዴፓ ሆዬ ህዝቡን ትቶ የቀበሌ ሠራተኞችን፣ የፓርቲው አባላትና የወጣት ፎረም አደረጃጀቶችን፣ እንዲሁም የህውሓት ካድሬዎችን በኮድ እየመረጠ ህዝቡን አላስገባ አለ። በዚህ መሃል ህዝቡ የክልሉ ፓርቲ የፈለገውን እያስገባ እኛን አላስገባ ብሎናል በማለት ጭቅጭቅና ግርግር ይፈጠራል። እነገባለን አትገቡም ጭቅጭቁ ሲበረታ ጊዜ ፖሊስ ጥይት በተኮስ የኃይል እርምጃ በመውሰዱ ብዙዎችን አበሳጭቷል፡፡ በኃይል እርምጃውም ወታደሮቹ በብዙ የአፋር ወጣቶች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የሚደርሱኝ መረጃዎች የሚያሳዩት።
ዶክተር ዐቢይም በአዳራሹ ውስጥ ባዩት ነገር ደስተኛ አልሆኑም። እንዲያውም እንዲህ ማለታቸው ነው የተሰማው። " እናንተ የአፋር አመራሮች ሁለት ሞት ትሞታላችሁ፡፡ አንድም ሐብቱና ንብረቱ በዘረፋችሁበት አፋር ህዝብ ዘንድ ትሞታላች፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በአምላክ ዘንድ ሞታችሁ ትጠየቁበታላችሁ፡፡ በማለት አብዴፓን አስደንግጠዋል ተብሏል።
በዚህ የዶክተር ዐቢይ ንግግር የተደፋፈረና በአዳራሹ በተአምር የተገኘ ጀግና የሆነ የአፋር ወጣት እራሱ የአብዴፓ ካድሬዎችን ሳያስቡት ያስጨበጨባቸውን ንግግር ማድረጉ ተነግሯል። ወጣቱ እንዲህ ነበር ያለው " የአፍዴራ ጨው ለ27 ዓመታት እየተጠቀመ ያለው የአብዴፓ አመራሮችና ነፍሰ አባታቸው የህወሓት መሪዎች ናቸው " ። እናም እኛ አፋሮች የኢኮነሚም የፖለቲካም ነፃነትና ፍትህ እንፈልጋለን በማለት እቅጯን ተናግሮ ለአፋሮች መተንፈሱ ነው የተነገረው።
ዶክተር ዐቢይ ዛሬ በአፋር አመራሮች ደስተኛ እንዳልሆኑ ነው የተነገረው። በዚህም የተነሳ አብዴፓ ያዘጋጀውን ምሳ እንኳን ሳይበሉ በመጡበት አውሮፕላን ተሳፍረው በወደ አዱ ገነት ተመልሰዋል ተብሏል።
ሽማግሌው የአፈር ሱልጣን አሊ ሚራህ ወጣቶቹ ከህውሀት ጥገኝነት እንላቀቅ የሚሉና ራሳቸውን ልክ እንደ ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ #ዱኮሄና እያሉ የሚጠሩ እንደሆነና ዱኮሄናዎችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጉልበት እያወጡ የመጡ ናቸው ተብሏል።
አሁን አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል እያለኝ ነበር። ጓደኛዬና የመረጃ ምንጬ ወታደሮቹ ዐቢይን ወደ አዳራሽ ካስገቡ በኋላ ከውጭ ያገኙትን ሰው ሁሉ እያፈሱ እንደሆነና የቢሮ ሠራተኞችም አፈሳውን ፈርተው ከቢሮ ሳይወጡ በቢሮ ውስጥ ለመቀመጥ መገደዳቸውን ነግሮኛል።
የመረጃ ምንጬ እንደሚለው ከሆነ ህዝቡ በጣም አዝኗል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በየሄዱበት ክልል እስረኞች እያስፈቱ አድናቆት ሰጥናቸው ሳናበቃ እነሆ ዛሬ ወደ አፋር ሲመጡ በእሳቸው ፊት ምሁራን ወጣቶች ታሰሩ ። ከ 32 በላይ ወጣቶች ተደበደቡ፣ ታሠሩም። ይሄ ሁሉ በደል የደረሰውና የታሰሩት ምሁራን የህዝብን ጥያቄ ለጠቅላይ ሚንስትሩና ለኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ ያደርሳሉ ተብሎ በመፈራቱ ነው ይላሉ።
ይሄ ግን መፍትሄ ይሆናል ወይ? ብለውም ይጠይቁና በጭራሽ መፍትሄ አይሆንም። መንግሥት ዛሬ በህዝቡ ላይ በወሰደው እርምጃ ህዝቡ እንዲያውም አንድነቱን እንዳጠነከረበት ይናገራሉ።
Image may contain: one or more people and people sitting
አፋሮቹ በእስር ቤት ታጉረዋል። ዶር ዐቢይም ቢያዩት መልካም ነበር። ነበር ባይቀር መደመር አለ አፋር።
Image may contain: 2 people, people smiling, people standing and text
የአፋሮቹ እነደ ቄሮ፣ ፋኖ እና ዘርማ ራሳቸውን ዱኮሂና ብለው ተከስተዋል። ብራቦ ዱኮሂናዎች ። በርቱ ።
Image may contain: one or more people

Wednesday, June 20, 2018

አሜሪካና ሰሜን ኮርያ ታሪካዊ ስምምነት ተፈራራሙ


  የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ታሪካዊ ስምምነት ተፈራራሙ።
ሁለቱ መሪዎች ዛሬ  ሲንጋፑር ወስጥ ባደረጉት ውይይት ለሁለቱ ሃገራት ሰላም እና ብልጽግና ለመስራት ቃል ገብተዋል።
በዚህም ሰሜን ኮርያ የኒውክለር ፕሮግራሟን ለመሰርዝ ቃል መግባቷም ተመልክቷል።
ኮርያ ሰሜን እና ደቡብ በሚል ከተከፈለችበት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1945 ጀምሮ ለ 73 ዓመታት ከአሜሪካ ጋር በጠላትነት የቆየቸው ሰሜን ኮርያ ይህንን ታሪካዊ ስምምነት ማድረጓ ሃገሪቱን ወደ ዓለም አቀፉ መድረክ እንደሚመልሳትም ተመልክቷል።ሆኖም ከአለም ተነጥለው በፍጥጫ ውስጥ ለቆዩት ሰሜን ኮርያውያን  ይህ ርምጃ ደስታን በቻ ሳይሆን ቅሬታን ማስከተሉም ተዘግቧል።የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ አን ወደ ታሪካዊው ስምምነት ለመምጣት ብዙ መሰናክሎችን ማለፋቸውን ተናግረዋል።በዚህም ስምምነት ዓለማችን መሰረታዊ ለውጥ ታያለች ሲሉም ቃል ገብተዋል።
ይህንኑ ስምምነት ታሪካዊ ሲሉ ያወደሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የትናንት  ግጭት የነገ ጦርነት አይሆንም፣የትናንቱም ጉዳይ የነገን ሁኔታ አይወስንም በማለት አዲስ ምዕራፍ ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።ሁለቱ መሪዎች በሲንጋፑር የደሴት ከተማ ሲንቶሳ ውስጥ ያደርጉት ሥምምነት የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አብይ ርዕስ ሆኖ ቀጥሏል።

ኤርትራ ወደ አዲስ አበባ የልኡካን ቡድኗን ልትልክ ነው


 ኤርትራ ወደ አዲስ አበባ የልኡካን ቡድን እንደምትልክ አስታወቀች።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ በተከበረው የሰማዕታት ቀን ላይ ወደ አዲስ አበባ ስለሚልኩት የልኡካን ቡድናቸው በይፋ መናገራቸውም ታውቋል።
በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ ለውጥ ቀልብ የሚስብ ነው በማለት የገለጹት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለቱ ሃገራት መካከል ለሚደረገው ገንቢ ውይይት የልኡካን ቡድናቸው ወደአዲስ አበባ ያመራል ብለዋል።
የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምላሽ የመጣው የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል መወሰኑን ተከትሎ ነው።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምላሽ ምስጋና ማቅረባቸውንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት ላይ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበለውና ለተግባራዊነቱም እንደሚሰራ ውሳኔ ላይ ከደረሰ በኋላ በኤርትራ በኩል ይፋዊ ምላሽ ሳይሰጥ ቆይቷል።
በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የኤርትራ አምባሳደሮችና የኤርትራ መንግስት ቃለ-አቀባይ ወዲያውኑ በሰጡት አጭር ምላሽም ቢሆን ስለ ኢሕአዴጉ መግለጫ የኤርትራን አቋም ከመግለጽ ተቆጥበው ነበር።
ከሁለት ሳምንት ቆይታ በኋላ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካኝነት ኤርትራ ምላሿን አስታውቃለች።
በሀገሪቱ ቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈና የሰማዕታትን ቀንን አስመልክቶ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የፖለቲካ ለውጥ ትኩረት የሚስብ እንደሆነም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሽግግር ወቅት ላይ መሆኗን ተገንዝበናል ያሉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ኢትዮጵያ አንድ የልዑካን ቡድን እንደሚልኩ ነው በይፋ ያስታወቁት።
አቶ ኢሳያስ ወደ ኢትዮጵያ የሚልኩት ቡድን ገንቢ ውይይት እንደሚያደርግ ከመግለጽ ባለፈ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም።
መቼና እንዴት የልዑካን ቡድኑ ወደኢትዮጵያ እንደሚያመራ የገለጹት ነገር ግን የለም።
በኢትዮጵያ የሚታየው ለውጥ ወዴት ያመራል የሚለው በጥያቄ የሚተው ነው ያሉት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጊዜ ቢወስድም የህወሀት አገዛዝ እያበቃለት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ በትኩረት የሚሰራ ተግባር እንደሆነም አስታውቀዋል።
የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምላሽን በደስታ እንደተቀበሉትም የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገልጸዋል።
ወልቂጤ ላይ ህዝባዊ መድረክ እየመሩ የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ምላሽ የሰሙት ዶክተር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ የኤርትራን የልዑካን ቡድን በታላቅ አክብሮት ተቀብላ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
የፕሬዝዳንት ኢሳያስን የዛሬ ምላሽ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በትኩረት የዘገቡት ሲሆን ከ20 ዓመታት በላይ ለዘለቀው የሁለቱ ሃገራት ፍጥጫ መፍትሄ በመስጠት አንጻር የመጀመሪያ ስኬታማ ድርድር ሊሆን እንደሚችል በመገለጽ ላይ ነው።
ሁለቱ ሀገራት እዚህ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ በሸምጋይነት መሀል  የገቡ ወገኖች ስለመኖራቸው የተገለጸ ነገር የለም።
በቀጣይም ያለአደራዳሪ ሁለቱ ሀገራት ለመወያየት መፍቀዳቸው ነው የተገለጸው።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የትጥቅ ትግሌን ላቆም እችላለሁ አለ


የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሕዝብ የሰጡትን የዲሞክራሲ ተስፋ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ የትጥቅ ትግሉን ሊያቆም እንደሚችል ገለጸ።
ንቅናቄው የሰለጠነ ፖለቲካ የምንመርጠው፣የምናውቀውና የምመኘው የትግል ስልት ነው በሚል ባወጣው መግለጫ እንዳለው አርበኞች ግንቦት ሰባት የመሳሪያ ትግልን ዋነኛ የትግል ስትራቴጂው በማድረግ የፖለቲካ ስልጣን የመያዝ አላማ ኖሮት አያውቅም።
ሆኖም ግን አገዛዙ ይከተለው በነበረው ኋላ ቀር ፖለቲካ ምክንያት ዜጎች ከመንግስት ሽብር ራሳቸውን እንዲከላከሉ ሲያበረታታና እራሱንም ከጥቃት ሲከላከል ቆይቷል ብሏል በመግለጫው።
አርበኞች ግንቦት ሰባት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሰሞኑን ለፓርላማ ያደረጉት ገለጻ የሚያበረታታና የሚደነቅ ሲል አወድሶታል።
መንግስት የሽብር ተግባር ይፈጽም እንደነበር ዶክተር አብይ በይፋ መናገራቸውና የፍትህ ስርአቱ ችግር ያለበት መሆኑን ማመናቸው ሃቅን ለመናገር የሚደፍሩ መሪ መሆናቸውን ይሳያል ሲል ንቅናቄው ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።
ይህ ብቻ አይደለም እሳቸው የሚመሩት ቡድንም ለሃገራዊ መግባባት ያለውን ዝግጁነትም ያሳያል ብሏል አርበኞች ግንቦት ሰባት።
ዶክተር አብይ በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን ክልል የሚያጠና ኮሚሽን ይቋቋማል ማለታቸውንም አዎንታዊ ነው ሲል በመግለጫው አመልክቷል።
ሕወሃትንና የትግራይን ሕዝብ ለይቶ ስለመመልከት ዶክተር አብይ አህመድ የተናገሩትም አርበኞች ግንቦት ሰባት ከልብ የሚያምንበትና በጽናት ሲያራምደው የቆየ እምነት መሆኑንም ገልጿል።
እንደ አርበኞች ግንቦት ሰባት መግለጫ ከሆነ በሕወሃት ውስጥ የለውጥ ሃይሎች መኖራቸው እሙን ነው።
እናም የኢትዮጵያን ሰቆቃ በመቀነስ ረገድ ሕወሃት ውስጥ ያሉ የለውጥ አራማጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን እናምናለን ብሏል አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በመግለጫው።
ስለሆነም ከእነዚህ የለውጥ ሃይሎች ጋር ተባብረን ለመታገል ዝግጁ ነን ሲል ንቅናቄው በመግለጫው አስታውቋል።
በመገዳደል ስልጣን መያዝም ሆነ በስልጣን መቆየት ኋላቀር ፖለቲካ ነው በሚል ዶክተር አብይ ግንቦት ሰባት የትጥቅ ትግሉን እንዲያቆም ላቀረቡት ጥሪም ንቅናቄው ምላሽ ሰጥቷል።
እንደ ንቅናቄው መግለጫ አርበኞች ግንቦት ሰባት የመሳሪያ ትግልን ዋናው ስትራቴጂው አድርጎም ሆነ በዚሁ መንገድ ስልጣን የመያዝ አላማ ኖሮት አያውቅም።
እናም ዶክተር አብይ ለዲሞክራሲ የሰጡትን ተስፋ በተግባር የሚለውጡ ከሆነ የትጥቅ ትግሉን ሊያቆም እንደሚችልም ንቅናቄው አስታውቋል።
አርበኞች ግንቦት ሰባት በዜጎች ላይ የሚደርስ ግልጽ ጥቃት እስከሌለ ድረስ በትጥቅ ትግል የምናባክነው ጊዜ፣ጉልበትና እውቀት የለንም ሲል መግለጫውን አጠናቋል።

ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሽብር ድርጊት ሲፈጽም ቆይቷል ተባለ


 ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ራሱ በኢትዮጵያውያን ላይ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም መቆየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
መከላከያና ደህንነቱ ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ እንዲሆን ሕገ መንግስቱ ቢያዝም በተግባር ግን ይህ ሳይፈጸም መቆየቱንም ይፋ አድርገዋል።
ግንቦት 7፣ኦነግና ኦብነግ ግዜ ካለፈበት የመሳሪያ ትግል ራሳቸውን አቅበው ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዶክተር ብርሃኑ እኔን ገድለው ወይንም አስገድለው ስልጣን ቢይዙ እኔም እሳቸውን ብገድል ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ጉዳይ አይደለም ሲሉ አመልክተዋል።
በአሸባሪነት የታሰሩ ሰዎች የሚፈቱበትን ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ በፓርላማው ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሽብር ምንድን ነው አሸባሪስ ማነው የሚለውን በማብራራት ምላሻቸውን ጀምረዋል።
ሕገ መንግስታዊ ባልሆነ መንገድ ስልጣንን ለመያዝ የሚደረግ እንቅስቃሴ አሸባሪነት ከሆነ ሕገ መንግስታዊ ባልሆነ መንገድ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረገውስ አካሄድ ምን ይባላል ሲሉ መልሰው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሕገ መንግስቱ እስረኛ ግረፉ፣እስረኛ ጭለማ ቤት አስገቡ ይላል ወይ ሲሉ ለፓርላማው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
ይህ የማንም ሳይሆን የእኛ አሸባሪነት ተግባር ነው ሲሉ ገልጸውታል።
የመከላከያ ሰራዊቱና ደህንነቱ ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ መሆን እንዳለበት በህገ መንግስቱ መደንገጉንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታውሰዋል።
በተግባር ግን ይህ ስራ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ የስርአቱን የህገወጥነት ጉዞ አሳይተዋል።
ግንቦት 7፣ ኦነግና ኦብነግ ግዜ ያለፈበትን የትጥቅ ትግል ትተው ከኤርትራ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መገዳደል እንዲያበቃም ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ብርሃኑ እኔን ገድለው ወይንም አስገድለው ስልጣን ላይ ቢወጡ እኔም እሳቸውን ገድዬ ስልጣን ላይ ብቆይ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት አይደለም ሲሉም አስምረውበታል።
በሽብር ታስረው የተፈቱ ሰዎችን በተመለከተ ለተነሳባቸው ጥያቄም ሕዝቡ ለእኛ ይቅርታ እንዳደረገው ለነርሱም መንግስት ይቅርታ ያደርጋል ብለዋል።
የሕዝቡም ምላሽ ታይቷል ብለዋል።

Monday, June 18, 2018

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት ከፖለቲካ ወገኝተኝነት ተላቆ ይሰራል ተባለ


 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት ከፖለቲካ ወገኝተኝነት ተላቆ ሕዝብን የሚያገለገል ተቋም እንደሚሆን አዲሱ የተቋሙ ዋና ዳየሬክተር ገለጹ።
በቅርቡ በጠቅላይ ሚንስትር አብየ እህመድ የተሾሙት የቀድሞው የአየር ሐይል አዣዥ ጄኔራል አደም መሀመድ እንደገለጹት ተቋሙ የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ በመደራጀት ማሻሻያ ይደረግበታል።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ትናንት ለፓርላማው ባደረጉት ገለጻ ደሕንነትና መከላከያው የፖለቲካ ወገንተኞችና የአፈና መሳሪያ ሆነው መቆየታቸውን መናገራቸው ይታወሳል።
ጄነራል አደም መሃመድ አዲሱ የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ትውወቅ አድርገዋል።
በሰነ ስርአቱም ጄነራል አደም ሕገመንግስታዊ ስርአቱን ከአደጋ መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል ።
ተቋሙ ተልዕኮውን ለማስፈጸም ከፖለቲካ ወገንተኝነት መላቀቅ ይኖርበታልም ነው ያሉት — ጄነራል አደም መሀመድ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩትን አቶ ጌታቸው አሰፋ ከሃላፊነት ማንሳታቸው ይታወሳል።
በአደባባይና በመገናኛ ብዙሃን ምስላቸው ሳይታይ ለረጅም አመታት የቆዩት አቶ ጌታቸው አሰፋ ከሃላፊነት ቢነሱም በጡረታ ይገለሉ ወይንም ሌላ ቦታ ይመደቡ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።
አቶ ጌታቸው አሰፋ በምዝበራና በርካታ ሰዎችን በመግደል እንዲሁም በማሰቃየት ይታወቃሉ።–ልጆቻቸውንም በውጭ ሃገራት በውድ ዋጋ እያስተማሩ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትናንት ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር መከላከያና ደህንነት ከገዥው ፓርቲ ፖለቲካ ያልተላቀቁና ወገንተኛ ሆነው ሲሰሩ እንደነበር መግለጻቸው ይታወሳል።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ለተፈጸሙ ግድያዎች አፈናዎችና ሰቆቃዎች ዋነኛ ፈጻሚ በመሆኑ በተለያዩ ወገኖች ሲወገዝ ቆይቷል።
የመከላከያ ሰራዊትም በተለያዩ ግድያዎች ተሳታፊ ነበር።
በቅርቡ አቶ ጌታቸው አሰፋ ከሃላፊነት ሲነሱ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም የነበሩት ጄኔራል ሳሞራ የኑስም ከቦታቸው ተነስተው በሕወሃቱ ጄኔራል ሳእረ መኮንን መተካታቸው አይዘነጋም ።
ጄናራል ሳሞራ የኑስና አቶ ጌታቸው አሰፋ በስልጣን ዘመናቸው ስምምነት ሳይኖራቸው አንዱ ለአንዱ የጠላትነት ስሜት ይዘው መቆየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Friday, June 15, 2018

የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አብዮታዊ ዲሞክራሲ እየተሸረሸረ ነው ሲል ቅሬታውን አቀረበ


የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ላይ ቅሬታውን አቀረበ።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ባድመን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሁም ግዙፍ የመንግስት ተቋማት በከፊል ወደ ግል እንዲዞሩ የተደረሰበትን ስምምነት ግን እንደሚቀበለው አረጋግጧል።
የእስከዛሬው ድላችንም ሆነ የነገው ስኬታችን በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር ብቻ ነው ብሏል የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ።
ይህ ተግባራዊ መስመር በኢሕአዴግ አመራር እየተሸረሸረ ነው ሲልም ማዕከላዊ ኮሚቴው ቅሬታውን አቅርቧል።
እየተካሄደ ያለውን የስልጣን ድልድል በተመለከተም ከኢሕአዴግ ሕገ ደንብ ያፈነገጠ ነው ያለው ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለድርጅታችን ነባር አመራሮች እውቅና እንዲሰጥና አስቸኳይ ጉባኤ እንደጠራ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
የሕወሃትና ማዕከላዊ ኮሚቴ ነባሮቹን አመራሮች አቶ ስብሃት ነጋን፣አቶ ስዩም መስፍንና አቶ ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ ከሰኔ 3 እስከ 5 በመቀሌ ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባ ተከትሎ ያወጣው መግለጫ በፓርቲውና በስርአቱ ውስጥ ያለውን ጥርጣሬና ቅሬታ በግልጽ አንጸባርቋል።
የ43 አመታት የድልና የጽናት ጉዟችን ስኬት ምንጭ የጠራና ብቁ አብዮታዊ መስመር የዘለቅን መሆኑ ነው ያለው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ያለፉት 27 አመታት የስልጣን አመታት ድልና የወደፊቱም ስኬት በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የጠራ መስመር እንደሆነ አመልክቷል።
ሆኖም ይህንን ሃገራችንን ከጥፋት የታደገ የብሔር ብሔረሰቦችን እኩልነት ያረጋገጠና ተአምርን የፈጠረ መስመር በአሁኑ ሰአት በኢሕአዴግ አመራር እየተሸረሸረ በከፋ የጥገኝነት ዝቅጠት አረንቋ ውስጥ ገብቷል ሲል ሕወሃት ገልጿል።
ይህንን ፈተና ለማለፍ በድርጅታችን የተጀመረው በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴ በሚፈለገው ደረጃ ሊሳካ አልቻለም ሲልም ሕወሃት አስታውቋል።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሁም ግዙፍ የሀገሪቱን ተቋማት በከፊል ለመሸጥ የደረሰበት ድምዳሜ ተገቢና ከመስመራችን ጋር የተጣጣመ ነው ያለው ሕወሃት ሆኖም ከሕዝብ ጋር ሳይመክር በአደባባይ መገለጽ አልነበረበትም ሲል ቅሬታውን አቅርቧል።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ላይ መወያየት ሲገባው ችግሩ ባስከተላቸው ውጤቶችና ጊዜያዊ መፍትሄዎች ላይ ማተኮሩ ግን ተገቢ አይደለም ሲል ሕወሃት የኢሕአዴግን አመራር ተችቷል።
በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሳቢያ ከኑሯቸውና ከስራቸው ተፈናቅለው ሉአላዊነት በማስከበር ለቆዩት የአካባቢው ሚሊሺያና ሕዝብ ከፌደራል መንግስት ጭምር በቂ ድጋፍ እንዲያገኙ መወሰኑንም አስታውቋል።
በዲሞክራሲና በጥገኝነት መካከል ትግል እየተካሄደ ይገኛል ያለው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የኢሕአዴግን ሕገ ደንብና ተቋማዊ አሰራር ያልተከተለ የአመራር ምደባ እየተካሄደ ነው በማለት የሹመት አሰጣጡ እርምት እንዲደረግበት ጠይቋል።
ለረጅም ጊዜያት በሕወሃት ውስጥ ተይዘው የነበሩት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ኢንሳና ሜቴክን ጨምሮ በርካታ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር አዳዲስ ሰዎች መመደባቸው ይታወቃል።
ሕወሃት ለድርጅታችን ነባር አመራሮች እውቅና ይሰጥ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች በሚገባ መልስ የተሰጣቸው በመሆናቸው የትግራይን ሕዝብ አንድነትና ሰላም ለመረበሽ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ከትግራይ ሕዝብ ጋር በመሆን በጽናት እንታገላለን ሲልም አስታውቋል።
የትግራይ ሕዝብና ሕወሃት የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መስመር ደጀን በመሆን ትግላቸውን እንደሚያጠናክሩም አስታዉቋል።
በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን ያለው ሕወሃት ከጸረ-ሕወሃትና ከጸረ-ትግራይ የውስጥና የውጭ ሃይሎች ጋር አምርሮ ትግሉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ወቅታዊውን ሁኔታ በፍጥነት ለመገምገም የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራም ሕወሃት ጥሪ አቅርቧል።

Thursday, June 14, 2018

በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የወሰነው አዲስ ነገር የለም ተባለ


 በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የተወሰነ ምንም አዲስ ጉዳይ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
ሕዝብ ሳይወያይበት ለምን በአደባባይ ተገለጸ በሚል ሕወሃት ያቀረበውን ጥያቄ በተመለከተም ከእንግዲህ የመደበቅ ፖለቲካ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
አሰብን ስንሰጥስ ሕዝብን አወያይተናል ወይ በማለት ጥያቄውን በጥያቄ የመለሱት ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ ውጥረቱ ሊረግብ በድንበር ላይ ያለውም ሕዝብ እፎይ ሊል ይገባል ብለዋል።
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስከፊው ጦርነት እንደሆነ ዛሬ በፓርላማ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ላለፉት 20 አመታትም ሃገራቱ በውጥረት ውስጥ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባድመን በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔም ቢሆን በፓርላማ የተወሰነውን ወደ ተግባር የመቀየር ርምጃ እንጂ አዲስ የተለወጠ ነገር የለም ብለዋል።
አዲስ የተወሰነ ውሳኔ እንደሌለ አጽንኦት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፓርላማው ሊጠይቅ የሚገባው የፓርላማው ውሳኔ እስካሁን ተግባራዊ ለምን አልሆነም በሚል መሆን እንደነበረበት አስገንዝበዋል።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚም ባድመን ነጥሎ እንዳልተወያየ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተወያየነው ሁለቱን ሃገራት ስለሚያዋስነው አንድ ሺ ኪሎ ሜትር ነው ብለዋል።
ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ሕዝብ ሳይወያይበት ለምን በይፋ ተገለጸ ማለቱን በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል።
ከሕዝብ የሚደበቅ ነገር መኖር የለበትም የስራ አስፈጻሚው ስብሰባም ቢሆን በየደቂቃው ለሕዝብ መገለጽ አለበት የድብቅ ፖለቲካ ማብቃት አለበት ሲሉ በግልጽ ተናግረዋል።

ሕዝብን በቅድሚያ ማወያየት አለብን የሚሉት ወገኖች አሰብን ሲሰጡ ሕዝብ አወያይተዋል ወይ የሚል ጥያቄንም ለፓርላማው አቅርበዋል።
መገናኛ ብዙሃንም ለሕዝብ ተደራሽ የሆኑና ነጻ መሆን አለባቸው ብለዋል።

missing Children በአሜሪካ ከወላጆቻቸው የሚነጠሉ ህጻናት ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ

በአሜሪካ ከወላጆቻቸው የሚነጠሉ ህጻናት ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ

 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የሚከተለውን የውጪ ፖሊሲ ተከትሎ ከወላጆቻቸው የሚነጠሉ ህጻናት ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ።
ፕሮ ፐብሊሺያ የተባለ የዜና ማሰራጫ ከቤተሰቦቻቸው ሲለያዩ ሕጻናቱ የሚያሰሙትን የሰቆቃ ድምጽ ቀርጾ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ተቃውሞ ማየሉ ተሰምቷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገወጥ በሚሏቸው ስደተኞች ላይ ያላቸው ፖሊሲ ርህራሄ የሌለው ነው በማለት በብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ ሲገጥመው ቆይቷል።
አሁን ላይ ደግሞ በስደተኛ ማቆያዎች ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው እንዲቀሩ የተደረጉ በርካታ ህጻናት መኖራቸውን ነው ፕሮ ፐብሊሺያ የተባለ የዜና ማሰራጫ በቅርቡ ቀርጾ ባሰራጨው የሕጻናት የሰቆቃ ድምጽ መረዳት የተቻለው።
በመገናኛ ድረገጾች በከፍተኛ ፍጥነት የተሰራጨውና በብዙ ሰዎች ዘንድ መደመጥ የቻለው ይህ ድምጽ የ6 አመት ሕጻን ቤተሰቦቿን እየጠራች ስታለቅስ የሚያሳይ ነው።
በአካባቢዋ ያለው ድንበር ጠባቂ ፖሊስ ደግሞ በሕጻኗ ለቅሶ ሲያፌዝ አብሮ የተቀረጸው ድምጽ ደግሞ ከፍተኛ ቁጣ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
የድንበር ተቆጣጣሪ ሰራተኞች በበኩላቸው ህጻናቱን ከቤተሰባቸው መነጠል ፍላጎታችን ባይሆንም ህጉን ተከትለን ግን ስራችንን እየሰራን ነው ማለታቸው ተገልጿል።
በበርካቶች ዘንድ ፕሬዝዳንቱ ትችት እየተሰነዘረባቸው ቢሆንም የትራምፕ አስተዳደር ግን ህገወጥ ናቸው ባላቸው ስደተኞች ላይ እየወሰደ ያለው ርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተገለጸው።
የትራምፕ አስተዳደር ይህንንም የሚያደርጉት በሜክሲኮ እና በአሜሪካ መካከል እገነባለሁ ላሉት ግንብ ዲሞክራቶች ላይ ጫና ለማድረግና በጀት እንዲፈቅዱላቸው ለማድረግ መሆኑን አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል።
በእስካሁኑ ሂደትም 2000 የሚደርሱ ሕጻናት ከወላጆቻቸው መነጠላቸውን ዘገባው አመልክቷል።

Wednesday, June 13, 2018

የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለጠ/ሚኒስትሩ አቀረቡ


የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለጠ/ሚኒስትሩ አቀረቡ
 ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ስብሰባ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል። “የጉራጌ ህዝብ የክልል ጥያቄ መልስ ያግኝ፣ የጉራጌ ምሁራንን ማግለል ለምን ተፈለገ? ጉራጌን ከንግድ አለም ለማስወጣት አሻጥር ሲፈጸምበት ደኢህዴን የት ነበር? በቀቢናና ጉራጌ ብሄረሰቦች መካካል ግጭት የቀሰቀሱት ለፍርድ ይቅረቡ” የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።
ዶ/ር አብይ ሰሞኑን በክልሉ ግጭት የቀሰቀሱ አካላት በራሳቸው ጊዜ ስልጣን ይለቃሉ ብለው እንደሚያምኑና ስልጣንም እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል።

Bildergebnis für የወልቂጤ ከተማ

Tuesday, June 12, 2018

የወልቂጤ ነዋሪ ህወሃትን በማውገዝ ተቃውሞ አሰማ


ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቀባበል የወጣው የወልቂጤ ነዋሪ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ህወሃትን በማውገዝ ተቃውሞ ማሰማቱ ተገለጸ።
በቅርቡ በወልቂጤ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ህዝቡን ለማነጋገር ወደ አካባቢው ያመሩት ዶክተር አብይ አህመድም በሀዋሳ፣ በወላይታና ወልቂጤ በደረሱት ግጭቶች እጃቸው ያለበት የመንግስት ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱና በህግ እንደሚጠየቁም አስታውቀዋል።
የወልቂጤ ነዋሪ በቅርቡ የተከሰተው ግጭት የህወሃት እጅ እንዳለበት በመግለጽ ተቃውሞውን ማቅረቡ ተሰምቷል።
በተያያዘ ዜና ከልደታ ፍርድ ቤት ችሎት የወጡ በርካታ እስረኞች ህወሃትን በማውገዝ መፈክር ማሰማታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወልቂጤ እንደሚገቡ ከተገለጸበት ዛሬ ጠዋት አንስቶ የወልቂጤ ጎዳናዎች በነዋሪው መሞላት መጀመራቸውን ነው መረጃዎች ያመለከቱት።
በእርስ በእርስ ግጭት ለሰነበተችው ወልቂጤ ዛሬ የተለየ ትዕይንት ይስተናገድባታል ተብሎ አልተጠበቀም።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል የወጣው ህዝብ ግን ምሬት ብሶቱን ለማሰማት መልካም አጋጣሚን ፈጥሮለታል።
ባለፈው ሳምንት በተከሰተውና ለሶስት ሰዎች መገደል ምክንያት የሆነው ግጭት ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የዘር ፖለቲካ የመነጨ ነው በሚል ተቃውሞውን በህወሃት ላይ ያደረገው የወልቂጤ ነዋሪ፣ ውግዘቱን ሲያሰማ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ኢሳት ያነጋገራቸው አንድ የወልቂጤ ነዋሪ ከኢትዮጵያ ከጫፍ እስከጫፍ እየተዘዋወረ በነጻነት ሲኖር የነበረው የጉራጌ ህዝብ በዘመነ ህወሃት በገዛ ቤቱ እንኳን መኖር አልቻለም ሲሉ በምሬት ተናግሯል።
የቅርብ ጊዜው ግጭትም የህወሃት ሴራ ውጤት ነው ብለዋል ነዋሪው።
ለዶክተር አብይ አቀባበል የወጣው የወልቂጤ ነዋሪዎች በአስቸኳይ የህወሃት አገዛዝ እንዲወርድ የጠየቁ ሲሆን ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወልቂጤው መድረክ የተገኙት በቀጥታ የሀውሳና የወላይታ ህዝባዊ ውይይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሲሆን በሶስቱም አካባቢዎች ለተፈጠረው ግጭት ተጠያቂ የሆኑ አመራሮች ራሳቸውን ከስልጣናን እንዲያገሉ ጠይቀዋል።
ምርመራ ተካሂዶ ጥፋተኞችም ለፍርድ እንደሚቀርቡ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የገለጹት።
በስም የትኞቹ አመራሮች ለፍርድ እንደሚቀርቡ ባይገለጽም በነዋሪው በኩል ግን አንዳንድ ባለስልጣናት ተጠቅሰው ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠይቋል።
በሲዳማ፣ በወላይታና በወልቂጤ ነዋሪዎች ዘንድ ስማቸው ተነስቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ ከተጠየቁት መካከል የደኢህዴን አመራሮች አቶ ሽፈራው ሽጉጤና አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ይገኙበታል።
በተያያዘ ዜና በአርባምንጭ ከተማም ህወሃትን የሚያወግዝ የተቃውሞ ትዕይንት የተደረገ ሲሆን በጅማ ለተፈቱ እስረኞች አቀባበል እያደረጉ ባሉ ነዋሪዎች ላይ የአገዛዙ ታጣቂዎች ርምጃ በመውሰድ በርካታ ሰዎችን ማቁሰላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በአዲስ አበባ ልደታ ፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበራቸው እስረኞችም ትላንት ከችሎት ሲወጡ የህወሃትን አገዛዝ በማውገዝ መፈክር ሲያሰሙ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል።
እስረኞቹ በእልህና ቁጣ የህወሀት አገዛዝ ዘረኛ ነው፣ ህወሃት ወንጀለኛ ነው የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን በማሰማት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

የብሄራዊ ባንክ ገዢው ከሥልጣን ተነሱ



በምትካቸው የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ደሴ ተሹመዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ተመልክቷል።
አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ሹመቱ ያልተጠበቀ እና ከሙያው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ለሌላቸው የተሰጠ ሲሉ ተችተዋል።
ከ10 ዓመታት በላይ በብሄራዊ  ባንክ ገዢነት የቆዩትና አሁን ከሃላፊነት የተነሱት  አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው መሾማቸውም ተዘግቧል።
ትናንት ሰኔ 11/2010 የብሄራዊ ባንክ ገዢ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ይናገር ደሴ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ቀደም ሲልም በተለያዩ ሃላፊነቶች ማገልገላቸው ተመልክቷል።
ዶክተር ይናገር ደሴ በሙያቸው ኢኮኖሚስት ቢሆኑም ፣ትምህርታቸው እንዲሁም ልምዳቸው  ለተሰጣቸው ስልጣን የማያበቃቸው መሆኑን አንዳንድ  የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ዶክተር ይናገር ደሴ በሙያቸው ኢንቫሮመንታል ኢኮኖሚስት ሲሆኑ፣ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት  የሚያስፈልገው ዘርፍ ማክሮ ኢኮኖሚስት እንደሆንም ተመልክቷል።
ምክትል ገዢ ሆነው መሾማቸው የሚጠቀሰው   አቶ በቃሉ ዘለቀ  ለረዥም አመታት የኢትዮጵ ንግድ  ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል።
እሳቸውም በሙያቸው አካውንታንት በመሆናቸው  የማክሮ ኢኮኖሚ ዕውቀት   በሚፈልገው ተቋም በምክትል ገዢነት  መሾማቸውንም   ባለሙያዎቹ ተችተዋል።አቶ በቃሉ  ዘለቀ የንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ከነበሩት አቶ አባይ ጸሃዬ ጋር በመሆን በንግድ ባንክ ላይ ባደረሱት ጉዳት ሊጠየቁ ሲገባቸው ወደ ሌላ ሥፍራ እንዲዛወሩ ማድረግም ተገቢ አለመሆኑን የባንክ ምንጮች ገልጸዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  ከፓርቲ አባላት ባሻገር ሄደው ባለሙያዎችን መፈልግ እና መሾም እንደሚገባቸው የሚያሳስቡት ባለሙያዎች በዚህ ረገድ የተደረገውንም ጥረት አስታውሰዋል።
በዓላም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩትን አቶ አበበ አዕምሮሥላሴን ለመሾም ጠይቀው እንዳልተሳካላቸው መዘገባችን ይታወሳል ።
በሃገር ውስጥም ብቁ  የመስኩ ባለሙያዎች  እያሉ ሹመቱ በፓርቲ መዋቅር ላይ መመርኮዝ  እንዳልነበረበትም ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው ከ10 ዓመታት  በላይ በብሄራዊ  ባንክ ገዢነት የቆዩትና አሁን ከሃላፊነት የተነሱት  አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

wanted officials