Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, September 30, 2015

የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን እየተካሄደ ካለው የተባበሩት መንግስታት 30ኛ ጉባኤ ስብሰባ ረግጠው ወጡ።







የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጄኔቭ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ካለው 30ኛ ጉባኤ ጋር ተያይዞ በተጠራ መድረክ ላይ የተጋበዙት የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ስብሰባ ረግጠው ወጡ። ስኞ እለት የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት በተመለከተ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተገኙትና በኋላ በቀረበው ሪፖርት ሳይደሰቱ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ወደ ስብሰባው አልተመለሱም። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተወካዮች ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ግለሰቦች በጄኔቭ ስዊዘርላንድ በመገኘት በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት አያያዞች ዙሪያ መወያየታቸውን እማኞች አስታውቀዋል። ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በመድረኩ ሊነሱ በሚችሉ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ ከጉባኤው ረግጠው መውጣታቸው ታውቋል። ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣና አፈና ተባብሶ መቀጠሉን ገልፀዋል። ሁሉንም የፓርላማ ወንበሮች በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የሚገኘው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት፣ የዜጎችን ሃሳብን የመግለጽ መብት ከማስፋፋቱ በተጨማሪ በነጻ የመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚወስደው እርምጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ድርጅቱ አመልክቷል። ከትናንት በስቲያ ሰኞ የተካሄደውን የሰብዓዊ መብት መድረክ ያዘጋጀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ ስላለው የሰብኣዊ መብት አያያዝ ስጋቶችን ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል። በጄኔብ በተካሄደው በዚሁ ልዩ መድረክ የተሳተፉ በርካታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ወቅታዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ረፖርት ማቅረባቸውንም በመድረኩ የተሳተፉ አካላት ገልፅዋል። የእንግሊዝ የፓርላማ አባላትን ጨምሮ በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጀቶች ኮሚሽኑ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አያያዝን ጨምሮ በተለያዩ የፖለቲካ እስረኞች ላይ ክትትልን እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበው እንደሚገኙም ተችሏል። የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች መድረኩን ረግጠው ስለወጡበት ምክንያት የሰጡት ምላሽ የለም።

Tuesday, September 29, 2015

ሰንደቅ አላማው ላይ የተለጠፈውን የሰይጣን ምልክት ኮከብ አለመቀበል ምክንያታዊ ነው!





ባለ ኮከቡን ሰንደቅ አላማ አለመቀበል ምክንያታዊ ነው!

(ጌታቸው ሺፈራው)

በዚህ የህዝብ ምርጫ በሚከበርበት ዓለም ሰንደቅ አላማ ያህል ነገር አንድ ገዥ ቡድን ‹‹ከአሁን በኋላ ሰንደቅ አላማው ይኼ ነው›› ብሎ አንዳች ምልክት ሊለጥፍበት አይገባም ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው ሰንደቅ አላማ የመጣው ግን በዚህ መንገድ ነው፡፡


ለዚህ ሰንደቅ አላማ በቅርቡ አዋጅ ወጥቶለታል፡፡ ስርዓቱም ግን አያከብረውም፡፡ ይህን አዋጅ እንዲያከብረው የሚፈለው ሌላው በተለይ ከስርዓቱ በተቃራኒ ያለው ህዝብ ነው፡፡ ይህን ስርዓቱ የሚጥሰው፣ ህዝብ ግን አክብረው ተብሎ የመጣበትን አዋጅ ያፀደቀው የ99.6 በመቶው ፓርላማ ነው፡፡ ህዝብ ለዚህ ፓርላማ ምን አይነት አመለካከት እንዳለው ደግሞ ግልፅ ነው፡፡ ህዝብ ይወክለኛል ብሎ የማያምነው ፓርላማ ነው፡፡ ለህዝብ ጥያቄ ሳይሆን የገዥውን ፓርቲ ትዕዛዝ በተዋረድ የሚያስፈፅም፣ እጅ እንኳን ሲያወጣ፣ ሲደግፍና ድምፀ ታዕቅቦ ነኝ ሲል በትዕዛዝ ነው፡፡ ይህን ፓርላማ የህዝብ ወኪል ነው ማለት ቀልድ ነው፡፡

ፓርላማው ይወክለኛል የሚል አካል እንኳን ቢኖር ፓርላማ አወጣው፣ ገዥው ፓርቲ አፀደቀው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገረው የሰላማዊ ትግል አንዱ መርህ ተገቢነት የለውም ብሎ ላመነው የአምባገነን ህግ አለመገዛት ነው፡፡ መቃወም የሚቻለው ደግሞ ተግባሩን በመቃወም ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ሰንደቁ ላይ የተለጠፈውን ኮከብ ምልክት ባለመቀበል፣ ወይንም ንፁሁን ሰንደቅ አላማ መጠቀም!

በሌላ በኩል በቅርብ አመታት ሰንደቅ አላማው ላይ የተለጠፈውን ምልክት ከሰይጣን አምላኪዎች ጋር አገናኝተው አይወክለንም የሚሉት ኢትዮጵያውያን እየተበራከቱ ነው፡፡ የእነዚህ ግለሰቦች ትንታኔ ለእውነታ የቀረበም ነው፡፡ ይህ የአብዛኛዎቹም ኢትዮጵያውያን እምነት የሚቃረን እና የተጠላ (የ666 ምልክት የሚባለው) ሰንደቁ ላይ ተቀምጦ ኢትዮጵያውያን ለሰንደቁ ክብር ይሰጣሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ በመሆኑም ኮከቡ የባዕድ አምልኮ ምልክት ነውና ይነሳልን ብለው የሚቃወሙት ምክንያታዊ ናቸው፡፡ እንደ ትንታኔያቸው መቃወም ግዴታቸውም ነው፡፡

በተለይ በቅርቡ ስርዓቱ የሰንደቅ አላማ በዓልን ያከብራል፡፡ ሰንደቁ ላይ የተለጠፈውን ምልክት አንቀበልም የሚሉ አካላትም በየራሳቸው መንገድ ምልክቱን አንቀበልም ብለው ለመዝመት ጊዜ አሁን ይመስለኛል፡፡ በየራሳቸው መንገድ!

የአምባገንንን ህግ መቃወም አፀፋ እንደሚያስከትል እሙን ነው፡፡ ይህን አፀፋ ለመቀነስ ትልቁ አማራጭ በጋራ፣ በዘመቻ፣ በአንድነት የአምባገነንን ህግ መቃወም ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የመስቀል በዓል እለት አንድ ወጣት ኮከቡ የተለጠፈበትን ሰንደቅ አላማ በራሱ መንገድ ተቃውሟል፡፡ ይህ ወጣት ያመነበትንና ምክንያታዊ ነው ያለውን ግን አድርጓል፡፡ ወጣቱ ከስርዓቱ ቅጣት ሊገጥመው ይችላል፡፡ በተግባር የተቃወመው ብቻውን በመሆኑ ቅጣቱም ሊበረታበትም ይችላል፡፡ በጋራና በተጠናከረ መንገድ ከሆነ ግን ስርዓቱ እርምጃም ለመውሰድ ይቸገራል፡፡ እርምጃ እንኳን ቢወስድ ሌላ ብሶት ይፈጥራል፣ ለተጠናከረ ትግልም መንገድ ይከፍታል፡፡ በተቀናጀ መንገድ የሚደረገው ተቃውሞም ህዝብ በስፋት የእንቅስቃሴው አካል እንዲሆንና መረጃውም እንዲደርሰው ማድረግ ይቻላል!

Monday, September 28, 2015

በሳዑዲው አሰቃቂ አደጋ የአገሪቱ ባለሥልጣናት እየተወዛገቡ ነው








131 ዜጎቿን ያጣችው ኢራን፤ ሳኡዲ አረቢያን ተጠያቂ አድርጋለች
እስካሁን በአደጋው 717 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል

በሳዑዲ አረቢያ በሀጂ ስነስርዓት ላይ ከትናንት በስቲያ 717 ሰዎች በሞቱበት አደጋ የአገሪቱ ባለስልጣናት እየተወዛገቡ ሲሆን፤ የኢራን መንግስት 131 ዜጐቹ መሞታቸውን በመግለጽ የሳዑዲን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል፡፡
ከመካ በ5 ኪ.ሜትር ርቀት በሚገኘው ሚና የሚባል አካባቢ፣ በሰይጣን ላይ ድንጋይ የመወርወር ሃይማኖታዊ ስነ ስርአት ላይ በተፈጠረ ግርግር ነው አደጋው የተከሰተው ተብሏል፡፡ የብዙዎችን ህይወት በቀጠፈው አደጋ፤ 863 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ለሃጂ ስነስርዓት በሄዱ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰ አደጋ ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም፡፡
የኢራን መንግስት መሪ አያቶላ ሆሚኒ፤ አደጋው የተፈጠረው በሳዑዲ መንግስት ዝርክርክ አሰራር ነው፤ ለአደጋው ሙሉ ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡
የሳኡዲ የጤና ሚኒስትር ካሊድ አል-ፍሌህ በዚህ አይስማሙም፡፡ አደጋው የተከሰተው በምዕመናን ጥፋት ነው ብለዋል፡፡ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መንሱር አልቱርኪ፤ ተመሳሳይ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡ ብዙ ምዕመናን፤ በተመሳሳይ ሰአት በጠባብ መተላለፊያ ላይ የፈጠሩት ግርግር የአደጋው መንስኤ ነው ብለዋል – ቃል አቀባዩ፡፡
የሀጂ ኮሚቴ ሊቀመንበር ልዑል መሃመድ ቢን ናይፍ በበኩላቸው፤ የአደጋው መንስኤ በአስቸኳይ ተጣርቶ እንዲቀርብላቸው ትዕዛዝ የሰጡ ሲሆን፣ የሀገሪቱ ንጉስ ሰልማን ግን የሀጂ ጉዳይ ድርጅቱ እንደገና እንዲዋቀር አዘዋል፡፡
በአደጋው ከሞቱት መካከል፣ 131 የኢራን፣ 14 የህንድ፣ 18 የቱርክ፣ 7 የፓኪስታን፤ 3 የአልጄሪያ እና 3 የኢንዶኔዢያ ዜጎችን ጨምሮ፣ ቁጥራቸው ያልተጠቀሰ የናይጄሪያ፣ ኒጀር፣ ቻድ፣ እና ሴኔጋል ዜጎች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል ተብሏል፡፡
በሳኡዲ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈ አደጋ በአንድ ወር ውስጥ ሲያጋጥም ያሁኑ ሁለተኛው ነው፡፡ ከቀናት በፊት በመካ ታላቁ መስጊድ ላይ፤ የግንባታ ክሬን ወድቆ፣ 109 ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል፡፡
ከትናንት በስቲያ ያጋጠመው አደጋ ከተሰማ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን እና የካቶሊክ ፓፓስ ፍራንሲስ የሀዘን መልዕክታቸው ካስተላለፉት ቀዳሚዎቹ ሆነዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ1990 ካጋጠመውና 1426 ሰዎችን ለህልፈት ከዳረገው ተመሳሳይ አደጋ ቀጥሎ የሰሞኑ የበርካታ ምዕመን ህይወት የተቀጠፈበት አደጋ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በሰበታ አይነውር ተማሪዎች በፓሊስ ተደበደቡ


 sebeta 1
ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2008 ዓም ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች በባንሳታቸው በፓሊሶች ክፉና የተደበደቡ ሲሆን የተማሪዎችን ተወካዮች ጨምሮ 17 ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች ተይዘው ታስረዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ሌኢሳት እንደገለጹት ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል በአንድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው ኮሌጅ በመስጠቱ ተማሪዎች እንዲመለስላቸው ሲጠይቁ ይፌደራል ፓሊስ በፍጥነት ገብቶ አይነስውራን ተማሪዎች ደብድባል ።
ተማሪዎቹ የመኝታ ክፍሉ እንዲመልስላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቢቆዩም መለስ በማጣታቸው የትምህርት ማቆም አድማ አድርገዋል።  ፓሊሶች ተማሪዎቹ ከመኝታ ክፍላቸው እንዲወጡ ትእዛዝ  ቢሰጡም ተማሪዎቹ ግን ፈቃደኛ አልሆኑም። ፓሊሶች ወደ ክፍል እየገቡ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ተማሪዎች ከባድ ድብደባ የፈፀሙ ሲሆን ብዙዎቹ እጆቻቸውና እግሮቻቸው በድብደባ ብዛት ተጎድቷል ። አንድ ተማሪ እሩጠን ለማምለጥ በማንችልበት ሁኔታ ፓሊስ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዶብናል ብሎአል ። 17  የታሰሩት  አይነስውራን ተማሪዎች እስካሁን አልተፈቱም ትምህርት አልተጀመረም።
የፌደራል ፓሊስ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።
Source/ESAT

ሑመራ የገበያ ማእከሏ በእሳት ጋየ








አምዶም ገብረሥላሴ እንደዘገበው

ሑመራ ከተማ የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነው የገበያ ማእከል በእሳት ቃጠሎ ሙሉ ወድሟል።

ቃጠለው ሓሙስ 13/ 01 / 2008 ዓ/ም ሌሊት ያጋጠመ ሲሆን የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነ ከ50 ሚልዮን ብር በላይ ንብረት በቃጠለው መውደሙ ታውቋል።
ህብረተሰቡ ቃጠለው ለማጥፋት የተቻለው ቢጥርም ሊሳካ እንዳልቻለ ኑዋሪዋሪዎች ገልፀዋል።

ከሁሉም በላይ ሒመራን የምታክል ትልቅ ከተማ የእሳት ማጥፍያ መኪና መንግስት ባለማዘጋጀቱ ቅሬታቸው ኣሰምተዋል።
የቃጠለው መነሻ እስካሁን ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ የለም።

መንግስት ለተለያዩ ምክንያት መሬቱ ሲፈልገው እሳት የማስገባት ልምድ እንዳለው ይታወቃል። ለምሳሌ በመቐለ ኢንዳስትሪ ቀበሌ በተነሳው ቃጠሎ ሱቃቸው የወደመባቸው ሰዎች መልሰው ለመገንባት ሲሞክሩ መንግስት ቦታው ለሌላ ስራ ስለፈለገው መስራት ኣትችሉም ተብለው ተከልክለዋል።

ሑመራ እነሞላ ኣስገዶም የገቡበት መንገድ ስለሆነ የጣሉት ወይም የተንጠባጠበ ቢሆንስ ማን ያውቃል።

ንብረታቸው ቃጠሎ ያወደመባቸው ዜጎቻችን ፅናት እንመኝላቸዋለን።
ህዝባችን በስንት ይቃጠል ባካቹ…?
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

ግብጽ የአባይን ግድብ ለመቆጣጠር በ43 ሚልዩን ዶላር ሳታላይት አምጥቃለች

ግብጽ ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ የምትገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የሚቆጣጠር ሳታላይት ካመነጨች ረዘም ያለ ግዜ ተቆጥሯል፡፡ የኦን ላይን ጋዜጣ የሆነው ናይል አሃራም የግብጽን የስፔስ ሳይንስና የብሄራዊ ደህንነት ምክትል ፕሬዘዳንት የሆኑትን አላኤል ዲን አልናሃሪን በመጥቀስ ባወጣው ዘገባው የሳታላይቱ ዋነኛ ስራ ግንባታውን የተመለከቱ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን በምስል የተደገፉ ማስረጃዎችን ማቅረብ ነው፡፡ ግብጽ ከሩሲያ እንደሸመተችው ለተነገረለት EGYSAT 43 ሚልዩን ዶላር ወጪ አድርጋለች፡፡ሳታላይቱ የኢትዮጵያን ግድብ ከመቆጣጠር በተጨማሪ ተመሳሳይ ፕሮጀክት የተቀረጸለትን የኮንጎውን የናይል ወንዝም እንደሚቆጣጠር ተነግሮለታል፡፡ በሳታላይቱ አማካኝነት ግብጽ ማናቸውንም አይነት ጥቅሟን የተመለከተ ነገር ሲፈጸም ካገኘችም መረጃዋን በማጠናቀር ወደ ክስ ልታመራበት ትችላለች ተብሏል፡፡ ግብጽ አባይ ላይ እየተሰራ የሚገኘውን ግድብ ለመቆጣጠር በማሰብ ሳታላይት ማምጠቋን የዘገቡት የአገሪቱ ጋዜጦች ብቻ አይደሉም፡፡ሳታላይቱን የሸጠችው ሩሲያም በሚዲያዎቿ አማካኝነት ነገሩን ይፋ አድርጋለች፡፡ታስ የተሰኘ የሩሲያ ድረ ገጽ ባወጣው ዘገባ ሩሲያ ያመረተችውና ሶዩዝ ሮኬት ሳታላይቷን ጭኖ መጥቋል ብሏል፡፡ 1.050 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሳታላይቱ ዋነኛ ተልእኮው ምድር ላይ አሰሳ ማድረግ ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ሪዞሊሽን የተገጠመለት በመሆኑ ከሳታላይቱ የሚገኙት የምስልና ተንቀሳቃሽ መረጃዎች ያለ ችግር ሁኔታዎችን ለመለየት የሚያስችሉ ይሆናሉ፡፡ለእርሻ፣ለአካባቢ ሳይንስና ለከርሰ ምድር ጥናት ታስቦ ሳታላይቱ መገንባቱንም ታስ ጨምሮ ዘግቧል፡፡ እንደ ታስ ዘገባ ከሆነም ሳታላይቱ የተገነባው ለ11 ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ ነው፡፡በኢትዮጵያ በኩል በዋናነት የግድቡን ሂደት እንዲቆጣጠር ግብጽ ባመጠቀችው ሳታላይት ዙሪያ የተሰጠ በጎም ይሁን ተቃራኒ አስተያየት አልተመዘገበም፡፡የስፔስ ሳይንስ አስገራሚ በሆኑ ግኝቶችና ታሪኮች የተሞላ ስለመሆኑ የሚናገሩ የዘርፉ ባለሞያዎች ግብጽ ሳታላይቱን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ ስለላዎችን ልታደርግም ትችላለች ይህም በግድቡ ዙሪያ የበላይነት እንዲኖራት ሊያደርግ ይችላል ይላሉ፡፡ የግብጽ መንግስት ለዚሁ አገልግሎት ባመጠቀው ሳታላይት አማካኝነት የግድቡን ግንባታ በቅርበት እየተከታተለ ለመሆኑ በቅርቡ የወጣ መረጃ በእማኝነት ሊቀርብ ይችላል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት የግብጽ ጋዜጦች በካይሮና ጊዛ በተባሉ አካባቢዎች የተፈጠረን የውሃ እጥረት ከግድቡ በውሃ መሞላት መጀመር ጋር በማያያዝ ዘግበው የነበረ ቢሆንም የግብጽ የአፈር ጥበቃ ሚኒስትር ሆሳም ሞግሃዚ በመስከረም ወር አጋማሽ የተወሰደን የሳታላይት የምስል ማስረጃን በመጥቀስ የጋዜጦቹ ዘገባ ስህተት መሆኑን አስምረውበታል፡፡ የግድቡ ግንባታ ለግብጽ መንግስት ከፍተኛና ቅድሚያ የሚቸረው ጉዳይ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡የፕሮጀክቱ እቅድ ይፋ ከተደረገበት ወቅት አንስቶም ወደ አስዋን ግድብና ወደ አገሯ የሚገባው የውሃ መጠን እንዳይቀንስ ስትከራከር መቆየቷም ለዚህ ማሳያ ይሆናል፡፡ ግብጽ፣ሱዳንና ኢትዮጵያ በመስማማት አለም አቀፍ አማካሪ ቡድኖችን በመቅጠር በግድቡ ዙሪያ ጥናት እንዲያቀርቡ ቢያዙም ዴልታርስ የተሰኘው የሆላንድ ድርጅት በቂ የሆነ የስራ ዋስትና አልተሰጠኝም በማለት ራሱን ማግለሉ አይዘነጋም፡፡


Friday, September 25, 2015

የ21 ሴቶችን ሀፍረተ ስጋ በመቁረጥ ፍሪጂ ውስጥ ያስቀመጠው ዴንማርካዊ ተያዘ

የሚያሳዝን፣ የሚያስቅም ዜና
ዴንማርካዊው የ 63 አመት አዛውንት የ21 ሴቶችን ሀፍረተ ስጋ በመቁረጥ ፍሪጂ ውስጥ አስቀምጦ ተያዘ፣ ፒተር: ፍሬድሬክሰን የሚባለው አረመኔ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው የደቡብ አፍሪካዊት ሚስቱን በጭካኔ ብልቷን ከቆረጠ በኋላ ነው ይላል የተያያዘው ዜና። እዚህች ሰው ጎማ አሸክማ በምታቃጥለው ደቡብ አፍሪካ እኮ ነው ይህ የሚፈፀመው። የሆነውስ ሆኖ
ፍሪጂ ውስጥ ማከማቸቱ ለምን ይሆን?
እስቲ ፈገግ ላስብላችሁ
ይህች ጉዳይ ኢትዮጵያ ብትሆን መቼም ኀውልት ይገነባ ነበር ከላዩ ላይ ነገርዮዋ ተቀምጣ አይመስላችሁም? መቼም ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መብት አይጠየቅ እንጂ ለሴት የሰውነት ክፍል ሀውልት መስራት በአለም ተወዳዳሪ የላትም።
ቱፍ ፣ ውኀ ለልማቱ አሉ አቡዮ ምንተስኖት
ሰይጣን ሰለጠነ ንስሀ እንግባ ወገኖቼ።
ጨረስኩ
ልያ ፋንታ/ፌስቡክ/
ከዋሽንግተን ፣


Pope Francis assures atheists: You don’t have to believe in God to go to heaven

 የሮማው ፖፖ ፍራንሲስ" ወደ ገነት ለመግባት እግዚአብሔርን ማመን አይጠበቅብንም " ብለውት አረፉ



In comments likely to enhance his progressive reputation, Pope Francis has written a long, open letter to the founder of La Repubblica newspaper, Eugenio Scalfari, stating that non-believers would be forgiven by God if they followed their consciences.
Responding to a list of questions published in the paper by Mr Scalfari, who is not a Roman Catholic, Francis wrote: “You ask me if the God of the Christians forgives those who don’t believe and who don’t seek the faith. I start by saying – and this is the fundamental thing – that God’s mercy has no limits if you go to him with a sincere and contrite heart. The issue for those who do not believe in God is to obey their conscience.
“Sin, even for those who have no faith, exists when people disobey their conscience.”

 Robert Mickens, the Vatican correspondent for the Catholicjournal The Tablet, said the pontiff’s comments were further evidence of his attempts to shake off the Catholic Church’s fusty image, reinforced by his extremely conservative predecessor Benedict XVI. “Francis is a still a conservative,” said Mr Mickens. “But what this is all about is him seeking to have a more meaningful dialogue with the world.”

In a welcoming response to the letter, Mr Scalfari said the Pope’s comments were “further evidence of his ability and desire to overcome barriers in dialogue with all”.
In July, Francis signalled a more progressive attitude on sexuality, asking: “If someone is gay and is looking for the Lord, who am I to judge him?”

http://www.independent.co.uk/news/world/europe/pope-francis-assures-atheists-you-dont-have-to-believe-in-god-to-go-to-heaven-8810062.html

ታዋቂው ዶ/ር ሽመልስ ተክለጻዲቅ መኩሪያ አረፉ

ዶ/ር ሽመልስ ተክለጻዲቅ መኩሪያ አረፉ
መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ሽመልስ ከሌሎች ታዋቂ ምሁራንና ፖለቲከኞች ጋር በመሆን ቀስተደመናን ፓርቲ፣ ከዚያም ቅንጅት እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቅንጅት መሪዎች በታሰሩበት ወቅትም ዶ/ር ሽመልስ፣ ትግሉ እንዳይቀዛቀዝ ከፍተኛ ስራ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አንድነት ፓርቲ በተመሰረተበት ወቅትም ፓርቲውን በአመራር አባልነት አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የተቋቋመውና በሁዋላ በስርዓቱ ሃላፊዎች እንዲፈርስ የተደረገውን አዲስ ብሮድካስቲንግ ኩባንያ ከሌሎች ምሁራንና ባላሀብቶች ጋር በመሆን መስርተዋል። ዶ/ር ሽመልስ የታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ የተክለጻዲቅ መኩሪያ ልጅ ነበሩ።

የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማስረጃ (TVET) እንደ ትምህርት ማስረጃ እንደማይቀበለው ገለጸ

የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማስረጃ (TVET) እንደ ትምህርት ማስረጃ እንደማይቀበለው ገለጸ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

ኤምባሲው የ2015 የዲቪ ሎተሪ የመጨረሻ ቀን ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም. መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ የትምህርት ማስረጃን እንደሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃነት ከዚህ ቀደም ሲቀበል መቆየቱን በማስታወስ ከአሁን በኃላ የማይቀበል መሆኑን አስታውቆአል፡፡ ኤምባሲው ይህን ለምን እንዳደረገ በመግለጫው የጠቀሰው ነገር ባይኖርም የኤምባሲው ምንጮች እንደጠቆሙት የአሜሪካ መንግስት የትምህርት መስፈርት ለውጥ ሊያደርግ የተገደደው በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ የአሜሪካንን ስታንዳርድ የሚጠብቅ ባለመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በቴክኒክና ሙያ የሰለጠኑ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የ2015 የዲቪ ዕድለኞች ወደአሜሪካ መግባት አይችሉም፡፡ 

ኤምባሲው በዚሁ መግለጫው የ2015 የዲቪ ሎተሪ ሒደት ማከናወኛ ጊዜ የፊታችን መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅጠቁሞ ፣ ዕድኞች እስከ አሁን ድረስ ከአሜሪካን ኤምባሲ ጥሪ ካልደረሳቸው ለ2015 የዲቪ ሎተሪ አለመመረጣቸውን እንዲያውቁ ብሎአል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2008 ድረስም ኤምባሲዉ ምንም አይነት አዲስ ጥሪ እንደማያካሂድም አስታውቆአል፡፡ በሚመጡት ጥቂት ቀናት ዉስጥ ቀጠሮ የተሰጣቸው ዕድለኞች የትምህርት መስፈርት ለዉጥ እንዳለ እንዲያውቁና በሥራ ልምድ መወዳደር ከፈለጉ አመልካቾች ለዲቪ ሎተሪ ፕሮግራም ማመልከቻ ብቁ የሚያደርጉትን የሥራ ልምዶች ከነዝርዝር መረጃዎቻቸዉ በኤምባሲዉ ድረ-ገፅ ላይ አስቀድመዉ እንዲመለከቱም አሳስቦአል፡፡ የ2017 የዲቪ ሎተሪ ምዝገባን የተመለከተ መረጃ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንም ኤምባሲው አስታውቆአል፡፡ በዲቪ 2015 ወደ 4ሺህ 988 ያህል ኢትዮጵያዊያንን እጣው ወጥቶላቸዋል።
DV Lottery help

ፓስተሩ በሽብርተኝነት ተከሰሱ





በናይሮቢ ኬንያ በምግብ ደህንነት ዙሪያ ወርክ ሾፕ ለመካፈል የተገኙ ስድስት አለም አቀፍ የልማት ተቋማትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ ያሰራቸውንና በሽብርተኝነት የከሰሳቸውን የአለም ባንክ አስተርጓሚና ሁለት ጓደኞቻቸውን በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡ ፓስተር ኦሞት አግዋ ከስድስት ወራት በፊት ተይዘው በቅርቡ በሽብርተኝነት መከሰሳቸው አይዘነጋም፡፡ ኦሞት አገዋ፣አሽኒ አስቲንና ጀማል ኦመር ሆጀሌ የታሰሩት በማርች 2015 በምግብ ደህንነት ዙሪያ የአለም አቀፍ ተቋማትና አንድ አገር በቀል ድርጅት ባዘጋጁት ሰሚናር ለመካፈል ወደ ናይሮቢ ለማምራት በተዘጋጁበት ወቅት ነበር፡፡አቃቤ ህግ በክሱ ሰሚናሩን ‹‹የሽብር ተግባር ለመፈጸም የታሰበ››ማለቱም ታውቋል፡፡

ከኦሞት ጋር ታስረው የነበሩት ጓዶቻቸው በኤፕሪልና ጁን ወሮች ያለምንም ዋስ በነጻ መለቀቃቸው ተዘግቧል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ በምግብ ደህንነቷና በምግብ ራስን መቻል ችግሮቿ ዙሪያ ውይይቶች እንዲደረጉ መፍቀድ አለባት የሚሉት የብሪድ ፎር ኦል የበጎ አድራጎት ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ሚገስ ባውማን ‹‹በአለም አቀፍ ደረጃ ክብር የተቸራቸው ድርጅቶች ባዘጋጁት ሰሚናር ሊካፈሉ የነበሩ ሰዎችን በሽብርተኝነት መወንጀል ተቀባይነት የለውም››ብለዋል፡፡ ኦሞት በጋምቤላ የወንጌላዊት መካነ ኢየሱሰ ቤተክርስቲያንን በመጋቢነት(ፓስተርነት)ሲያገለግሉ ከመቆየታቸውም በላይ በ2014 ከአለም ባንክ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በአኙዋክ ማህበረሰብ ስለደረሰ መፈናቀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ጥናት ለማድረግ በአካባቢው ለተገኙ የአለም ባንክ የምርመራ ቡድን አስተርጓሚ በመሆን አገልግለዋል፡፡ኦሞት ለእስር ከመዳረጋቸው ቀደም ብሎም ከትርጉም ስራቸው ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ መንግስት ደህንነቶች ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች እየደረሰባቸው መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡

dawit solomon

የአራት ሴቶች ‹‹ባል›› የሆነችውን ‹‹ሴት›› ተዋወቋት









የአራት ሴቶች ‹‹ባል›› የሆነችውን ‹‹ሴት›› ተዋወቋት 
  በኬንያ እንግዳና በጣም አስገራሚ የሆኑ የጋብቻ ልምምዶችን በአገሪቱ ማህበረሰቦች መካከል ሲከናወኑ ታገኛላችሁ፡፡በእነዚህ ያልተለመዱ የጋብቻ ልምምዶች መንስኤነትም ብዙዎች ከውሃ አጣጪዎቻቸው ለመለያየት መብቃታቸውን ትረዳላችሁ፡፡ ለምሳሌ ስቴሲ የተባለችን አንዲት ሴት እንውሰድ ከባሏ ጋር ጋብቻ ከመሰረቱ ስምንት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ነገር ግን የባሏን ቤተሰቦች መጎብኘት የቻለችው ለስድስት ግዜያት ብቻ ነው፡፡ምክንያቱን ስታብራራም ‹‹ባህላቸውን እጠላዋለሁ፣እርሱ ከምዕራብ ነው፣እነርሱ አላስፈላጊ የሆኑና እንግዳ የሆኑ ልምምዶች አሏቸው፡፡

የእርሱ ሰዎች ወደቤታቸው እንዳልገባ አግደውኛል ምክንያቱም የሁለተኛ ልጃችንን የመጀመሪያ ጸጉር ማስላጨት ግዴታ እንዳለብኝ በመናገራቸውና እኔ ስላልተቀበልኳቸው ነው››ብላለች፡፡ ሴት ለሴት ጋብቻ ብዛት ያላቸው መሐን የኬንያ ሴቶች በትዳር አጋሮቻቸው ለእንዲህ አይነት ጋብቻ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡ሴት ባሎች ለትዳር ለሚመርጧት ሴት ቤተሰብ ጥሎሽ ይሰጣሉ እናም በቁጥጥራቸው ስር ያደርጓቸዋል፣አንዳንድ ግዜም በድብቅ ሚስቶቻቸው ልጅ እንዲወልዱላቸው የወንድ ዘር የሚሰጧቸውን ወንዶች ይቀጥሩላቸዋል ወይም ያመጡላቸዋል፡፡ የሴት ባሏም ሚስቷ ልጅ ስትወልድ ህጋዊና በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያላት ‹‹አባት›› ተደርጋ ትወሰዳለች፡፡እንዲህ አይነት ጋብቻ በካፕሱንዲ ፣ኡሲን ጊሹ ካውንቲዎች የተለመደ ነው፡፡በአካባቢው የምትኖር አንዲት ሴት ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ አራት ሴቶችን አግብታለች፡፡ ከወንድ ጋ ያልተሳካ ጋብቻ  አሁን ኤልሳቤጥ ቼማሱንዴ የ92 ዓመት አሮጊት ናቸው፡፡በናሮክ ካውንቲ ትዳር መስርተው ይኖሩ ነበር፡፡ነገር ግን ለአስር አመታት የዘለቀው ትዳር ልጅ አላፈራም፡፡በዚህ ምክንያትም ከማህበረሰቡ የሚደርስባቸውን ነቀፋ መሸከም ባለመቻላቸው ወደ ናንዲ ካውንቲ ተሰደዱ፡፡ 

በናንዲ ማህበረሰብ ዘንድ መሀን ሴቶች የጾታ ተመሳሳያቸውን እንዲያገቡና ልጅ እንዲያገኙ የሚፈቀድ በመሆኑም ኤልሳቤጥ ይግረማችሁ ብለው አራት ሴቶችን አገቡ፡፡አናዳጁ ነገር ቼማሱንዴ ካገቧቸው አራት ሴቶች መካከል ሁለቱን ወንዶች የነጠቋቸው መሆኑ ነው፡፡ ለመጀመሪያዋ ሚስታቸው ጥሎሽ ስድስት ላሞችና አራት ፍየሎችን ጥለው የነበሩት ኤልሳቤጥ ከትዳራቸው አንድ ወንድና ሴት ተበርክቶላቸዋል፡፡የልጆቻቸው እናት ግን በአሁኑ ወቅት አብራቸው አትኖርም፡፡ከሁለተኛ ትዳራቸውም ሁለት ወንዶችና ሴቶችን ብያገኙም አብራ ለመዝለቅ አልፈቀደችም፡፡ሴቶቹ የወንድ ዘራቸውን የለገሷቸውን እውነተኞቹን የልጆቻቸውን አባቶች ተከትለው መሄዳቸው ደግሞ አሮጌቷን ባል ያበሳጫቸዋል፡፡
Dawit selomon
https://thevoiceofunity.wordpress.com/2015/09/25

Wednesday, September 23, 2015

ዲያስፖራው ተቃውሞውን ይበልጥ ወደ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ያሳድግ ዘንድ የቀረበ ታላቅ ሕዝባዊ ጥሪ --ድምፃችን ይሰማ

ዲያስፖራው ተቃውሞውን ይበልጥ ወደ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ያሳድግ ዘንድ የቀረበ ታላቅ ሕዝባዊ ጥሪ! ከተባበርን ብዙ መስራት እንችላለን! ማክሰኞ መስከረም 11/2008
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ስንገልጽ እንደቆየነው የዲያስፖራው ማህበረሰባችን ለትግሉ እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ከትግሉ ጅማሮ አንስቶም ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ይህ ታላቅ ድጋፍ የበለጠ ይጠናከር እና ውጤታማ ይሆን ዘንድ ደግሞ የትግሉን አድማስ በማስፋት የተለያዩ የዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በመስራት ጫናቸውን ማጠናከር አለባቸው፡፡ የዲፕሎማሲያዊ ስራዎች በአጠቃላይ የትግላችንን ምንነትና ሂደቱን በምንኖርባቸው አካባቢ ለሚገኙ የተለያዩ የውጭ መንግስታት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች ማስገንዘብን ያካትታል፡፡ ከማስገንዘብ ባሻገርም እነዚህ አካላት የበኩላቸውን ጫና እንዲፈጥሩ ማድረግ ይቻላል፡፡ ዲያስፖራው ማህበረሰብ አካባቢያዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች እስከፈቀዱለት ድረስ የሚከተሉትን ተግባራት በመፈጸም ትግሉን ይበልጥ ይደግፍ ዘንድ አደራ ለማለት እንወዳለን፡-
1/ ግልፅ ደብዳቤዎችን በሚኖሩባቸው አገራት ለሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የፓርላማ ወይም የምክር ቤት አባላት መፃፍ፤ ቀጠሮዎችን በማስያዝ ተደጋጋሚ ስብሰባዎችን ከእነዚህ ኣካላት ጋር ማድረግ፤
2/ በየአገራቱ ከሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ጋር ግንኙነት መፍጠር፤ በተለይም በኢትዮጵያና በአፍሪካ ጉዳይ ላይ የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን ስልክ በመደወል፣ ኢሜልና ትዊት በማድረግ፣ ቀጠሮ በመያዝና ኢንተርቪው በመስጠት፣ እንዲሁም በመሳሰሉ መንገዶች የትግሉን ምንነትና የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለውን የመብት ረገጣ በሚገባ ማሳየት፤
3/ በተለያዩ ቋንቋዎች በሚታተሙ ኘ ጋዜጦች ላይ መጣጥፎችን በአገሪቱ ቋንቋ በመፃፍ መላክና ማሳተም፤
4/ በሚሰግዱበት መስጊድ ለሚገኙ ኢማሞችና ዑለሞች የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሞች ላይ እየፈፀመ ስላለው ብሄራዊ ጭቆና በሰፊው ማስረዳት ፤ ስለሁኔታው በአጭሩ በማብራራት በራሪ ወረቀቶችን ማሳተምና መስጊድ ለሚገባው ሁሉ በማደል መረጃውን የበለጠ ማሰራጨት፤
እነዚህ እንደአብነት የተጠቀሱ ተግባራት እንጂ የዲያስፖራው ማህበረሰብ በየጀመዓውና በየኮሚኒቲው ይህንን የዲፕሎማሲ ስራ እንዴት የበለጠ መስራት እንዳለበት በመወያየት ይበልጥ ማዳበር ይጠበቅበታል፡፡ እኒህ ተግባራት በአላህ ፈቃድ ውጤት ሊያስገኙ የሚችሉ ስራዎች በመሆናቸው የዳያስፖራው ማህበረሰባችን በሙሉ ልብ እና በቁርጠኝነት በስፋት እንዲተገብራቸው በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ስም የትብብር ጥሪያችንን እናቀርባለን!
ብሄራዊ ጭቆናን አንቀበልም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማል! አላሁ አክበር!

ከስህተት ወደ ጥፋት የተሸጋገረው የቋንቋ ግድፈታችን!





ከስህተት ወደ ጥፋት የተሸጋገረው የቋንቋ ግድፈታችን!
(የትነበርክ ታደለ)
ከቅርብ አመታት ወዲህ በሀገሪቱ ውስጥ እየታየ ያለው የቋንቋ ግድፈትና የቋንቋ አጠቃቀም ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ህጻናትን "አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ሁለቱም ወንጀል ናቸው።" ብሎ እስከ ማስተማር የደረሱ ትምህርት ቤቶችን አፈራን። ስህተት ነው ይታረም ስንል ተንጫጫን~ ችግሩ ግን ዛሬም ድረስ ተሸፋፍኖ እንዳለ ነው።


ቀጠለና በየአደባባይ የምንለጥፋቸው የህዝብ ማስታወቂያዎች ላይም ስህተት የማይመስሉና ሆን ተብለው የሚደረጉ እስኪመስሉ ድረስ ቃላት ማጣመምና ፊደላት መግደፍን ስራዬ ብለን ተያያዝነው። ለዚህም የትኛውም የሚመለከተው ክፍል መልስ ሳይሰጥ እኛም በዋዛ ፈዛዛ አለፍነው።

በተለይ ደግሞ ሰሞኑን የኤሌክትሪክ ባቡሩን ስራ መጀመር ተከትሎ ለአካባቢ መለያነት የተለጠፉት ታፔላዎች ፍጹም ወንጀል በሆነ መልኩ በሁሉም አቅጣጫዎች በህዝብ ፊት ተለጣጥፈው እያየን ነው። ለዚህም እስካሁን ሀላፊነት የወሰደ አላየንም።

እነዚህን እንደ ተራ ስህተት ብንወስዳቸውም ከጅምሩም እንዳይፈጠሩ ብቃት ባላቸው ሰዎች ማሰራት ይቻል ነበር።

ከሁሉ በላይ የሚያሳስበው ግን ለዘመናት ራሱን ችሎ ለብዙ አዳዲስ ጽንሰ ሀሳቦችም ሆነ ቁስ አካል ሁነቶች ስያሜ ሲወልድ የኖረን ቋንቋ በፍጹም ሊወከል በማይገባው በባእዳን ቋንቋ ሲተካ ማየት ከግርምትም በላይ እጅግ በጣም ይከነክናል።


አሁን "የህዝብ መጓጓዣ" የሚለውን ሀረግ "ፐብሊክ ትራንስፖርት" ብሎ ማለት ምን ማለት ነው? ያውም በቋንቋው ፊደላት። ይህ ምንድነው? ስንፍና? ንቀት? ምን አገባኝ? ምን ታመጣላችሁ? ጥላቻ? ወይስ ምን?

እጅግ በጣም ይገርማል! ይህ ስርአት ራሱን ከሚገልጽበት ዋናው ባህሪ የቋንቋን መብት ማስከበር ነው። ሀገር ወለድ ቋንቋዎች በትምህርትና በጥናት ተደግፈው እንዲያድጉና ተናጋሪዎቹም ያለምንም መሸማቀቅ እንዲገለገሉበት ማስቻል "በትግል አስገኘሁት" የሚለው አንዱ ውጤት ነው።

አማርኛ ቋንቋ ደግሞ የፌደራል የስራ ቋንቋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይበልጥ ጥበቃና ክብካቤ ሊደረግለት የሚገባና ሁላችንም ጥብቅና ልንቆምለት የሚገባ እንጂ እንዲህ መዘባበቻ ሊሆን የሚገባው ቋንቋ አይደለም። በፍጹም!!

እና ምንድነው የምንሰማውና የምናየው ነገር? ለምንድነው ለምንፈጥራቸው ችግሮች ሀላፊነት የማንወስደው? ለምንድነው ያለንን ነገር ለመጣልና ለማስጣል የምንራወጠው? ለምን?

ይህ የፖለቲካ ጥያቄ አይደለም! እንደ ቋንቋ መምህርነቴ ፊደል አስጠንቼ፣ ቃላት አስመስርቼ አረፍተ ነገር ብሎም አንቀጽ ጻፉ ብዬ ያስተማርኳቸው ተማሪዎች እንዲህ ያለ የሁለተኛ ክፍል ተማሪ የማይሰራውን አይነት ስህተት በየጎዳናውና በየአገልግሎት መስጫው ሲገጥማቸው ሳይ እኔ ስለነሱ አዝናለሁ።

ይህ ደግሞ ቀስ በቀስ ሊያመጣ የሚችለውን ሀገራዊ የቋንቋ ግድ የለሽነት መዘንጋት ነው!። ይህ እያወቅን የሰደድነው እሳት ነውና በጊዜ ልናጠፋው ይገባል! በጊዜ! አሁን ነገሩ ከስህተት ወደ ጥፋት አድጓልና! [From Error to Mistake then a crime!]

በመተማ ከተማ “በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች” በሚል የሕወሃት/ብአዴን ታጣቂዎች 2 ነዋሪዎችን ገደሉ፣ ከ50 በላይ አቆሰሉ

በመተማ ከተማ “በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች” በሚል የሕወሃት/ብአዴን ታጣቂዎች 2 ነዋሪዎችን ገደሉ፣ ከ50 በላይ አቆሰሉ
http://www.goolgule.com/2-died-50-wonded-in-mettema-in-con…/
የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ሕወሃት) የፈጠረው የብአዴን ታጣቂዎች በመተማ ከተማ “በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች” በሚል ሁለት ነዋሪዎችን መግደላቸው፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው እንዲሁም ከሃምሳ በላይ ማቁሰላቸው ተሰማ።
የብአዴን አባላት እና መሪዎች የዐማራን ሕዝብ እያሰቃዩ እና እያስፈጁ የሚያካብቱት ማንኛውም ሃብት በክህደትና በግፍ የተሰበሰበ በመሆኑ ለህዝብ የሚያስረክቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም።
ለዚህ የክህደት ተግባራችው ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፣ በባህርዳር እና በጎንደር በሰፊው እየተሳሳቡ አገር እየዘረፋ መሆኑን እያንዳንዷንም ተግባራቸውንም እየተከታተልን ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን።
እነኝህ ስግብግቦች በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት፣ የሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአምሳ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። (ምንጭ፦ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት Dr.Getachew Reda ጠቅሶ መስከረም ፱ ቀን ፪ሺህ፰ ዓም የላከው መረጃ)
*************************
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ

ከዳባት አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ ታቅዶ የነበረው መንገድ በአገዛዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውሳኔ መታጠፉ ተገለፀ፡፡

#‎የአርበኞች_ግንቦት_7_ህዝብ_ግንኙነት‬
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
ከዳባት አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ ታቅዶ የነበረው መንገድ በአገዛዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውሳኔ መታጠፉ ተገለፀ፡፡
የህወሓት አገዛዝ ከዚህ ቀደም መንገዱ የሚገነባበትን አካባቢ ህዝብ ማለትም ከዳባት እስከ ጠገዴ ለሚገኘው ነዋሪ መንገድ ሊገነባለት ዕቅዱ እና በጀቱ አልቆ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገባ ቃል ከመግባት አልፎ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ አድርጎ ነበር፡፡ የይስሙላሁ ጠ/ሚንስትር ኃ/ማሪያም ደሰላኝም በተመሳሳይ ሁኔታ ከአንድ ዓመት በፊት ጎንደር ተገኝቶ "ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ የሚደርስ መንገድ በፌድራል መንግስቱ ወጭ እንገነባለን..." ሲል ቃል ገብቷ፡፡ ነገር ግን ከሰሞኑ ዕቅዱ መሰረዙ ለወረዳው ባለስልጣናት ከፌድራል አገዛዙ ባለስልጣናት በቀጥታ ተገልፆላችዋል፡፡
ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ድረስ ሊሰራ የተከለለው መንገድ ግንባታ ዕቅድ የታጠፈው መንገዱ ጠገዴ ከደረሰ በቀላሉ ከወልቃይት ጋር ይገናኛል በሚል ምክኒያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ የህወሓት አገዛዝ የወልቃይትን ህዝብ ያለፍላጎቱ ከጎንደር ገንጥሎ ከትግራይ ጋር በመቀላቀል በኃይል አፍኖ ረግጦ እየገዛው መሆኑ የሚታወቅ ነው በመሆኑም መከረኛው የወልቃይት ህዝብ ከማንም እንዳይገናኝ ለማድረግ እና ነጥሎ ለማቆየት ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ የታቀደው መንገድ ተሰርዟል፡፡
ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ በዕቅድ ተይዞ የወልቃይትን ህዝብ ለመነጠል ሲባል ብቻ የተሰረዘው መንገድ እንዲገነባ በህዝቡ የተጠየቀው ከ1997 ዓ.ም በፊት ነበር፡፡
የአካባቢው ህዝብ መንገዱ አይሰራም በመባሉ ብቻ ሳይሆን አገዛዙ ዕቅዱን ለመሰረዝ የተነሳሳበት ምክንያት እጅግ በጣም እያበሳጨው እንደሆነ እና ለለውጥ ለመታገል ውስጥ ለውስጥ መደራጀት መጀመሩን የአርበኞች ግንቦት 7ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ ያረጋግጣል፡፡

“የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ በደል እየፈጸመ ነው” ተጓዦች

“የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ በደል እየፈጸመ ነው” ተጓዦች
በአየር መንገዱ የተመደቡ የደኅንነት ሰዎች ግልጽ ጉቦ ይጠይቃሉ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚጓዙ መንገደኞችን በአሮጌው ተርሚናል በኩል በማስተናገድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜጎች በማንነታቸው ተለይተው እየተዋከቡ መሆኑን መንገደኞቹ የደረሰባቸውን በደል ዋቢ በማድረግ ምንጮች ገልጸዋል። በተለይ ከሳውዲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ተጓዦችን በአየር መንገዱ የሚገኙ የደኅንነት ሰዎች ግልጽ ጉቦ እየጠየቁ እንደሆነ ተነገረ፡፡
በተለይ ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚጓዘው ኢትዮጵያውያዊ አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ እንደመሆኑ መጠን ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚደረግባቸው የሚገልጹ እነዚህ ምንጮች ዜጎች በገዛ አገራቸውና አየር መንገዳቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየታችው የመንግስት እጅ እንዳለበት አመላካች መሆኑን ይጠቁማሉ።
በአሮጌው ተርሚናል የሚስተናገድ እነዚህ የአየር መንገዱ ተገልገላይ ኢትዮጵያውያን ደምበኞች ይዘውት በሚወጡትና በሚገቡት እቃዎቻቸው ላይ ያለአግባብ ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል፤ ለቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ስጦታ የሚውል እቃዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ይጣላል፤ የመንገደኛው ሻንጣ ቁልፍ ተሰብሮ ይዘረፋል፤ ሻንጣዎቹ እስክነ አካቴው የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ፣ ወዘተ። ከዚህም ሌላ በዚህ ተርሚናል የሚስተናገዱ ደንበኞች በአየር መንግዱ ሰራተኞች ክብር አይሰጣቸውም መብቱን ለማስከበር “ለምን?” ብሎ የጠየቀ መንገደኛ ይሰደባል፣ ይገለመጣል፣ አልፎ አልፎ በጥፊና በካልቾ የሚሰተናገድበት አሳዛኝ አጋጣሚ እንደሚከሰት የአይን እማኞች ገልፀዋል።
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው እና የከፋው ሳውዲ አረቢያ “መካ” ለሃጅ የፀሎት ሥርዓት በቤተሰብ አጀብ የሚሸኙ የጸሎት ተጓዥ ምእመናን ወደ አሮጌው ተርሚናል ከገቡ በኋላ እንደ ፀሎት ተጓዥ ሳይሆን አንደ አንድ መንገደኛ ማግኘት የሚገባቸውን ክብር አጥተው ስርዓት በሌላቸው አንዳንድ የአየር መንገዱ አስተናጋጆችና የፀጥታ አባላት እንደሚዋከቡ በደሉ የደረሰባቸውን ዜጎች ዋቢ በማድረግ ይገልጻሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሮጌው ተርሚናል እያደረገ ካለው የወረደ መስተንግዶ ይልቅ “ጅዳ” ሳውዲ አረቢያ አየር ማረፊያ በባዕዳኑ የአየር መንገዱ ሰራተኞችና የፀጥታ ሃይሎች የሚደረጉላቸው አቀባበልና መስተንግዶ ምንም እንደማይገናኝ ሰሞኑን ጅዳ ከገቡ ምዕመናን የሃጅ ጸሎት ተጓዥ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ማረጋገጥ ተችሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገዱ መስተንግዶ “አገዛዙ ሃገር ውስጥ በጋራ እና በተናጠል ህዝበ ሙስሊሙ ተቋም ላይ ከሚፈጽመው በደል አይለይም” የሚሉ አንዳንድ ወገኖች፤ በአሮጌው ተርሚናል በኩል የሚያልፍ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም እንደ ዜጋ ቀርቶ አንድ ቆዳው ነጣ ያለ መንገደኛ የሚሰጠውን ክብር ያህል ቦታ የለንም ይላሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገዱ መስተንግዶ በኢትዮጵያዊን ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ብቻ ያነጣጠር ይሁን እስካሁን ማረጋገጫ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም “ከተልባ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” እንዲሉ በኮንተራት ስራም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተጠቀሱት ሃገርት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ በደሉ እየተፈፀመባቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የሃገሪቱን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ አርማው በማድረግ ከግማሽ መዕተ አመት በላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ይህ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሆነው አየር መንገድ በገዥው ፓርቲ ህ.ወ.ሃ.ት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርአት ካድሬዎች እጅ ከወደቀ ወዲህ ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ የዜግነት ክብራቸውን የሚያጡበት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገዱ ሰራተኞች ጭምር በብሄር ማንነታቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው እየተለዩ ግፍና በደል የሚፈፀምባቸው ማዕከል እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል።
የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት የዜጎችን ከሃገር ወደ ሃገር የመዘዋወር ህገመንግስታዊ መብት በመጣስ ከሳውዲ አረቢያ ቤተዘመድ ጥየቃ ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎች የዕረፍት ግዜያቸውን ጨርሰው ሲመለሱ የሚኖሩበትን ሃገር የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ “ኢቃማ” ካላመጣችሁ አታልፉም በሚል ምክንያት በአየር መንግዱ ውስጥ በተሰገሰጉ የፀጥታ ሃይሎች እስከ 10 ሺህ ሪያል የሚደርስ ጉቦ በግልጽ እንደሚጠየቁ ለመረዳት ተችሏል።
በሳውዲ አረቢያ ህግ ማንኛውም የውጭ ሃገር ዜጋ ፓስፖርቱን ከአሰሪው እጅ ሲቀበል የመኖሪያ ፈቃዱን ለአሰሪው ማስረከብ እንደሚገባ ይደነግጋል። (Ethiopian Hagere Jed Bewadi ለጎልጉል የላኩት)
**********************
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

የመንግስትን ቀጣይ እቅድ አስመልክቶ ለውውይት የተጠራው የአዲስ አበባ ህዝብ “ያልተጠበቁ” ጥያቄዎችን አነሳ

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የኢህዴግ ድርጅት ጽ/ቤት ፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ ዙሪያ በከተማው 10 ክ/ከተሞች በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎችን በሚያወያይበት መድረክ ፣ ነዋሪዎች አወያይ ካድሬዎችን ያስደነገጡ ጥያቄዎችን አንስተዋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር የሚገኙ የ10 ወረዳዎችን የህብረተሰብ ክፍል በያዘው የወረዳ 9 አዳራሽ በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ስብሰባውን የተካፈሉ ዜጎች ለኢሳት ገልጸዋል። በእለቱ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል ግንቦት7ትን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቧል። ጠያቂዎች " የእውነት ለለውጥ ከሆነ የምታስቡት ግንቦት 7 የሚባል ጠንካራ የምሁራን ስብስብ ያሉበት ድርጅት እንዳለ እየሰማን ነው፤ ይህን ድርጅት አሸባሪ እያላችሁ በድርጅቱ ሰበብ ወጣቱ እንዲታሰርና ምሁራን ከሃገር እንዲሰደድ ምክንያት ሆናችኋል፣ ዕቅዱ እንዲሳካ ከተፈለገ፣ለውጥ እንዲመጣም ከተፈለገ ዕርቀ ሠላም መምጣት አለበት አለዚያ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደማይመጣ ከሁኔታዎች መረዳት እየተቻለ ነው" የሚል ይገኝበታል። እንዲሁም " ድርጅታችን የምትሉት የውሸት ነው፤ ድርጅታችሁ ገምቷል፣ ድርጅታችሁ ሸቷል፣ በአሁኑ ወቅት የ17 ብር ሽንኩርት ለአንድ ጊዜ ወጥ አይበቃም፣ ኑሮው ተወዷል፣የኮንዶሚኒየም ቤት የምትሉትንም በኑሮ ውድነት መክፈል አቅቶን አቋርጠናል እናንተ ግን ልማት ልማት ትላላችሁ፤ ህዝብ ጠግቧል፣ኢኮኖሚ አድጓል ትላላችሁ፣ ለምን ዝቅ ብላችሁ ወደ ታች አታዩም! ፤ መንገድ ሰርታችኋል ትክክል ነው! ባቡር ተጀምሯል ትክክል ነው! ነገር ግን በዚህ ልማት ሰበብ በዲዛይንና በመንገዱ አቅጣጫ እቅድ ችግር ብዙ ዜጎች ቦታቸውንና ቤታቸውን አጥተው ተጎድተዋል፤ አዳዲስ የመንገድ አስፋልቶች በስህተት ዕቅድ ምክንያት ፈርሰዋል! ኪራይ ሰብሳቢነትን መዋጋት ያለበት ህዝቡ ነው ትላላችሁ ችግሩ ግን ከላይ ነው! ድርጅታችሁ ምንድን ነው የሚሰራው?" የሚል ጥያቄ ለካድሬዎቹ ቀርቦላቸዋል። " ልማቱን ማየት አልቻላችሁም፣ በዓለም ፈጣን እድገት እያመጣን ነው ትላላችሁ፡፡ ሃገራችን እንዲታድግ ከተፈለገ ነገሮችን በግልጽ መነጋገር አለብን! ቆሻሻ ዘይት ከውጪ ታስገባላችሁ በምትኩ የሃገራችንን ንጹህ ዘይት ወደ ውጪ ትልካላችሁ! ቆሻሻ ዘይቱን እንኳን በአግባቡ ማግኘት አልቻልንም! " የሚሉ አስተያየቶች ሲቀርቡ፣ አንዳንድ ደጋፊ አስተያየት ሰጪዎች መልስ ለመስጠት ሲሞክሩ፣ በተቃውሞ ጭብጨባ ንግግራቸው ተቋርጧል። "ለምን ችግሩን ለመሸፈን ትሞክራላችሁ? አልሠራችሁም! የወረዳ አመራር ተብለው የሚሾሙት ምንድን ነው ስራቸው?" የሚሉ ጠንካራ ጥያቄዎች መቅረባቸውንም ተሳታፊዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

Monday, September 21, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ካቢኒያቸውን መረጡ






የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ እጩ የኮሚቴ አባላት ብቃት መርምሮ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት 10 የካቢን አባላትን ለብሔራዊ ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን ከእንዚህም መካከል ፣ምክር ቤቱ ኃላፊነታቸውን ተቀብሎ ያፀደቃቸው ፡-

1ኛ. አቶ ነገሰ ተፋረደኝ፡- ም/ሊቀመንበር
2ኛ .አቶ አበበ አካሉ፡- የውጭ ጉዳይ ኃላፊ
3ኛ. አቶ እስክንድር ጥላሁን ፡-የጥናት እና ስትራቴጂ ኃላፊ
4ኛ. አቶ ዮናታን ተስፋዬ ፡-የህዝብ ግኑኙነት ኃላፊ
5ኛ. ወ/ሮ መዓዛ መሃመድ፡- የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ
6ኛ. አቶ ጋሻው መርሻ፡- የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
7ኛ. አቶ አዲሱ ጌታነህ ፡-የሕግ ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ፓርቲውን እንዲያገለግሉ የብሐራዊ ምክር ቤት ድጋፉን የሰጠ ሲሆን፣ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ምክር ቤት ያልተቀበላቸው፤
1ኛ. አቶ እያስጴድ ተስፋዬ
2ኛ. አቶ ወረታው ዋሴ ሲሆኑ ፣የአባላት መረጃ እና ደህንነት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ለምክር ቤት የቀረቡት እጩ አቶ ስለሺ ፋይሳ ራሳቸውን ከእጩነት አግልለዋል፡፡
በጠቅላላ ጉባሄ የተመረጡት የኦዲት እና ምርመራ ኮሚሽን አባላት በመካከላቸው የሥራ ክፍፍ ያደረጉ ሲሆን፣
1ኛ. አቶ አበራ ገብሩ ፡- ሰብሳቢ
2ኛ. አቶ ሳምሶን ገረመው ፡- ምክትል ሰብሳቢ
3ኛ. አቶ ሀይለገብርኤል አያሌው ፡- ፀሃፊ
4ኛ. አቶ ብርሃኑ መሠለ ፡- አባል
5ኛ. አቶ ሀብታሙ ደመቀ ፡- አበል ፣
በቀጣይ በተጓደሉትን የሥራ ክፍልች፣የአባላት መረጃ እና ደህንነት፣ የወጣቶች እና የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊዎች፤ የፓርቲው ሊቀመንብር አቅርበው ያፀደቃሉ፡፡



Burkina Faso coup sparks deadly street protests








The opposition has called for people to resist the coup

BBC News

Presidential guard officers in Burkina Faso have seized power in a coup, with reports of more than 10 deaths amid protests in the capital, Ouagadougou.

A close ally of former President Blaise Compaore has been named the country’s new leader, state television reports.

The US, France and African Union (AU) condemned the coup in the former French colony.

Those killed were shot dead by presidential guard forces in the capital, a civil society group said.

The claim by the influential Balai Citoyen group could not be independently verified.

A medical source in the city’s main hospital said three people had been killed.

An unknown number of protesters have been detained.
‘Rise up’

The coup leaders have imposed a night-time curfew across the West African state, and have ordered the closure of land and air borders, AFP news agency reports.


The headquarters of Mr Compaore’s Congress for Democracy and Progress (CDP) party were ransacked in Ouagadougou as news of the coup spread, it adds.

The AU and regional body Ecowas, the Economic Community of West African States, called for the immediate release of “hostages”, referring to interim President Michel Kafando and Prime Minister Isaac Zida, who were detained at a cabinet meeting in the president palace on Wednesday.

Their transitional authority was due to hand power to a new government after elections on 11 October.
Seven things about Burkina Faso:Image copyrightAFP
It is one of the world’s poorest countries – its main export is cotton
A former French colony, it gained independence as Upper Volta in 1960
Capt Thomas Sankara seized power in 1983 and adopted radical left-wing policies – he is often referred to as “Africa’s Che Guevara”
The anti-imperialist revolutionary renamed the country Burkina Faso, which translates as “land of honest men”
Mr Compaore took power in the coup that killed Mr Sankara, and ruled for 27 years, until he was ousted last year following street protests
People in Burkina Faso, known as Burkinabes, love riding motor scooters
It is renowned for its pan-African film festival, Fespaco, held every two years in Ouagadougou



Mr Compaore was ousted in a popular uprising, partly organised by Balai Citoyen, in 2014 after 27 years in power, and is currently in exile.

He was accused of committing widespread abuses, and trying to change the constitution to extend his term in office.

Some of his key allies had been barred from contesting the election.Image copyrightAP
Image captionProtesters have been showing their anger against the coup leadersImage copyrightAFP
Image captionStreets were barricaded in the capitalImage copyrightAP
Image captionThose wounded in the clashes have been taken to hospital

A statement issued by the coup leaders said the West African state would be led by Gen Gilbert Diendere, Mr Compaore’s former chief-of-staff.

In media interviews, he said he had no contact with Mr Compaore and would do everything to “avoid violence that could plunge the country into chaos”.

An earlier announcement on state television said wide-ranging talks would be held to form a new interim government that would organise “peaceful and inclusive elections”.

Transitional parliamentary speaker Cheriff Sy called for people to “immediately rise up” against the coup, and declared himself the leader of the West African state.

“We are in a resistance situation against adversity,” Mr Sy added.Image copyrightAFP
Image captionGen Diendere says he will act to prevent chaos

The US State Department said it was deeply concerned about the events unfolding in Burkina Faso.

French President Francois Hollande said he strongly condemned the coup “because an electoral process was under way”.

However, France would not intervene militarily, he said.

The US said it was deeply concerned about events in Burkina Faso, and it condemned the seizure of power through unconstitutional means.

Burkina Faso is a key ally of the US and France in the campaign against militant Islamists in the region.
Analysis: Thomas Fessy, BBC West Africa correspondentImage copyrightAFP
Image captionMr Compaore was accused of committing widespread abuses

The elite presidential guard has been trained, in part, by the US. It is the most powerful armed group in Burkina Faso and often disrupted the activities of the transitional government as it tried to cling to the privileges it enjoyed under Mr Compaore’s rule.

It is seen to be close to him, and is not popular on the streets. So its seizure of power could be a recipe for serious violence.

The transitional government might have made two mistakes – preventing politicians loyal to Mr Compaore from running in next month’s elections and allowing the Reconciliation Commission, formed to heal wounds after the end of his authoritarian rule, to release a report calling for the presidential guard to be disbanded.

Some argue that a newly elected president would have had greater legitimacy to take such action.

Saturday, September 19, 2015

ሞላ አስገዶም የኤርትራን በርሃ አያዉቀዉም ሲል ተስፋሁን አለምነህ አጣጣለው



ከነበረው ሃላፊነት አንፃር ምንም የሚያዉ ቀዉ ነገር የለም ማለት አይቻልም :: እንጅ ከነበረ የሞላዉ ሃላፊነት ይሁን የሚመጣጠን ግንዛቤ ስለለዉ በመክዳቱና በመግለጫዉ የተናገረዉ የለዉጥ ሃይሉን የሚጎዳ ነገር የለዉም :: ፕሮፌሰር ፈሪ አሁን ነዉ ማለት ምን ማለት ነዉ ? የፈሪነት መገለጫዉ ምንድን ነዉ? በእኔ እምነት ፈሪ አይደሉም :: ፈሪ ናቸዉ እንበል እሽ የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ አንዴት ይፈራል? ትግል አይደል ወዲ የህዝብአስገዶም ከዳ ማለት ትህዴኖች ከሃዲ  ናቸው … ማለት ነዉ?አይደለም :: ስለ ጥምረቱ የአለውን ሌላዉ አዴሃንን መጥራት ሲያቅተው ጥምረቱ ዉስጥ የሌለ ድርጅት እያነሳ መቀባጠሩ የትናትን እዉነት ማስታወስ የማይችል ገልቱ መሆኑን ያመለክታል ::

እንዳለዉ ተብሎ ሊጠቀስ ሞላ የሚችል እዉነት መግለጫዉ የለዉም :: ወያኔ እንዲሆንለት የሚፈልገዉን ነዉ የተናዘዘዉ ::


ምን አልባት የትናት እዉነት ለሚዘነጋ ዝንጉ ኤርትራ ዉስጥ የተመለከታቸዉን ተራራ ማስታወሱንም እጠራጠራለሁ ::
የትጥቅ ትግሉን በጥልቀት ለተመለከተው ህዝባዊ መሰረት ይዞል :: ባይሆን ወያኔ በመቅበዝበና ይህ ባሰልች ኘሮፖጋንዳ ወዲ
አስገዶምን ባላናዘዘዉ: :
ኤርትራ ዉስጥ የሚካሄደዉ ትግል መልኩን እየቀየረ ነዉ :: ወረዳ ተይዞ የትግሉ ገዠ ባለቤት ህዝብ የሁሉ ነገር ሞተርነቱን ሲያሳይ ደናቁርት ቦታ አይኖራቸዉ :: ዘመድ ከዘመዱ..ብለዉ መኮብለሉ የሚጠበቅ ነው :: ንዛዜውም ቢሆን ለተገነዘበው ይህን ያስረዳል :: ክደት ሞላ
ፈጠመ :: ወያኔ ዘፈነ: : እሱ ስለሄደ ወያኔ ከመዉደቅ አትድንም ::

ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል


ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል




በነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።


የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግን አልሸሸጉም።

አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በሁመራ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ተኩስና ድብደባ መሰማቱን የተለያዩ ድረገጾች ዘግበው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሻእቢያ “ህወሃት ሊወረኝ ነው” ሲል ክስ ማሰማቱ አይዘነጋም።

ኦምሃጀር በሚባለው ስፍራ የከረረ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እንደሰሙ የገለጹ በውጊያው የትኛው ወገን ድል እንደተቀዳጀ ለጊዜው መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። ውጊያው ጠርዙን አስፍቶ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ከህወሃት በኩል ውጊያው ከሻዕቢያ ጋር እንደሆነ ቢገለጽም ከሌላ ወገን “ህወሃትን የወጋሁት እኔ ነኝ” ባይ ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ አልተሰማም። የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ህወሃትን በነፍጥ አንበረክካለሁ በማለት ማወጁና አመራሮቹም ወደ ውጊያው አውድ ማምራታቸው ይታወቃል። ህወሃት ኤርትራን በአራት አቅጣጫ የመውጋት እቅድ እንዳለው ጎልጉል መዘገቡ የሚታወስ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከሰራዊቱ እየሸሹና እየተሰወሩ መሆናቸው ህወሃትን እንዳሳሰበው፣ ጦሩ የመዋጋት ፍላጎት ያጣል የሚል ሥጋት እንዳለ የሚጠቁሙ ክፍሎች “የአሁኑ የውጊያ አቅጣጫ በዚህ መልኩ እንዲሆን መደረጉ ይህንኑ ለመፈተንም ጭምር ነው” ብለዋል።

በሌላ ዜና በሶማሌ ያለው ሰራዊት የመመለስ ጥያቄ ማንሳቱና ሁለት ጄኔራሎች ጦሩን ለማወያየት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አቅንተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ጦሩ መስዋዕትነት እየከፈለ በተደጋጋሚ የተቆጣጠረውን ቦታ እንዲለቅ ትዕዛዝ ሲቀበል መቆየቱ ሌላው የቅሬታው መነሻ ሲሆን በሶማሌ ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ይህንኑ ነቅፎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በህወሃት የሚመሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሶማሌ ስለተገደሉት ወገኖች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይህንን አክርረው አለመጠየቃቸው፣ ላለፉት አምስት ዓመታት 99.6 በመቶ ህወሃት የነገሰበት ማኅበርም (ፓርላማ) ለይስሙላ እንኳን ጥያቄ አቅርቦ እንደማያውቅ በርካቶች የሚተቹበት አገራዊ ጉዳይ ነው።

የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

ወደ ኢትዮጵያ የሸሹት የትሂዴን አባላት ከ70 የማይበልጡ መሆናቸው ታወቀ

ወደ ኢትዮጵያ የሸሹት የትሂዴን አባላት ከ70 የማይበልጡ መሆናቸው ታወቀ
ኢሳት ዜና (መስከረም 7, 2008)
ባለፈው ሳምንት ትግል በቃኝ በሚል ታጣቂዎችን አስከትለው እጃቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት የሰጡት አቶ ሞላ አስገዶም ይዘውት የሄዱት ታጣቂ ብዛት 70 ብቻ መሆኑን እንዲሁም ከድርጅቱ 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከአቶ ሞላ በቀር እጃቸውን የሰጠ ኣንደሌለ ተገለጠ።
አርብ ጻጉሜ 6 ቀን 2007 አም በኢትዮጵያ አዲስ አመት ዋዜማ ከኤርትራ ወደሱዳን የተሻገሩትና ከዚያም ለኢትዮጵያ መንግስት እጃቸውን የሰጡት አቶ ሞላ አስገዶም፣ ለዘመቻ በሚል ከንቀሳቀሷቸው 115 ወታደሮች 45ቱን መመለስ እንደተቻለ ተመልክቷል። 
የትሕዴን ም/ሊቀመንበር የነበሩትና አሁን በተጠባባቂነት የድርጅቱን የመሪነት ስፍራ የጨበጡት አቶ መኮንን ተስፋዬ እንደተናገሩት ከአቶ ሞላ በስተቀር አንድም የትሕዴን አመራር ለኢትዮጵያ መንግስት እጁን አልሰጠም።
ከድርጅቱ 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ወደ ኢትዮጵያ የተሻገሩትና እጃቸውን የሰጡት አቶ ሞላ አስገዶም ብቻ መሆናቸውን አቶ መኮንን ተስፋዬ ገልጸዋል። ተገደው የሚሄዱትን ወታደሮች ለመመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ ግጭት መከፈቱን በማውሳትም፣ በመሰደድ ላይ ከነበሩት 115 ታጣቂዎች 45ቱን መመለስ መቻላቸውን አስረድተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትሒዴን ሃይል ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያ መግባቱን የገለጸው መንግስት በገዢው ፓርቲ ይፋዊ ያልሆኑ ልሳናት በኩል ተጨማሪ ታጣቂዎች ኤርትራ ቀርተዋል ሲል የቀደመውን መግለጫ የሚያስተባብል መረጃ አስራጭቷል። ከበሽተኞቹ በቀር ሁሉም ሃይል ወጥቷል ሲል መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግስት 200 ተጨማሪ ታጣቂዎች ቀርተዋል ሲል ትናንት ሃሙስ ይፋ አድርጓል።
በድንበር አካባቢ ግጭት መኖሩን ይህም ትጥቅ እንዲፈቱ በተጠየቁ ሁለት መቶ የደምሄት (ትሂዴን) ሰራዊትና በኤርትራ ወታደሮች መካከል ነው ሲልም አክሏል። በአካባቢው ግጭት ስለመኖሩ ከገለልተኛ ምንጭ ማግኘት አልተቻለም።

mola asgedom

በዐማሮች ላይ በሚፈፀመው አሰቃቂና ዘግናኝ ዕልቂት ላይ ለሚሣለቀው ለኢሕአፓ ፍኖተ-ዴሞክራሲ ሬዲዮ የተሰጠ አጸፋዊ መልስ



ዐማሮች ላይ በሚፈፀመው አሰቃቂና ዘግናኝ ዕልቂት ላይ መሣለቅ በታሪክና በሕዝብ ያስጠይቃል
በፍኖተ-ሞክራሲ ሬዮ ለቀረበው ውንጀላ ተሰጠ አጸፋ መልስ
ሠሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ንብረት የሆነው «ፍኖተ-ሞክራሲ» በመባል የሚታወቀው የሳተላይት ሬዲዮ ጣቢያ በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የጅምላ ክስ አቅርቧል። ክሱ «በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው» በሚል ርዕስ ዘጋጀውን መግለጫ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በሬዲዮ አስተላልፏል[1]፤ በጽሑፍ ደግሞ በተባባሪ ድረ-ገፆች «አሲምባ[2]» እና «ደብተራው[3]» ሠራጭቷል። ከሁሉም የሚያሣዝነው የ«አሲምባ» ድረ-ገፅ አስቀድሞ ለጥፎት የነበረውን የሞረሽ-ወገኔን መግለጫ ሲያነሣ እና የ«ፍኖተ-ሞክራሲን» መግለጫ ሲለጥፍ ለአንባብያን ሚዛናዊ አስተያዬት ሲባል እንኳን ሁለቱንም መግለጫዎች ጎን-ለጎን ያለማቅረቡ ነው። ይህም የድረ-ገፁ አስተዳዳሪዎች የወሰዱትን ሚዛናዊ ያልሆነ ውሣኔ በግልፅ ያመለክታል። የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» መግለጫ ዓላማ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት«በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል» በሚል ርዕስ ማክሰኞ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. የሰጠውን በሃቅና በተጨባጭ መረጃ የተደገፈውን ዘገባ ለማጣጣል ነው። ሆኖም «የፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ ዝግጅት ክፍል ምንም ዓይነት የማጣራት ሙከራ ሣያደርግ፣ መግለጫ ያወጣውንም ሞረሽ-ወገኔን «እንዴት ነው? ምን መረጃ አላችሁ? መረጃው የቱን ያህል አስተማማኝ ነው? ሌላስ ሁለተኛ እና ሦሥተኛ አካል መረጃውን እንዴት ማግኘት ይችላል?» ብሎ ሣይጠይቅ «በጉምዝ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጸያፍ ዘመቻ የአማራን ሕዝብ ተገን አድርጎ በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ነው።» በማለት በጭፍኑ ተበዳዩን ዐማራ መልሶ ወንጅሏል። «በደለኛ፣ በደለኛ ወታደር በደለኛ ነው፤ ነገር ግን ባላገር (ገበሬ) ይክሣል» ሆነና ነገሩ፣ «ፍኖተ-ሞክራሲ» በዳዮቹን የትግሬ-ወያኔ ሎሌ የሆኑትን የጉምዝ ልሂቃን ድርጊት ከማውገዝ ይልቅ በዐማራው ላይ በሚፈፀመው ዕልቂት ላይ ተሣልቋል።
 አንባቢያን ዕውነቱን ከሐሰቱ፣ እርጥቡን ከደረቁ ለመለየት ይችሉ ዘንድ፣ «ፍኖተ-ሞክራሲ» ሞረሽ-ወገኔን የወነጀለባቸውን ነጥቦች እና በዐማራው ላይ በሚፈፀመው ዕልቂት ላይ ያሠራጨውን ሥላቅ አንድ በአንድ እያነሣን እንተችባቸው።
 1          «በዐማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው፣» ይህ የመግለጫው ርዕስ ነው።  ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተመሠረተው በዐማራው  ነገድ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ለዓለም ማኅበረሰብ፣ በተለይም ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለማሰማት ነው። ድርጅታችን የሲቪክ ድርጅት እንጂ፣ የዐማራ ሕዝብ ውክልና አለን፣ አለኝ ያለ አይደለም። አባላቱ እና መሥራቶቹ ዐማራዎች በመሆናቸው፣ ለወገናቸው ችግር አጋዥ ኃይል እንዲፈጠር ድምፅ የሚያሰሙ ተቆርቋሪዎች እንጂ፣ ዐማራው በነቂስ ወጥቶ «ወክለውናል» አላሉም። የውክልና መረጋገጫ ሠነድም የለንም። ይህንም እንድናደርግ እስካሁን ባለው ሁኔታ የሚያስገድድም ሆነ፣ ስሕተት ነው የሚልም የሞራልም ሆነ የሕግ ማዕቀፍ የለም። «ያልተከለከለ ነገር ሁሉ ለማድረግ የተፈቀደ ነው» ይባላልና፣ ሞረሽ-ወገኔም በዚሁ ባልተከለከ መንገድ በመግባት፣ በፖለቲካዊ መንገድ «ትክክለኛ ነው» የሚያሰኘውን አካሄድ ሣንከተል፣ በዐማራው ላይ ጉዳት ያደረሱ ቡድኖችን ድርጊት ደረቁን ሃቅ እናቀርባለን። በመሆኑም ሞረሽ-ወገኔ የሚጨነቀው፦ «ነገሩ ተፈጽሟል ወይ? ከተፈጸመ፣ መቼ? እንዴት? በማን? በምን ምክንያት? እነማን ፈጸሙት?» ለሚሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ እና ትክክለኛ መልስ ማግኘት ነው። በዚህም መሠረት በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ አሠቃቂ እና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያካሄዱት የጉምዝ ነገድ አባሎች መሆናቸውን በማረጋገጥ መግለጫው በሞረሽ ወገኔ ስም ተሠጥቷል። የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል ግን ሃቁን ከማጣራት ይልቅ «የጅብ ችኩል---» ሆኑና ለአስተዛዛቢ ትችት ተጣደፉ፤ በዐማራው ላይ በተፈፀመው አሠቃቂ ዕልቂት ላይም ተሣለቁ።
2          « --ዝምታ ሕዝብን ለጥቃት አሳልፎ መስጠት በመሆኑ ግዳጅና ኃላፊነትን መካድ ይሆንብናል።» የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል በግላቸው የወሰዱት ኃላፊነት እና ግዳጅ ካለ ያንን ኃላፊነታቸውን እና ግዴታቸውን መወጣት የእነርሱ ኃላፊነት ነው። ከዚህ ላይ አንባቢ እና አድማጭ ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ፣ ባወጡት መግለጫ መሠረት ለራሣቸው ከሰጡት ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች መካከል፣ ምንጊዜም በዐማራው ላይ ጥቃት ሲፈፀም አጥፊዎቹን፦ «አይዟችሁ፣ እነዚህ ዐማሮች ጨፍጭፏቸው፣ ግደሉዋቸው» ማለት መሆኑን ነው። ሰብአዊነት የሚሰማው ሰው ጉዳት ለደረሰበት፣ ለተጠቃ ዋስ ጠበቃ ይሆናል እንጂ፣ በትግሬ-ወያኔ ተደራጅተው ዐማራውን ቆራርጠው ለገደሉት፣ ጠብሰው ለበሉት ለአጥቂዎቹ ጉምዞች ባልሆነ ነበር። እንዲህ ዓይነቱን ቅጥ ያጣ እብሪት በምንም ተዓምር የዐማራው ልጅ ሊታገሰው አይገባም። ጅልነቱ ትናንት ቀረ! «እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል!» ሊባል ይገባዋል።
3          «የጉምዝ ሕዝብ/ ቤንሻጉሎች አማራውን ገድለው ጉበቱን፣ ኩላሊቱን፣ የታፋ ሥጋውን በሉ ብሎ ዓይንን በጨው አጥቦ ሕዝብን መዝለፍ አፍሪካን ከሚጠሉ ነጮች የሚጠበቅ እንጂ፣ ለዐማራ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ሊሰጥ የሚገባው አደለም ።» ከዚህ ላይ መግለጫውን ያወጣው የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል ያሳሰበው የዐማራውን ሥጋ ጠብሰው የበሉት ገዳዮቹ ጉምዞች፣ «ለምን የሰው ሥጋ በሉ ተባሉ?» ብሎ ነው። ሥጋቸው ተጠበሶ የተበሉት ዐማሮች ለእነርሱ ምናቸውም አይደሉም፤ ሰውም አይደሉም፤ በእነርሱ ቤት ሙክት ወይም ጠቦት ናቸው። ሥቃይ የተፈጸመባቸው ዐማሮች ሳያሳዝኗቸው፣ ሥቃይ አድራሾቹ ጉምዞች እንዴት ሊያሳዝኗቸው ቻሉ? በመሠረቱ የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል በሬዲዮ ያስተላለፈውን ና በጽሑፍ ያዘጋጀውንመግለጫ ሲያሰራጭ ያጣራው አንዳችም ነገር የለም። ቢያጣሩ ኖሮ እንዲህ ያለ ከሃቅ ጋር የሚጣረስ መግለጫ ባላወጡ ነበር። ልብ ካላቸው መልካን እና አይጋሊ-ሞዛምቢክ ቀበሌዎች (መተከል) ስልክ ደውለው ጉምዞችን ቢያነጋግሩ፣ ጉምዞች በባህላቸው ውሸት ነውር ነውና፣ «አዎ ዐማሮችን አርደን በላናቸው! ሥጋቸው ይጥማል፤» እንደሚሏቸው አንጠራጠርም!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ለሁለት ወገን፦ ለበዳዩም ሆነ ለተበዳዩ፣ ጥብቅና አይቆምም። የቆመው በአሁኑ ዘመን አንዳችም ተሟጋች ጠበቃ ለሌለው ለዐማራው ነው። በዐማራው ላይ የደረሱ ችግሮችን፣ ከነችግሩ ምንጮች እና ችግር አድራሾቹ በመረጃ በማስደገፍ የተለያዩ መግለጫዎችን አውጥቷል፣ ለወደፊቱም ያወጣል። ሥራችን ወንጀለኞችን ማጋለጥ እና ለፍርድ ማቅረብ ስለሆነ ወደፊትም ይህ አሠራራችን ይቀጥላል። እንደ ሞረሽ-ወገኔ እምነት በዐማራው ላይ በማንኛውም ዘመን ወንጀል የፈጸሙ የማናቸውም ነገዶች ልሂቃን እና ተወላጆች እንዲሁም የፖለቲካም ሆነ «የእገሌ ሕዝብ ነፃ አውጪ ነን» ባይ ድርጅቶች በሕግ መጠየቅ አለባቸው ብለን እናምናለን። ጉምዞችም በትግሬ-ወያኔዎች ጃዝ-ባይነት ወገኖቻችንን ዐማሮችን አርደው በልተዋቸዋልና እፋረዳቸዋለን። የዚያን ጊዜ የ«ፍኖተ-ምክራሲ» ዝግጅት ክፍል እና በባለቤትነት የያዘው ድርጅት ኢሕአፓ ጥብቅና መቆም  ይችላል።
4          «ሊደመጥ የማይገባውን  ትምክሕትም አንጸባራቂ ነው።» «ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ» እንዲሉ፣ የ«ፍኖተ-ምክራሲ» ዝግጅት ክፍል ዛሬም ያ ሰዎችን ለማጥፋት የተለያዩ የማጥላያ ስሞች ይጠቀም የነበረው የግራ ዘመሙ የዓለም አመለካከት ካከተመ ከ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በኋላ፣ ለዐማራው ድምፅ ለመሆን የሚጥሩ ሰዎችን በትምክህተኛነት ሊከስ፣ ሊወነጅል ይፈልጋል። የተበላ ዕቁብ ነው እንላቸዋለን። ከዚህ ላይ አንባቢ ልብ እንዲልልን የምንፈልገው ጉዳይ አለ፦ የትግሬ-ወያኔም ዐማራውን «ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ጨቋኝ ገዥ መደብ፣ የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት፣ የብሔር-ብሔረሰቦች ጠላት፣ ወዘተርፈ» እያለ በታሪክ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ዐማራውን ተጠያቂ ያደርጋል። የዚህ አስተሣሰብ ቆስቋሽ የነበረው ደግሞ ዋለልኝ መኮንን የተባለው «የዐማራ ጠላት የሆነ ዐማራ» ነው። የዋለልኝ መኮንን የነፍስ አባት ደግሞ ከ፸(ሰባ) ዓመታት በፊት «ኢትዮጵያ፥ የባሩድ በርሚል (Abyssinia: The Powder Barrel)» በሚል ርዕስ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ መርዝ አሣትሞ ያሠራጨው አፍቃሬ-ናዚ ወፋሽስት-ጣሊያን የነበረው ሮማን ፕሮቻዝካ የተባለው የኦስትሪያ ዜጋ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ረገድ ከ፲፱፻፶`ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀንደኛው አንቀሣቃሽ የሆነው እና ግራ-ዘመም ርዕዮተ-ዓለም የሚያራምደው ትውልድ፣ ዛሬም ኮሚኒዝም ተንኮታኩቶ ከወደቀ ከ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በኋላ ከዚሁ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ አመለካከት ያልጠራ መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል።
ከዚህ የምንረዳው መሠረታዊ ሃቅ ቢኖር፣ የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን በነገድ እና በጎሣ ከፋፍሎ የማጥፋትን ተልዕኮ የወረሰው ከዚሁ ግራ-ዘመም የፖለቲካ እንቅስቃሴ መሆኑን ነው። አገሪቱ እና የዐማራ ነገድ ተወላጆችንም አሁን ላሉበት አጠቃላይ ችግር የዳረጋቸው የግራ-ዘመሙ የፖለቲካ ትውልድ በኢትዮጵያዊነት እና በዐማራው ላይ የዘሩት የጥፋት ዘር መሆኑን የአሁኑ ወጣት ትውልድ ሊገነዘብ ይገባል። ከግራ-ዘመሙ የፖለቲካ ትውልድ አባሎች መካከል የተወሰኑት ለሻዕቢያ ኤርትራን የማስገንጠል ዓላማ ዕውቅና ሰጥተው፣ ኢትዮጵያውያን በየጎሣቸው እና ነገዶቻቸው እንዲከፋፈሉ ታግለዋል። ስለዚህ በኢትዮጵያውያን መካከል ልዩነቶችን ጥላቻን ሲያራቡ የኖሩ ግለሰቦች እና የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ «ፍኖተ-ሞክራሲ» ባሉ «በሬ-ወለደ» ባይ ልሣኖቻቸው አማካይነት «ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት እቆማለሁ፤ ለሕዝብ ልዕልና ድምፅ እሆናለሁ የሚሉበት የሞራል ብቃት የላቸውም። 
5          «ሕዝባችን ሰው አይበላም፤ ይህን ውሸት ማሰራጨት ኢትዮጵያ ላይ መዝመት ነው።» በመጀመሪያ ደረጃ ሞረሽ-ወገኔ ያሠራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን በተጨባጭ መረጃ ተመርኩዞ ለአንባቢ እና አድማጭ ሳያረጋግጡ «ውሸት ነው» ማለት ተገቢ አይደለም። ለመሆኑ የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል በመሬት ያለውን ሃቅ ለማጣራት ምን ሙከራ አድርገዋል? ወይስ ሰው-አልባ የስለላ አውሮፕላን (drone) ወደሥፍራው ልከው አረጋግጠዋል? ካቀረቡልን ሐተታ ግን ይህንን ሃቅ ሊያስተባብሉበት የሚችሉበት አንድም መረጃ የለም። አልያ ሃቁን ለማስተባበል ወያኔያዊ ሥራ መሥራት ይኖርባቸዋል። ስለሆነም ድርጊቱ የተፈጸመ ስለሆነ ሞረሽ-ወገኔ ትላንትም ሆነ ዛሬ ያለው አቋም አንድ ነው፦ በመተከል ዞን መልካን እና አይጋሊ-ሞዛምቢክ ቀበሌዎች ጉምዞች ዐማሮችን ገድለው ሥጋቸውን በልተውታል። ደረቁ ሃቅ ይህ ነው!
6          «የሚከሰሱት አሕዛብ ናቸው፣ ሃይማኖት የላቸውም፣ ለዚህም ነው ሰው የሚበሉ አውሬዎች ናቸው ብሎ ልፈፋም አማራ ነን ባዮች ምንኛ ኋላቀር የሀገርና ሰላምና የአንድነት መሠረት አውዳሚ እንደሆኑ ያሳያል።» ይህ አባባል አንድ ነገር ያስታውሰናል፦ አበው «ከሣሽ ተከሣሽ የሚለውን ቢያውቅ ኖሮ፣ ክስ አይመሠርትም ነበር፣» ይላሉ። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት «ጉምዞች አሕዛብ ናቸው፣ ኃይማኖት የላቸውም፣ ስለዚህም ሰው የሚበሉ አውሬዎች ናቸው» አላም። ከመግለጫችን ውስጥ ይህን የሚያስረዳ አንዳችም አረፍተነገር የለም። «በመልካን እና አይጋሊ-ሞዛምቢክ ቀበሌዎች ጉምዞች ዐማሮችን አርደው በሏቸው፤ ጉበትና ኩላሊታቸውን በሚጥሚጣ አጣፍጠው በሉት፤» ብለናል። ይህ ደግሞ የተፈጸመውን ድርጊት አመልካች ዕውነት፣ የማያወላውል ደረቅ ሃቅ ነው።
የፍኖተ-ሞክራሲ ዝግጅት ክፍል፣ እኛ ጉምዞችን በጅምላ ፈርጀን ያላልነውን «አሉ» ብሎ ሲወነጅለን አንድ ታሪካዊ ክስተት እንድናስታውስ አደረጉን። ቀድሞ የኢሕአፓ አባል፣ ከዚያም የኢሕዴን/ብአዴን መሥራች እና ሊቀመንበር የነበረው እና አሁን ደግሞ የፕሮቴስታንት ዕምነት ሰባኪ የሆነው ጌታቸው ማሞ (ታምራት ላይኔ) በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ጅጅጋ ወርዶ ነበር። ታምራት ላይኔ የተናገረው ንግግር፦ «እነዚህን ሽርጣም ሶማሌ የሚሏችሁን ዐማሮች አሁን በሏቸው» ሲላቸው፣ ብልሆቹ የሶማሌ አዛውንት «ወላሂ አሁን ገና አንተ ሰደብከን፣ እነርሱ በየጓዳቸው ያሙን እንደሆን እንጂ፣ እንዲህ ብለው በአደባባይ ሲሰድቡን አልሰማንም፤» በማለት ነበር ቅንድቡን ያሉት። በትይዩ ሲታይ የጉምዝ ነገድ ተወላጆችን በጅምላ «አሕዛብ፣ ኃይማኖት የሌላቸው፣ ሰው የሚበሉ አውሬዎች» ብሎ የዘለፋቸው የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬድዮ ጣቢያ ነው። በዚህ ረገድ ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ሞረሽ-ወገኔ የማንኛውንም ነገድ ወይም ጎሣ አባሎችን በጅምላ አይወነጅልም፣ የድርጅቱ መርሆም አይደለም።
አልፎም ሞረሽ-ወገኔን በኢትዮጵያ አንድነት «አውዳሚነት» መወንጀል የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ ባለቤቶችን ትክክለኛ ማንነት በትልቁ ያሣብቅባቸዋል። ለመሆኑ ወያኔ በሕገ-አራዊቱ አንቀፅ ፴፱(ሰላሣ ዘጠኝ) ያፀደቀውን «የብሔር-ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል» የሚለውን አገር-አፍራሽ አጀንዳ አውቀው እና ፈቅደው ለመጀመሪያ ጊዜ የድርጅታቸው መርህ አድርገው የተነሱ እነማን ነበሩ? ከዚያም አልፎ ይህን አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን አደራጅቶ፣ ሠራዊት አሰልጥኖ ጫካ ገበቶ በኢትዮጵያውያን ልጆች ንጹህ ደም የታጠበውማን ሆነና ነው?  ስለዚህ «አንድነታችን ተናጋ፤ የአገሪቱ አንድነት መሠረት የሆነው ዐማራ የትግሬ-ወያኔ እና አጋሮቹ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጸሙበት፤ ከዚህም አልፈው ጉምዞችን አደራጅተው አስፈጁት፣ ሥጋውንም አስበሉት» እያለ የሚጮኸውን ሞረሽ-ወገኔን በአገር አፍራሽነት መክሰስ ምን ይሉታል? ለነገሩ «መበደል መበደል ወታደር በድሏል፣ መካሱን ግን ባላገር (ገበሬ) ይካስ፤» ዓይነት አባባል እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጥልቀት ያውቀዋል።
7          « የጉምዝ ቤንሻንጉልን ሕዝብ በጸያፍ ውንጀላ የከሰሱ ሁሉ ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው፤»  ልብ በሉ ወገኖች፣ የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ ዝግጅት ክፍል በአሠቃቂ እና አረመኔያዊ ሁኔታ ለተገደሉት እና ሥጋቸውን ለተበሉት፣ እንዲሁም ኃብት ንብረታቸውን ተቀምተው ለተፈናቀሉት ዐማሮች አላዘነም። ይባስ ብሎ ጥብቅና የቆመው ለወያኔ እጀታ ሆነው ዐማራውን ለገደሉት እና ሥጋውን ለበሉት የጉምዝ ሰዎች ሆነ። አልፎ ተርፎም «እንዴት ጉምዞች እንዲህ ይባላሉ?» ብሎ እኛን ሞረሽ-ወገኔን ይቅርታ እንድንጠይቅ ያስጠነቅቃል። ይቅርታ የሚጠይቅ እኮ ጥፋት ያጠፋ፣ የዋሸ፣ የሰረቀ፣ የገደለ እንጂ እውነቱን የተናገረ አይደለም። ስለዚህ ሞረሽ-ወገኔ የዐማራ ድርጅት ባወጣው መግለጫ አጥፊዎቹን የጉምዝ ነገድ ተወላጆች ይቅርታ አይጠይቅም፤ ይፋረዳቸዋል እንጂ!
8          «ኢትዮጵያን ሲጎዳ የቆየውን ትምክህት በማናፈሳቸውም በሕዝብ መከፋፈል ልክ እንደ ወያኔ ሊከሰሱ ይገባቸዋል።» ይላል ጉዱ አያልቅበት «ፍኖተ-ሞክራሲ» የሬዮ ጣቢያ! ልብ በሉ ዐማራውን ትምክህተኛ እያለ በየሜዳው የሚያርደው እና የሚያሣርደው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ነው። ይህ በላኤ-ሰብ የአገዛዝ ሥርዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ከቤተክህነት እስከ ቤተመንግሥት፣ ከጽዳት ሠራተኛ እስከ ሚኒስቴር፣ ከተራ ወታደር እስከ ሙሉ ጄኔራል ያሉትን የሥልጣን ሥፍራዎች እና የኃላፊነት ደረጃዎች በሙሉ በትግራይ ተወላጆች አስይዟል። የሥላቁ ብዛት የትግሬ-ወያኔ ዘወትር ዐማራውን «ትምክህተኛ» ይለዋል። አዎ! ዐማራው በባህሉ፣ በቋንቋው፣ በኢትዮጵያዊነቱ፣ በስፋት አመለካከቱ፣ በእንግዳ ተቀባይነቱ፣ በአብሮነት ስሜቱ፣ በኃይማኖተኝነቱ፣ በይሉኝታው፣ ወዘተርፈ አብዝቶ ይመካል። መመካት በራስ የመተማመን፣ ራስን የመሆን ምልክት ነው። ይህ የሌለው የትግሬ-ወያኔ አይነቱ ንፉግ እና ጠባብ፣ ከፋፋይ እና አገርሻጭ፣ የእፉኝት ልጅ ባንዳ በምኑ ይመካል? እናም የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ የዝግጅት ክፍል ምኑ ያስነውራል ብሎ ይሆን «ኢትዮጵያን ሲጎዳ የቆየውን ትምክህት በማናፈሳቸው» እያለ ሞረሽ-ወገኔን የሚከስሰው? መቼም «በምኒልክ ጊዜ የደነቆረ በምኒልክ አምላክ እያለ ይኖራል» እንደሚሉት በግራው ርዕዮተዓለም የመደብ ጠላት ለመፍጠር ሲጠቀሙበት የኖሩትን የዝባዝንኬ ቃል በመጠቀም የሞረሽ-ወገኔን አባሎች እና ደጋፊዎች ለማሸማቀቅ ከጅለዋል። የኢትዮጵያን ሕዝብ በመከፋፈል የሚጠየቅ ካለ በመጀመሪያ ተጠያቂዎቹ «ፍኖተ-ሞክራሲን» በባለቤትነት የሚያስተዳድረው አካል መሪዎች ናቸው። ከትግሬ-ወያኔ በፊት «የብሔር፣ ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል» የሚለውን መርሆ በማራመድ የኢትዮጵያን ሕዝብ በነገድ እና በጎሣ ተከፋፍሎ እንዲባላ ትልሙን ተልመዋል፤ ኤርትራ እንድትገነጠልም ታግለዋል። የትግሬ-ወያኔም ያደረገው ይኸንኑ ነው። ስለዚህ የእነርሱ ችግር «እኔ ሳላደርገው ተቀደምኩ» ቁጭት እንጂ፣ በአፈጻጸም ደረጃ ከታዬ ከትግሬ-ወያኔ በባሰ በአገር ላይ ጦስ ያመጡ እንደነበረ ጥርጥር የለውም። ደግነቱ «እባብን የልቡን አይቶ እግር ነሣው» እንዲሉ ሆነና ምኒልክ ቤተመንግሥት ለመግባት የሕልም ሩጫ እንደሮጡ አረጁ።
ከዚህ በላይ በዝርዝር ለማሣዬት እንደተሞከረው፣ የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ ዝግጅት ክፍል በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ላይ የሠነዘረው ክስ መሠረተ-ቢስ የአሉባልታ ወሬ ነው። ለወደፊቱም የ«ፍኖተ-ዲሞክራሲ» ሬድዮም ሆነ ሌሎች በ«ኢትዮጵያዊነት» ስም የሚንቀሣቀሱ የብዙሃን መገናኛ ተቋሞች በዐማራው ተወላጆች ላይ ጥቁር ነጥብ የሚጥል እንዲህ ዓይነት የአሉባልታ ወሬ ከማሠራጨት ይልቅ በሃቅ ላይ የተመሠረተ እና ከጭፍን ወገናዊነት የራቀ ሚዛናዊ ዘገባ እንዲያቀርቡ አደራ እንላለን።
ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

wanted officials