Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, May 31, 2018

Ethiopiain Political prisoners goes on hunger strike


ESAT News 
Political prisoners at Ethiopia’s notorious Qillinto prison went on hunger strike today on the occasion of May 28, a day the ruling EPRDF took power in Addis Ababa.
The prisoners say the day has brought tyranny and repression to Ethiopians and hence they said they wanted to mark it with hunger strike. According to the prisoners, it is a day tyrants reign on power in Ethiopia.
The about 250 political prisoners at the Qillinto prison have reportedly refuse food today.
Ethiopia has released thousands of political prisoners in the last few months but many more thousands are still in jails and undisclosed detention centers across the country.

ብረት ያነሱ አርበኞች ስርነቀል ለውጥ እስከሚመጣ ትግላችንን እንቀጥላለን አሉ

በኢትዮጵያ ስርነቀል ለውጥ እስከሚመጣ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ብረት ያነሱ አርበኞች ገለጹ።

በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል በተለያዩ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል በማድረግ በአገዛዙ የተለያዩ ወታደራዊና መንግስታዊ ተቋማት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ላይ የሚገኙት አርበኞች ሰሞኑን በአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን እየቀረበ ያለው ዜና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባብለዋል።
ሁለት የአርበኛ መሪዎች ወደ አገዛዙ የገቡበት ምክንያት ከጤና ጋር የተያያዘ ነው ያሉት አርበኞች ትግሉን ከድተው እንደገቡ ተደርጎ የሚቀርበው ፕሮፖጋንዳ ህዝቡን ለማደናገር ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነው ሲሉ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።
አሁንም በረሃ ላይ ነን፡ በኢትዮጵያ እውነተኛ ለውጥ እስከሚመጣ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል።

በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ደስታቸውን በመግለጽ ላይናቸው ።


 በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ደስታቸውን በመግለጽ ላይ መሆናቸው ታወቀ።
በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በእስራኤልና በሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ስነስርዓቶች ደስታቸውን እየገለጹ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በሌላ በኩል  በጓዳችን መፈታት ደስ ብሎናል፤ የሚጠብቀን ብዙ መሆኑን እናውቃለን ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት መግለጫ አውጥቷል።
የአቃቤ ህግ መግለጫ ከተሰጠበት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የኢትዮጵያውያን አይንና ጆሮ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተተክለው ነበር ያለፉትን አራት ቀናት ይቆዩት።
በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መፈታት፡ በሰላማዊ ሰልፍና በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲጠይቁ ቆይተዋል።
ሰሞኑን እንደሚፈታ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ አቶ አንዳርጋቸውን በአካል ወጥተው ለማየት በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር።
ትላንት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ አቶ አንዳርጋቸ ጽጌን የጫነችው የፖሊስ መኪና ቦሌ ከሚገኘው የአባቱ መኖሪያ ቤት ስትደርስ በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ይከታተሉት ነበር።
አቶ አንዳርጋቸው ከአራት አመት እስራት በኋላ ከቤተሰቦቻቸውና ከደጋፊዎቻቸው ጋር በአካል ሲገናኙ ስሜቱ ልዩ እንደነበረ ከአዲስ አበባ ሲተላለፍ ከነበረው የቀጥታ ስርጭት መከታተል ተችሏል።
ይህ ስሜት በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የተንጸባረቀ ሲሆን በተለያዩ ስነስርዓቶች የአንዳርጋቸው ጽጌን መፈታት በልዩ የድስታ ስሜት ተቀብለውታል።
በሲውዲን ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ድስታቸውን የገለጹ ሲሆን በኖርዌይ ኦስሎ፡ በስዊዘርላንድ በርን፡ በጀርመን፡ በካናዳ ቶሮንቶና ካልጋሪ፡ በአሜሪካን በበርካታ ከተሞች ኢትዮጵያውያን በልዩ ሁኔታ ዕለቱን በደስታ አሳልፈውታል።
በዋሽንግተን ዲሲ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታትን በተመለከተ የተዘጋጅ ልዩ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በእስራኤል በደቡብ አፍሪካ እንዲሁ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለጽ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የዓላማ ጽናት ያላቸውን አክብሮት አሳይተዋል።
ዛሬም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ ፕሮግራሞች በመካሄድ ላይ ናቸው።
በሌላ በኩል አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታትን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
በጓዳችን መፈታት ደስ ብሎናል፣የሚጠብቀን ብዙ ስራ እንዳለ እናውቃለን በሚል ርዕስ ንቅናቄው ባወጣው መግለጫ  ይህ እውን እንዲሆን ጥረት ላደረጉ ኢትዮጵያዊያንን ዜጎች እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እንዲሁም ከጎናችን ለቆሙ የውጭ አገር ዜጎችና ድርጅቶች ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል ሲል አስታውቋል።
ደስታችን የተሟላ የሚሆነው ግን ወገኖቻችን የሞቱለት፣ የታሰሩለት፣ የተሰደዱለትና የተሰቃዩበት ዓላማ ሲሳካ ነው።
ዛሬም አቶ አበበ ካሴ፣ ሰይፉ አለሙ፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ ማስረሻ ሰጤ፣ መስፍን አበበ፣ አበበ ኡርጌሳ፣ ራቪድ ሳላ እና ሌሎች በርካታ ወገኖቻችን በእስር ላይ ይገኛሉ።
ለእነዚህ ሁሉ ወገኖቻችን ነፃነት የምናደርገው ትግል አጠናክረን መቀጠል ግዴታችን መሆኑን እንገነዘባለን ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት በመግለጫው ገልጿል።
በጓዳችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ምክንያት ደስታችን ከፍተኛ ቢሆንም ከእንግዲህ የሚጠብቀን ትግል ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ መስዋትነት ሊጠይቅ የሚችል መሆኑን በመገንዘብ ተዘጋጅተናል።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሀገሩ ባለሙሉ መብት ዜጋ እስኪሆን ትግላችንን እንቀጥላለን በማለት ንቅናቄው በመግለጫው አስታውቋል።

በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ ነው


 በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማፈን ነባር የብአዴን እና የህወሃት አባላት በሙሉ ሃይላቸው እየተንቀሳቀሱ ነው።
ለውጥ የሚፈልጉ የኢህአዴግ አባላት ቁጥራቸው እየጨመረ ቢሆንም፣ ነባር የኢህአዴግ አመራሮች ከአዲሶቹ የድርጅቱ አመራሮች ጋር ተስማምተው ለመጓዝ ተቸግረዋል።
ህወሃት በብአዴን ውስጥ ያለውን ክፍፍል ለራሱ ጥቅም ለማዋል እየተንቀሳቀ ሲሆን በተለይ የለውጡን እንቅስቃሴ አይደግፉም የሚባሉትን ነባር የድርጅቱን አመራሮችና አንዳንድ ወጣት አመራሮችን በመያዝ፣ ለውጡን ለመቀልበስ እየሰራ ነው። በብአዴን ውስጥ የለውጡ እንቅስቃሴ አገራዊ በሆነና የህዝቡን ፍላጎት በሚያሟላ መንገድ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ቡድኖች እየጎለበቱ ቢመጡም፣ አቶ በረከት ስምዖን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ከበደ ጫኔና የመሳሰሉ ነባር አመራሮች የለውጡን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ ከህወሃት ጎን ተሰልፈው ስራዎችን እየሰሩ ነው።
የህወሃት መሪዎች ከደህዴን የተወሰኑ አመራሮችን ከጎናቸው ማሰልፍ ቢችሉም በኦህዴድ በኩል የሚከተሉዋቸውን ሰዎች ማግኘት አለመቻላቸው እንዲሁም በርካታ የብአዴን ወጣት አመራሮች የህወሃትን ሴራ ቀድሞ በመገንዘብ ለመተባባር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህወሃት እንደልቡ መንቀሳቀስ አልቻለም። ለውጥ ፈላጊ የብአዴን አመራሮች የእነ በረከትን ፍላጎት ለማስፈጸም ፈቃደኛ አለመሆናቸው እነ አቶ በረከት የመጨረሻ የሚሉትን እድላቸውን ለመጠቀም ላይ ታች እያሉ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ።
በድርጅቶች ውስጥ ያለው የሃሳብ ልዩነት እየሰፋ መሄዱ ኢህአዴግን ከ2 ሊከፍለው ይችላል ተብሏል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በለውጥ ፈላጊዎች እንጅ በነባር አመራሮች ዘንድ ድጋፍ የላቸውም። አንዳንድ ነባር አመራሮችን በጡረታ አሰናብተው የግል ስራ እየፈለጉ እንዲቀጠሩ ለሌሎች ደግሞ በቦርድ አባልነት እየሾሙ የግል ህይወታቸውን እንዲመሩ ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ነባር አመራሮች ግን ከአመራር ቦታ መገለላቸውን በጸጋ አልተቀበሉትም።
ህወሃት በመከላከያው እና ደህንነቱ ያለው የበላይነት እንዳይነካበት ጥረት እያደረገ ነው።

Wednesday, May 30, 2018

Andargachew Tsege says PM spoke to him on various issues


ESAT News
Andargachew Tsege, a political prisoner who was on death row and released yesterday after four years of imprisonment, said Prime Minister Abiy Ahmed spoke to him on a number of issues.
He however told ESAT on a phone interview that he would not give details of the discussions with the PM.
“I have spoken to the Prime Minister on a number of issues. We have discussed so many important issues, but I would not go to the details,” he said on the phone from Addis Ababa.
Speaking about his health, Andy said his health is even better after four years. “I am physically and mentally fit. I am in a better mental and physical condition than four years ago. I came out of prison stronger physically and spiritually.”
Ethiopians at home and in the Diaspora yesterday euphorically celebrated the release of Andy Tsege.
In the capital Addis Ababa, hundreds of people gathered at the residence of Andy’s parents singing and chanting slogans praising the prominent freedom fighter. Andy briefly addressed the crowd saying he was free but there are many issues that the country needs to deal with.
Ethiopians in Washington, DC, Toronto, Switherland and other corners of the world gathered to celebrate the release of a man seen by many as a freedom icon.
Meanwhile UK Foreign Secretary issued a statement on the release Andy, who is a British national. “I am pleased Andargachew Tsege is now able to reunite with his loved ones after being separated from them for so long,” Foreign Secretary Boris Johnson said.
“After four unbelievably hard years on death row this is wonderful news for Andy, his partner and their children. The new Ethiopian government should be recognised for what they have done today. The most important thing now is that Andy is released from prison and able to reunite with his family as soon as possible,” Reprieve, an international organization that campaigned for the release of Andy said in a statement.
His wife, Yemi Hailemariam hopes Andy will come home to London soon to reunite with her and their three children. “I am so thankful that the pain and anguish my children have had to go through could now soon be coming to an end. Helawit, Yilak and Menabe have spent too long without their father and we are all hoping Andy will be free to come home to us soon.”
The leader of an opposition group based abroad, Andargachew Tsege,63, was kidnapped at the Yemeni airport in June 2014, in a joint operation by the Yemeni and Ethiopian intelligence. He was sentenced to death in absentia in 2009.
The popular political leader is not new to Ethiopian politics. He spent his tender years as a young revolutionary and at the time of his arrest, he was the general-secretary for Patriotic Ginbot 7, a group outlawed by the regime

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከረጅም እስር በኋላ ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መገናኘቱ ለእንግሊዝ መንግስት ትልቅ ደስታ ነው

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር በመለቀቃቸው የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደስታቸውን ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሪስ ጆንሰን እንዳሉት የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ለእንግሊዝ መንግስት ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ ከእስር ለማስፈታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።
እናም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከረጅም እስር በኋላ ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መገናኘቱ ለእንግሊዝ መንግስት ትልቅ ደስታ ነው ብለዋል።
በአንዳርጋቸው ጽጌ መለቀቅ በርካታ ሰዎች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከየመን ታፍነው በኢትዮጵያ ደህንነቶች ከተወሰዱ በኋላ የእንግሊዝ መንግስት የእስር ርምጃውን በማውገዝ ከኢትዮጵያው አገዛዝ ጋር ሲወዛገብ ቆይቷል።
በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች ኢትዮጵያ በመጡ ቁጥር ቀዳሚ አጀንዳቸው በማድረግ ከሀገሪቱ አገዛዙ ባለስልጣናት ጋር መክረዋል፣ከፍተኛ ጫና ለማድረግም ሞክረዋል።
በኢትዮጵያ አገዛዝ ባላስልጣናት በኩል ግን የሕዝብ ተቃውሞ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ ጉዳዩን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ነው የቆዩት።
እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ በመቀነስም ማድረግ የምትችለውን  ጥረት ሁሉ ማድረጓም ነው የሚታወቀው።
ሪፕሪቭ የተባለው የእንግሊዝ የሲቪክ ተቋምና የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች እንዲሁም የሃገሪቱ የተወሰኑ ዜጎች የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲለቀቁ በቂ ግፊት አላደረገም በሚል ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር።
ጉዳዩ እየተጠናከረ ሲመጣም እንግሊዝ ከ2 ጊዜ በላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን እስከመላክም ደርሳለች።
ይህ ሁሉ ሆን በመጨረሻ የሕዝቡ ተቃውሞ ገፍቶ የፖለቲካ እስረኞች መለቀቅ ከጀመሩ በኋላ አቶ አንዳርጋቸው የመለቀቅ ተስፋ ይኖራቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ ቆይቷል።
እንደተገመተውም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር ተለቀው ከቤተሰባቸው ጋር ለመገናኘት በመብቃታቸው የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ገልጸዋል።
እናም የኢትዮጵያ መንግስት የጀመረውን የለውጥ ሒደት መነሻ በማድረግ አቶ አንዳርጋቸውን መልቀቁ የሚያበረታታ ርምጃ ነው ብለዋል።
አቶ አንዳርጋቸው ከእስር ባለመለቀቃቸው ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ መንግስት ልታገኝ የምትችለውን በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ማጣቷን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ መግለጻቸው ይታወሳል።

Tuesday, May 29, 2018

“ፍርዱን ተፈጻሚ አድርጉትና ሰው እየሳቀ እንደሚሞት ላሳያችሁ እያልኩ ደህንነቱን ጠይቄያቸዋለሁ” ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ

Image may contain: 1 person, smiling
(ኢሳት ዜና ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ ከእስር ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው እና ከደጋፊዎቻቸው ጋር የተገናኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፣ ደህንነቶች ምርምራ ቢያመደርጉበት ወቅት፣ በእንዲህ አይነት አገር ከምኖር ፍርድ ቤት የወሰነውን የሞት ፍርድ ቤት ፈርዳችሁ እንድትገድሉኝ፣ ዛሬም እዚህ ቁጭ ብዬ የምናገረው ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ በአስቸኳይ እንዲወስኑ ነው። ሰው እየሳቀ ሊሞት እንደሚችል አሳያችሁዋለሁ።” ብለው እንደተናገሩና በቴለቪዥን ቆራርጠው እንዳቀረቡባቸው ተናግረዋል።
አቶ አንዳርጋቸው ፣ ዛሬ ተፈትቻለሁ፣ ግን ብዙ ያልተፈቱ ጉዳዮች አሉ፣ ቀኑ የደስታ ቀን ነው፣ ግን ቀኑ የደስታ ብቻ ሳይሆን በእናንተ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት ነው ወደ ተሻለ ሁኔታ የምንቀይረው የሚለው ዋናው ነገር ነው ብለዋል። አራት አመት ብዙ መስዋትነት የተከፈለበት ሊመስላችሁ ይችላል፣ ግን መስዋትነቱ ትንሽ ነው። የዚህ አገር ችግር ለመፍታት ብዙ መስዋትነት ይጠይቃል ብለዋል፡
አቶ አንዳርጋቸው ፣ በአረብ አገር ተሰደው ስቃይ የተፈጸመባቸው የኢትዮጵያ ሴቶች ላይ የደረሰው ግፍ በስልጣን ላይ ባሉት ገዢዎች ላይ ጠንካራ ንግግር እንዲናገሩ እንዳደረጋቸው ይህም ጥያቄ በደህንነቶች ይቀርብላቸው እንደነበር ተናግረዋል።
የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው ፣ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደ ትግል ጓደኛዬ በመፈታቱ በጣም ደስ ብሎኛል፣ ዋናው ከዚህ በሁዋላ እሱ የታሰረለት ሁላችንም የምንታገልለት አላማ አገሪቱን ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ነው፣ እሱም የሚፈልገው ይህንን ነው ብለዋል።
ለአቶ አንዳርጋቸው የተደረገው አቀባበል ምን ያሳያል ተብለው የተጠየቁት ፕ/ር ብርሃኑ፣ ህዝቡ ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውን ፍቅር ከመግለጽ በተጨማሪ ህዝቡ ፍትህ ፣ ዲሞክራሲና ነጻነት የጠማው መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በዝግጀቱ ላይ ተገኝተው አስተ|ያየታቸውን ከሰጡት መካከል ወ/ት እየሩሳሌም ተስፋውን አነጋግረናታል።
Image may contain: 3 people, people smiling, people standing

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋና ጃዋር መሀመድ ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ ተቋረጠ


 አቃቤ ሕግ በአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋና ጃዋር መሀመድ ላይ መስርቶት የነበረውን ክስ ማቋረጡ ተነገረ።
በሁለት መገናኛ ብዙሃን ማለትም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) እና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦ ኤም ኤን)፣ ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስም አቃቤሕግ ማንሳቱ ታውቋል።
ይሕ በእንዲህ እንዳለ ግን በአርበኞች ግንቦት 7 ስም የተከሰሱ በርካታ ተከሳሾች ክስአሁንም አልተቋረጠም።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በእነ ዶክተር መረራ ጉዲና ክስ መዝገብ በሁለት መገናኛ ብዙሃንና ሁለት ታዋቂ ግለሰቦች ላይ አቅርቦት የነበረውን ክስ ማንሳቱን ምንጮች ገልጸዋል።
በእነ ዶክተር መረራ ክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት)፣ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦ ኤም ኤን)፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር ሞሃመድ ክሳቸው ተቋርጧል።
ሁለቱ ታዋቂ ሰዎች በሌሉበት በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው አይዘነጋም።
የዶክተር መረራ ጉዲና ክስ ቀደም ብሎ በመቋረጡ ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል።
ዐቃቤ ሕግ የ137 ተከሳሾችን ክስ እንዳነሳ ነው የተገለጸው።
ይሕ በእንዲህ እንዳለ ግን በግንቦት 7 ተከሰው በማዕከላዊ ስቃይ የደረሰባቸው፣ ብልታቸው የተኮላሸው አስቻለው ደሴ እና ዮናስ ጋሻው ክሳቸው እንዳልተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል።
በተያየዘም የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህሩ ጌታ አስራደን ጨምሮ የበርካታ አማራ ተወላጆች ክስ አለመቋረጡን ምንጮች ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ያሉትን ክስ ከማቋረጥ ይልቅ ቀደም ብሎ ክሳቸው የተቋረጠላቸውን ስም በማካተት የብዙ ተከሳሾች ክስ እንደተቋረጠ ነው የተነገረው።
ከአሁን ቀደም ከእስር የተፈቱን አስቻለው አብርሃምና ሌሎች ተከሳሾችን ስም በማካተት ዐቃቤ ሕግ  ክሳቸውን አቋርጫለሁ ማለቱ የቁጥር ማሟያ ለማድረግ ነው መባሉን አዲስ አበባ የሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል።

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቀረቡ

Image may contain: 6 people, people smiling, text

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቀረቡ
 የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር መፈታታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያን ላዳረጉት ድጋፍ ቤተሰቦቻቸው ምስጋናቸውን ገልጸዋል። የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወ/ሮ የምስራች ሃይለማርያም እንዲሁም ታላቅ እህቱ ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ፣ ደስታቸውን በመግለጽ፣ ላለፉት 4 አመታት ህዝቡ ሲያደርገው ለነበረው ትግል ደስታቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ አርበኞች ግንቦት7 በአቶ አንዳርጋቸው መፈታት የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
ንቅናቄው “ በጓዳችን መፈታት ደስ ብሎናል፤ የሚጠብቀን ብዙ መሆኑን እናውቃለን” በሚለው መግለጫው፣ “አቶ አንዳርጋቸው ዛሬ ተፈቶ በጉጉት ከሚጠብቀው ሕዝብና ቤተሰቦቹ ጋር ሲቀላቀል ‘ሰው እየሳቀ ለመብቱም ለሕዝቡም መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ’ ብሎ መናገሩን የጠቀሰው መግለጫው፣ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ለሁሉም የህሊና እስረኞች መፈታት የበርካታ ዜጎች ሕይወት ማለፉን፣ ብዙዎች መታሰራቸውን ፣መደብደባቸውን፣ መሰደዳቸውንና ሰቆቃ የተፈጸመባቸው መሆኑን ገልጿል።
ትግሉ እሚፈለገው ግብ ላይ ለመድረስ ገና ብዙ መንገድ እንደሚቀረው የገለጸው የድርጅቱ መግለጫ፣ በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ የለውጥ ኃይሎች ለዚህ ድል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን እንደሚገነዘብም አትቷል።
አርበኞች ግንቦት7 አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጥረት ላደረጉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እንዲሁም ከጎናቸው ለቆሙ የውጭ አገር ዜጎችና ድርጅቶች ሁሉ ከፍተኛ ምስጋናውን አቅርቧል።
“ደስታችን የተሟላ የሚሆነው ወገኖቻችን የሞቱለት፣ የታሰሩለት፣ የተሰደዱለትና የተሰቃዩበት ዓላማ ሲሳካ ነው” ያለው መግለጫው፣ ዛሬም አቶ አበበ ካሴ፣ ሰይፉ አለሙ፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ ማስረሻ ሰጤ፣ መስፍን አበበ፣ አበበ ኡርጌሳ፣ ራቪድ ሳላ እና ሌሎች በርካታ ወገኖቻችን በእስር ላይ ይገኛሉ። ለእነዚህ ሁሉ ወገኖቻችን ነፃነት የምናደርገው ትግል አጠናክረን መቀጠል ግዴታችን ነው። “ ብሎአል።
“ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ የምናደርገው ትግል ገና በጅማሮ ላይ ያለው ነው። ዛሬ በአገራችን ያየነው መልካም ጅማሮ የኢትዮጵያን ሕዝብ እውነተኛ የስልጣን ባለቤት ወደሚያደርግ መሠረታዊ ለውጥ እንዲያመራ ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል” ሲል አሳስቧል።
ድርጅቱ በማጠቃለያው “ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ምክንያት ደስታችን ከፍተኛ ቢሆንም ከእንግዲህ የሚጠብቀን ትግል ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ መስዋትነት ሊጠይቅ የሚችል መሆኑን በመገንዘብ ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሀገሩ ባለሙሉ መብት ዜጋ እስኪሆን ትግሉን መቀጠል” አለበት ሲል ጥሪ አቅርቧል።

በአፋር ሰመራ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ


(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 21/2010)በአፋር ክልል ሰመራ ህዝባዊ ተቃውሞ ተደረገ።
የሰመራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በአፋር ያለው የመልካም አስተዳደር እጦት በመባባሱ ተቃውሞ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
እስራትና ማፈናቀል በአፋሮች ላይ እየተጠናከረ መሆኑን በመጥቀስም ህዝቡ ተቃውሞውን ሲያሰማ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በአፋር ክልል ሰመራና ሌሎች ከተሞች ህዝባዊ የተቃውሞ ጥሪ የሚያደርግ በራሪ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ተቃውሞ ሊኖር እንደሚችል ነው የኢሳት የመረጃ ምንጮች የገለጹት።

Monday, May 28, 2018

The windows 10 new features: Share files to nearby devices,use key board for Emoji,



This Windows 10 update contains a lot of new features. Start here.



To Share a picture with a nearby device
Open Photos  and select the picture you want to share. Select Share , then select the PC you want to share it to. On the other PC, select Save & Open when the notification appears.
Get back to something you were doing recently by finding it in your timeline.

Start browsing the web, writing emails, and using apps on your phone, then continue on your PC, instantly. Add your phone in Settings  > Phone .

To open your timeline, select Task View  on the taskbar, or press Windows logo key  + Tab. Scroll down until you find the thing you want to return to, and then click it to pick up right where you left off.



transfer  app PC to Phone 
Open the Google Play Store app on your Android phone, then type Microsoft Launcher in the search box and install it. Once installed, you can get beautiful Bing wallpapers that refresh daily, sync your Office docs and calendar, and more. 

To Add Emoticons, Emoji from your keybaord
Express yourself however and wherever you want. Press Windows logo key  + period (.) to open an emoji panel.

To write what you speak, Narration type from your mouth to window screen
On the touch keyboard, select microphone . On a physical keyboard, press Windows logo key  + H to dictate what’s on your mind.

Bildergebnis für new windows 10 features
Save time while type, writing
To see text suggestions while you type, select Start  > Settings  > Devices  > Typing  > Hardware keyboard > Show text suggestions as I type

Focus only one idea
Hide distractions while you work. Turn on focus assist to send notifications directly to action center. Select action center  on the taskbar > focus assist.

how to pin the sites you often visit
Get to websites from the taskbar. In Microsoft Edge, open a site, select Settings and more  > Pin this page to the taskbar.

በፓሪስ ከአራተኛ ፎቅ ቁልቁል ሊወድቅ የነበረን የአራት ዓመት ህጻን ልጅ የታደገው ማላዊ ስደተኛ፣ የፈረንሳይ ዜግነት ተሰጠው።


በፓሪስ ከአራተኛ ፎቅ ቁልቁል ሊወድቅ የነበረን የአራት ዓመት ህጻን ልጅ የታደገው ማላዊ ስደተኛ፣ የፈረንሳይ ዜግነት ተሰጠው።
 ማሞዱ ጋሴማ የተባለው ይህ ወጣት ማላዊ ከፎቅ ላይ ቁልቁል ሊከሰከስ የነበረን ህጻን በደረቱ ተስቦ በመውጣት የመታደጉ ዜና ከተሰማ በኋላ፣በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንና በመላው ፈረንሳውያን ዘንድ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ተችሮታል። በኤሊሴ በሚገኘው ቤተሰምንግስ ከፕሬዚዳንት ማክሮን ጋር ከተገናኘም በኋላ የፈረንሳይ ዜግነት ተሰጥቶታል።
ፕሬዚዳንቱ ከዚህም ባሻገር ለማሞዱ-ሜዳሊያ ያበረከቱለት ሲሆን፣ በሀገሪቱ እሳት አደጋ ብርጌድ ውስጥ እንዲሠራ ሀሳብ አቅርበውለታል።የማሊው ወጣት ማሞዱ፣ ከአስከፊና አደገኛ ጉዞ በኋላ ባለፈው ዓመት ሜዲትራኒያን ባህርን አቆራርጦ በጀልባ አውሮፓ መግባቱን ገልጿል። ፈረንሳውያኑ-በደረቱ እየተሳበ እስከ አራተኛው ፎቅ ድረስ በመውጣት የአራት ዓመቱን ህጻን የታደገውን ማሞዱን፣”ሸረሪቱ” የሚል ቅጽል ስም ሰጥተውታል።
Bildergebnis für spiderman paris

Sunday, May 27, 2018

የጅማ ከተማ ህዝብ በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የጀግና አቀባባል አደረገ።


የጅማ ከተማ ህዝብ በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የጀግና አቀባባል አደረገ።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) እጅግ በርካታ የከተማዋ ህዝብ በጅማ ስቴዲየም ተገኝቶ አህመዲን ጀበልን የተቀበለው ሲሆን፣ ከህዝቡ የተዋጣውን የገንዘብ ስጦታም አበርክቶለታል። ኡስታዝ አህመዲን “ ከዚህ በሁዋላ ውሸታም መሪ፣ አስመሳይ አስተዳደር የኢትዮጵያ ህዝብ አይፈልግም። እኔ ሁሉንም ዘር ሃይማኖት ሳልለይ እውዳለሁ።
ኦሮሞ ነኝ፣ ሙስሊም ነኝ፣ ሰው ነኝ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ከሁሉም ፋር የምጋራቸው ነገሮች ስላሉ ሁሉንም እወዳለሁ። በዘር ፣ በብሄር፣ በሃይማኖት አንለያይም” በማለት የህዝቡን ስሜት የገዛ ንግግር አድርጓል። ኡስታዝ አህመዲን ይህንን ህዝብ ፍቅር እንጅ ክላሽ አይገዛውም ያለው አቶ አህመዲን፣ ባለፈው ተቃውሞ ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 20 ሺ ብር በአጠቃላይ 100 ሺ ብር ለግሷቸዋል።

Tuesday, May 22, 2018

ለደቡብ ሱዳን ተወላጆች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሊሰጥ ነው


በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ተወላጆች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለመስጠት መወ ሰኑ ተቃውሞ አስነሳ።
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት በፌደራል መንግስቱ የተደረሰውን ስምምነት ለማስፈጸም ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል።
ለደቡብ ሱዳናውያን በጅምላ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጣቸው የተወሰነበት ይፋዊ ምክንያት አልተገለጸም።
የጋምቤላ የመብት ተሟጋቾች ዜግነት የሚሰጣቸው ደቡብ ሱዳናውያን ቁጥራቸው 400ሺህ እንደሚጠጋ ይገልጻሉ።
የኢትዮጵያውያን አኝዋኮችን ህልውና ለማጥፋት የሚደረገውን ሚስጥራዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያስቆም የመብት ተሟጋቾቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፈው ዓመት ነበር በኒውዮርክ የተባበሩት መንግስታት ስብስባ ላይ የተገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ችግር ለመፍታት የገንዘብ አቅም ባለመኖሩ በባህሪ፣በቋንቋ ከሚመሳሰሏቸው ጋር መቀላቀል በሚል በስደት ኢትዮጵያ ወስጥ ለሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለመስጠት የተስማሙት።
የአኙዋክ መብት ተከራካሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ይህ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ህዝብ ተደብቆ ሊፈጸም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ጠቅሰው የፊዴሬሽን ም ክር ቤት፣በርካታ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አባላት እንደማያውቁት ይጠቅሳሉ ።
አቶ አዜኑ ጀማል የስደተኞችና ከስደተኛ ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ዳይሬክተር ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር በመሆን ጋምቤላ ተጉዘው መናገራቸው ተጠቅሷል።የጋምቤላ ከልልም ይህንኑ የፌዴራል መንግስተን እቅድ ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተነግሯል።
በአሁኑ ሰዓት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች በስደተኝነት በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሲሆን ለምን ያህሎቹ የኢትዮጵያዊ ዜግነት እንደሚሰጥ በትክክል ባይታወቅም አንዳንድ ወገኖች ቁጥሩን በአስር ሺዎች ሲያደርሱት ሊሎች በመቶ ሺዎች ናቸው በማለት ይናግራሉ።
ለኢሳት ቃለምልልስ የሰጡት የአኙዋክ የልማት ማህበር ጸሀፊ አቶ ኡጁሉ ቻ በርካታ ደቡብ ሱዳናዊያን ከጋምቤላ ክልል መታወቂያ የወሰዱ ሲሆን የኢትዮጵያን ፓስፖርት የወሰዱም አንዳሉና በተለያዩ የዓለም ከፍል መኖራቸውን ያነሳሉ። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ አኙዋኮች ላይ የህልውና አደጋ ደቅኗልም የሚሉት የመብተ ተከራራሪዎቹ ።
ችግሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው የሚሉት አቶ ኡጁሉ ቻ የኢትዮጵያ ህዝብ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ሊጠይቅ ይገባዋል ብለዋል።
ከደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ድንበር ጥሰው የሚገቡት ደቡብ ሱዳናውያን በተዳጋጋሚ ግዜ የጋምቤላ አኝዋክ ተወላጆችን መግደላቸው፣አፍነው መውሰዳቸው ይታወቃል ።
በተዳጋጋሚ ግዜም በደቡብ ሱዳን ኑዌሮችና በኢትዮጵያ አኙዋኮች መካከል በድንበር አካባቢ በግጦሽ መሬት የተነሳ ከፍተኛ ጸብ መኖሩ ይነሳል ።
ይህ ሁኔታ ባለበት በሺዎች ለሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ኢትዮጵያዊ ዜግነት መስጠት ችግሩን የከፋ ያደርገዋል የሚሉት አቶ ኡጁሉ ቻ በሂደት የሕገመንግስት ጥያቄ እና የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ እንደማይነሳም ማረጋገጫ የለም ሲሉ እሳቸውና የአኝዋክ አክቲቪስቶች ስጋታቸውን ይገልጻሉ።

Prison's Davil የህወሀት የሠላዮች ዋና አዛዥ ጌታቸው አሰፋ ይህ ነው


ይህ ፎቶ አገር ውስጥ ከሚገኙ ተባባሪዎቻችን ያገኘነው መረጃ ሲሆን ከሶስት አመት በፊት የተነሳው ስለመሆኑ ከተጨማሪ መረጃ ጋር ልከውልናል ።
ብዙውን ጊዜ ራሱን ይደብቃል ያገር ውስጥም ሆነ የውጭ ካሜራዎችን ይሸሻል! ያላወቀ ጋዜጠኛ ድንገት ቢያነሳው ካሜራውን ነጥቆ ሲሰባብርም ታይቷል!!!በብዙ የንፁሀን ኢትዮጵያኖች ደም እጁ የተጨማለቀ ጨካኝ ሰው እንደሆነ ጓደኞቹ ሳይቀሩ ይናገራሉ! ይህ ነፍሰገዳይ ግለሰብ ነገ ለህዝባዊው ፍርድ ከሚቀርቡት ቀንደኛው ከሟቹ መለስ ቀጥሎ ያለ አረመኔ ሰው ነው።

ሐሰተኛው ነቢይ እስራኤል ዳንሳ የብዙ ሰዎችን ገንዘብ ያጭበረበርበት ሰነድ ይፋ ሆነ*

ሐሰተኛው ነቢይ እስራኤል ዳንሳ የብዙ ሰዎችን ገንዘብ ያጭበረበርበት ሰነድ ይፋ ሆነ**
**የኢትዮጵያ መንግስት እስራኤል ዳንሳን ካላሰረ ታምራት ገለታን ይፍታው ሁለቱም የሕግ የበላይነትን የሚቃረን ማጭበርበር የፈጸሙ ወንጀለኞች ናቸው ።***
መ/ር ታሪኩ አበራ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ነቢይ ነኝ ብሎ ሕዝብ ሲያጭበረብር የነበረውና ሐሰተኛነቱ ሲታወቅበት ደግሞ ሐዋርያ ነኝ በማለት በቅሰጣ ሥራ ላይ የተሰማራው እስራኤል ዳንሳ ቀድሞ ይሰራበት ከነበረው ወላይታ ሶዶ ባንክ ቤት በተለያየ ጊዜ ሲፈጽም በነበረው የስርቆትና የማጭበርበር ወንጀል ከመስሪያ ቤቱ በከፍተኛ ውርደት የተባረረበት ሰነድ ከተደበቀበት ይፋ ሆኗል።
ይህ ግለሰብ ከፍተኛ በሆነ ፍቅረ ንዋይ ኅሊናው የደነዘዘበት ሰው ሲሆን ሰይጣን በገንዘብ ፍቅር የማረከውን ልቡን ለማርካት የተለያዩ ዘዴዎችን ሲጠቀም የኖረና በቅርብ ጊዜ ደግሞ ከጠንቋዮች ባገኘው መተትና ድግምት በመታገዝ ብዙዎችን በእምነት ስም እያታለለ የጽድቅና የድኅነት መንገድ የሆነውን ወንጌልን በሐሰት በመሸቃቀጥ በአቋራጭ ለመክበር ሕዝብን በማተለል ላይ የተሰማራ ወንጀለኛ ነው።
የወንጌላውያን ኅብረት ጽ/ቤት በተደጋጋሚ እንዳሳወቀው ግለሰቡ በተለያዩ ጊዜያት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም ተገኝቶ ጥፋተኛነቱ በሰውና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠበት በመሆኑ ሕብረቱ በይፋ ሐሰተኛ ነቢይነቱን ለሕዝብ አሳውቋል ።
የኢትዮጵያ መንግስት እንዲህ ዓይነቱን ለሀገርና ለወገን ጠንቅ የሆነን ወንጀለኛን በሕግ ጥላ ሥር በማዋል በሀገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ሕዝብን ከዘረፋና ከመጭበርበር ሊጠብቅ ይገባል።
አጭበርባሪነት በሃይማኖት ኃጢአት፣በባህል ነውር፣በሕግ ወንጀል የሆነ እኩይ ምግባር በመሆኑ የሀገሪቱ ሕግ አስከባሪ አካል ሰንዶችን ሰብስቦ በአስቸኮይ ፍትሕ ሊሰጥ ይገባል።
እምነትን ከለላ አድርገው በሃገሪቱ ውስጥ ሕዝብን እያጭበረበሩና በሐሰት እያምታቱ ያሉት ሐሰተኛ ነቢያት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሕግ ቸልተኝነት በመመልከት በአደባባይ በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ውስጥ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን በመጣስ የሞራልና የሥነ ምግባር ብልሹነትን በሕብረተሰቡ ዘንድ በስፋት እያስፋፋ ይገኛሉ።
ስለሆነም የኢትዮጵያ የሕግ አስፈጻሚ አካላት የጎረቤት ሀገሮችን ተሞክሮ ከግንዛቤ በማስገባት በሐሰተኛ ነቢያት ላይ የማያዳግም ፍትሐዊ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።
እሥራኤል ዳንሳ ቀሳጢ የጥፋት ልጅ በመሆኑ እርሱን እውነተኛ ነቢይ ነው ብላችሁ
የምትከተሉ ሰዎች የወንጀሉ ተባባሪ በመሆን በእግዚአብሔር ላይ እያመጻችሁ ነውና ፈጥናችሁ ንስሐ ግቡ ራሳችሁንም ለዩ
No automatic alt text available.
እባካችሁ ይህንን መልህክት ሼር በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ እናድርግ።

Image may contain: 1 person, sitting
No automatic alt text available.

Monday, May 21, 2018

ኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅሟ በመዳከሙ የአጭር ጊዜ ብድር መውሰድ አቆመች

 ኢትዮጵያ ባጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት የተነሳ የተበደረችውን ብድር በወቅቱ ለመክፈል አቅሟ እየተዳከመ መምጣቱን ተከትሎ በአጭር የክፍያ ጊዜና በከፍተኛ የወለድ መጠን የሚሰጡ ብድሮችን መበደር ማቆሟን የገንዘብ ሚኒስትሩ ለሪፖርተር ተናግረዋል። አገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች በቂ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች ተብሎ ቢታቀድም እቅዱ ሊሳካ አለመቻሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በአጭር ጊዜ የሚመለስ ብድሮችን ከምዕራባውያን ባንኮች፣ ከቻይናና ከሌሎችም አገሮች በከፍተኛ ወለድ ስትበደር ቆይታለች። እነዚህ ብድሮች ብዙዎቹ የመክፈያ ጊዜያቸው በመድረሱ አገሪቱ ለወለድና ለዋናው ብድር ክፍያ ከፍተኛ ወጪ እያወጣች ነው። አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ የእዳ ጫና አሳሳቢ መሆኑን በመግለጽ፣ እጅግ ከፍተኛ የእዳ ጫና ካለባቸው አገሮች ተርታ የመደባት ሲሆን፣ መንግስት ብድር ለመውሰድ ያለውን ፍላጎት እንዲያጤነው መክሮ ነበር። ኢትዮጵያ በራሷ ፍላጎት የአጭር ጊዜ ብድሮችን መውሰድ ታቁም ወይም አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ለማበደር ፈቀደኛ ሳይሆኑ ይቅር የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ የቻይና ባንኮች ለኢትዮጵያ የሚሰጡት ብድር ይመለሳል የሚል እምነት እያጡ በመምጣታቸው፣ በአሁኑ ሰአት ከዚህ በፊት ያደርጉት እንደነበረው ለኢትዮጵያ በቀላሉ ለማበደር ፍላጎታቸው እየቀነሰ ነው። ባለፉት 2 ዓመታት በአገሪቱ የታየው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቀቃሴ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል። በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞና በሌሎች ምክንያቶች ወደ አገሪቱ የሚልኩት ገንዘብ በመቀነሱ ለውጭ ምንዛሬው መባባስ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። የአገሪቱን ዋና ዋና የሚባሉ ባለሀብቶች ገንዘባቸውን በማሸሻቸው ለውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። በአገሪቱ የሚታዬው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ያሳሰባቸው ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ በውጭ ባንኮች ገንዘብ ያስቀመጡ ባለስልጣኖቻቸውን አካውንት እንደሚያስመረምሩ፣ በዱባይና ሌሎችም አገራት ገንዘባቸውን ያስቀመጡ ባለሃብቶች ገንዘቡን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመልሱ፣ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ገንዘብ ወደአገራቸው እንዲልኩና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው ነበር። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አዲሱ ጠ/ሚኒስትር መሰረታዊ የሆነ የፖለቲካ ለውጥ እስካላመጡ ድረስ የዶላር ተአቆቦ ጥሪያቸውን እንደሚያስቀጥሉ በመግለጽ ላይ ናቸው። የዶላር እጥረቱን ተከትሎ በርካታ ፋብሪካዎች ስራ በማይሰሩበት ደረጃ ደርሰዋል። ስርዓቱ አብዛኛውን የውጭ ምንዛሬ ራሱ ላወጣቸው ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚያውል በመሆኑ፣ የግል ባላሀብቶች ዋነኛ ተጎጂዎች መሆናቸውን ይናገራሉ። ብዙዎቹ እቃዎችን እንደ ልብ ለማስገባትና የጀመሩዋቸውን ግንባታዎች ለማስፈጸም እንደተቸገሩ ሲገልጹ፣ በስራ ላይ ያሉት እንዱስትሪዎች ደግሞ ሰራተኞችን እስከመ መቀነስ የሚደርስ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ዶላር በጥቁር ገበያ እስከ 40 ብር እየተመነዘረ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

Thursday, May 17, 2018

ትግራይ ውስጥ የታሰሩት ዳግማዊውን ሊቁ አለቃ ተክሌ ሊፈቱ ይገባል | በዲ/ን ዳን ኤል ክብረት


‹አራቱ ኃያላን› የተባለውን መጽሐፍ በ2006 ዓ.ም. ጎንደር ላይ ስንመርቅ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ መሪጌታ እንደ ሥራቸው ስለሚባሉ የተክሌ አቋቋም ሊቅ አንሥተው ‹የተክሌ አቋቋም ከጊዜ በኋላ ቢጠፋ ወይም እኔ አንድ ነገር ብሆን ብለው 9 ካሴት የሚሆን ዜማ በካሴት ቀርጸው አስቀምጠዋል› ሲሉ ተናገሩ፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም ‹እንደሥራቸው መቋሚያ ይዞ ሲዘም እንኳን ሰዎች ንቦች ይመሰጣሉ› ሲሉ ስለ እርሳቸው መሰከሩ፡፡
ከዚያ በኋላ ‹እንደሥራቸው› ማን ናቸው? የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ ይመላለስ ጀመር፡፡ በተለያየ አጋጣሚ የደብረ ታቦርና የተክሌ አቋቋም ሊቃውንትን ባገኘሁ ቁጥር እኒህን ሊቅ በተመለከተ እጠይቃቸው ነበር፡፡ ሁሉም የሚመሰክሩልኝ ‹ከአለቃ ተክሌ በኋላ የመምህር እንደሥራቸውን ያህል አቋቋምን የሚያውቀው የለም› በማለት ነው፡፡ ዛሬ በቦታው የሚገኙት የደብረ ታቦር ኢየሱስ አለቃ መልአከ ታቦር ኃይለ ኢየሱስ ፋንታሁንና የተክሌ ምስክሩ የኔታ መርሻ መምህር እንደሥራቸውን ሲያነሡ ዕንባ ይቀድማቸዋል፡፡ በምስክር ትምህርት ቤቱ ዛሬም ‹የእንደ ሥራቸው ዜማ› እየተባለ የእርሳቸው ስልት ይሰጣል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የድጓና የአቋቋም ሊቃውንት አስተያየት ሊቁ እንደሥራቸው በዜማ ዕውቀታቸውና ስልታቸው ከተድባበ ማርያሞቹ አዛዥ ጌራና አዛዥ ራጉኤል፣ ከቤተ ልሔሙ እጨጌ ቃለ ዐዋዲ ጋር የሚተካከሉ ናቸው፡፡

ከአቶ አግማሴ መኮነንና ከወ/ሮ ሙሉነሽ ዓይናለም በ1939ዓ.ም. ሚያዚያ 23 ቀን በደብረ ታቦር አካባቢ ልዩ ስሙ ‹ሰላምኮ› በተባለ ቦታ ተወለዱ፡፡ በዚህም የተነሣ አምኃ ጊዮርጊስ ተባሉ፡፡
በእናት አባታቸውና በዘመድ አዝማድ በጣም ብርቅና ድንቅ የሆኑ ልጅ ነበሩ፡፡ መጀመሪያ በአካባቢያቸው ከነበሩ መምህር አባ ባያፈርስ ከመምህር መርሻ ዓለሙ ጋር ከፊደል እስከ ፆመ ድጓ ተምረዋል፡፡ ቀጥለዉም ፀዋትዎ ዜማ ከአለቃ ማኅተም ጌጤ፤ ቅኔ ወረታ አካባቢ ከሚገኙት መሪጌታ ጌቴ ተምረዋል፡፡ እንደገናም ከመምህር ጥበቡ ቅኔና ምሥጢር አደላድለዋል፡፡ የተክሌን አቋቋም ከአለቃ ማኅተም ጌጤ ካጠኑቁ በኋላ አዛወር ኪዳነ ምሕረት ከመሪጌታ ጀንበር ድጓን እንደ ገና ተምረውታል፡፡ ቀጥለውም ታች ጋይንት ከምትገኘው የኢትዮጵያ የድጓ ዩኒቨርሲቲ ቅድስት ቤተ ልሔም ገብተው ድጓን ከመምህር ጥበቡ አስመስከረው የድጓ መምህር ሆነዋል፡፡
ሊቁ እንደሥራቸው ድጓን አስመስክረው ከተመረቁ በኋላ በደብረ ታቦር ኢየሱስ የተክሌ አቋቋም ምስክር ከሆኑት ከአለቃ ቀለመ ወርቅ ይማም የተክሌ ዝማሜን ጥሩ አድርገው ተምረው አስመስክረዋል፡፡ በቅድስት ቤተልሔም በዐቢይ ጾም ዝማሜ ይሰጥ የነበረው ለመምህር እንደሥራቸው እንደ ነበር የሚያስታዉሱ ሊቃውንት አሉ፡፡ መምህር እንደሥራቸው ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጸሎተ ሃይማኖትን በዝማሜ በሚዘምሩበት ጊዜ ንብ ከእጃቸው ላይ ያርፍባቸው እንደ ነበር የዓይን ምስክሮች ዛሬም በአድናቆት ይተርኩታል፡፡
ወደ ጎንደር ከተማ ከመጡ በኋላ በጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በጎንደር ለማንም የማይሰጠው የተክሌ ዝማሜ ለመምህር እንደሥራቸው ይሰጥ ነበር፡፡ ጎንደር በነበሩበት ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ የታሪክ፣ የሂሳብና የዜማ መምህር በመሆን ሰፊ አገልግሎት ፈጽመዋል፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ፤ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ የሊቃውንት ጉባዔ ሰብሳቢ፤ ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት መንክር መኮነን የጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም የአራቱ ጉባኤ መምህር የነበሩት፤ ክቡሩ ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ የጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም የአራቱ ጉባዔ መምህር እኒህን ሊቅ ሲያስታውሱ በቁጭት፣ በግርምትና በዕንባ ነው፡፡
ከዚህ አልፈው በጎንደር የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ዋና የአስተዳዳር ክፍል ሆነው ያገለገሉት ሊቁ እንደሥራቸው 2 ሴት ልጆችና 7 ወንድ ልጆች አሏቸው፡፡
እኒህ በጳጳሳቱ የተፈቀሩ፤ በሊቃውንቱ የተደነቁ፣ በካህናቱ የተወደዱና በምእመኑ የተናፈቁ ሊቅ ድንገት በሐምሌ 1986 ዓ.ም. የውኃ ሽታ ሆነው ጠፉ፡፡ ይህም የተክሌ ዝማሜ ሊቃውንትንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን አስደነገጠ፡፡ አንዳንዶቹ መንነዋል ሲሉ አንዳንዶቹ ተሠውረዋል አሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ሞተዋል ሲሉ ደመደሙ፡፡
ቤተሰቡ፣ ወዳጆቻቸው፤ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት፣ ምእመናንና ታሪክና ኪነ ጥበብ ወዳጆች ሊቁን እንደሥራቸውን ፍለጋ አገሩን ማሰሥ ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም ጉዳዩ እንዲህ ሆኖ ተገኘ፡፡
ሐምሌ 12 ቀን 1986 ዓ.ም. ሲሠሩበት ከነበረው የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ቢሮ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የሆኑ ሰዎች ይቀርቧቸውና ወደ መኪናቸው ያስገቧቸዋል፡፡ ከሌሎች የታፈኑ ሰዎች ጋር ጎንደር ራስ ግንብ ተብሎ ወደሚጠራው እሥር ቤት ይወሰዳሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ያያቸው የለም፡፡ ከሦስት ቀናት በኋላ ቤተሰቦቻቸው ጭንቀት ውስጥ ወደቁ፡፡ ‹‹የእስር ቤቱ ጠባቂ ያውቃቸው ስለነበር፣ ማታ ማታ የታሠሩበትን ሰንሰለት ያላላላቸው ነበር፡፡ በቅዳጅ ወረቀት መታሠራቸውንና ከእርሳቸው ጋር የነበሩት እንደተገደሉ፣ ከእርሳቸው ላይ ሲደርስ ግድያ አቁሙ የሚል ትእዛዝ መድረሱን፣ ጠቅሰው መልእክት በእሥር ቤት ጠባቂው በኩል ለቤተሰብ ላኩ፡፡ በወቅቱም ባለቤታቸውና ትልቁ ልጃቸው ለማስፈታት ጥረትም ቢያደርጉ የሚሰማቸው አካል አጡ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የት እንደተወሰዱ ሳይታወቅ እንቆቅልሽ ሆኖ ቀረ› ይላሉ ታሪኩን የሚያውቁት የአካባቢው ሰዎችና ቤተ ዘመዶች፡፡
መምህር እንደሥራቸው ዛሬም በሕይወት በአንድ እሥር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ከእሥር ተፈትተው ለቤተሰቦቻቸው መረጃ የሰጡ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ አንዳንዶችም በአካል ባያዩዋቸውም ዜማቸውን መስማታቸውን መስክረዋል፡፡ እነሆ ከተሠወሩ 24 ዓመት ሆነ፡፡ ሀገሪቱ ብዙ ዘመናትን አሳለፈች፡፡ አሳልፋም አይለቀቁም የተባሉ የፖለቲካ እሥረኞችንም ለቀቀች፡፡ እኒህ ሰው ቢፈረድባቸው እንኳን እስከ ዛሬ ሊፈቱ ይገባ ነበር፡፡ ሀገሪቱ ካለፉት ዘመናት ችግሮቿ ራሷን ለማላቀቅ በምትጥርበት በዚህ ዘመን ሊቁን መምህር እንደ ሥራቸውን ያሠረ አካል እንዲፈታቸው በልዑል እግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ፡፡ በሕይወት መኖራቸው ይታወቃል፡፡ እኒህን ሊቅ በዚህ ሁኔታ ጠፍተው እንዲሞቱ ማድረግ የተክሌ አቋቋምን መግደል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይም የሞት ፍርድ መፍረድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ መከራ መሸመት ነው፡፡ ምናልባት ያጠፉት ነገር አለ ቢባል እንኳን 24 ዓመት ከበቂ በላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሕግ የእድሜ ልክ የተፈረደበት ሰው እንኳን የሚታሠረው 25 ዓመት ነው፡፡ ይህ ወቅት የይቅርታና ንስሐ ነው ይባላል፡፡ ይቅርታና መሻሻል ደግሞ ያለፉትን ስሕተቶች ከማረም ይጀምራል፡፡ አያሌ ሊቃውንትና ደቀ መዛሙርት ‹ወደፊት የኔታ እንደ ሥራቸው ሲመጡ እንቀጽለዋለን› እያሉ ዛሬም በጉጉትና በጸሎት ይጠብቋቸዋል፡፡
ዳግማዊውን አለቃ ተክሌን መልሱልን፡፡
(ዳንኤል ክብረት ጥሩ ፅፎ ሊቁ ትግራይ ውስጥ መታፈናቸውን እያወቀ “አንድ እስር ቤት” ብሎ አልፎታል። ጎንደር የታሰሩበትን ገልፆአል። የትግራዩን እስር ቤት በስም ሳይጠቅስ አልፎታል። ይህን ያህል ምን እንደሚያስፈራ ግራ ያጋባል። ሊቁ የሚማቅቁበትን፣ እኛ ለምን መግለፅ እንፈራለን?)

Wednesday, May 16, 2018

ጠቅ/ሚኒስትሩ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሀገር ቤቱ የውጩ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕርቀ ሰላሙ ሥምረት ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታወቁ

በግላቸውም ኾነ በመንግሥት ደረጃ፣ለዕርቀ ሰላሙ ሥምረት ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታወቁ

አንዲትና ታላቅነቷ የተጠበቀ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የማየት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ
“ለአንድነት ታሪካዊ ሚና ያላት ተቋም፣ራሷ መከፋፈሏ ለብሔራዊ ተግባቦቱ ተግዳሮት ነው፤”
“ልዩነቱ ምንም ቢኾን የማይፈታ አይደለም፤ችግር ፈቺዎቹ ከተቸገሩ ትልቁ ችግር እርሱ ነው፤”
“በጥረታችሁ ግፉበት፤ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን፤ልዩነቱን ሥበሩና ለኛም አርኣያ ኹኑን፤”
“የልኡካን አባቶችን ስጋት የሚያስወግድና የሰላም ኮሚቴውን የሚያበረታታ ነው፤”/ታዛቢዎች/

†††
በውጭ ሀገር በስደት በሚኖሩት አባቶች ከተቋቋመው ሲኖዶስ ጋራ ለተጀመረው የዕርቀ ሰላም ጥረት መሳካት፣ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ኹሉ እንደሚሰጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ትላንት ቅዳሜ፣ ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ረፋድ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሯቸው ሲኾን፤ ቅዱስነታቸውና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ አንድነት ለማስጠበቅ በጀመሩት የዕርቀ ሰላም ጥረት እንዲገፉበት አሳስበዋል፤ለሥምረቱም መንግሥታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
ለሀገራችን ኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላት ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሲኖዶሳዊ አስተዳደሯ መከፋፈሏ በግላቸውም ቢኾን እንደሚያሳዝናቸው ያልሸሸጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ አንዲትና ታላቅነቷ የተጠበቀ የተጠናከረች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ማየት ፍላጎታቸው እንደኾነ ለቅዱስነታቸው ገልጸውላቸዋል፡፡
በሀገራችን ለግጭት መንሥኤ የኾኑ ልዩነቶችን በጋራ ለመፍታት እየተደረገ ባለው ጥረት፣ ለሀገራዊ አንድነት መጠበቅ ታሪካዊ ሚና ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሷ በማዕከላዊ አስተዳደሯ ለሁለት መከፈሏ፣ ለብሔራዊ ተግባቦቱ ትልቅ ተግዳሮት በመኾኑ በተጀመረው የአባቶች ዕርቀ ሰላም ጥረት መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
“ልዩነቶቹ በተለያየ ምክንያት ተከሥተው ሊኾን ይችላል፤ ነገር ግን ለመፍታት የማይቻሉ አይመስለኝም፤ ይቻላል፤ ሃይማኖታዊ ሰው ደግሞ አይደለም የውስጡንና የራሱን፣ የሌሎችንም ችግር መፍታት አይሳነውም ተብሎ ነው የሚታመነው፤” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አያይዘውም፣“የሌሎችን ችግር ይፈታሉ የተባሉት ችግር ፈቺዎቹ ራሳቸው ከተቸገሩና ሌላ ችግር ፈቺ ካስፈለጋቸው ትልቁ ችግር የሚኾነው እርሱ ነው፤” በማለት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ልዩነቷን ለማስወገድ በያዘችው ጥረት እንድትቀጥልበት አበረታታዋል – “እንደ ግልም እንደ መንግሥትም ከእኛ የሚፈለገውን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን፤ እናንተ ግን ግፉበት፤ ይህን ልዩነት በመሥበር ለእኛም አርኣያ ኹኑን፤”ብለዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ስለ ማበረታቻ ሐሳባቸውና አቋማቸው በማድነቅና በማመስገን፣ በውጭ ከሚኖሩት አባቶች ጋራ የተጀመረው ዕርቀ ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ በየጊዜው ስላደረጋቸው ጥረቶች አብራርተውላቸዋል፤ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ባጠናቀቀው የግንቦቱ ርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤውም፣በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው የሰላምና አንድነት ኮሚቴ፣ ከቀድሞው በተሻለ አያያዝ ሒደቱን ለማስቀጠል ላቀረበው ጥያቄ ይኹንታውን በመስጠት የሚነጋገሩ ልኡካን አባቶች መሠየሙንም ነግረዋቸዋል፡፡
ትላንት ማምሻውን፣ ከአማራ ክልል የመጡና የባሕር ዳር ልዩ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት፣ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ባደረጉት የራት ግብዣ ላይም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልእክት፤ ለሀገር አንድነት ለመሥራት የሃይማኖት ተቋማት ውስጣዊ አንድነት ወሳኝ መኾኑን በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡ መድኃኒቱ ራሱ ሲበከል መጥፎ በመኾኑ፣ ውስጣዊ ችግራቸውን በራሳቸው በመፍታት ለሀገራዊ ተግባቦት መጠናከር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት በጋራ እንዲሰለፉ አሳስበዋል፡፡
ስለጉዳዩ የተጠየቁ አስተያየት ሰጭዎች፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ አስተዋፅኦ በመነሣት ለሲኖዶሳዊ አንድነቷ መጠበቅ ያሳዩት መቆርቆር እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፤ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ወደ ጽ/ቤታቸው በመጥራት ማበረታታቸውም፣ ቢያንስ ሦስት ፋይዳዎች እንዳሉት አመልክተዋል፡፡ በመንግሥት እያመካኙ ወይም መንግሥት እንዲህ ሊያስብ ይችላል፤ እያሉ ወደ ኋላ የሚሉትንና በዕርቀ ሰላሙ ሒደት ላይ ሻጥር የሚፈጥሩትን የሀገር ቤት አካላት ያስታግሣል፤ የሚለው የመጀመሪያው ነው፤ በውጭ ባሉትም ዘንድ፣ “ዕርቀ ሰላሙን መንግሥት አይፈልገውም፤” የሚለውን ስጋታቸውን ያስወግዳል፤ ከዚህም ጋራ ተያይዞ፣ የዕርቀ ሰላም ሒደቱን በተሻለ አያያዝ ለማስቀጠልና ከዳር ለማድረስ ተነሣሽነቱን ለወሰዱ ሁለተኛው ዙር ዓለም አቀፍ የሰላምና አንድነት ኮሚቴ አባላት ጉልበት ይኾናቸዋል፡፡
የሀገር ቤቱ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሚያዝያ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሔደው የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ ስብሰባው፥ ለዕርቀ ሰላሙ እንዲነጋገሩ፣ በብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሚመሩ ሦስት አባቶችን የሠየመ ሲኾን፤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው የውጩ ሲኖዶስም፣ ከጥቅምት 22 እስከ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በኮለምበስ ኦሃዮ ባደረገው ጉባኤ፣ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሊቀ ጳጳስ የሚመራ ሦስት አባላት ያሉት ተደራዳሪ ልኡክ ሠይሟል፤ “እግዚአብሔር ይጨመርበት፤ አምላከ አበው ሥራችሁን የተቃና ያድርግላችሁ፤” ሲልም ለሰላምና አንድነት ኮሚቴውቡራኬውን ሰጥቷል፡፡ በተለያዩ ሀገራት ቅርንጫፎችን በማቋቋም የሚንቀሳቀሰው፣ሁለተኛው ዙር የሰላምና አንድነት ዓለም አቀፍ ኮሚቴ፣ ልኡካን አባቶች የሚገናኙበትንና ድርድሩ የሚካሔድበትን ቦታና ጊዜ በቅርቡ ለኹለቱም ወገኖች እንደሚያሳውቅ መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
Source: ሐራ ዘተዋሕዶ

Tuesday, May 15, 2018

እነዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ዛሬ ከእስር ቤት ወጡ



(ዘ-ሐበሻ) ቅሊንጦን በማቃጠል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 464 እና 494 በመተላለፍ ተከላከሉ ተብለው በተፈረደባቸው በነጋታው ክሳቸው እንዲደተነሳላቸውና እንደሚለቀቁ የተነገረው እነ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ዛሬ ከ እስር ቤት መውጣታቸው ተዘገበ::
ክስ ተቋርጦላቸዋል ተብሎ ሲነገር የነበረው 62 ተከሳሾች የነበሩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ምን ያህሉ በዛሬው ዕለት እንደተለቀቁ ለማወቅ አልቻልም:: ሆኖም ግን ከተፈቱት መካከል ዶክተር ፍቅሩ ማሩ; አግባው ሰጠኝ; ሲሳይ ባቱ; ፋሲል አለማየሁ እንዲሁም ከበደ ጨመዳ እንደሚገኙበት ለማረጋገጥ ችለናል::
በእነ ማስረሻ ሰጠኝ መዝገብ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ጉዳያቸው ሲታይ ከነበሩት 38 ተከሳሾች ደግሞ፤ አራቱ በሰው መግደል ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው እንዲከላከሉ፤ ስምንቱ ግን በነጻ እንዲሰናበቱ መወሰኑ ይታወሳል።

Monday, May 14, 2018

Ethiopia: Andargachew Tsige To Be Released From Prison

Andargachew Tsige To Be Released From Prison

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንደሚፈታ መወሰኑ ውሳኔ ተላለፈ

በእስርና እንግልት ላይ የነበረውን የአርበኞች ግንቦት ስባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ከእስር ለመፍታት ተወስኖ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የተመራ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመለከቱ።
መረጃውን ለዋዜማ ያደረሱና ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደነገሩን አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈታ ውሳኔ ከተላለፈ በርካታ ቀናት ተቆጥረዋል። በቅርቡ ከእስር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።
አንድ የፍትሕ ሚንስቴር ባልደረባ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ጉዳዩ በመስሪያ ቤታቸው አካባቢ መነጋገሪያ እንደነበርና ጉዳዩ በከፍተኛ ባለሥልጣናት በኩል በምስጢር ተይዞ ቆይቷል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ሲፈታ በቀጣይ በሚኖራቸው የፖለቲካ ሚና ላይ ንግግር መደረግ አለበት ብለው የሚያምኑ ወገኖች እንዳሉ የነገሩን እኚሁ ግለሰብ በማረሚያ ቤቶች፣ በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ፣ ግንባሩ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ብድኖች እና በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽሕፈት ቤት መካከል መግባባት ለመፍጠር እየተሞከረ መሆኑን መስማታቸውን ነግረውናል። በአንዳርጋቸው ጉዳይ በአራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች መካከል ስለነበረ ውይይት ብዙ የተሰማ ነገር የለም። ይሁንና ብአዴን የሚደርስበትን የሕዝብ ጫና ለማስታገስ የአንዳርጋቸውን መለቀቅ ሳይገፋፋ እንዳልቀረ ይገመታል።
ስለጉዳዩ ከአንዳርጋቸው ቤተሰቦችም ሆነ ከአርበኞች ግንቦት 7 እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ወሬው ባለፉት 3 ቀናት በስፋት መሰማት የጀመረው ውሳኔውን በተለያየ ደረጃ ያሉ ሰዎች እንዲያውቁት በመደረጉ ሊሆን እንደሚችል የዋዜማ ምንጮች ተናግረዋል። የአቶ አንዳርጋቸው መፈታት በድርጅታቸው፣ አልፎም በአገሪቱ ፖለቲካ አቅጣጫ ላይ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ ብዙዎች በቅርበት የሚከታተሉት ጉዳይ ይሆናል።
አቶ አንዳርጋቸው ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ከሰንአ አውሮፕላን ጣቢያ በየመን እና በኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ሰራተኞች ታፍኖ መወሰዱ ይታወሳል። በእስር ላይም የተለያዩ ግፍና ማሰቃየት እንደተፈጸመበት ቤተሰቦቹ እና የትግል ጓዶቹ ይናገራሉ። በተቃራኒው፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ ቀርበው አንዳርጋቸው በጥሩ ሁኔታ መያዙን እንዲያውም “ከተማ ይጎበኛል፣ ላብቶፕ ተሰጥቶች መጽሐፍ እየጻፈ ነው” ብለው መናገራቸው ይታወሳል። ተመድ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የእንግሊዝ መንግሥት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አንዳርጋቸው እንዲፈታ ሲጎተጉቱ መቆየታቸው ይታወቃል።
#ዋዜማ ራዲዮ#

Sunday, May 13, 2018

መንግስት ከሌንጮ ለታ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ጋር ስላደረገው ድርድር መግለጫ ሰጠ



ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚ/ር የተሰጠ መግለጫ:
ራሱን የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ብሎ ከሰየመው ግንባር ጋር ስለተካሄደው ውይይትና ድርድር ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ፡፡
ይህች ሀገር የሁሉም ኢትዮጰየዊ የጋራ ቤት ናት፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊም ይህችን ምትክ የሌላት ቤቱን ሰላሟን የመጠበቅ፣ ለብልጽግናዋ የመትጋት፣ ወደፊት ያራምዳታል ብሎ ያሰበውን አመለካከትም በግሉ እና በቡድን በመሆን የማራመድና ተከታዮችንም የማፍራት ህገመንግስታዊ እና እንደዜጋም ያለገደብ የሚጠቀምበት ሙሉ መብት እንዳለው ይታወቀል፡፡ ይህ ሁሉ ለሀገር እና ለወገን የሚበጅ ተግባር የምንጠብቀውን እና የምንናፍቀውን መልካም ውጤት ሊያስገኝልን የሚችለው በህግ እና በስርዓት ማእቀፍ ውስጥ ሲከናወን ብቻ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስትም የአገራችንን ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ያላሰለሰ ጥረትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ በዚህም የአገራችንን ህገ-መንግስት ተቀብለውና በህጋዊ የመጫወቻ ሜዳ ላይ ሆነው በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ አቋማቸውን ማራመድ ከሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶች/ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ ለመወያየትና ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን በየጊዜው ሲያሳውቅ ቆይቷል፡፡ በቅርቡም መንግስት ለተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የሰላም ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት ምንም እንኳን ከዚህ በፊት የተካሄዱት መሰል ውይይቶችና ድርድሮች ፍሬያማ ያልነበሩ ቢሆኑም በአሁኑ ወቅት የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ፖለቲካዊ አሰላለፉን ከኦነግ ከለየውና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴፍ) በሚል ስያሜ ራሱን በመጥራት ከሚንቀሳቀሰው ግንባር ጋር ባካሄዱት ውይይትና ድርድር ድርጅቱ ከመንግስት የቀረበለትን ጥሪ አክብሮ፣ ህገ-መንግስቱን በማክበር በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ ይህ የግንባሩ አቋም በመንግስት በኩል ከከፍተኛ አድናቆት ጋር ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ አጠቃላይ ውይይቱ የተሳካ፣ ጥሩ አገራዊ መንፈስና መግባባትም የሰፈነበት ነበር፡፡ ይህንን በሰከነ፣ ሀገር እና ህዝብን ባስቀደመ እና በሰለጠነ መንገድ የሚደረግን ውይይት እና ድርድር መንግስት የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል፤ ሰላማዊ በሆነ መስመር መታገልም ውጤታማ ያደርጋል ብለው ከሚያምኑ አካላት ጋር በቀጣይም ውይይትና ድርድር ለማድረግ በጽኑ ይፈልጋል- ለተግባራዊነቱም አበክሮ ይሰራል፡፡
የኦዴፍ ከፍተኛ አመራሮችም በቅርብ ቀናት አዲስ አበባ እንዲገቡም ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ቀሪዎቹ ውይይቶችም እዚሁ አዲስ አበባ እንደሚደረጉ ይጠበቃል፡፡ ለወደፊቱም ህገመንግስቱን ባከበረ አና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በሀገራቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ ከሚፈልጉ አካላት ጋር ለመወያየት እና ለመደራደር መንግስት ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡
ግንቦት 6/2010 ዓ.ም

wanted officials