ከፌዴሬሽኑ ውስጥ አዋቂ በተገኘ መረጃ የጨዋታው ኮሚሽነር በቀረበ ጥያቄና የኮማንድ ፖስት አዋጁን በመተላለፉ ትላንትና ምሽት ለጥያቄ ወደ 3ኛ ፖሏስ ጣቢያ ተወስዶ ቃሉን ከሰጠ በኋላ በዋስ ተለቋል። ክለቡ ወልዋሎ በዲሲፕሊን ቀልድ አላውቅም በሚል ከስራ ያሰናበተው ቢሆንም የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጠንካራ በትር ይጠብቀዋል።
በሌላ በኩል ኳሷን መያዝ አቅቶት መስመሩን በማለፏ ስህተቱን ለመሸፈን የጨዋታውን አቅጣጫ ያስቀየረው በረኛው በረከት ላይ ከባድ ቅጣት እንዲተላለፍ የፌዴሬሽኑ ሰዎች እየተነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። በራሱ ስህተት መስመር ያለፈች ኳስ አላለፈችም ብሎ ወደ ዳኛው የሮጠውን በረከትን ጨምሮ ወደ 5 የሚጠጉ የወልዋሎ ተጨዋቾችና 3 የመከላከያ ተጨዋቾች የዳኛውና ኮሚሽነሩ ሪፖርትን ተንተርሶ ዲሲፕሊን ኮሚቴ በቀናት ውስጥ የሚወስደው ሪፖርት ይጠበቃል።
ምንጭ – የአዲስ አበባ ወሬዎች
No comments:
Post a Comment