Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, May 6, 2018

አንዱዓለም አራጌ በፍራንክፈርት ከተማ – መዘክረ ቴዎድሮስ – ሜይ 12 ቀን 2018



Image may contain: 2 people, text


በጀርመን የኢትዮጵያዉያን የዉይይትና የትብብር መድረክ አዘጋጅነት ሜይ 12 ቀን 2018 በፍራንክፈርት ከተማ የሚካሄደዉ ጉባዔ ላይ አንዱዓለም አራጌ በክብር እንግድነት ይገኛል። በእለቱ ጥናታዊና ወቅታዊ ጽሁፎች ከሚያቀርቡ ተጋባዥ እንግዶች ውስጥ ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ እና የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ቤተዘመ ፤ አብዩ በለዉ ይገኙበታል። ለበለጠ መረጃ መድረኩ ለኢ.ኤም.ኤፍ የላከው ማስታወቂያ ከዚህ በታች ይመልከቱ።

በጀርመን የኢትዮጵያዊያን የዉይይትና ትብብር መድረክ
Ethiopian Forum for Dialogue and Cooperation in Germany
Äthiopisches Forum für Dialog und Zusammenarbeit in Deutschland
_______________________________________________________________________

መዘክረ ቴዎድሮስ
የግማሽ ቀን ጉባዔ በፍራንክፈርት ከተማ

በኢትዮጵያ የአንድነት ታሪክ ጉልህ ሥፍራ ያላቸዉና የታሪክ ስጦታን ለትዉልድ አዉርሰዉ ያለፉት ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ የተሰዉበት 150 ኛ ዓመት ሜይ 12 ቀን 2018 በፍራንክፈርት ከተማ ከ 14 ሰዓት ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። ተቀማጭነቱ ፍራንክፈርት ከተማ የሆነዉ … በጀርመን የኢትዮጵያዉያን የዉይይትና የትብብር መድረክ …. አዘጋጅነት የሚካሄደዉ ይኽዉ የግማሽ ቀን ጉባዔ በተለያዩ አርስቶች የተጋበዙ እንግዶች በሚያቀርቧቸዉ ጥናታዊና ወቅታዊ ጽሁፎች ላይ በመመርኮዝ ትምህርታዊ ዉይይት ይካሄዳል። የሚቀርቡ ዝግጅቶም የሚከተሉት ናቸዉ።

1. የኢትዮጵያ አንድነትና የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ራዕይ (በጋዜጠኛ – ተክሌ የኋላ)
2. ታሪክ የወረሰ ትዉልድ በዲሞክራሲ ሥርዓት የግንባታ ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች (በፖለቲከኛ- አንዱዓለም አራጌ)
3. ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ፤ በቤተሰብ ዙሪያ ምን ዓይነት ሰብዕና ነበራቸው? (በአብዩ በለዉ ከዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ቤተዘመድ)

ከዚህም በተጨማሪ …. የቴዎድሮስ አደራ… በሚል ርዕስ አጭር ተዉኔትና የተለያዩ ሥነ ግጥሞች በየፕሮግራሙ ጣልቃ ይቀርባሉ። በመሆኑም የዚህ ዕለት ታዳሚ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ቦታ – Haus der Jugend Frankfurt, Deutschherrenufer. 12, 60594 Frankfurt am Main
Email: ethiopianforumfordialogue@gmail.com Tel. Nr.: +4915773912794 or +491782844931
Adresse: Mainzer Landstraße 504, 65933 Frankfurt am Main

በጀርመን የኢትዮጵዉያን ዉይይትና የትብብር መድረክ

No comments:

Post a Comment

wanted officials