Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, June 29, 2015

በጀርመን፣ ዱስለዶረፈ ኢትዮጵያውያን አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈታ ዘንድ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

የነጻነት ታጋዩ አንዳረጋቸው ጽጌ በዘረኛው የወያኔ ደህንነት ሃይል ከየመን ታፍኖ ከተወሰደና በዚሁ ዘረኛ እስር ቤት የተወረወረበትን ሰኔ 16 2007 ዓ.ም. (ጁን 23 2015) አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፤ በቦን፤ ኮሎኝ፤ ዶስልዶርፍና እንዲሁም ራቅ ካለው ፈራንክፉርት ከተሞች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በኖርድ ራይን ዌሰትፋለን ዋና ከተማ ዱስለዶረፍ በሚገኘው የብሪቴን ኮንሱላት ፊትለፊት በመገኘት የእንገሊዝ መንግስት ዜጋ የሆነውን አንዳርጋቸው ጽጌን እንዲፈታ የእንግሊዝ መንግስት በወያኔ ላይ ጫና እንዲያደርግ ድምጻቸውን አሰሙ።
Protest in Germany Dusseldorf
Protest in Germany Dusseldorf
Protest in Germany Dusseldorf

የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው

ገለታው ዘለቀ
በድርጅት ከዚያም ከፍ ብሎ በመንግስት ደረጃና በሃገር ደረጃ ግምገማ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ሁሉ ያምናል። የኣንድ ድርጅት ብቃትም በግምገማው ችሎታና ጥራት ሊለካ ይችላል።የኣንድ ሃገር የፖለቲካ መረጋጋት በፖለቲካ ለሂቆቹ የጠራ የሃገር የምናብ ስእልና ብስለት ሊለካም ይችላል። የፖለቲካ ቤቶች ሲኮለኮሉ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ ከፍ ያለ ግምገማን ይጠይቃል። ሃገሪቱ ያለፈችበትን የህይወት ጎዳና፣ የገጠማትን ችግር መንስዔና ውጤቶች በሰፊው መገምገም ለሚመሰረቱ የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረትና ለሚቀረጹ ፖሊሲዎች ጥራት ወሳኝ ነው። እንግዲህ በሃገራችን ኢትዮጵያ ግምገማ በሰፊው የተወራለት ጉዳይ የሆነው በዚህ መንግስት ጊዜ ነው። ህወሃት በጫካ ኑሮው ጊዜ የነበረው ማህበራዊ ህይወትና የትግሉም ባህርይ የየቀን ውሎውን እየገመገመ እንዲሄድ የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ስለከተተው በግለሰቦች ድክመትና ጥንካሬ ዙሪያ ሲገማገም ነው ያደገው። የግምገማው ዓይነት ኣውጫጭኝ ኣይነት ግምገማ ተፈጥሮ ያለው ነው። በመርህ ደረጃ ግምገማ መኖሩ በራሱ ጥሩ ሆኖ ሳለ የግምገማውን ባህርይና ያመጣውን ፍሬ ማየት ግን ኣለብን።
ህወሃት “ኢሃዴግ” ስልጣን ከያዘ በሁዋላ የመጣው ይህ ግምገማ ከድርጅት ኣልፎ ታች በየመስሪያ ቤቱ እንዲሁም ገበሬው ድረስ ወርዶ እንደነበር ይታወሳል። ባህሪው ለየት ያለ በመሆኑና ያልተለመደ በመሆኑ ኣስተማሪዎችን፣ የህክምና ባለሙያዎችን፣ የግብርና ባለሙያዎችን ወዘተ ግራ ኣጋብቶ ነበር። ግራ ያጋባበት ምክንያት በሃሳብ ደረጃ መጥፎ ስለሚባል ኣይመስለኝም። ችግር ያመጣው ኣውጫጭኝ ኣይነት በመሆኑና ከሲስተምና ከፖሊሲ ይልቅ በግለሰቦች ባህርያትና ክህሎት ብቃት ላይ ያተኮረ በመሆኑ እንዲሁም የግምገማው መስፈርት የጠራ ባለመሆኑ የግለሰቦችን ግላዊ ህይወት ሳይቀር ኣደባባይ በማውጣቱ መዘበራረቅን ኣምጥቶ ነበር።
“ኢሃዴግ” ግምገማ ሲል በጣም የሚብከነከነው በኣክተሮቹ ፣ በሲስተሙ ተዋንያን ላይ በመሆኑ የግለሰቦቹን ድክመትና ጥንካሬ በኣደባባይ ኣውጥቶ መወያየት ኣንድን የስራ ሃላፊ ወይም ባለሙያ ያለውን ጠንካራ ጎንና ደካማ ጎን ኣብጠርጥሮ በገበያ ላይ ማውጣት ነው ትልቁ ግምገማ። የሰውን ልጅ ይለውጠዋል የሚል እምነት ኖሮት እንደሆነ ኣላውቅም። የግምገማው ስነ ልቦና ትንሽ ለየት ይላል።ግለሰቦች ባህርያቸውን በጥልቀት ይገመገማሉ። በተለይ በፖለቲካ ድርጅቶች ኣካባቢ የሚበሉበትን የሚጠጡበትን ቤት ሁሉ እያነሱ ማብጠልጠል ሁሉም በየማስታወሻው በኣንድ ኣባል ላይ የያዘውን እያወጣ ድክመት ነው ያለውን በጉባዔ ፊት ለዚያ ሰው መግለጥ ዋና ተግባር ነው።ህወሃት በግለሰቦች በተለይም በታችኛው ኣካል ኣካባቢ ግምገማውን ያብዛ እንጂ እንደ ድርጅት እንደ ሲስተም ሲበዛ ሚስጥረኛና ግልጽነት የጎደለው ድርጅት ነው።
“የኢህ ኣዴግ” ኣይነቱ ግምገማ በሌሎች ኣገሮች ከሚደረጉ ግምገማዎች ሁሉ የሚለይ ይመስላል። በግምገማ ክህሎትን፣ ባህርይን ለማረቅ የሚሞክር ኣካሄድ ይመስላል። የድርጅት ኣባላት ሲናገሩ በኣንድ ሰው ዙሪያ ሁለት ቀን ድረስ የሚፈጅ ግምገማ የሚደረግበት ጊዜ ኣለ። ውሳኔ ያንስሃል፣ ትፈራለህ፣ ታዳላለህ፣ ከእከሊት ጋር ትወጣለህ፣ ብስለትና እድገት ኣይታይብህም፣ ሙስና ውስጥ ገብተሃል፣ ከእከሌ ጋር ያለህ ቅርበት በዝቱዋል፣ ከእከሌ ጋር ለምን ተኳረፍክ፣ ትኮራለህ፣ ኣድርባይ ነህ፣ ወዘተ ወዘተ…. እየተባለ የሚገመገም ብዙ ሰው ኣለ። ኣባላት ሁሉ እየተነሱ ግለሰቡን ቁጭ ኣርገው ያብጠለጥላሉ። ሂስህን ዋጥ፣ ኣልውጥም… ዋጥ፣ ኣልውጥም… ብዙ ሰዓት ይፈጅና ተገምጋሚው “ውጫለሁ” ካለ ይታለፍና ሌላው በተራው ደግሞ እንዲሁ ይብጠለጠላል። ኣንዳንዴም ኣባላት በሆነ ነገር ያናደዳቸውን ሰው ለማጥቃት ሲያስቡ በዚያ ሰው ዙሪያ ሲሰልሉ፣ ድክመት የተባሉትን ሲያሰባስቡ ይቆዩና በግምገማው ሰዓት ኣንጀታቸውን የሚያርሱበት መድረክ እንደሆነም ይነገራል። በኣጠቃላይ እምነቱ ግን የሰዎችን ድክመት በተለይ በኣደባባይ በማውጣትና በመግለጥ የሰው ልጅ ይማራል፣ ምን ኣልባትም በግል በሱፐርቪዥን ከሚድረገው ግምገማ ይልቅ በኣደባባይ በቡድን ፊት መጋለጡ ለባህርይ ለውጥ የተሻለ ነው የሚል ነገር ይመስላል። ኣጠቃላይ ሂደቱ ባህርይንና ክህሎትን ለመቅረጽ ነው ብለን በቅንነት እንውሰድና በተግባር ግን በተለይ በሃገር መሪዎች ኣካባቢ ሰፋ ባለው በሃገር ደረጃ በርግጥ ይህ ኣካሄድ የሚፈለገውን ለውጥ ያመጣል ወይ? ህወሃት “ኢህዓዴግ” በዚህ የግምገማ ስልቱ የተሻሉ መሪዎችን ኣፈራልን ወይ? ኣገራችን መሪዎችን ኣገኘች ወይ? ግልጽነትና ተጠያቂነት እያደገ ሙስና ቀነሰ ወይ? ኣድረን ወደ ዴሞክራሲ ተመነደግን ወይ? የሚለውን መገምገም ተገቢ ነው። ግምገማ ቀላል ነገር ኣይደለም። ፍርድ ነው። ለዚህ ደግሞ ከፍ ያለ ተመልካችነትን የሙያ ቅርበትን ይጠይቃል። “ኢህኣዴግ” ግምገማ የሚለው እርስ በርስ ከተሞሸላለቁ በሁዋላ ሂስ በመዋጥና ባለመዋጥ የሚቋጭ ነው ። ከዚህ በላይ ግን የግምገማው ውጤት ከፍትህ ጋር ጥብቅ ቁርኝት የሌለው ተገንጥሎ የወጣ ነው። ለማናቸውም ግን ግምገማው ጥሩ ነው ጥሩ ኣይደለም ከሚለው በላይ ለዛሬው ጽሁፍፌ መነሻ የሆነኝ ምን ትርፍ ኣገኘን? የሚለው ጉዳይ ነው ::
ከፍ ሲል እንዳልኩት “ኢህኣዴግ” ከተፈጠረ ጀምሮ ከዚያም በፊት በህወሃት ጊዜ ግምገማ በተለይም በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ግምገማ የሚካሄድ ሲሆን በርግጥ ከዚህ ፍሬ ኣግኝተን መሪዎችን ኣፈራን ወይ? መሪዎቹ ክህሎት ጨመሩ ወይ? ትህትናና ዴሞክራሲ፣ የህግ የበላይነት በመሪዎቹ ኣካባቢ እያደገ መጣ ወይ? ብለን ኣጥብቀን መጠየቅ ኣለብን። ኣቶ ኣባዱላ ገመዳ ላለፉት ሰላሳ በላይ ኣመታት የሰላ ግምገማ ተካሂዶባቸው ኣሁን ክህሎት ጨምረዋል ወይ? ። “ኣዎ!” ከተባለ ከሰላሳ ዓመት በፊት ምን ዓይነት ሰው ነበሩ ማለት ነው? ብለን እንደመማለን። ለኣርባ ኣመት ገደማ የተገመገሙት እነ ኣባይ ጸሃየ፣ እነ ሳሞራ፣ እነ ስዩም ወዘተ በዓርባ ዓመት ግምገማ ውስጥ ኣልፈው ለምን የተሻለ ስብእና ኣላዳበሩም? እነ ኣዲሱ ለገሰና እነ ስብሃት ነጋ ሌሎች መሪዎች በዚህ ግምገማ ተወቅረው…. ተወቅረው …..ተወቅረው….. ምን ወጣቸው? እንዴውም በተግባር የምናየው ህግን ሲጥሱ፣ ኣድረው ጭካኔ ሲያሳድጉ፣ ዴሞክራሲ እንዳያድግ ሲያደርጉ ነው። ይህን ስናይ የዚህ “የኢሃዴግ” ግምገማ ጉዳይ የሆነ ችግር ያለበት መሆኑን እንረዳለን። በዚህ ዙሪያ ነው ኣንዲት ትንሽ ኣስተያየት ለማቀበል የፈለኩት። ቅን የሆኑ “የኢሃዴግ” ኣባላትም ይሰሙኛል ብየ ኣምኜ ነው።
በሃሳብ ደረጃ እንዲህ ኣይነቱ ግምገማ ጥሩ ቢመስልም የሳተው ትልቁ ነገር ግን ሊፈጥር ያሰበው ስብእና መያዣ ኣቁማዳ ተበጅቶለት ኣናይም። የግምገማው ሂደት “ኢሃዴግን” ራሱን እንደ ድርጅት በሲስተምና በፖሊሲ ደረጃ ኣብጠርጥሮ ከመገምገም ይልቅ በኣክተሮቹ፣ በግለሰቦቹ የግል ባህርይና ክህሎት ላይ በማተኮሩ የሰላሳ ኣመቱ ግምገማ ፍሬ ኣላመጣም። ኣንዳንዶቹን እንዴውም በደንብ ኣድርጎ ያደነዘዛቸው ይመስላል። ግምገማን ከመልመዳቸው የተነሳ “ሂሴን ውጪያለሁ” ምንትሴ…… እያሉ ማለፉን መርጠው ለውጥ ሳይመጣ ቀርቶኣል። ኣንዳንዶቹም የሰው ሃጢያት ሲዘረዘር ደስ እያላቸው የግምገማ ጊዜ ሱስ የሆነባቸው ይህን ጊዜም የሚደሰቱበትም እንዳሉ ይሰማል። “የኢሃዴግ” ግምገማ ውጤታማ እንዳይሆን ያደረገው በግምገማ መድረኩ ለማጠብ የሞከረውን ኣባላቶቹን ኣጣጥቦ ኣመድ ላይ መጎለቱ ነው።። ለምሳሌ ኣንድ የፖሊስ ተጠሪ ለህገ መንግስቱ ታዛዥ ኣይደለህም ወዘተ….. ተብሎ ቢገመገምና ሂሱን ውጦ ከመድረክ ቢመለስ ነገ የት ነው የሚገባው? መቼ ፖሊስ ራሱ ነጻ ተቋም ሆኖ ተፈጠረ? የብር ዋጋው ሲወርድ (devaluate ሲደረግ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ሃላፊ ሳያውቅ በሚወሰንበት ኣገር እንዴት ሆኖ ነው ይህ የባንክ ሃላፊ ውሳኔ ያንስሃል፣ ኣቅም ያንስሃል፣ ወዘተ እየተባለ ሊገመገም የሚችለው? በነጻነት መፍረድ በማይቻልበት ኣገር እንዴት ሆኖ ነው ኣንድ ዳኛ በሙያው የሚገመገመው? ዋናው ችግር ይህ ተቋም ነጻ ኣለመሆኑ ሲሆን ግለሰቡን ገምግመው ኣብጠልጥለው ሂሱን ኣስውጠው ቢልኩት ነገ ሄዶ የሚቀመጠው ኣመድ ላይ ነው። ለዚህ ነው ግምገማው ሲስተሙን ራሱን ጨክኖ የሚፈትሽ ባለመሆኑ የግለሰቦች ኣውጫጭኝ ሆኖ የሰላሳና የኣርባ ዓመት ፍሬው ባዶ የሆነው።
“ኢሃዴግ” ባለፉት ኣመታት ከግለሰቦች ኣውጫጭኝ ይልቅ ሲስተምን የሚያይ “የኢሃዴግን” ተፈጥሮና ፖሊሲዎቹን በሚገባ የሚገመግም ቢሆን ኣገሪቱ ወደ ተሻለ ዴሞክራሲና ልማት ታድግ ነበር። “ኢሃዴግ” ጨክኖ ራሱን እንደ ሲስተም እያየ ምርጫ ቦርድን ነጻ ኣድርገን ፈጥረናል ወይ? ወታደሩ ነጻ ነው ወይ? ፍርድ ቤት ውስጥ ጣልቃ ኣንገባም ወይ? ባንኮችና ኣጠቃላይ የሃገሪቱ ተቋማት በነጻነት ይሰራሉ ወይ? ህወሃት “በኢሃዴግ” ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ምን ኣደረገው? ይህ ትክክል ኣይደለም! የብሄር ፖለቲካ የመጨረሻ ግብ ኣለው ወይ? እኛ ራሳችን ተሰባስበንበታል የምንለው “ኢሃዴግ” በርግጥ በዚህ ዓለም በህይወት ኣለ ወይ? በኢትዮጵያዊነት ጽንሰ ሃሳብና “በኢሃዴግ” ተፈጥሮ መካከል ያለው ዝምድናና መስተጋብር ምን ይመስላል? የቱን ያህል ጥብቅ ነው? ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ ምንድነው? በህገ መንግስቱና በኣብዮታዊ ዴሞክራሲ መካከል ምን ዝምድና ኣለ? የብሄር ፖለቲካና የዴሞክራሲ መርሆዎች ኣብረው ይሄዳሉ ወይ? ህወሃት ለዖህዴድ ምኑ ነው? ወዘተ… ደግሞም ግምገማ በጣም በበዛበት ዘመን በሃገራችን የነበረ ጉቦ እንዴት ወደ ሙስና ያድጋል? እጅግ ብዙ ጥያቄ ለማኝ የሆኑ ጉዳዮች ስላሉ እነዚህ በሚገባ ቢገመግሙ የተሻለ ቤት መስራት ይቻል ነበር። ማህበራዊ ሃብትን የሚንከባከብ የህብረተሰቡን ኢነርጂ የማይቃረን ስርዓትና ፖሊሲ ከተፈጠረ በዚያ ውስጥ የሚኖረው ግምገማ የተሻለ ፍሬ ባመጣ። በመከላከያ ኣካባቢ በኢኮኖሚው ኣካባቢ የህወሃት የበላይነት መታየት የለበትም፣ ኣንድ ግለሰብ ሰረቀ ተብሎ ለሁለት ቀን የሚገመገም ከሆነ የህወሃት ድርጅታዊ ሙስና ለምን በሰፊው ኣይገመገምም? የመሳሰሉትን ስናይ የዚህ መንግስት ትልቅ ችግር ግምገማው ሲስተሙን ጨክኖ የሚገመግም ኣለመሆኑ፣ የሚፈራ በመሆኑ ነው። ሲስተምን ችላ ብሎ ሙስና በተጠናወተው ሲስተም ውስጥ ጥሩ መሪዎችን ለማውጣት መሞከር ኣይቻልም። ታጥቦ ጭቃ ነው የሚሆነው።በድርጅት ህይወት ውስጥ መጀመሪያ መታየት ያለበት ቤቱ ንጹህ ተደርጎ መሰራቱን ነው። ቤቱ ካልጸዳ በውስጡ ያሉት ኣይጸዱም:: ዝም ብለን ብንቀጥል ደግሞ እጥበቱ ድብኝት ኣጠባ ነው የሚሆነው።
በሃገራችን ኣጠቃላይ የፖለቲካ ቅርጽ ኣካባቢ ይህ ችግር ይታየኛል። ሃገራችንን ኢትዮጵያን ተፈጥሮዋንና ማንነቱዋን በሚገባ መረዳት፣ ያለፈችበትን ህይወት በሚገባ መገምገም ችግሮቹን ኣንጥሮ ማውጣት የቀረን ይመስለኛል። ለዚህም ነው ዛሬ ኣንዱ የብሄር ጥያቄ ኣንዱ የግለሰብ እያለ በሁለት ውጥረት ውስጥ የወደቀችው። ችግርን በሚገባ ኣለመለየትና ኣለመገምገም ወደፊት ለምንሰራው የፖለቲካ ቤትም ሆነ ፖሊሲ ተጽእኖው ከባድ ነው። በመሆኑም “የኢሃዴግ” ኣባላት ጨክነው “ኢሃዴግን” ተፈጥሮውን የህወሃትን ግዝፈት የተቋማትን ነጻነት ኣብጠርጥረው ቢገመግሙ ነበር የምንለወጠው። ይህ ግን ኣልሆነም። ህወሃት በግምገማ ስም የበታቾቹን እያመሰ የሃገሪቱን ሃብት ሲቦጠቡጥ ነው የሚታየው። “ኢሃዴግ” በግለሰቦች ኣካባቢ ግምገማ ጊዜ ያለውን ጭካኔ በሲስተም ላይ ማሳየት ኣይፈልግም። እንዴውም ግምገማን የማይፈልገውን ሰው ለመቅጫም ጥሩ መሳሪያ ኣድርጎ በሚገባ ሲጠቀምበት ይታያል።
“ኢሃዴግ” ቁጭ ብሎ ግምገማውን ራሱን መገምገም ነበረበት። ኣርባ ኣመት የተገመገሙትን ሰዎች እያየ ለምን ወደ ፍጹምነት የተጠጋ ስብእና ኣላዳበራችሁም ብቻ ሳይሆን እንዴት በዚያ ግምገማ ውስጥ ኣልፋችሁ ክፋትንና ተንኮልን ትጨምራላችሁ? ብሎ መጠየቅ ካልቻለ እሴት ኣልጨመረም። ነጻ ያልሆኑት ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ውሳኔ ላይ ደካማ ነዎት፣ ይህን ጉዳይ በሚገባ ኣልተወጡም ሊባሉ ኣይችሉም። ከዚህ ይልቅ “የኢሃዴግ” ኣባላት ቆራጥ ቢሆኑ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይል የላቸውም! እንደ ቃል ኣቀባይ ኣይነት ነው ስራቸው በሚል የህወሃትን ጣልቃ ገብነትና እጅ ኣዙር ኣገዛዝ መገምገም ፍሬ ያመጣ ነበር። ለኚህ ሰው የፈጀው ሰፊ የግምገማ ሰዓት ድራማ ከመሆን የሚያልፈው ተገምግመው ሲያበቁ ነጻ በሆነ የሃላፊነት ወንበር ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ነበር። የቡድን ኣመራርን መቃወሜ ኣይደለም። ይሁን እንጂ በቡድን ኣመራር ስም የህወሃት ፈቃድ ብቻ በሚፈጸምበት ኣገር የኣቶ ሃይለማርያም ድርሻ ከቃል ኣቀባይነት ያለፈ ስራ ስለማይሆን ይህን ደፍሮ የሚሰብር ጠንካራ ግምገማ ያስፈልጋል።
በግምገማ ጊዜ ስለ ሙስና ተነስቶ ሰዎች ይወቀሳሉ። ኦዲተሮች ግን በነጻነት ኣይሰሩም። ኣንዳንዱ በሙስና የሚገመገመው ኦዲት በማይደረግ መስሪያ ቤት ነው። ኦዲት ተደርጎ የኦዲት ሪፖርቱ በማይታወቅበት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ኣንዳንድ ግለሰቦችን በግምገማ ላይ ማንሳቱ ምን ኣልባትም በሙስና ስም ለማጥቃት ካልሆነ ፍሬ የሌለው መሆኑ ይታወቃል። ሳይንሳዊ ይሁን ስንልም በኣሰራርና ስራንና ሰራተኛን በማገናኘት ሊስተካከሉ የሚችሉትን በቡድን ኣውጫጭኝና ሂስህን ዋጥ ኣልውጥም ሊስተካከል ኣይችልም።
ከዚህ በፊት ኣንድ የብዓዴን ኣባል ኣናግሬ ኣውቃለሁ። ይህ ሰው በድርጅቱ ውስጥ ስልጣን ያለው ነው። እንዴውም የድርጅት ጉዳይ ሆኖ ነበር። እንዴት ነው እናንተ ብዓዴኖች ህወሃትን ኣታሙትም ወይ ? ብየ ጠየኩት:: በደንብ ነው ውጭ ውጭውን የምንንሾካሸከው ብሎኛል። ኦህዴድም እንደዚሁ ነው። ይህ የሚያሳየው በጣም በተበላሸ ሲስተም ውስጥ ነው ግለሰቦች እየተብጠለጠሉ ያሉት። ይህ ደግሞ ለድርጅቱም ለሃገርም ለውጥ ኣያመጣም።
ኣንዳንዱ ሰው ደግሞ የሚወቀሰው ከተፈጥሮው ክህሎት ጋር በተያያዘ ነው። ውሳኔ ያንስሃል ሲባል ይህ ሰው ወስን…. ወስን…. ወስን…… ስለተባለ ኣይደለም የሚወስነው።ውሳኔ በኣብዛኛው መረጃን ከመረዳትና ከመገምገም ጋር ነው የሚያያዘው።በተለይ በከፍተኛ ስልጣን ላይ ያለ ሰው ውሳኔ የሚያጥረው ብዙ ጊዜ የሚመጡ መረጃዎችን የመተንተንና በኣእምሮ የመሳል ኣቅም ሲያጥረው ይመስለኛል:: ባለስልጣን ሆኘ ባላየውም። የውሳኔና ኣመራር ችሎታ በትምህርትና ከተፈጥሮም ጋር ከተያያዘ ተሰጥዖ ጋር ሊሄድ ይችላል። በስብሰባ ኣባላት ስለጮሁበት ኣይደለም። በዚህ መልኩ የመሻሻል እድል ጠባብ ነው የሚሆነው። ኣንዳንዱ ሰው ትላልቅ ፒክቸሮችን በኣይምሮው የማየትና የመደመም(a strong impression) ብሎም ውሳኔ የመስጠት ተሰጦ ላይኖረው ይችላል። ፖሊሲ ውሳኔ ነው። ሚሊዮን ህዝቦችን ተጽእኖ ሊያደርግ የሚችልን ፖሊሲ ሲያመጡ ወስነው ነውና ለዚህ ምናብ ኣስፈላጊ ነው። በሌላ በኩል ቴክኒካል የሆኑ ጉዳዮችን የመፈጸም ኣቅምና ፍላጎት ያላቸው ለዚህ ስራ ስሜታቸው የሚነቃቃ ሰዎች ደግሞ ኣሉ። በመሆኑም ስራና ሰራተኛን ማገናኘት የሚፈታውን ችግር “ኢሃደግ” ከየቦታው ታዛዞቹን ይሰበስብና የማይገባ ቦታ እየሰጠ እንደገና ደግሞ ኣቅም ኣነሰህ እያለ ይገመግማቸዋል። ስራና ሰራተኛን ማገናኘት በራሱ የሚፈታቸውን ጉዳዮች ችላ ማለት ኣገራዊ ኪሳራው ሰፊ ነው።
በየደረጃው ያሉ ባለስልጣናት መረጃዎችን የሚያዩበት መጠነ ርእይ ይለያያል። የታችኛው ኣካል በተወሰነ ኣጥር ውስጥ የሚያይ ሲሆን ወደ ላይ ከፍ ያሉ ባለስልጣናት ደግሞ በሰፊ ስኮፕ ያዩታል። ከፖሊሲና ከማህበራዊ ተጽእኖ (Impact) ጋር ስለሚያዩት የሚደመሙት በዚህ ሰፋ ባለ ተጽእኖና በዚያ ተጽእኖ ውጤት ላይ ነው። ለዚህ የሚመጥኑ ሰዎችን በየደረጃው ማስቀመጥ የተሻለ ሲሆን በፖለቲካ ታማኝነት ብቻ ኣንዱን የቴክኒክ ሰው ሚንስትር ማድረጉ ኣገሪቱን በጣም ጎዳት። ከግምገማ ይልቅ በትምህርት ሊበለጽጉ የሚችሉትን መለየት፣ ግምገማውን ሳይንሳዊ ማድረግ ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን በተለይ ሲስተምን የማጽዳት ስራ መስራት ጠቃሚ ነበር። ስኮፕ የሌላቸውን ሰፋ ኣድርገው ማየት የማይችሉትን ኣጉሮ ኣጉሮ ምንም ለውጥ ማምጣት ኣይቻልም። በተበላሸ ፖሊሲ ስር የቱንም ያህል የግለሰብ ግምገማ ብናካሂድ ኣንለወጥም።ኢትዮጵያ ትታየናለች ወይ? የጥንት ኣባቶች ድካም ይታየናል ወይ? ስለ ሃገሪቱ ማንነት ስናስብ የጠራ ስእል ኣለን ወይ? እያልን የሚሾመው ቢሾም ይሻል ነበር። ኣንድ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻን ሲለምን እኔ ተራው ሰውና ኣንድ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ሰው ብናገኝና ብናናግር የሁለታችን ምናብና መደመም መለያየት ኣለበት። እኔ ካለኝ ኣካፍየ ካልሆነ ኣዝኘ እሄዳለሁ። ያ ባለስልጣን ግን ከፍ ካሉ ሃገራዊ ጉዳዮች ጋር ኣገናኝቶ ኣገራዊ ተጽእኖ ሊፈጥር የሚችል ስእል ሊያይ ይገባል። በዚያ ጎዳና ተዳዳሪ ህጻን ምላሽ ፖሊሲን እስከማስቀየር በሚደርስ ሃይል ይህ ባለስልጣን ሊመሰጥበት ሊመታበት ይገባዋል። ስኮፕ እንዲህ ነው። ኢትዮጵያንም ኣጠቃላይ ኣካሉዋን በሚገባ የማየትና የመረዳት ብቃትን ይጠይቃል። ከዚህ ውጭ በኣካባቢያችን ያለችውን ችግር ኣይተን በዚያችው ዙሪያ የፖለቲካ ድርጅት መስርተን ለዚያች ችግር መፍትሄ ለማምጣት ብቻ የምንሞት ከሆነ ኢትዮጵያን ለመምራት ኣንመጥንም። መሪዎቻችን ባደጉበት ኣካባቢ ያዩትን ችግር በሰፊ ምናብ ካላዩት በብሄር ፖለቲካና በኢትዮጵያዊነት መካከል ውጥረት ውስጥ ገብተው ራእይ ኣጥተው ሊኖሩ ይችላሉ። ምናብ ለመሪዎቻችን በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ታላቁ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ኣንዱ ትልቁ ችሎታቸው ደቡብ ኣፍሪካን በይቅርታ መሰረት ላይ ቆማ በጠራ ምናብ ማየት መቻላቸው ነው። በጣም ግትር ከሆነ የፍትህ ኣስተሳሰብ ኣውጥቶ በዚህ ከፍታ ላይ ያስቀመጣቸው ምናባቸው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥም እንዲህ ዓይነት መሪዎችን እንሻለን።
ትልቅ ችግር ያመጣው “ኢሃዴግ” እንደ ድርጅት ራሱን ኣለማየቱ ብቻ ሳይሆን ይህ ኣካል ስልጣን ላይ በመሆኑ ተጽእኖው ኣገራዊ ይዘት እንዲኖረው በማድረጉ ኣሁን ላለንበት ውስብስብ ችግሮች ቀንደኛ ምክንያት ሆነ። የተቋማትን ነጻነት ለመገምገም ወይም የፓርቲውን ጣልቃ ገብነት ለመገምገም ባለሞሞከሩ ዛሬ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ገለልተኛ ኣልሆነም። ዛሬ “ኢሃዴግ”በኣምስተኛው ዙር “ምርጫ” በኦሮሚያ፣ በኣዲስ ኣበባ፣ በትግራይ፣ በኣማራ በደቡብ መቶ በመቶ ማሸነፉን ሲሰሙ “ኢሃዴጎች” ዴሞክራሲ ኣደገ ነው የሚሉት? ያ “ግምገማ” በርግጥ ሃቀኛ ከሆነ የዚህ ድርጅት ኣባላት እምቢኝ ማለት ነበረባቸው።ይህቺን ጽሁፍ ስጭር የቅርቡን የምርጫ ውጤት ሲሰሙ ኣንዳንዶቹ “የኢሕዓዴግ” ኣባላት ምን ይሉ ይሆን? ብየ ኣስቢያለሁ። እውነተኛ ለኣገር ኣሳቢ የሆነ ፓርቲ ውስጥ ነው ያለሁት የሚል ለኣገር ኣሳቢ የሆነ “የኢህዓዴግ” ኣባል በግምገማ ወጥሮ መጠየቅ ኣዲስ ምርጫ መካሄድ ኣለበት ኣለያ ሞቼ እገኛለሁ ማለት ነበረበት፣ ኣልነበረበትም?:: በዴሞክራሲ የሚያምኑ ከሆነ ፣ ከዴሞክራሲ መገለጫዎች መካከል ኣንዱና ዋነኛው ምርጫ ሲሆን ውጥንቅጡ በወጣና ተዓማኒነት በጎደለው ምርጫ መቶ በመቶ ኣሸነፍኩ ሲለኝ በርግጥ ለዚህ መሞት ኣለብኝ።መቶ በመቶ ኣሸነፍኩ ብሎ “ኢሃዴግ” ሲያውጅ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የሆነ የዚህ ፓርቲ ኣባል ድግሱን ኣይበላም። ኣይበላም ብቻ ሳይሆን ይህ ታሪክ እንዲገለበጥ ኣጥብቆ ይሰራል። ኣለያ ቢሞት ይሻለዋል። ኣሁንም ቢሆን ሃቀኛ የሆኑ የኢህዓዴግ ኣባላት ለለውጥ መታገል ኣለባቸው። በስማቸው የሚነግዱትን ጥቂት የበላይ ኣካላት በመፍራት ዝም ማለት የለባቸውም። ለለውጥ ለተሻለ ስርዓት በቻሉት ኣቅም መታገል ኣለባቸው። ህዝባዊ እምቢተኝነት ሲነሳ ከህዝብ ጎን በመቆም ትግሉን ማፋጠን ይጠበቅባቸዋል። ፖሊሶች፣ ዳኞች፣ የባንክ ሰራተኞች፣ ወታደሮች፣ በኣየር ሃይል ኣካባቢ የሚታየውን ኣይነት ትግል ማፋፋም ኣለባቸው። ይህን በማድረጋቸው ከህሊና ፍርድ ነጻ መሆን ብቻ ሳይሆን ከለውጥ ባሻገር ኢትዮጵያ ትኮራባቸዋለች።
እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
geletawzeleke@gmail.com

የበረሃው ጂኒ፣ የባህሩ ጋኔል (በልጅግ ዓሊ)

በልጅግ ዓሊ
ብቻውን ሆኖ ከጥግ ቆሞ ይቆዝማል። ጸጉሩን እየፈተለ ይናደዳል . . . ብቻውን ያልጎመጉማል። ትንሽ ቆይቶ ያለቅሳል። ለጉድ! ያነባዋል። ሰው እንዳለ እንደሌለ አካባቢውን ይቃኛል። ገና ወደዚህ አካባቢ እንደመጣ ሲብስበት በሰው ፊት ያለቅስ ነበር። አሁን አሁን ግን ሲያለቅስ ሰው ሲያየው አይወድም። መጀመሪያ አካባቢ ጎረቤቶቹ ሲያለቅስ ሲመለከቱ ያጽናኑት ነበር። በኋላ ግን ቀውሷል ብለው ደመደሙ። እንዲያው በደፈናው ግማሾቹ ፍቅር ይዞት ነው ሲሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ የሳሃራ በረሃ ጋኔል አግኝቶት ነው. . . ወይም የባሕር ጂኒ ተጠናውታው ይሆናል ማለት ጀመሩ። በየሄደበት ሁሉም እብድ ነው፣ ቀውሷል ብለው ደምድመዋል። ስለሚናገረው ነገር ግን ማንም ልብ ብሎ ያስተዋለውም፣ የጠየቀውም የለም። እሱም መናገር አይወድም። በእርግጥም ስለሱ የሚያውቅ ማንም የለም።Ethiopian refugees drown
ብቸኝነቱን ሲያስብ፣ የውስጥ ሃዘኑ የአዕምሮውን ጣሪያ ሲነካበት ከቤት ተነስቶ ውልቅ ይላል። ባቡር ይሳፈርና ወደ ፍራንክፈርት ይሄዳል። መሄጃ እንደሌለው የሚያውቀው ግን ፍራንክፈርት ሲደርስ ነው። ለምን ከቤቱ እንደወጣ ግራ ይገባዋል። ባቡር ጣቢያ ከሚገኘው ማክዶናልድስ ይገባና ቁጭ ይላል። እዛም ሆኖ በሃሳብ እንደገና ይወረሳል። ወዲያው ደግሞ እንባው ድቅን ይላል። የጸጋዬ ገብረ መድህንን ወንድ ልጅ ተደብቆ ነው የሚለቅሰው የሚለውን ግጥም በቃሉ ይወጣዋል።
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ፣
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ፣ 
ተሸሽጎ ተገልሎ ተሸማቆ ተሸምቆ፣ 
ከቤተሰብ ተደብቆ፣ 
መሽቶ የማታ ማታ ነው፣ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው ።
እውነት ነው! ወንድ ልጅ በቀን አያለቅስም ብሎ ራሱን ያሳምናል።
በእንባ የጠበቡ ዓይኖቹን እየደጋገመ ጠረግ ጠረግ ያደርጋቸዋል። ጭንቅላቱ ግን በሃሳብ እንደተወጠረ ነው። እዬ! ዬ! ብሎ . . . አልቅሶ ቢወጣለት ምንኛ በወደደ ነበር። አካባቢውን ዞር ዞር ብሎ ይቃኛል። የሚያውቀው ሰው የለም። ማልቀስ እችላለሁ። ማን እንዳይታዘበኝ? ከማን ነው የምደበቀው? እዚህ አበሻ የለም . . .ቀውስ የሚለኝ የለም . . . እያለ ራሱን በራሱ በሚጽናኑ ቃላት ማባበል ይጀምራል። ብቻው ሲያለቅስ አበሾች አይተው ቀውሷል እንዳይሉት መፍራቱን ግን አልተወም።
ቁጭ ባለበት በሃሳብ ይነጉዳል። እንቅልፍ እንደያዘው ሰው በመሃል እንደገና ከሃሳቡ ይባንናል። በቀስታ ድምጽ ማዕበል፣ ማዕበል ፣ ማዕበል ይላል። አጠገቡ ያሉት ሰዎች ቋንቁው ባይገባቸውም በትዝብት ይመለከቱታል፤ በመቀጠልም ጮክ ብሎ እጄን ያዢኝ ፣ እጄን ያዢኝ ፣ እጄን ያዢኝ እያለ ይጮኻል። ሁሉም ሰው ወደ እሱ ይመለከታል፣ እሱ ግን ሰው እንደሚመለከተው ከቶ አያስተውልም። ለምን ለቀቅሽኝ ፣ ለምን?. . . ለምን ለቀቅሽኝ ብሎ ይጮኻል። ከዚያም ወዲያው ፈቱን የእንባ ዘለላ ያርሰዋል። ያለቅሳል ፣ ይንሰቀሰቃል. . . በጉንጩ ላይ ከሚፈሰው ይልቅ ደረቱን ሰንጥቆ ወደ ውስጥ የሚገባው እንባ ይብሳል ።
ጥቂት ቆይቶ ራሱን የጸጋዬን ግጥም ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል። እሱም አልመች ሲለው ግጥሙን እያሰላሰለ ማን ነው . . . ወንድ ልጅ ተደብቆ ነው የሚያለቅሰው፣ የሚንሰቀሰቀው ያለው? . . . ስህተት ነው ፀጋዬ! ወንድ ልጅ የሚያነባው አደባባይ ላይ ነው እንጂ! . . . ፀጋዬ ተሳስተሃል! ግጥምህን አርመው! ባንተ ዘመን ይሆናል በምሽት ተደብቆ የሚያለቅስው፣ በእኛ ዘመን ግን ተቀይሯል። በእኛ ዘመን ወንድ ልጅ ሲደላው ብቻ ነው ተደብቆ በምሽት የሚያነባው፣ እንደዚህ ቀይረነዋል፣ አንተም ቀይረዋ!
ጣሩ ሲበዛበት ግፍ መከራው፣ 
በቀን በጠራራ ፀሐይ አደባባይ ሕዝብ ፊት ነው፣
ወንድ ልጅ የሚያለቅሰው፣ የሚንሰቀሰቀው።
ማንነቱ የተደፈረበት፣ 
እሱነቱን ያጣበት፣
ብሶቱን የሚገልጽበት፣ 
ቁጭቱን የሚያሳይበት፣ 
ብቸኝነቱን የሚወጣበት።
ቀን ነው የሚያነባው፣
ሰው ፊት ነው የሚያለቅሰው፣
አደባባይ ነው ስቅስቅ የሚለው፣
ሕዝበ አዳም፣ የሃበሻ ዘር ብሶቱን እንዲያይለት ፣ 
አይቶም እንዲያላግጥበት . . . ።
ፀጋዬ ግጥምህን ቀይረው። . . . ይላል።
ወዲያው ቀና ብሎ ላፍታ ሰውን ሁሉ ከገላመጠ በኋላ፣ የአዳም ልጅ ሁላ አላግጥ . . . እኔን እያየህ ተዝናና ብሎ ከማክዶናልድ ይወጣል። ነገር ግን፣ ውጭ ወጥቶ የሚሄድበትን አያውቀውም። መሃል መንገድ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቆሞ፣ እንደገና ለራሱ ብቻ በሚገባው ቋንቋ ማልጎምጎም ይቀጥላል፡፡
ከዚያም ፈጠን ፈጠን እያለ በርካታ እርምጃዎች ይራመዳል ። ወዲያውም ዘው ብሎ አንዱ አበሻ ቡና ቤት ይገባል። እዚያም ላፍታ አይቆይም። ይወጣል። እንደገና ሌላው ጋ ይገባል። ከዚያም ይወጣል። ከረንቦላ መጫወቻ ቤት ይሄዳል። . . . እዚያም እንደደረሰ፣ ተጫዋቾቹንና የከረንቡላ መጫወቻወን ጠረንጴዛና ኳሶች ትኩር ብሎ ቆሞ ያስተውላል።
ይኽ ትዕይንት ለሱ የዕለት ተዕለት ኑሮው ነው።
ከእነዚህ ቀናት በአንዱ ግን፣ እንዲህ ሆነ። …. በዚው በለመደው ቤት የከንቡላ ጨዋታ እያስዋለ ሳለ፣ ድንገት ሳይታሰብ . . . “ማዕበል ! ማዕበል ! እጄን አትልቀቂ ! . . . ጀልባውን ይዤዋለሁ እጄን አትልቀቂ ! ሲል አንቧረቀ። በአንድ እጁ ጀልባውን፣ በሌላኛው እሷን እንደሚጎትት ያህል ሰውነቱ ተወጣጠረ። ጮኸ ! ተጣራ ! ከረንቦላ ቤቱ ላፍታም ቢሆን በጸጥታ ተሞላ። ሁላችንም በአንክሮ ወደ እሱ ተመለከትን። በአዕምሮው አንድ ነገር እንዳስታወሰ ዓይኖቹ ፈጠጡ። እንባው በፊቱ ላይ ቦይ ቀዶ ቁልቁል መንዠቅዠቅ ጀመረ። . . . በከረንቦላው ጠረቤዛ ላይ ያሉትን ድንጋዮች በታተናቸው። ጨዋታውን ተረበሸ። ተጫዋቾቹ ጮኹበት። “ይህንን ቀውስ አስወጡት” ብሎ አንዱ ጮኸ ። ባለቤቶቹ “ውጣ! እንግዳ አትረብሽ” ብለው ገፍትረው አስወጡት።
የእሱን እግር ተከትሎ፣ በከረንቦላ ቤቱ ውስጥ የጦፈ ክርክር ተነሳ። “ይህንን ሰውዬ መምህር ግርማ ቢያገኙት ያድኑታል” አለ አንዱ። “እባክህ ተወን! በዓለም የታወቀው የጀርመን ሃኪም ያላዳነውን እንዴት ነው መምህር ግርማ የሚያድኑት?” አለ ሌላኛው። ክርክሩ ከእሱ አለፈና ወደ መምህር ግርማ ሥራና ተዓምር ተቀየረ። አንዱ የእሳቸው አድናቂ ሌላው ደግሞ ጽኑ ተቃዋሚ ሆነው ይከራከሩ ጀመር።
እኔንም በውል የማላውቀው ስሜት ገፍትሮ ከውስጥ አስወጣኝ። ተከተልኩት። እንደተለመደው ለማጽናናት ሞከርኩ። “ፀሐፊ ነኝ ትል የለም እንዴ?” ሳላስበው ጠየቀኝ። መልሱን ሳይጠብቅ ቀጠለ። “እስቲ ጻፈውና እንይህ? እስቲ ንገርልን ምን እንደደረሰብን ? አቦ ጀግና ሁና ! እውነቱን ጻፈዋ ? ቀውሷል እያሉ ከየአበሻው ቡና ቤት ከሚያባርሩኝ የደረሰብኝን ንገራቸው። ሳሃራን አየሁት. . . ባህሩን አየሁት ብለኸኝ የለም እንዴ ? ጻፈዋ እናንብበው ? ወይስ ሰሃራ ድረስ የሄድከው የአሸዋውን ማማር፣ የቴምሩን ጣእም፣ የፀሃዩን ግለት፣ የሙቀቱን ትእይንት ለማያውቁት ልታሳውቅ ነበር? ወይንስ ዕረፍት አምሮህ ነው ? …. ጉድ እኮ ነው! የኛ ስቃይ ለእናንተ መዝናኛ መሆኑ አይገርምህም ! ” በማለት ሳላስበው በጥያቄ ላይ ጥያቄ እአደራረበ ጠየቀኝ።
“ለመሆኑ ኩፍራን ታውቀዋለህ ? ከሱዳን ተነስተን እስከ ሊቢያ ኩፍራ ድረስ ምን ያህል የሰው ልጅ ስቃይና መከራ እንዳለ ታውቃለህ ? ሳሃራን አቋርጠህ ሰዎች የሚኖሩበት ቦታ ስትደርስ የሚሰማህን ታውቃለህ ? አንተ አታውቅም ! መች ይህን ጉድ ቀመስክና ! አንተ ኤር ኮንድሽን ባለው መኪና ውስጥ ተቀምጠህ አይደል እንዴ ሳሃራን የጎበኘኸው ? እሱንም እንኳ ቢሆን ጻፍና አስረዳቸው. . . መቀወስ ይነሰኝ እንዴ ? ቀውስ ነው እያሉ የሚያሽሟጥጡኝን በውል አስረዳቸው እንጂ ? ዳሩ አንተ ብትጽፈው መች አንብበውት፤ ለእሱ መች ጊዜ አላቸውና፤ አንዳንዶቹም ማንበብ አይችሉም። መታወቂያቸው ላይ ያለውን ስማቸውን እንኳ በውል አያውቁትም እኮ ! . . . እኔ ግን ቀውስ አይደለሁም። እነርሱ ናቸው አውቆ አበዶች። ሙሉ ቀን ድንጋይ ሲያፋትጉ የሚውሉ፣ ቤት ሞልተው በባዶ ሁካታ ሲንጫጩ የሚውሉ፣ ጫት እንደ ከብት እያመነዥኩ በቅዠት ምናብ የሚደሰኩሩ፣ በቁማር ፍቅር ሲነዱ ለሚያድሩ፣ የቡና ቅራሪ ሲጋቱ የሚውሉ፣ እነርሱ ናቸው እንጅ ቀውሶች። …. ህ’ ህ ! …. የህሊና ሚዛናቸው የተዛባ፣ አዙሮ የሚያይ አንገት የሌላቸው፣ የመጡበትን የረሱ፣ የሚሄዱበት ካርታ የጠፋባቸው።” መድረሻቸው ከከንቱ የሆነ ። “ሰው መሳይ በሸንጎ ማለት እነሱ ናቸው።”
“ደግሞ ንገራቸው. . . በሳር ውስጥ ተሸሸጎ፣ ታፍኖ፣ ከኩርፋ ትራቫሎስ ድረስ ያለውን መከራ። ስለ ባሕሩም፣ ስለ ጀልባውም ንገራቸው ለእነዚህ አረመኔዎች። እኔን ቀውሷል እያሉ ከየቡና ቤቱ የሚያባርሩኝን ። ቀውስ ነው በላቸው። በፍቅር ነው ያበደው ይሉ የለም? አዎ በፍቅር ነው የቀወሰው በላቸው። ስለ ፍቅር ምን ያውቃሉ? በሃሳብ የሚገለሙቱ፣ በሥራ ቦዝነው ከረንቦላ የሚጫወቱ፣ ጫት እያመነዠኩ በከንቱ ፍልስፍና ለሚሟገቱ፣ የመንፈስ ድኩማኖች፣ ሲመሽ አንቡላ እየጋፉ በየጎዳናው ለሚጣለዙ ግብዞች፣ አስረግጠህ ንገራቸው። እኔ ሰው ወድጄ ስለሰው ነው ያበድኩት . . . እነርሱ ግን የራሳቸውን ጠልተው ሰለ ሆዳቸው አብደዋል። አዎ አሁን በእኔና በእነሱ መካከል ልዩነት አለ። ይኸውም እኔ ሰው ወድጄ ስለፍቅር እራሴን ሰጥቻለሁ፣ እነሱ ደግሞ ሞራል አጥተው ለሱስ ስብዕናቸውን ጥለዋል።”
“አይገርምም! ለሴት ፍቅር እንዴት ታለቅሳለህ ብሎ ጠየቀኝ እኮ አንዱ። እንዴት አላለቅስም? አለቅሳለሁ እንጂ! ሱዳን ነበር የተዋወቅነው። እዚያ ነው ያፈቀራት በላቸው።”
ሻይ የምትሸጥበት ቦታ ነው የተዋወቅነው። ገንዘብ አልነበረኝም። ርቦኝ ነበር ። ምንም ሳልፈራ መራቤን ነገርኳት። ዳቦና ሻይ ሰጠችኝ። እንደ እናቴም እንደ እህቴም ታየችኝ። ደግነትዋ እንድቀርባት አደረገኝ። በልቼ ስጨርስ ሲርብህ ሁል ጊዜ ና አለችኝ። እኔም ከእሷ አካባቢ መጥፋትን አልደፈርኩም። ስቀርባት ወደድኳት ። ስቀርባት ወደደችኝ ። ተዋደድን። እኔ ገንዘብ አልነበረኝም። ከውጭ ይልኩልኛል ብዬ የተማመንኳቸው ወንድሞቼና እህቶቼን በቃላቸው አላገኘኋቸውም። ታሪኬን ነገርኳት። አዘነችልኝና እኔ አለሁልህ አለችኝ። ገንዘብ ሠርተን አውሮፓ እንደርሳለን አይዞህ አለችኝ። ከወንድሞቼና ከእህቶቼ ያጣሁትን የሰው እምነት እንደገና የሰጠችኝን ካላፈቀርኩ ማንን ላፍቅር?”
“ንገራቸው ለእነዚህ ብኩኖች! ሻይ ሽጣ ነበር ወደ ሊቢያ የምንሄድበትን የከፈለችው። ያንን ሁሉ መከራ አልፈን አብረን ነበር ሊቢያ የደረስነው። ካንተ አልለይም ብላ አብራኝ የተሰቃየችው። ሳጣ ያጣችው፣ ሳገኝ የተደሰተችው፣ የፍቅር ማጀቴ ነበረች እኮ ። አንድ ለእኔ የተፈጠረች፣ ውብ ቆንጆ፣ ደግ ለሰው አዛኝ፣ ጠይቅ ድፍን ሱዳንን፣ ጠይቅ ድፍን ሊብያን፣ ማን እንደነበረች ይነግሩሃል። . . . እርጉዝ እኮ ነበረች፣ የመጀመሪያው ልጄ እናት፣ አውሮፓ እናሳድጋለን ስንል ነው እኮ ጥላኝ የሄደችው፣ እንዴት አላብድ? እንዴት አልቀውስ፣ እንዴት አላለቅስ፣ ለእሷ ያልታበደ ለሌላ ለማን ይታበድ?”
“እነዚህ ስለ ፍቅር ምን ያውቃሉ? እነዚህ ከልጃቸው አፍ ቀምተው ለቁማር የሚገብሩ እብዶች እኔን እንዴት ቀውስ ይሉኛል? እነሱ አሉ አይደሉም እንዴ ጨርቃቸውን ያልጣሉ በቁም ሙቶች። ይህንን ቀውስ አስወጡት ሲሉ በጫት አፋቸው ሲለፈልፉ አያፍሩም እኮ።”
ነገሩን ለማወቅ ቸኩዬ “. . .ታዲያ ለምን ተጣላችሁ? የትነች ያለችው? እናስታርቃችሁ እንጂ. . .?” ብዬ ጠየቅኩት። ዓይኑን ፈጠጥ አድርጎ አይቶኝ ። ቀጠለ።
“እኔ ጠቤ እንደነሱ ከሰው አይደለም። እኔ ጠቤ ከተፈጥሮ ነው። ከበረሃው ነው በልልኝ፣ ከማዕበሉ ጋር ነው በልልኝ። ያንን የሳሃራን በረሃ አቋርጠን ሊቢያ ስንደርስ ደስታችን ብዙ ነበር ። መለያያችን መድረሱን መች አስብንና። ሁለት ወር ሊቢያ ውስጥ ተደብቀን ኖርን። በተለይ እሷ ራሱዋን ደባብቃ አስቀያሚ ለመምሰል ትጥር ነበር። የእሷን ቁንጅና ያዩ ሊቢያኖች እሷንም እንደማይለቋት እኔንም እንደማይለቁኝ አውቀን ነበር። ለነገሩ ሁላችንም ተደብቀን አልነበረም የምንኖረው? እዛ ነበር እርጉዝ መሆኗን የነገረችኝ ። የመደንገጥም፣ የመደሰትም፣ የማዘንም ስሜት ተሰማኝ። እንደ ምንም ገንዘቡ ተከፍሎ፣ ጀልባው ተዘጋጀና ጉዞ ጀመርን። የሊቢያን የባሀር ክልል ስንወጣ ጀልባው ላይ ችግር እንዳለ ተረዳን። ከአንድ ወገን ያሉ ሰዎች በተፈጠረው ግርግር ወደ እኛ አካባቢ መጡ ። ጀልበዋ ተገለበጠች። ብዙዎቹ ሰመጡ። እኔ እጇን እንደያዝኳት እሷም እጄን እንደያዘችኝ ነበር ጀልባው መስጠም የጀመረው። በአንድ እጄ እሷን በሌላው ጀልባውን እንደያዝኩ፣ እሷ ደግሞ በአንድ እጇ እኔን በአንድ እጇ ባዶውን ጀርካን እንደያዘች ነበር። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሳይታሰብ ማዕበል ተነሳ። ይህንን ጊዜ ስትጸልይ ነበር። ፈጣሪ ላልተወለደው ልጃችን ብለህ ማረን፣ ማዕበሉን አቁምልን እያለች ነበር የምትጸልየው፣ ማርያምን ነበር የምትማጸነው።”
“በአንድ እጄ እሷን በአንድ እጄ ጀልባውን ይዤ ነበር ማዕበሉን ለመቋቋም የታገልኩት። በከፍታ የተነሳው ማዕበል ውሃውን ፊታችን ላይ ስለረጨን አፈነን። እጄን ለቀቀችው። ለመያዝ ሞከርኩ አልቻልኩም። እሷም ታገለች። ስሜን እየጠራች ጮኸች። ከአጠገቤ ድምጿ ራቀኝ። ድምጿ በአራቱም ማዕዘን ይሰማኝ ጀመር። ወዴት ልሂድ? ዋና አልችል። እዚህ ነኝ ብዬ መለስኩ። አበድኩ፣ በዚያ ጨለማ ምን ላድርግ፣ አበድኩ፣ ጮኩ፣ ምን ልሁን? ሌሊቱን ሁሉ ተጣራሁ፣ ድምጿ እየራቀ መጣ። እንዲሁ እንዳበድኩ ምሽቱ እየነጋ መጣ። ጠዋት ላይ የለችም፣ ትልቅ መርከብ መጥቶ እኛን አዳነን፣ ጀሪካኑን በሩቅ አየሁት። ፈለኳት ነገር ግን ላገኛት አልቻልኩም፣ የለችም። ከዚያ ቀን ጀምሮ መንፈሴ ታወከ፣ ህሊናየ ተነካ፣ ሰላሜና ፍቅሬ አብሮ በማእበል ዳግም ላይመለስ ተወሰደ፣ እኔም የሰውና የመንፈስ ደሃ ሆንኩ። አበድኩ፣ ቀወሰኩ። ንገራቸው ለምን እንደቀወስኩ። መቼም አይሰሙህም። ቁማር ተበልቶ አበደ ብትላቸው ነበር የሚሰሙህ!”
“ለእነዚህ ሃይማኖት ለሌላቸው ግብዞች። ለእሷ ያላበድኩ ለማን ልበድ?. . . ለማን ልቀውስ? እንደነርሱ ለቁማር፣ ለጫት፣ ለዝሙት . . . ? ጂኒ ባሕር ላይ መታው አይደል የሚሉህ? አዎ! የባህር ነውጥ ጭካኔና የሰው ፍቅር ማዕበል፣ የሳህራ በረሃ አባዜና የሰው ልጅ ውዴታውና ውለታው ነው እሱን ያቀወሰው በላቸው። እንደ እናንተ በየመሸታ ቤቱ ከበርቻቻና ጫት ቁማርና አደንዛዥ ዕጽ አይደለም እኔን ያሳበደኝ ብሏል በላቸው። መቼም ስለደነዘዙ አይሰሙህም እንጅ፣ ንገራቸው። ሰው ለሰው እንደ ተፈጠረና እንደሚኖር ሁሉ፣ ሰው ለሰው እንደሚሞትም ይወቁ።”
ካለኝ በሁዋላ፣ ጥሎኝ እያለቀሰ ሄደ። እያነባ፣ እየጮኸ፣ እያጉተመተመ፣ ሄደ . . . የባህሩ ጂኒ፣ የባሕሩ ጋኔል ነው ፍቅሬን የወሰዳት እያለ ሄደ። ቀን ከሌሊት አነባለሁ፣ አለቀስሳለሁ፣ ለእንባና ለሃዘን ቀጠሮ የለውም ጸጋዬ አንተም አልተረዳኸውም እያለ ፈጠን ፈጠን እያለ ሄደ።
መከራ ሲመጣ አይነግርም አዋጅ ፡ 
ሲገሰግስ አድሮ ሌት ይደርሳል እንጅ
እንዲሉ፣ ጸጋዬ ተሳስተሃል፣ እኔ ዛሬም ነገም አነባለሁ፣ ዓይኔ እስከሚከዳኝ አነባለሁ። የሰው ልጅ አሳር ፍፃሜ እስከሚያገኝ፣ ፍቅር፣ ደግነት ልግስናና ርህራሄ ሚዛን እስከሚደፋ፣ ፣ የሰውልጅ ሃብቱ ሰው መሆኑ እስኪታወቅ ድረስ ዛሬም ነገም አነሆ አለቅሳለሁ.፣ማዕበሉ ፀጥ እስከሚል አነባለሁ . . እያለ እያጉተመተመ፣ ከዓይኔ ራቀ።
ተፈጸመ
(ግንቦት፡ 2015 ዓ.ም)
Beljig.ali@gmail.com
• በፍራንክፈርት ከተማ የሊቢያንና የደቡብ አፍሪካን ሰማዕታት ለማስታወስ በተዘጋጀው የሐገር ፍቅር ሥነ ጥበብ ዝግጅት ላይ የቀረበ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልብ ወለድ።

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው



እነ ቴዎድሮስ አስፋው ጥፋተኛ ተባሉ

• ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር


ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ‹‹ኢህአዴግ ሌባ ነው፣ ህገ መንግስቱ ወረቀት ነው፣ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው፣ ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው›› በሚል ብጥብጥና ሁከት ፈጥራችኋል፣ የሀሰት ወሬ አውርታችኋል ተብለው የተከሰሱት እነ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ሰኔ 22/2007 ዓ.ም አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

ጥፋተኛ ከተባሉት መካከል አንደኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ አስፋው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሆን ያሬድ ደመቀ እና አንዋር ከድር የፓርቲው አባል አይደሉም፡፡ እነ ቴዎድሮስ ጥፋተኛ የተባሉት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 486/ለ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ተብሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ቴዎድሮስ ‹‹የተመሰረተብኝ ክስ የሀሰት ነው፡፡ የተሰማው ምስክርም የሀሰት ነው›› ሲል ውሳኔው ፖለቲካዊ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

ዳኛው አንዴ ጠፋተኛ መባሉን በመግለፅ ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑን ቅሬታ ማቅረብ እንደማይችል ገልጸው ማቅለያ እንዲያቀርብ በጠየቁበት ወቅትም ወጣት ቴዎድሮስ ‹‹የተባለውን ወንጀል ፈጽመዋል ብንባል እንኳ የነበረው ሁኔታ መታየት አለበት፡፡ 30 ኢትዮጵያውያን በጭካኔ የታረዱበት ወቅት ነው፡፡ በታሪካችን እንዲህ አይነት ውርደት አጋጥሞን አያውቅም፡፡ መንግስት የታረዱትን ወገኖቻችን ኢትዮጵያውይነት በሚክድ መልኩ ያወጣው መግለጫ ደግሞ የሚያበሳጭ ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆን አለመሆናቸውን ላጣራ ከማለቱ በተጨማሪ ለሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን መቀጣጫ እንደሚሆን መግለፁ ደግሞ በጣም አሳፋሪ ነበር፡፡ ተፈፀመ የተባለውን ነገር እውነት ነው ቢባል እንኳ በዚህ ስሜታዊ በሚያደርግ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል›› ብሏል፡፡

ወጣት ቴዎድሮስ አክሎም ‹‹እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ህግ ተርጓሚው ገለልተኛ ሆኖ እንዲሰራ በመታገል ህግ እንዲሰፍን የራሴን አስተዋጽኦ እያደረኩ እገኛለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገሉ ከሚገኙት ወጣቶች መካከል አንዱ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ሲል የክስ ማቅለያ አቅርቧል፡፡ ከቴዎድሮስ በተጨማሪ ያሬድ ደመቀና አንዋር ከድርም የክስ ማቅለያዎችን አቅርበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ቴዎድሮስ ለክስ ማቅለያነት ያቀረባቸው የመንግስት መግለጫ፣ ህግ እንዲሰፍን እየሰራ መሆኑና ቀሪዎቹ ተከሳሾች በማቅለያነት ያቀረቧቸው ጉዳዮችን በማስረጃ እንዲያቀርቡና በማቅለያነት የቀረቡት ጉዳዮችም ማቅለያ መሆን እንደሚችሉና እንደማይችሉ ለመወሰን ለሐምሌ 3/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው



እነ ቴዎድሮስ አስፋው ጥፋተኛ ተባሉ

• ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር


ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ‹‹ኢህአዴግ ሌባ ነው፣ ህገ መንግስቱ ወረቀት ነው፣ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው፣ ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው›› በሚል ብጥብጥና ሁከት ፈጥራችኋል፣ የሀሰት ወሬ አውርታችኋል ተብለው የተከሰሱት እነ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ሰኔ 22/2007 ዓ.ም አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

ጥፋተኛ ከተባሉት መካከል አንደኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ አስፋው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሆን ያሬድ ደመቀ እና አንዋር ከድር የፓርቲው አባል አይደሉም፡፡ እነ ቴዎድሮስ ጥፋተኛ የተባሉት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 486/ለ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ተብሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ቴዎድሮስ ‹‹የተመሰረተብኝ ክስ የሀሰት ነው፡፡ የተሰማው ምስክርም የሀሰት ነው›› ሲል ውሳኔው ፖለቲካዊ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

ዳኛው አንዴ ጠፋተኛ መባሉን በመግለፅ ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑን ቅሬታ ማቅረብ እንደማይችል ገልጸው ማቅለያ እንዲያቀርብ በጠየቁበት ወቅትም ወጣት ቴዎድሮስ ‹‹የተባለውን ወንጀል ፈጽመዋል ብንባል እንኳ የነበረው ሁኔታ መታየት አለበት፡፡ 30 ኢትዮጵያውያን በጭካኔ የታረዱበት ወቅት ነው፡፡ በታሪካችን እንዲህ አይነት ውርደት አጋጥሞን አያውቅም፡፡ መንግስት የታረዱትን ወገኖቻችን ኢትዮጵያውይነት በሚክድ መልኩ ያወጣው መግለጫ ደግሞ የሚያበሳጭ ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆን አለመሆናቸውን ላጣራ ከማለቱ በተጨማሪ ለሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን መቀጣጫ እንደሚሆን መግለፁ ደግሞ በጣም አሳፋሪ ነበር፡፡ ተፈፀመ የተባለውን ነገር እውነት ነው ቢባል እንኳ በዚህ ስሜታዊ በሚያደርግ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል›› ብሏል፡፡

ወጣት ቴዎድሮስ አክሎም ‹‹እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ህግ ተርጓሚው ገለልተኛ ሆኖ እንዲሰራ በመታገል ህግ እንዲሰፍን የራሴን አስተዋጽኦ እያደረኩ እገኛለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገሉ ከሚገኙት ወጣቶች መካከል አንዱ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ሲል የክስ ማቅለያ አቅርቧል፡፡ ከቴዎድሮስ በተጨማሪ ያሬድ ደመቀና አንዋር ከድርም የክስ ማቅለያዎችን አቅርበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ቴዎድሮስ ለክስ ማቅለያነት ያቀረባቸው የመንግስት መግለጫ፣ ህግ እንዲሰፍን እየሰራ መሆኑና ቀሪዎቹ ተከሳሾች በማቅለያነት ያቀረቧቸው ጉዳዮችን በማስረጃ እንዲያቀርቡና በማቅለያነት የቀረቡት ጉዳዮችም ማቅለያ መሆን እንደሚችሉና እንደማይችሉ ለመወሰን ለሐምሌ 3/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ሻለቃ አርጋው ካብታሙ ከአገር እንዳይወጡ ተከለከሉ

ሻለቃ አርጋው ካብታሙ ከአገር እንዳይወጡ ተከለከሉ
ሻለቃ አርጋው ካብታሙ የቀድሞውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተለያዩ እርከኖች ሲያገለግሉና በገዢው ስርዓት አፈና ተፈጽሞባቸው ወህኒ የተወረወሩ ኢትዮጵያዊያንን ዘር፣የሐይማኖትና የፓርቲ አጥር ሳይከልላቸው በመጠየቅና በማጽናናት ይጠቀሳሉ፡፡ሻለቃ በቅርቡ አሜሪካን አገር የሚገኘው ልጃቸው ለሚፈጽመው የሰርግ ሰነ ስርዓት በቦታው ለመገኘት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው በበረራቸው ቀን ቦሌ ኤርፖርት እንዳመሩ ስማቸው ከአገር እንዳይወጡ መመሪያ ከተላለፈባቸው ሰዎች አንዱ በመሆናቸው በልጃቸው ሰርግ ለመታደም ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ግኑኝነት አላቸው አልያም ስርዓቱን ይቃወማሉ ተብለው በጥርጣሬ ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች መካከል የ500 ሰዎችን የስም ዝርዝር በቦሌ ኤርፖርት ተርሚናል ውስጥ የሚሰሩ የምዝገባ ሰራተኞች መያዛቸውን መረጃዎቸ ይጠቁማሉ፡፡
በዛ ያሉ ወጣቶችም በቦሌ በኩል ከአገር ለመውጣት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ፓስፖርቶቻቸውን ተነጥቀው እንዲመለሱ መደረጋቸውና አንዳንዶቹም በድንበር በኩል በሟቋረጥ ከአገር መውጣታቸው ይታወቃል፡፡
ህገ መንግስቱ የዜጎች የመዘዋወር መብት መከበሩን በወረቀት ደረጃ የሚያትት ቢሆንም መንግስት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ህገ መንግስቱን በመጨፍለቅ የዜጎችን እንቅስቃሴ በመገደብ የበቀል እርምጃ መውሰዱ አምባገነንነቱን ወለል አድርጎ ያሳያል ፡፡

Indian woman hits record by giving birth to 11 babies at once





An Indian woman has just broken the world record after she gave birth
to eleven babies at once. Congratulations!

Indian woman hits record by giving birth to 11 babies at once


Released on – Monday,06 February , 2012 -16:30 By: Mohamed Gabal An Indian Woman delivered eleven babies at once inside an Indian hospital and she enjoys good health after the operation, many internet forums reported. The woman should be listed in Guinness book of records.

በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል/ESFNA ዛሬ በድምቀት ተከፈተ

በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ በሜሪላንድ በርድ ስታዲየም በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በድምቀት ተከበረ:: ከአሜሪካ እና ከካናዳ የመጡ ከ30 በላይ ቡድኖች በስታዲየሙ በመገኘት በዚሁ በመክፈቻ ዝግጅት ላይ ራሳቸውን አስተዋውቀዋል:: በዚህ ዝግጅት ላይ ለእንግሊዙ አርሰናል ክለብ እየተጫወተ የሚገኘው ጌድዮን ዘላለም የተገኘ ሲሆን ከሕዝቡም ደመቅ ያለ አድናቆት ተችሮታል:: በዚሁ የመክፈቻ ዝግጅት የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ባሰሙት ንግግር የዘንድሮው ዝግጅት በርካታ ሕዝብ በመገኘት በመከፈቱ መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ቀናት ደማቅ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል:: እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ረቡዕ ምሽት የብሄራዊ ትያትር 60ኛ ዓመት በዓል በታሪካዊ ሁኔታ ይከበራል; የፊታችን ሐሙስ አርብና ቅዳሜም ከ እግር ኳሱ በተጨማሪ ታላላቅ አርቲስቶች የሚገኙባቸው ትልልቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እንደተዘጋጁና ሕዝቡም በነዚህ ስፍራዎች እየተገኘ እንዲዝናና ጥሪያቸውን አቅርበዋል:: የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 32ኛ ዓመት በዓል መታሰቢያነቱ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ ላለቁት ኢትዮጵያን መታሰቢያ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዋል:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተወካይ ባሰሙት ንግግር የሊቢያውን ሰቆቃ አስታውሰው “እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አይረሳትም” ብለዋል:: የመድሃኔዓለም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ተወካይ ቄስ በሪሁን መኮንን በሊቢያው ሰቆቃ ሊያስተምረን ስለሚገባ ነገር ተናግረዋል:: የሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ልዩነት ሳይበግራቸው በአንድነት በመቆም ሊሰሩ እንደሚገባ ይህ ሃዘን አስተምሮናል ብለዋል:: በሰሜን አሜሪካ የሙስሊም ኮሙዩኒቲ ተወካይ ሼክ ሱለይማን ነስረዲን በበኩላቸው በሊቢያ የተገደሉት ወገኖች የተገደሉት ክርስቲያን በመሆናቸው ሳይሆን ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሃይማኖቶች መከባበር ለመጠቆም ሞክረዋል:: በዛሬው የመክፈቻ ጨዋታ የላስቬጋሱ አበበ ቢቂላ የሲያትሉን ዳሸን 2ለ0 – ዴንቨር የሚኒሶታውን ኒያላ 4ለ0 – ቺካጎ ፒላደልፊያን 2ለ1 – ኦሃዮ ቦስተንን 4ለ1 ሲያሸንፉ የሎሳንጀለሱ ዳሎል የዲሲው ዩናይትድ 1ለ1 እንዲሁም የሎሳንጀለሱ ስታርስ ከሜሪላንዱ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር 1ለ1 ተለያይተዋል:: በሌላ በኩል የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሃፊ አቶ ያሬድ ነጋሽ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት በዛሬው የመክፈቻ ዝግጅት መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ቀናት በርካታ ሰው እንደሚገኝ ያላቸውን ግምት ገልጸዋል:: በሃይማኖት አባቶቹ መል ዕክት መደሰታቸውንም ገልጸዋል:: በድምቀት የተከፈተው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫልን በስፍራው የሚገኙት የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች በየቀኑ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይዘግቡላችኋል:: -
Like · Comment · 

Saturday, June 27, 2015

የመሀይማን ቁጥር በሚልዮን ጨምሮ ዕድገት እንዴት አለ ይባላል? ኢህአዴግ/ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ ወዲህ በኢትዮጵያ ማንበብ እና መፃፍ የማይችሉ ጎልማሶች (የመሃይማን) ብዛት ከሰባት ሚልዮን በላይ መጨመሩን የዩኔስኮ ሰነድ ያመላክታል (ትኩረት - ጉዳያችን )

ኢትዮጵያ በዘመናዊ መንግስት ስሪቷ የጎልማሶች ትምህርትን ለማስፋፋት በቀዳማዊ  ኃይለ ስላሴ ዘመን ''የፊደል ሰራዊት'' በሚል በደርግ ዘመን ደግሞ ''የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ'' በሚል ሁለት አበይት ጎልማሶችን የማስተማር ዘመቻ አድርጋለች።በተለይ በደርግ ዘመን መሃይምነትን በማጥፋት ዘመቻ ከአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትም በበለጠ መልክ በመስራቷ ''የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣የሳይንስ እና የባህል ድርጅት'' (UNESCO) ኢትዮጵያን ተሸላሚ እንድትሆን ማድረጉ ይታወቃል።በወቅቱ በርካቶች ለማንበብ እና ለመፃፍ ከመቻላቸውም በላይ በመደበኛ ትምህርት እራሳቸውን አሻሽለው ለከፍተኛ ትምህርት ደረጃም የበቁ ነበሩ።

የዩኔስኮ መረጃ እንድሚያሳየው ኢትዮጵያ ከዘመነ ደርግ ወዲህ በኢህአዲግ/ወያኔ የስልጣን ዘመን ይህ ነው የሚባል የጎልማሶች ትምህርት ዘመቻ ካለመደረጉም በላይ ሀገሪቱ ለዘርፉ የመደበችው በጀት እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ይታወቃል።የጎልማሶች ትምህርት አለመስፋፋት ማለት ባብዛኛው ሕዝብ በግብርና በሚተዳደርባት ሀገር ውስጥ ህዝቡ የተፃፈ ማስታወቂያ ማንበብ አለመቻሉን ብቻ ሳይሆን የጤና ማስታወቂያዎች፣መመሪያዎች እና የመንገድ ላይ ማስታወቂያዎችንም አያነብም ማለት ነው።

''ትምህርት የእድገት ሁሉ ቁልፍ ነው''።ስለ እድገት ስናወራ ቁልፉ የትምህርት መስፋፋት ብሎም የጎልማሶች ከመሃይምነት መላቀቅ ነው።የኢህአዲግ/ወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያ አድጋለች የትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ ወዘተ የሚለው እንግዲህ የእድገት ትልቁን ቁልፍ ጉዳይ ህዝብን ከመሃይምነት ማላቀቅ የሚለውን ታሳቢ ሳያደርግ መሆኑ የእድገት እቅዱ ምን ያህል ሳይንሳዊ መንገድን እንዳልተከተለ አመላካች ነው።

እንደ ዩኔስኮ መረጃ መሰረት  ኢትዮጵያ ባለፉት 21 ዓመታት ውስጥ የጎልማሶች መሃይማን ቁጥር ከሰባት ሚልዮን በላይ መጨመሩን ያመላክታል።ጉዳዩ የስርዓቱን መሰረታዊ ችግር ያመላክታል።በእዚህ አይነት የስታስቲክስ ስሌት የጎዳና ተዳዳሪ ቁጥር ከጥቂት ሺዎች አሁን በኢትዮጵያ ከተሞች የሚንከራተቱት የጎዳና ተዳዳሪዎች ቁጥር በመቶሺህ መቆጠሩ ወዘተ እያልን ብናሰለው በእውነት ኢትዮጵያ ያለችበትን ችግር እና በትራንስፎርሜሽኑ እቅድ መሰረት አደገች! ተመነደገች! ተብሎ የሚነገረን ከልማት መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ ጋር የተቃረነ መሆኑን ለመረዳት ይረዳን ነበር።

በጥቂት ሰዎች እና ድርጅቶች እጅ የሚገኘውን ሀብት ለጠቅላላ ሕዝብ እያካፈሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገቢ ይህንን ያክል ደረሰ እየተባለ የሚነገረው ፈፅሞ ከእውነታው ጋር አይገናኝም።ከእዚህ በታች ዩኔስኮ የሀገራት የጎልማሶች መሃይማን ቁጥር ያመላከተበት ሰንጠረዥ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።በመቀጠል በቀደመው መንግስት በከፍተኛ ስኬት የተከናወነው ''የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ'' ተሳታፊ የነበረው ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ ያዜመው ''ማንበብ እና መፃፍ የተሰኘው ዜማ በወቅቱ ከፍተኛ የሕዝብ አትኩሮት ስቦ ነበረ።

ሚኒስትር ዲኤታዎች ድምጽ አልባና ደካሞች ናቸው ተባሉ

ሚኒስትር ዲኤታዎች ድምጽ አልባና ደካሞች ናቸው ተባሉ


ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“በኢትዮጵያ ያሉ ሚንስትር ድኤታዎች ድምፅ አልባ እና ተሳትፎ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው” ሲል የኢህአዴግ ጽ/ቤት የአመራር ግንባታ የመለስ ዜናዊ የአመራር ግንባታ ክፍል ያወጣው ደብዳቤ አመለከተ። ደብዳቤው ዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ያላቸውን ሚኒስትር ድኤታዎች ዘርዝሮ አስቀምጧል።
በአቶ አዲሱ ለገሰ የሚመራው እና ከፍተኛ የኢህአዴግ አባላትን ብቻ የሚያሰለጥነው የኢህአዴግ አመራር ማሰልጠኛ ክፍል የአመራሮችን አቅም በመገምገም በሚንስትር ድኤታ ደረጃ ያሉትን ብቻ ለይቶ በመጥራት ውይይት አካሂዷል፡፡ በዚህም በመሪነት ደረጃ ለኢህአዴግ አቅም መጎልበት አስተዋጽኦ ያላደረጉ እና ቀዳሚ መሆን ያልቻሉ ያላቸውን አካላትን ዘርዝሮ አስቀምጧል፡
በዝቅተኛ ደረጃ የተመደቡት የፊደራል ጉዳዩች ሚንስቴር ሚንስተር ድኤታ አቶ ሙሉጌታ ውለታው፣ የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ አቶ ወንዲራድ ማንደፍሮ፣ የኢፌድሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ አምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታው አቶ ፉኢድ ኢብራሒም፣ የኢንዱስትሪ ሚንስትር ድኤታ ልዩ አማካሪ አህመድ ኑሩ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ድኤታ አቶ ሙልጌታ ሰኢድ ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ድኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፣ የትምህርት ሚኒስትር ሚንስትር ድኤታ ዶክተር ካባ ኡርጌሳ፣ እንዲሁም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ድኤታ አቶ ማህሙድ አህመድ ጋአስ ናቸው።
በመካከለኛ ደረጃ የተቀመጡት ደግሞ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ታደሰ ኃይሌ፣ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ድኤታ አቶ ጌታቸው ነጋሽ፣ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ድኤታ አቶ አህመድ ሽዴ እና የፍትህ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ናቸው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ባለባቸው የአቅም ውስንነት ምክንያት ወደ ሚንስትርነት ማእረግ ደረጃ ማደግ ስለማይችሉ የአቅም ግንባታ ስልጠና በክረሙቱ ተከታታይ ወራት ያስፈልጋቸዋል ተብሎአል። ይህም ሁኖ መሻሻል ካላሳዩ ከስልጣናቸው ወርደው በምትካቸው በአዲሱ ሰው እንዲተኩ የኢህአዴግ አመራር ማሰልጠኛ ኢንስትትዩት በአሁኑ ስያሜው የመለስ አመራር ማሰልጠኛ አካዳሚ ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ አስተያየታቻውን አስፍረዋል፡፡
የከፍተኛ አመራሩ ምደባ ግምገማ ኮሚቴ ተዋቅሮ በድክመት ፣ ጥንካሬ እና አማራጭ ተብሎ እየተለየ ሲሆን ፣ ከነድክመታቸው የሚያሰቀጥላቸውንና ወደ አመራር የሚያመጣቸውን አዳዲስ የፖለቲካ መሪዎች ስም ዝርዝር እና ግለ ታሪክ ተዘጋጅቶ እንዳለቀና እንደደረሰን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

በወጣት ተመስገን ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል የኢህአዴግ የግፍ አስተዳደር መገለጫ ነው ሲል መድረክ አስታወቀ

በወጣት ተመስገን ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል የኢህአዴግ የግፍ አስተዳደር መገለጫ ነው ሲል መድረክ አስታወቀ


ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣት ተመስገን ታፈሰ ተሰማ ዕድሜው 22 ዓመት ሲሆን በትምህርት ደረጃውም በማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ ያገኘ ወጣት ነው፡፡ ትውልዱና ዕድገቱ በደቡብ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ወረዳ ውስጥ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኢማዴ-ደህአፓ/መድረክ አባል ሆኖ ለመታገል የወሰነና በመድረክ አባልነታቸው ምክንያት በሀገራቸው ሠርተው የመኖር የዜግነት መብታቸውን እየተነፈጉ አስተዳደራዊ ግፍ እየተፈጸመባቸው ካሉ ወጣቶች አንዱና ተጫባጭ ምሳሌ ሆኖ የሚገኝ ወጣት ነው ብሎአል መድረክ።
መድረክ የወጣቱን በደል ሲዘረዝር “የቡርጂ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ለትራንስፖርት አቅርቦት አደረጃጀት ስምሪት ባለሙያ፣ የሥራ መደብ ሠራተኛ ለመቅጠር በ05/09/07 የቅጥር ማስታወቂያ አወጣ፡፡ በማስታወቂያው መሠረት የጽሑፍና የቃል ፈተናዎች የተሰጡ ሲሆን የጽሑፍ ፈተናው ከመቶ ዘጠና፣ የቃል ፈተናው ከመቶ አምስት እና የትምህርት ማስረጃው ከመቶ አምስት እንዲይዝ ተደርጎ ውድድሩ ተካሄደ፡፡ ይኼው ጽ/ቤት በ18/09/07 በቁጥር 327-ኢ2-05 ባወጣው የውድድር ውጤት መግለጫ ማስታወቂያ መሠረት አቶ ተመስገን በጽሑፍ ፈተናው 84፣ በቃል ፈተናው 5፣ እና በትምህርት ማስረጃው 5 በድምሩ 94 ከመቶ በመግኘት በከፍተኛ ነጥብ አንደኛ ወጥቶ አለፈ፡፡ ” ይላል።
መድረክ በመቀጠልም ” በ19/09/07 ልክ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ለጽ/ቤቱ ሪፖርት እንዲያደርግም በማስታወቂያው ተገልጾለት፣ ወጣቱም በተገለጸለት መሠረት ሪፖርት አደረገ፡፡ ጽ/ቤቱም በዕለቱ ወጣቱ የጤናና የጣት አሻራ ምርመራ ውጤቶችን እንዲያቀርብ ለቡርጂ ወረዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እና ለወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት በቁጥር 328/አ-1/ሠ14/07 እና 329/አ-1/ሠ14/07 የትብብር ደብዳቤ ጽፎ ለወጣቱ ሰጠ፡፡ የቡርጂ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ለጌዴዎ ዞን ፖሊስ መምሪያ የጣት አሻራ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ እንዲቀርብ ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን የዞኑ ፖሊስ መምሪያና የቡርጂ ወረዳ ጤና ጣቢያም ከወንጀል ነፃ የጣት አሻራና ሙሉ ጤናማነቱን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ሰጥተውት እነዚሁኑ ማስረጃዎች ወጣቱ ለቀጣሪው ጽ/ቤት አቅርቦአል፡፡” ብሎአል።
ወጣት ተመስገን ከላይ በተራ ቁጥር 5 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ለጽ/ቤቱ ለማቅረብ ሲንቀሳቀስ በነበረበት ወቅት ፣ወጣቱ የመድረክ አባል መሆኑና በ16/09/07 በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው ምርጫ በወረዳው ውስጥ በሚገኝ ደኬ በተባለ ምርጫ ክልል የመድረክ ታዛቢ/ወኪል ሆኖ መሥራቱ በወረዳው የኢህአዴግ ባለሥልጣናትና በቀጣሪዎቹ በመታወቁ፣ ወጣቱ ማስረጃዎቹን ይዞ በቀረበበት ዕለት ፣ ጽ/ቤቱ የበጀት እጥረትን በማሳበብ በ21/09/07 የተጻፈ የሥራ መደቡ የቅጥር ስረዛ ማስታወቂያ አወጣ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ እሥራኤል ገብረ በጽ/ቤቱ በር ላይ አገኝተውት የመድረክ አባልነቱንና የምርጫ ታዛቢነቱን እንደበጥባጭነት ቆጥረው ” ለካ አንተ ሀገር በጥባጭ ነህ፣ ደርሰንብሃል” በማለት በምስጉን ፀባዩና በታታሪ ተማሪነቱ በአካባቢው ሕብረተሰብና በተማረባቸው ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች የሚታወቀውን ተመስገንን በመሳደብ ሊቀጠር እንደማይችል ፎክሮበታል” ብሎአል።
ከዞኑ ሲቭል ሰርቪስ ጽ/ቤት ድርጊቱ ሕገወጥ ስለሆነ በወጣቱ ላይ የተፈጸመው በደል እንዲታረም ደብዳቤ ለወረዳው የተጻፈ ቢሆንም የወረዳው ባለስልጣናት በሥራው ላይ ሊመድቡት ፈቃደኞች ሆነው አልተገኙም የሚለው መድረክ፣ ስለሆነም ወጣቱ በወረዳውም ሆነ በዞን ደረጃ ላሉትና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች እየተመላለሰ ላቀረባቸው አቤታዎች እልባት ስላልተሰጠ በከፍተኛ ደረጃ እየተጉላላ ይገኛል ብሎአል።
በአሁኑ ወቅት በብዙ አከባቢዎች በርካታ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት በዚህ አይነቱ ፖለቲካዊ ወገንተኝነት በሰፈነበት ብልሹ አስተዳደራቸው እንደተመስገን ታፈሰ ያሉ በርካታ ብርቅዬ ወጣቶቻችንን በሀገራቸው ሠርተው የመኖር መብታቸውን እየገፈፉ “ለአስከፊ ስደት፣ በሰው ሀገር ለስቃይና ለእንግልት እንዲሁም ለአሰቃቂ ሞት እንዲዳረጉ በማድረግ ላይ ናቸው ሲል መድረክ ወቅሷል።
“ይህ አይነቱ ጭፍን አምባገነናዊ እርምጃቸው ግን የሀገራችን ወጣቶች እነርሱ እንደተመኙት እንዲንበረከኩላቸው የሚያደርግ ሳይሆን በይበልጥ የግፍ አገዛዛቸውን እንዲረዱና ከዚሁ የግፍ አገዛዛቸው ነፃ ለመውጣትና ሕገመንግሥታዊ የዜግነት መብታቸውን በተግባር ለማረጋገጥ በቆራጥነት ለትግል እንዲነሱ እንደሚያደርጋቸው የሚያጠራጥር አይደለም” ሲል መድረክ መግለጫውን አጣቃሏል።

የኢህአዴግ መንግስት በረመዳን ጾም ተቃውሞ ሊያይልብኛል ይችላል በሚል ፍርሃት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው

የኢህአዴግ መንግስት በረመዳን ጾም ተቃውሞ ሊያይልብኛል ይችላል በሚል ፍርሃት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው
ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት የሮመዳንን ጾም ተከትሎ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት፣ 53 ሚሊየን ብር በጀት በመመደብ የመስጊድ ኢማሞችን በአክራሪነት ዙሪያ የማሰልጠን እና የማግባባት ስራውን እያከናወነ ነው፡፡
አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ ሲል የሚታየው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሁንም መንግስትን እንቅልፍ እንደነሳው ነው፡፡
በሁሉም ክልልች ለሚገኙ የእስልምና የሃይማኖት አባቶች ህገመንግስቱ እና አክራሪነት በሚል ስልጠና ለመስጠት ሙሉ ለሙሉ የገንዘብ በጀቱን አፅድቆ ለክልል የአሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮዎች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡በቅርቡ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የደህንነት ሰራተኞች እና አንዳንድ የሙስሊም መሪዎች በዝግ ስብሰባ ያደረጉትን ውይይት ኢሳት በተከታታይ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በሌላ በኩል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ያላቸውን ድጋፍ ዛሬ ገልጸዋል።
በታላቁ አንዋር መስጊድ ሙስሊም በተካሄደው ተቃውሞ “የተከሰስነው እኛ ነን ፣ ኮሚቴው ነጻ ነው፣ ከማናምንበት ውጪ ፍርድ አንቀበልም” የሚሉ መፈክሮችን በማሳየት ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል።

5 የመኢአድ አባሎች አንዳርጋቸው ፅጌን ይመስክርልን አሉ

5 የመኢአድ አባሎች አንዳርጋቸው ፅጌን ይመስክርልን አሉ
በነ ዘመነ ካሴ መዝገብ የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባሎች ናቸው አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርብላቸው ነው የጠየቁት የተከሰሱት የግንቦት 7 አባል ናችሁ ተብለው ነው በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ስልጠና ተሰጥቷችሁ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ላለፉት ሁለት አመታት በእስር የሚገኙት
እነዚህ ተከሳሾች አንዳርጋቸው ፅጌ የሚባል ሰው አናውቅም አንዳርጋቸው አሱ አውቃቸዋለሁ አሰልጥኛቸዋለሁ የሚል ከሆነም በናንተ ቁጥጥር ስር ስላለ ችሎቱ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ይዘዝልን እና ይመስክርልን ወይም ይመስክርብን ሲሉ ለፍርድ ቤት አመልክተዋል አቶ አንዳርጋቸው ቀርቦ ምስክርነት ይሰጥ ይሆን ? አቃቤ ህግ በህይወት ይኑር አይኑር የማይታወቅ ሠው ይቅረብልን ማለት አግባብነት የለውም ብሏል ለማንኛው ቀጠሮው ሀምሌ 03/2007 ዓም ስንተኛ ችሎት እንደሆነ አጣርቼ አሳውቃለሁ ፍርድ ቤቱ ግን ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው
አሰግድ ታመነ

daughter of ‘Ethiopian Mandela’ stars in play dramatising plight of kidnapped father

I need my dad to be here, pleads daughter of ‘Ethiopian Mandela’ as she stars in play dramatising plight of kidnapped father

I need my dad to be here, pleads daughter of ‘Ethiopian Mandela’ as she stars in play dramatising plight of kidnapped father






Helawit Hailemariam, centre, with, from left, Doyin Ajiboye, Justine Onokoko, Nadia Carrier Solomon and Nubia Servina

by KOOS COUVÉE

IMAGINE celebrating your 16th birthday while your loving dad, who has committed no crime, is on death row 4,000 miles away in a jail where you fear he may be tortured.

This scenario is in fact reality for Helawit “Holly” Hailemariam, 15, from Clerkenwell, whose father, Andargachew Tsege, a British man from Holloway and a prominent opposition activist in his native Ethiopia, is languishing in a jail in the East African country.

On Wednesday, a new play by Islington Community Theatre starring Helawit and five of her friends marked the anniversary of Mr Tsege’s kidnapping while he was travelling through Yemen.

Her father, also known as Andy, has been kept in secret detention in Ethiopia ever since – the authorities will not even tell his family where he is being held, or allow any contact.

The family hopes the play will pile pressurise on the UK government to press the Ethiopians to release Mr Tsege. It had its first showing at Platform, in Holloway, this week in front of a packed audience, who included his partner and two other children.

Helawit, who plays herself, is seen living the life of a normal teenage girl while at the same time having to deal with her father’s chilling disappearance. In real life, she has just finished her GCSEs at Elizabeth Garrett Anderson School in Angel.

The play highlights government inaction over the plight of “the Ethiopian Nelson Mandela”. After the performance, Helawit said: “My dad has been absent for a year and I am going through so many changes and I need him to be here.



Helawit “Holly” Hailemariam and dad Andargachew Tsege

“We are very worried and we feel the Prime Minister and the government are not doing anything at all.”

She said she was grateful for the way friends had rallied round. “They have really supported me, especially Nadia [Carrier Solomon],” she said. “She knew what I was going through early on.”

The teenager, who will be starting her A-levels at LaSWAP Sixth Form in Parliament Hill in September, said the play may transfer to a south London theatre and be seen at the Edinburgh Festival Fringe.

Mr Tsege, a naturalised British citizen who has lived in London since 1979, is an outspoken critic of the Ethiopian regime and a member of the exiled opposition group Ginbot 7.

The jazz fan was on his way to an opposition conference in Eritrea when he was kidnapped by the Yemenis and handed over to Ethiopian authorities, who had sentenced him to death in absentia in 2009 for conspiring to commit “terrorist acts”.

Human rights organisation Reprieve is concerned that he is being held in solitary confinement and has been tortured.

On Wednesday, Foreign Secretary Philip Hammond said he had spoken to Ethiopia’s Foreign Minister and expressed “deep concern” over Mr Tsege’s solitary confinement.

Helawit’s mother, Yemi Hailemariam, 47, who is spearheading a campaign to have her partner released, was tearful after the play. She said: “It makes me so sad. The government is not pushing enough. We have to make them so we can get him back.”

A petition calling for the release of Mr Tsege has been signed by more than 120,000 people.




http://www.islingtontribune.com/news/2015/jun/i-need-my-dad-be-here-pleads-daughter-%E2%80%98ethiopian-mandela%E2%80%99-she-stars-play-dramatising-p

“ከሀገር ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጦች ላገሬ ያደረኩትን ዉለታ ዋጋ አልሰጡትም” ሼህ አላሙዲ (ገበየሁ ባልቻ)

ሼህ አላሙዲ
በተከታታይ በደቡብ አፍሪካና በአረብ ምድር ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉን እልቂት ከተመለከትኩ በሗላ የሀገራችንን ፖለቲካ መከታተል የበለጠ አሳዛኝ ዜና ያመጣብኝ ይሆናል በሚል ስጋት ኮምፒተሬን በእጅጉ ፈርቸዉ ከረምኩ አንዱ ሳይቋጭ ሌላ መከራ፡ በመከራ ላይ መከራ፡ መሪዎቻችን የመከራ አምካሪዎች፡ ምን ይበጀን ይሆን?። ባለፈዉ ስፈራ ስቸር በተለመደዉ በድር ጥንጥን ስተላለፍ ሼህ አላሙዲ በዉጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች የእሳቸዉን ስራ ዋጋ ሰጥተዉት ለዉይይት ባለማቅረባቸዉ የተሰማቸዉን ሐዘን ፍንጭ የሰጡበት አጋጣሚ ቀልቤን ስቦት ሀሳቤን ልናኘዉ በማለት ወረቀትን ከብእር አገናኘሁ የዜናዉ ምንጭ ኢሳት ለኳሺ ኤልያስ ክፍሌ።
ሼህ አላሙዲ ከኢትዮጵያ አፈር ተበጥብጠዉ እንደዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያነሰ ወይም የጎደለ ኢትዮጵያዊነት ሳይኖራቸዉ እንደኔዉ በትንሿ መንደራቸዉ ተወልደዉ አድገዉ ከጓደኞቻቸዉ ጋር ዘር ሀይማኖት ሳይለዩ ከሰፈራቸዉ ልጆች ጋር ቡድን ተቧድነዉ  ኳስ አቃብለኝ ብለዉ ሲጮሁ፤ ላዘገየባቸዉ ወይም ላላቃበላቸዉ ደግሞ ቆይ ጠብቅ ባንተ ምክንያት ነዉ የተሸነፍነዉ ብለዉ ሲዝቱ፤ ጎል ጠባቂ ተረኛ ሁነዉ ደግሞ ብዙ ጎል ሲገባባቸዉ ሁለተኛ አንመርጥህም እንደዉም ከኛ ጋር አትጫወትም ሲባሉ ሆድ ሲብሳቸዉ። ከዛ ደግሞ አለፍ ብሎ ተማሪ ቤት አጠገባቸዉ የተቀመጠዉን ተማሪ ዞር ሲል ሲቆነጥጡ እሱም ባንኖ አንተነህ ሲላቸዉ እሳቸዉም እኔ አይደለሁም ብለዉ ሲክዱ፤ እሱም ጊዜ ጠብቆ ብድሩን ሲወጣ። እርሳሳቸዉ ሲጠፋባቸዉ አጠገባቸዉ ካለዉ ጓደኛቸዉ ነድፈዉ  አይኔን ግምባር ያድረገዉ ብለዉ ሲክዱ።እንዲህ አንዳንዴ ደግሞ ሾለክ ብለዉ ብይ ሲጫወቱ ፤ ወደ ሁዋላ ደግሞ አንድ ቀላ ድምቡሺቡሺ ያለች ልጅ ወድደዉ እንዳይጠይቁ ፍርሀት በሰራ አከላታቸዉ ገብቶ መላ አጥተዉ በልጅቱ አጠገብ ሲያለፉ እጃቸዉን ኪሳቸዉ ከትተዉ ድንጋይ በጫማቸዉ እየመቱ ልጅቱ እንደበደለቻቸዉ ሁሉ ቆይ ነገ ባላገኝሺ ብለዉ ፎክረዉ በቄንጥ ባጠገቧ ሲያልፉ። ለልጅቱ የላኩት የፍቅር ደብዳቤ ተጠልፎ ዲሊክተሩ ቢሮ ደርሰዉ የተግሳጽና የኩርኩም ናዳ ሲወርድባቸዉ እንዲያ እንዲያ እያሉ ከዛሬዉ ከዲታነታቸዉ ዘመን በላይ የልጅነት ጊዜያቸዉን  በምድረ ኢትዮጵያ እስከ መጨረሻዉ የማይረሳ ህልም ሁኖ የሚቀር የደስታ ኑሮ ኑረዉ እንደእኔዉ ኑሮን ለማቅናት በረሃዉን ተከትለዉ ልባቸዉ ወደመራቸዉ ቦታ ተጓዙ። ምድር በሰጠችህ በረከት ትኖራለህ ተብለዉ ነበርና የዛሬዉን አላሙዲን ሲሆኑ እኔም በላብህ ጥረህ ግረህ ትኖራለህ የሚለዉ የግድ ተግባራዊ እንዲሆን ከሳቸዉ በተቃራኒ ሂጄ  በአንድ የምእራብ ሀገር እኔን ሁኜ እኖራለሁ።
ከተረሳ ሁሉም ይረሳል የፖሊስ ጥፊ የባለስልጣን ግልምጫ ሳያየኝ አምላክን እያመሰገንሁ እኖራለሁ። ምርጫ ሲመጣ አንዴ አንዱን በሌላ ጊዛ ደግሞ የወደፊት እቅዴ ደሀን ሀብት በሀብት ማድረግ ነዉ ሲለኝ ብዙ ጊዜ ብታለልም እዉነት እየመሰለኝ መልሼ ያንኑ እመርጣለሁ። ደግነቱ ወረቀቴ በገባችበት ሳጥን ቆይታ ለመረጥኩት ተፎካካሪ ማንም ሳይነካት ትደርሳለች ክፉም አይነካትም። አደራ እፍረት ባጠገባችሁ ያላለፈ የስርአቱ ደጋፊዎች ኢትዮጵያም  እንዲሁ ነዉ ብላችሁ እንዳታስቁኝ። ይሄኛዉ ነገሩ ሌላ ነዉ እናንተም ታዉቁታላችሁ ብቻ ለማደናቆር ስትፈልጉ ዶሮዋን ቆቅ ታደርጓታላችሁ።
ስለልጂነት ዘመናቸዉ ይህን ካልኩ በሗላ በቀጣዩ ደግሞ እኝህ ግለሰብ በኢትዮጵያዉያኑ መሀል የተለያየ ስምና ስብእና እየተሰጣቸዉ እኛም ከወሬዉ ብዛት ትክክለኛዉ እሳቸዉ የትኛዉ እንደሆኑ ማመን ተቸገርን እዚህ ደርሰናል። ኑሮ እንጨት እንጨት ሲለዉ ገመድ አዘጋጅቶ የመጨረሻ ትንፋሹን ሊዉጥ ሲል ገመዱን በብር ሺራፊ ቆረጡት ይላል በአይኔ በብረቱ አየሁ የሚል አዳናቂ፤ አይ ያንተ ነገር ይሄማ ምን አለዉ ይለዋል ሌላዉ አላሙዲን በአይኑ አይቶ የማያዉቅ ተራኪ። አየር ለመቀበል ወጣ ሲሉ አንዷ ደሀ በትካዜ ተዉጣ እድሌ ነዉ እንግዲህ ምን ይደረጋል እሱ ያዉቃል ብላ እምባዋን ጠራርጋ ስትነሳ አንች ሴት ከቅድም ጀምሮ ስመለከተሺ ነበር ምን ችግር ቢገጥምሺ ነዉ ቢሏት ማንነታቻዉን ያላወቀች አንዲት ያገሬ ሰዉ ልብ በሚሰብር አነጋገር ኑሮዋን ብታወጋቸዉ ልባቸዉ ተነክቶ 3 ልጆቿን ወደ ባህር ማዶ ልከዉ አስተማሩላት ይላል ሌላዉ። ሌላዉ ደግሞ ባለፈዉ አንድ የሰፈራችን ሰዉ የተሰጠዉ እድሜ አልቆ አትድንም አትልፋ ብሎ ሀኪም ቢነግረዉ ጆሮ ጠባቂያቸዉ ጉዳዩን ቢያደርስላቸዉ ባህር ማዶ ልከዉ አሳክመዉት ይባስ ብሎ ሩጫ ጀምሯል ይላል  ለሰዉ የተደረገለተ ወደሱ የሚጋባ የሚመስለዉ ምናበኛ።  ሌላዉ ደግሞ ተሰባስበን የሙዚቃ ክፍል ልናቋቋም ነዉ ብለዉ ወጣቶቹ አቤቱታ ቢያቀርቡ አይናቸዉ ሳያይ እጃቸዉ ብቻ ዘግኖ ያወጣዉን 30000 ዶላር ቢሰጧቸዉ ነገሩ ለዉሻ እንደ ተወረወረ ስጋ አይነት ነገር ሁኖ ተካክደዉ አንዱ ሌላዉ በደረሰበት አይደርስም ይላል። ቡና ቤት ከፈቱላት፤ መኪና ገዙላት፤ የወር ደሞዝተኛ አደረጉት፤ ወደ ትምህርት ተቋም ልከዉ አስተማሩት፤ አቋቋሙት፤ዳሩት የሚለዉ ነገር ችሮታዉ ከተደረገበት ቦታ እያለፈ ሲሄድ በከፍተኛ ፍጥነት እየተባዛና እየገዘፈ የሼህ አላሙዲን ነገር አንዴም እንደ ሮቢን ሁድ(Robin Hood) ለድሀ ተቆርቋሪ አይነት ሲያደርጋቸዉ ሌለዉ ደግሞ ከሰማዩና ከመንፈሳዉያን መሀል ካልሆነ በስተቀር እንዲህ ያለ ነገር ከምድራዊ ሰዉ ሊሆን አይችልም ብሎ ነገሩን ይዘጋዋል።
እኚህ ሼህ በኢትዮጵያ አፈር በቅለዉ ለፍሬ መብቃታቸዉ ሀብታቸዉ ብቻ ሳይሆን መልካቸዉ እና ሌሎች አረቦች ላይ የማናየዉን  እሴቶች በሳቸዉ ላይ ተንጸባርቆ ይታያል። አንድ ቀን ስለ ሀብታም የማላዉቀዉ የለም የሚለዉ ፎርበስ (Forbus) መጽሄትም በኢትዮጵያ ባንድራ ጥለት በተንቆጠቆጠ እጀ ጠባብ እና ኩታ ያሳየን ይሆናል የሚል ተስፋም አለን። እንደዉ አሁን ማን ይሙት ኢትዮጵያዊ መሆን  ምኑ ያሳፍራል? ስለ ሰዉ ልጂ አፈጣጠር ንትርክ ሲነሳ ችግር መፍቻ እና ማነጻጸሪያ የሚሆነዉ ያዉ ኢትዮጵያ ነዉ ።  ነጻነት የጠማዉ የየሀገሩ ዜጋ በምናብ የሚያየዉ ይህችኑ የነጻነት ተምሳሌት ኢትዮጵያን ነዉ አረ ስንቱ መለስ ዘራዊ አዋርዶን ሄደ እንጂ ምን እሱ ቢሞት ሌሎች የማይሞቱትን ተክቷል እንደዉም እሱ ጥሩ ሰዉ ነዉ ቀድሞ መሞቱ። ያነጋገር፤ የባህል፤ ሰዉ የማክበር ምሳሌ ኢትዮጵያዊ ሁኖ እያለ በየምክንያቱ በኢትዮጵያዊነት እንዲታፈር የሚደረግበት ምክንያቱ ምን ይሆን?  ክቡር አቶ መለስ አንዱ ፓርላመንተኛ ደጋግሞ ኢትዮጵያን ብዙ ጊዜ  ፓርላማዉ ዉስጥ ቢያነሳባቸዉ ደማቸዉ ፈልቶ ምነዉ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት አበዛህ ብለዉ ለህዝብ በሚተላለፍ ቴሌቨዢን ዉቃቢዉን ገፈዉት የለ? ዛሬ ሙት ወቃሺ አያድረገኝ እንጂ በዉነቱ በዛን ቀን እዚያ ምስኪን ላይ አቶ መለስ በብስጭት የጮሁት ጩኸት አበበ ከላዉም ከዛ በላይ እሳቸዉ ላይ አልጮኸም ነበር ሰበብ ሁነዉበት አረፉት እንጂ። ነገር ነገርን አስነስቶ ወዳልፈለግሁት አቅጣጫ ገፋኝ እንጂ ነገሬን ለማሳጠር  ዲታ አላሙዲ ገንዘቡን ከላያቸዉ ስናነሳ ኢትዮጵያዊ አንጂ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም ለማለት ፈልጌ ነዉ እንጂ አቶ መለስማ ወደ ማይመለሱበት ሂደዋል።
እንግዲህ ከዚሁ ተንደርድረን ጌታ አላሙዲ ለስራዬ እዉቅና ተነፈግሁ ከህዘቡ ጋር አላገናኙኝ አሉ የዜና ተቋሞችን መዉቀሳቸዉ የወዳጂነት እንጂ የክፋት ስላልሆነ እሳቸዉም በድፍረት ኢትዮጵያዉያን ሰፈር ቀርበዉ ኢትዮጵያዉያን ጋር የሆድ የሆዳቸዉን  ቢወያዩ መልካም ነዉ እላለሁ።  ከእነ አቦይ ስብሀት፤ በረከት ሰምኦን፤  ከመለስ ዘራዊ ጋር አንዴ ሲያጨበጭቡ አንዴ ሲፍነከነኩ ደስታ በደስታ ሁነዉ ሲዝናኑ ብዙ መረጃዎች ደርሰዉናል። ኢትዮጵያዉያን መሀል ግን በእንዲህ ሁኔታ ደፍረዉ የታዩበት አጋጣሚ ብዙም አናስታዉስም።
በነገራችን ላይ ሼህ አላሙዲ በዉጭ የሚኖሩ ኢንቨስተር እንጂ የህዝብ አደራ የተቀበሉ ባለስልጣንም አይደሉም አንዳንዶቻችንም ከአንድ መንግስትና ጥሩ ዜጋ የማይጠበቅ ሰብአዊ፤ልማታዊ፤በጎአድራጎታዊ ስራ ከሼህ አላሙዲ ስንጠብቅ እንታያለን። በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ነገሩን ስናየዉ ሼህ አላሙዲ ግለሰብ ብቻ አይደሉም እሳቸዉ የሚወስዱት የኢንቨስትመንት ዉሳኔ ጉዳቱና ጥቅሙ የሀገራችን ጥቅም እና ጉዳት በመሆኑ ዜጋ አይኑን ከፍቶ ሊመለከተዉ ይገባል። ስለዚህ ሼክ አላሙዲ የግል ሳይሆኑ የህዝብ በመሆናቸዉ የህዝብ የሆነ ደግሞ በሀገሩ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ በግልጽ መገምገም ስላለበት ሼህ አላሙዲም የዚህ ክስተት አንዱ መሆናቸዉን እሳቸዉም ሊገነዘቡልን ይገባል። ጥሩ ሲያደርጉ ጀግና፤ ከኢትዮጵያዊነት መስፈርት ሲወርዱ ደግሞ በህግ አምላክ ማለታችን ግድ ይላል ምንም እንኳን አሁን ህግ ባይኖርም የኢትዮጵያ ሊቃዉንት በየሀገሩ ስለተበተኑ መደበቂያ ጠፍቷል። ባለፈዉ ሼክስፒር ፈይሳ የወያኔን መሪዎች ከሀገር ወጥተዉ ሺቶ እንኳን እንዳይገዙ አስጨንቆ ይዟቸዉ መላ ጠፍቷቸዉ ነበር። ሼክ ሰፒር ፈይሳና ፕሮፌሰር አልማርያም እግር ላይ ወድቀዉ ምህረት ጠየቁ መሰል ዛሬ ፍርሀቱ ለቋቸዉ እየመጡ ሺቶ ነገር እየገዙ፤የቤት ክራይ እየተቀበሉ፤ ቱቦ እያስቀየሩ መመለስ ጀምረዋል።

እንግዲህ ሼህ አላሙዲ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍ ያለ ኢንቨስትመንት የሚያደርጉ ግለሰብ በመሆናቸዉ የሳቸዉ ኢንቨስትመንት ጥቅም እና ጉዳቱን ለመለካት ብቃት ያላቸዉ ባለሙያዎች ጉዳዩን አስመልከተዉ ማብራሪያ እንዲሰጡን ስለጉዳዩ እናዉቃለን የሚሉ ዜጎች ደግሞ የግል ሀሳባቸዉን፤መረጃቸዉን፤ጽሁፋቸዉን ወደ ጋዜጣዉ ቢሮ አከታትለዉ ቢልኩ ስለሳቸዉ ተጨባጭ ግንዛቤ እንይዘለን የሚል ግምት አለኝ።
እሳቸዉም ረቂቅ የሆነዉን የአማርኛ እዉቀታቸዉን ተጠቅመዉ ማብራሪያ እንዲሰጡ ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አለበለዚያ ከክፉ መሪዎች ጋር ተመሳጥረዉ የሀገርን ንብረት አባከኑ የሚለዉ ክስ ተከላካይ እስካልቀረበበት ድረስ እዉነት ሁኖ ሊቀር ይችላል። በአንጻሩ ደግሞ ኢትዮየጵያ ላይ የሚያደርጉት የመዋእለ ንዋይ ፍሰት እሳቸዉም ተጠቅመዉ ህዝቡንና አገሪቱን ለመጠቀም ከሆነ እሳቸዉም ለዚህ ሀሳብ ትክክለኛነት ድፍረቱ ካላቸዉ የፖለቲካ ድርጅቱን እምነት ብቻ እንደ ፖለቲካ ሳይሆን እንደ ሀይማኖት አክርሮ በሚሰብክ የሚዲያ ተቋማት ሳይሆን ኢትዮጵያዉያን ክብር የሚሰጧቸዉና ተአማኒነት ባላቸዉ የዜና ተቋሞች ማብራሪያ እንዲሰጡ ይጠበቃሉ (አይጋ ፎረምን ማለቴ እንዳልሆነ ማስታወሻ ይያዝልኝ አስመሮም ለገሰንም የኢትዮጵያ ችግር ፈላጊ አድርጎ የሚያቀርብ ከክቡር ኢሳይያስ አፈወርቂ ቀጥተኛ ትእዛዝ የሚሰጠዉ በመሆኑ እሱም  አይመቸኝም)።
ሼህ አላሙዲ ላገራችን/ቸዉ ጥሩ ሰርተዉ በመረጃ እጥረት ስራቸዉን ካቃለልንባቸዉ በጣም ያሳዝናል በሌላ በኩል ደግሞ ሼህ አላሙዲ በዉጭ ሀገር እንደተመለከቱት ሁሉ በገለልተኝነት በኢንቨስትመንት ስራቸዉ ላይ ብቻ አተኩረዉ እጃቸዉን ሰብስበዉ ከመቀመጥ ይልቅ ከዚህ አፋኝ ስርአት ጋር እጅና ጓንት ሁነዉ ከሰሩም ኢትዮጵያዉያን የወያኔ መሪዎችን ባየንበት አይን የምንመለከታቸዉ መሆኑን በግልጽ ማስገንዘብም ያስፈልጋል።
ለማንኛዉም ይህንን ነገር ለማጥራት ሼክ አላሙዲ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ/ዶ/ር ጌታቸዉ በጋሻዉ ጋር በመሆን ፓናል ዉይይት ቢያደርጉልን ይህንን የጥርጣሬ ደመና ያጠራዋል የሚል እምነት አለኝ። እዚህ ላይ የወያኔ መሪዎች ሰዉን ለማሳሳት እንደ ሀዉዜዉ ድራማ ሁኔታ ጠብቀዉ በተቀረጸ ምስል ሰዉን ማሳሳት ልማዳቸዉ ስለሆነ አንባቢ የነዚህን ሰዎች ተንኮል ከነሱ ቀድሞ ሊገነዘብ ግድ ይላል ባለፈዉ ንብ ይሁን ዝንብ ያለበት ሸሚዝ እኝህን ሼህ አልበሰዋቸዉ በማየቴ ነዉ። ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ክርስቶስን በአካል አግኝቸዋለሁ ማለት የሚዳዳቸዉ፤ መጠጥ ወደዚህ አለም ከመጡ ጀምሮ ሸቷቸዉ የማያዉቅ  አፍሪካ መሪዎች ስብሰባ አቶ በረከት በጆሯቸዉ ምን እንዳላቸዉ አይታወቅም በእለቱ በሳቸዉ ሻምፓኝ ፍጆታ ምክንያት መሪዎቹ ሳይቃመሱ እንዳለቀ በትዝብት ተስተዉሏል። እንግዲህ እንዲህ ለነብሳቸዉ ያደሩትን መጠጥ የጋቱ ሼክ አላሙዲን ተናዳፊ ንብ ቢያለብሱም ብዙም ሊገርም አይገባም።
በእርግጥ ካፒታል ኢንቨስትመንት ከምእራብ አገሮች በላይ ወደ ታዳጊ አገሮች ቢፈስ በብዙ እጥፍ ትርፍ ሊያመጣ ቢችልም እኚህ ሼህ ግን ወደ ትዉልድ ሀገራቸዉ መዋእለ ንዋያቸዉን መሳባቸዉ ሊያስመሰግናቸዉ ሊያስከብራቸዉም ይገባል ለማንኛዉም ከሊቃዉንቱ ጋር የሚያድርጉት ዉይይት ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎችን ስለሚመለስልን በዚህ ነገር ትርፍ ለማምጣት የሚክለፈለፉ ወገኖች በጋዜጠኝነት ስም ወደዚህ አካባቢ ዝር ሳይሉ ጉዳዩ ክብርና እዉቅና ባላቸዉ ወገኖች እና ምሁራን ዉይይት ቢደረግበት ዜጋ ብዙ ጥቅም ሊያገኝበት ይችላል የሚል ጽኑ እምነት ሲኖረኝ ሼህ አላሙዲም በሄዱበት ሁሉ አጃቢያቸዉ ኢትዮጵያዉ ሁኖ ያለሃሳብ የኢትዮጵያዊነት ነጻነት የሚያስገኘዉን ጥቅም ተቋዳሺ ይሆናሉ የሚል ሙሉ እምነት አለኝ።እንግዲህ እንደተለመደዉ ለእርምትና፤ለትንኮሳ በዚህ ድርሱኝ gebeyhubalcha@yahoo.com
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ገበየሁ ባልቻ
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/7950#sthash.Xx56su9G.dpuf

ራሱ እግር እግሩ ራስ የሆነበት፣ በአፍጢሙ የተደፋ የሕግ ስርዓት (በወይንሸት ሞላ ዙሪያ)

ላይ ላዩን ስናየው የጨለመ ቢመስለንም በርግጥ የኢትዮጵያ ትንሳኤ መድረሱን የሚያመላክቱ ብዙ ምልክቶች እያታዩ ነው። ከነዚህ ምልክቶች መካከል በዋናነት ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ፣ የሚገርሙ፣ የሚያስደንቁና ወኔ የሞላባቸው ጀግና ልጆች እየተፈጠሩ መሆናቸው ነው።
ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ስለ አሁኑ የለዉጥ ፈላጊ ትዉልድ ሳስብ፣ በፊቴ የሚደቀኑ እጅግ ወገኖች በጣም ብዙ ናቸው። ከነዚህ ወገኖች መካከል ዛሬ ስለ አንዲት እህት እጽፋለሁ። ከፍተኛ የሆነ የዘረኛው ህወሃት አገዛዝ ዱላ ያረፍባት። ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ፣ ከአንድ አመት በፊት “የማታውቋት ካላችሁ፣ በሰውነት ‹‹ቀጫጫ ነች›› ብዬ ብነግራችሁ አልተሳሳትኩም፡፡ ግን ጥንካሬዋ ይገርመኝ ነበር” ሲል የጻፈላት።
ወይንሸት ሞላ
ወይንሸት ሞላ
ቀኑ የካቲት 30 2006 ዓ.ም ነው። እሑድ ቀን ። የሴቶች የ5000 ሩጫ ተዘጋጅቷል። በርካቶች ይሮጣሉ። ቢጫ ኬኔቴራ ለብሰዋል። ሩጫዉ እንደተጀመረ ድምጾች መሰማት ጀመሩ። የስድብ፣ የክፉ አይደለም። «የጣይቱ ልጆችን ነን፤ የሚኒሊክ ልጆች ነን፣ ለነጻነት ነው የምንሮጠዉ፣ እርቦናል፣ መብታችን ይከበር፣ የታስሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ …» የሚሉ ድምጾች። በሌሎች ሯጮች ላይ ጠጠር አልተወረወረም። የወደመ ንብረት የለም። መንገዶች አልተዘጉም። ሩጫዉ አልተስተጓጎለም። በሰላም ተጀመሮ በሰላም ነው ያለቀው። ሆኖም ሕወሃቶች ተቆጡ። ሕግ አክብረው፣ ሕግ ምንግስቱ የሚፈቅድላቸውን መብት ተጠቅመው ሰላማዊ የነጻነት ድምጾችን ያሰሙት ወጣት ሴቶችን ያዟቸው። ለሶስት ሳምንታት አስረው ከፍተኛ ግፍ ፈጸሙባቸው። እነዚህ ልጆች የጣይቱ ልጆች ተብለው ይታወቃሉ። ከነዚህ መካከል አንዷ የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችው፣ ወይንሸት ሞላ ናት።
ብዙም አልቆየም፣ በአኑዋር መስኪድ አካባቢ በዚያ ሙስሊሞች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመታዘብ ወይንሸት በሄደችበት ጊዜ፣ እንደገና ፖሊሶች ይይዟታል። ከፍተኛ ድብደባ ይፈጽሙባታል። ጭንቅላቷ በደብደባ ተጎድቶ የተሰፋ ሲሆን፣ የቀኝ እጇን ቀጥቅጥው ሰብረዉታል። አዚዛ መሃመድ ከምትባል የአዲስ ጉዳይ ጋዜጣ ፎቶ ግራፍ አንሺ ጋር, ፍርድ ቤት ትቀርባለች። ብዙ ሰቃይ ለሳምንታት ከተቀበለች በኋላ እንደገና ትፈታለች።
በአዲስ አበባ ከፍተኛ ተቃዉሞ በቀረበት በሚያዚያ 14 ቀን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ( 8 AM ) ፣ ኢያስፔድ ተስፋዬ ከሚባል የሰማያዊ ከፍተኛ አመራር ጋር በስልክ ታወራለች። ያኔ ፖሊሶች አሁን ይይዟታል። ኢያስፔድ ለአንድ ለአመራር አባላቱ ወይንሸት መታሰሯን ያሳውቃል። በሶሻል ሜዲያም ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ( 9 AM) ይለጥፋል። ሌላ የሰማያዊ አመራር አቶ ወሮታው ዋሴ ወዲያው በሶስት ሰዓት ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሯን ያረጋግጣል።
የሕወሃት ፖሊሶች ወይንሽትን ጨምሮ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ጸጋዬ፣ ማስተዋል ፍቃዱ እና ቤተልሄም አካለወርቅ የተባሉ የሰማያዊ አባላትን ብዙ ካንገላቱ በኋላ ፍርድ ቤት ያቀርቧቸዋል። “አራት ሰዓት ተኩል ላይ መስቀል አደባባይ ሲበጥብጡ ያዝናቸው” የሚል ክስ ይመሰርታሉ። ወይንሸት የተያዘችው ከጠዋቱ በሁለት ሰዓት በሌላ ቦታ፤ ፖሊስ ግን በሌሎች እስረኞች ማድረግ እንደለመደው የዉሽትና የፈጠራ ክሱን አዥጎደጎደው። እንደው ተሳስትው እዉነት መናገር የማይችሉ ፍጥረቶች !!!

እነ ወይንሸት ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት፣ ተያዙ በተባሉበት ወቅት መስቀል አደባባይ ላይ እንዳልነበሩ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ያሰማሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወረታው ዋሴን እና የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ወጣት እያስፔድ ተስፋዬን በመከላከያ ምስክርነት ወይንሸት አቀረበች፡፡ ሌሎችም እስረኞች እንደዚሁ በቦታው በተባለው ወቅት እንዳልነበሩ ምስክር አቀርቡ። ፍርድ ቤቱ ለዉሳኔ ሰኔ 15 ቀን ቀጠሮ ይሰጣል። ሰኔ 15 ቀን፣ “የወንይሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ የመከላከያ ምስክሮች ተከሳሾቹ በቦታው እንዳልነበሩና ወንጀሉን እንዳልፈፀሙ አላስረዱም በሚል” ፍርድ ቤቱ ጥፋተኞች ይላቸዋል። የተከሰሱበት ወንጀል እስከ 6 ወር እንደሚያስቀጣ የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ እነ ወይንሸት ሞላ የሁለት ወር እስር ፈርዶባቸው፣ የታሰሩት ከሚያዝያ 14/ 2007 ጀምሮ ሁለት ወር ከአንድ ቀን ስለሆነ ከ እስር እንዲፈቱ ይወስናል።
አቅቢ ህግ ዜጎችን ሲከስ፣ ወንጀል ስለመስራቱ መረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ሆኖም በአገራችን ያለው የፍርድ ሂደት ዜጎች ሲታሰሩ ጥፋተኛ የሚባሉት፣ አቃቤ ሕግ ጥፋት ስለመፈጸማቸው በቂ ማስረጃ ሲያቀርብ ሳይሆን፣ ተከሳሾች ጥፋተኛ አለመሆናቸውን መረጃ ሲያቀርቡ ነው። ራሱ እግር ፣ እግሩ ራስ የሆነበት ፣ በአፍጢሙ የተደፋ የሕግ ስርዓት !!!!!
የአገራችችን አሰቂኝና አሳፋሪ የሕግ ስርዓት ድራማ እዚህ ላይ አላበቃም። ሰኔ 15 ቀን ቄራ የሚገኘው ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ትእዛዝ ቢሰጥም የሕወሃት ፖሊሶች እንደገና የፍርድ ቤትን ትእዛዝ ጨፈለቁ። በነጋታው፣ ስኔ 16 ቀን፣ እነ ወይንሸት ሞላን እንደ ወንበዴ፣ የፍርድ ቤት መዛዣ ሳይዙ አፍነው ወሰዱ።
እንግዲህ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ይችን ትመስላለች። ኢትዮጵያዉያንን ልብን በሚያደማ ሁኔታ ፣ ስልጣኔ ባልገባቸው፣ በቂምና በጥላቻ በተሞሉ ፣ ከጫካ አስተሳሰብ ባልተላቀቁ፣ ፍጹም ኋላ ቀርና ዓዉሬ በሆኑ ዘረኞች፣ አንገታችቸው ደፍተው፣ ፈርተዉ፣ ተሽማቀውና ተዋርደው፣ ጥቅሮች በአፓርታይድ ዘመን ይኖሩ እንደነበረው በባርነት የሚኖሩባት አገር !!!
ደግነቱ ግን ባርነት፣ ጭቆና በቃን ብለልው የተነሱ በብዛት ያሉበት፣ ትዉልድ ነው የአሁኑ ትዉልድ። “በሀገራችን፣ ብዙ እንስቶቻችን በፍርሃት ወጥመድ ሥር ወድቀው፣ በጣም ልስልስ የሆነ የህይወትን መስመርን ምርጫቸው አድርገውና ‹‹ፖለቲካን በሩቁ!›› በሚል መሪ ቃል የዘወትር ድግግሞሻዊ ሕይወት ውስጥ በምርጫ እየተጓዙ ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ፣ እንደወይንሸት አይነት ጥቂቶችን በፖለቲካ ዓለም ውስጥ ስመለከት እንደኢትዮጵዊ ዜጋ ደስታን ይፈጥርብኝ ነበር” ሲል እንደጻፈው ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ፣ እኔም እንደ ወይንሸት ያሉ ፣ ብረትና ታንክ የማይፈሩ፣ “ነጻነቴን ከምትወስዱብኝ ሞቴን ስጡኝ” የሚሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየበዙ መምጣታቸው በርግጥ ኢትዮያጵያችን የምትታሰብበት ጊዜ መድረሱን፣ የጨቃኝ፣ ቂመኛ፣ ከፋፋይና ዘረኛ አገዛዝም ፍጻሜ መድረሱን የሚያሳይ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት የብር ኖቶች እንደሚንቀሳቀሱ ታወቀ

unnamed (3)

ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት የብር ኖቶች እንደሚንቀሳቀሱ ታወቀ፡፡ አትዮጵያ ውስጥ ባሉሁሉም ባንኮች ሳይቀር እየተዘዋወረ የሚገኘው ገንዘብ 2 አይነት መሆኑን ከብሄራዊ ባንክ አፈትልኮ የወጣው መረጃ ያሳያል ፡፡ #1ኛው አይነት የብር ኖት ብሄራዊ ባንክ በህጋዊ መንገድ በጨረታ የሚያሳትመው ሲሆን #2ተኛው አይነት የብር ኖት ደግሞ በ1997 ዓም ከቻይና ሃገር በሚስጥር በገባ 1 Sinocolor Solvent money printer በተባለ የብር ማተሚያ ማሽን በእነ #አዜብመስፍን እና አብሮአበሮቾ የሚታተም የባለ 50 እና ባለ 100 የብር ኖት ነው ፡፡ ይኽም የእነ አዜብ መስፍን የብር ኖት ከብሄራዊ ባንኩ የብር ኞት የጎላ ልዩነት የሌለው ቢሆንም በጣም ስስ በመሆኑ በገጠሩ ክፍል ተቀባይነት እንዳጣ ለማወቅ ተችሎል ፡፡

አበበ በለውና አብዩቱ በዳላስ (ቲክሳስ) – ከዘላለም ሽፈራው

በዳላስ ፎርትወርዝ የኢትዩጵያውያን የዉውይይት ፎረም በ6/07/15 በጠራው ስብሰባ ተገይቼ ነበር ። የሁለት ተጋባዥ እንግዶች ማለትም የታሪክ ሙሁርና ተማራማሪ ዶክተር ፍቅሪ ቶሎሳና ታዋቂው ጋዜጠኛ አበበ በለው  ያደረጉት ንግግር ሰሞኑን አነጋጋሪና አከራካሪ ሁኖአል ። ዶ/ር ፍቅሪ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሑፍ አገራችን የረጅም አመታት ታሪክ እንዳላት ታሪካዊ ማስረጃውችን በማቅረብ የዚችን ጥንታዊ ሀገር ታሪክ በመበረዝ የለለ ታሪክ በመፍጠር በዘረኝነትናበጎጠኝነት ሰም የሚደረገው ሀገርን ለመበተን የሚደረገው ንቅናቄ የታሪክ መሰረት የለላቸው በጭፍንና ታሪክን በመበረዝ ላይ የተመሰረተ መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል። ታሪካችን የብዙ ሺህ ዓመታት መሆኑን ህዝቡ ተፋቅሮና ተቻችሎ የኖረናለአንድነቱ፤ለነጻነቱናለሀገሩ ሉዐላዊነቱን  ደሙን አፍሶና አጥንቱን ከስክሶ ያቆማትና ያቆያት ሀገር መሆኖን ዶክተር ፍቅሪ አስተምረዋል ትምህርቱ ቀርቶ ለብሔርተኛው ና ለፅንፈኛው.  የአንድነት ኃይሉ ይበልጥ የረጅም ዘመን ታሪኩን በመማር ኢትጵያዊነቱን ይበልጥ በማረጋገጥ በታሪኩና በማንነቱ የኮራንበት ትምህርት ነው። ሌላው ተጋባዥ እንግዳና ተናጋሪ ተዋቂው ጋዜጠኛ የወያኔን ስርአት በማጋለጥና በመተቸት የሚታወቀው በዚህ ተግባሩ ስርአቱ አስራ ሰባት አመት የፈረደበት በፅናቱ፤ በበሳልናበሰላ ሒሱ አመለካከቱ  የሚወደደው አበበ በለው ነበር። እንደሰማሁት የአበበ በለው በተናጋሪ እንግድነት ወደዳላስ ቲክሳስመምጣት  ያልወደዱትና ስብሰባው እንዳይሳካ እንቅስቃሴ ያደረጉ ስብስቦች ነበሩ እነሱም በግንቦት ሰባት የሰረገ የወያኔ ደህንነቶች፣አፍቃሪ ሻቢያዎችና አበበ የበለጠ ጠላት ነው ብለው የፈረጅ የወያኔ ደጋፊወች ናቸው። ምክንያታቸው የእሳት ራዲዪናቴሌብጅን ጋዜጠኞች ኤርትራ ምድር በመጎዝ ግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር መፍጠራቸውን ሲዘግቡ ስለ ኤርትራው ፕሪዘርዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ እንደ ብዙ ህዝብ አዲስ ድምፅ ራዲዮ ብዥታ ስለነበረው ያ የምናውቃቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ሀገራችን አሁን ላለችበትና ለደረሰችበት የቁልቁለት ጉዞና ቀውስ ዋነኛ መሀንዱስና መሪ ተዋናይ የነበሩ ሀገራችን እንደ ሀገር እንዳትቀጥል ከሀገራችን መሰረታዊናታሪካዊ ጠላታቶች ጋር አብረው የሰሩ  ከህዝባዊ ወያኔ ትግራይ ነጻአውጭ ድርጅት ጀምሮ ሊሎችም ከዘጠኝ የበለጡ በነፃ አውጭ ድርጅት ስም ድርጅቶችን ጠፍጥፎ በመፍጠር ኢትዮጵያን ለመበተን የሰሩት ኢስያስ አፍወርቂን የእሳት ራዲዪ ዘጋቤዎች የእኒህን ሰው ተክለ ሰውነት ከፍ ከፍ በማድረግ ፕረዘርዳንት ኢሳያስ የኢትዪጵያ አንድነት ፣ሰላምና አለመረጋጋት እንደሚሳስባቸው በዚች ሀገር በጉልበትናበጠበንጃ ኅይል በሥልጣን ተቀምጦ ያለውን የህዋት ነፃ አውጭ ድርጅትን በማስወገድ ሰላም የተረጋገጠ አንድ ዲሞክራሲን ኢትዮጵያ  ለመመስረት ከአንድ ብሔራዊ ግንባርና ከዘጠኝ የነፃ አውጭ  ድርጅቶች ጋር አብረን እየሰራን ነው ያለትን በመቀጠል ቀድሞም ቢሆን ህዋቶች አልሰማም አሉን እንጅ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፣ሰላምና መረጋጋት ብዙ መክረናቸው ባለመስማታቸው ይህች ታርካዊና ጥንታዊ ሀገር በሚሳዝን ሆላቀርነትና አደጋ ወድቃለች ይህን ለመለወጥ አብረን እንሰራለን የሚል የፕሪዘርዳንት ኢሳያስ ቃለመጠይቅ በታወቁት የእሳትና የራዲዮ ጋዜጠኞች ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በተዋበ ድምፁ ባማረ ቅንብረ ጠፍቶ እንደተገኘ ልጅ በአድናቆትና በስሜት የቀረበ ቃለ~መጠይቅና ዜና መሰረትያደረገ ቃለ መጠየቅ መሰረት ያደረገ ነበር። ይህን ታሪክዊ የተባለናየሀገራችን እጣ ፈንታ ይውስናል የተባለ ቃለ መጠይቅ አንደ አስርቱ ትእዛዛት ማመንና መቀበል ብቻ ሳይሃን ህዝብ ሊወያይበትና ሊመክርበት ይገባል። በተለይ የቃለ መጠይቁ ባለቤት ሻቢያ፤ ኤርትራናኢሳያስ አፈወርቂ በመሆናቸው  ይህን የአዱስ ድምፅ  ራዱዪ አዘጋጅ አበበ በለው እንደ ብዙሀን ኢትዪጵያዊ ብሽታ ስለ ነበረው ለውይይት አቀረበው ። ለውይይት መደርደሪያ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራ በርሀ ድረስ በመሄድከኢትዩጵያ አርበኞች ግንባር መሪወች፣ከኤርትራ ባለ ሥልጣናትና ከፕሪዘርዳንት ኤሳያስ አፈወርቂ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ወንድሞችን በማቅረብ ጋዜጠኛ አበበ በለው አነጋገረ እንግዶችም አንደኛ ግንባር ላይ ያ እነርሱ የሚውቂት ሠራዊት ካለ በማመስገን፣ ለሀገራችን ነፃነት ብለው ብረት ያነሱ ወንድምችን በማድነቅ የእሳት ጋዝልጠኞችም ስለእደረጉት የኤርትራ ጉዞና ዘገባ አመስግነው በጥቅሉ ወዲ አፈወርቂ ወያኔን ለማስወገድ  መነሻው ኤርትራ ያደረገው የአርበኞች ግንባር ለአሰራ ስድስት አመት ምንም እንቅስቃሴ እንዲደረግ በኤርትራ መንግስት ስላልተፈቀደለት በግዞትና በጉልበት ሥራ ብቻ እንዳለ ይህን ያልፈቀድና የታገሉ የአርበኞች ግንባር መሪዎችና አባላት በኤርትራ ባለስልጣናትናደህንነቶች እየተያዙ የተገደሉትንና መዳረሻቸው ያልታወቀ አርበኞች በማስረጃ አቅርበዋል ። ይህንን ውይይት ያልፈቀድና ያልወደድና በእሳት ጋዜጠኞች የቀረበ ድብቅና አስመሳይ የኢትዪጵያን ህዝብ የእውቀት ግንዛቤ የናቀ ዘገባ በጭፍንና በመጫን ያለ ምንም ውይይት ህዝቡ እንዱቀበለውና እንዲምንበት የፈለጉ የግንቦት ሰባት ሰወች፣ የፕረዘርዳንት ኢሳያስና የሻቢያ አፍቃሪዎች በአዲስ ድምዕ አዘጋጅ በአበበው በለው ላይ የማጥላላት ዘመቻ ላይ ማድረግ ጀመሩ በሆላም ግንቦት ሰባት በላይ ጠንቀኛ ጠላታችን አበበው በለው ስለሆነ በዚህ ዘመቻ እንድንሳተፍ በማለት የወያኔ ካድሬዎችከግንቦት ሰባት ደጋፊወች  ጋር ተቀላቀሉ ሰለዚህ በአዲስ ድምፅ አዘጋጅ በአበበ በለው ሦስት ለአመታት የማይነጋጋሩ ፣ በደምና በጦርነትየሚፈላለጉ ኃይሎች ግንባር ፈጥረው በታዋቂው ኢትዪጵያዊ ጋዜጠኛና አክትቢስት አበበ በለው ላይ ጦርነት ከፈቱ። እንደሰማሁት የዳላስ ግንቦት ሰባት ቻፕተር በአበበ በለው በእንግድነት ና በተጋብዥነት በተገኘበት ሰብሰባ ከአጋር ኃይሎች ጋር ያለመሳተፍና ስብሰባው እንዳይሳካ ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል እነ እሰየ አብረሀ ለነ ዳዊት ከበደ መድረክ ያዘጋጀ እነ ተስፋገ/አብን በተጋባዥ እንግድነት ጠርቶ የነበር የግንቦት ሰባት ፎረም የራሳቸውን ወዳጅ እሳትን ካቆቆሙትና ከመሰረቱት አንድ የሆነ ለእሳት መጠናከር በየአገሩ በመዛወር በሰው ፊት እየተገረፈ ፈንድረይዚግ ያስደረገ ፤ እነ ብርሀኑን ነጋ ከቅንጅት መፍረስና ከእስር በሆላ ፕረሞት በማድረግ በየስቲቱ ይዞ በመዛወር አሁን ላሉበት ቀጣይ ትግል ያበቃ አበበ በለው ስለ ኤሳያስ አፈወርቅ ቃለ መጠይቅ አደረክህ ተብሎ ማእቀብ ተደረገበት የመጀረያው ተፈጠረ የተባለው ግንባር ሌሎች አጋር ኃይሎችን በመጨመር በአበበ በለው ላይ ጦርነት ከፈቱ። የሀሳብ ልዩነቴን ተቀብለው የትግል ጎደኝነታችን ይቀጥላል ብሎ የሚምናቸው ወዳጆቹ በተፋየ ገ/አብ ከሚመራው የሻቢያ ዲስፓራና በዳዊት ከበደ ማኔጅመንት የህዋት የዳይስፓራ ካድሪዎች ጋር በማወቅ ሆነ ባለማወቅ ተጣመሩ።ይህ ሁሉ ሁኖ ቀላል የማይባል ህዝብመጣ ስብሰባው በቀጥታ በአዲስ ድምፅና በፕልቶክ ሩሞች በተለይ በታወቀው፣ በድፍረቱና በሀርድ ቶክ ትንታኔው ተሰሚነት ያለው የአባ መላ ክፍል ኢትዮ ስብሊቲ መተላለፍ የስብሰባው መልእክት በሁሉም አለም ተሰማ። ከታሪኩ ምሁር ከዶ/ር ፍቅሪ ቶሎሳ በኃላ የመድረኩ አስተዋዋቁ ባልሳሳት ዶ/ ስሜነህ ሲናገሩ ጋዜጠኛ አበበ በለው እንዲቀርብ የተሰጠው ርእስ ባለፍት ሀያ አራት አመት የተቃዋሚ ድርጅቶች ትግሉን ምን ደረጃ አደረሱት? ምን ተግባር ሰርተው ምን ተሳካላቸው? ገዥው ሥርአት ወያኔ ኢህአደግ አገዛዙ በተራዘመ ቁጥር በኢትዮጵያ ህዝብ እያደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የመብት ገፈፋ፣የዘረኝነት አድለዎ በአጠቃላይ አገዛዙ ግፈኝነቱ በደሉ አየጨመረና እየጠጠረ ህዝቡ ሊሽከመውና ሊስተናግደው በማይችልበት  የመከራውና የዘረኝነት ጽዋው በዝቶበታል።ከግፈኞችና ከአድርባይ ሆዳሞች ንሮ በታች ከሞቱት በላይ ሁኖ በተፋጠጠበት ሰአት ተቃሚ ድርጅቶች ይህን የተገፋ ህዝብ አደራጅቶ ና አቀናጅቶ ሥርዐቱን ለመለወጥ የሚደረገው ትግል ዳር ያለመድረስ ችግሩ ምንድን ነው?የሚልና እኛ ኢትዮጵውያን (ዲያስፖራ) ለሥርዐት ለውጥ የምናደርገው ትግል ምን ደረጃ ደርሶል የሚል ነው። ጋዜጠኛ አበበ ንግግሩን እንደሰማሁት የፖለቲካ እውቀቱን ናግንዛቤውን ብቻ ሳይሆን ይህን የግፈኝነት አስተዳደር ለመለወጥ ያለውን ቁርጠኝነትና ብርታት እጅግ የሚደነቅ ነው።አበበ ንግግሩን ሲጀምር ያለው ህዋትን በማውገዝና በማልቀስ ብቻ የትም አይደረስም የሰው ልጅ ይፈጽመዋል ተብሎ የማይታሰብ ወንጀል በወገኖቻችን ላይ ተፈጽሞብናል በዘርናበኃይማኖት ከፋፍለው አፋጅተውናል የሞትና የውርደት ሽማ አልብስርውናል።በአለም ፊት የተዋረድና የረክስን ዜጎች አድርገውልናል። ይህን ብሶት ሀያ አራት አመት ደግመን ደጋግመን አወራን አለቀስን ከዚህ በኃላ መጠየቅ፣መተቸትና መታገልም ያለብን የተቃዋሜ ድርጅቶችን ነው። ለምንድን ትግሉን ወደተሻለ ደረጃ ያላሻገሩት? ለምንድን ነው የህዝብን ተደጋጋሚ ጥሪ ተቀብለው አንድነት የማይፈጥሩት? ከኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣትና የራሴን አገር እመሰርታለሁ ከሚል ብሄርተኛ ድርጅት ጋር ግንባር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅት ለምንድን ነው ከኢትዮያውያንህብረ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ችግሩ ምንድነው? በቅንጅት ጊዜ የነበረው የዲስፓራው ህብረትና የተቀናጀ ትግል መሪት አንቀጥቅጥ የሆነ ሰላማዊ ስልፍ በማድረግ መሪዎቻችን ከእስር እስከ ማስፈታት ያደረሰው ህብረታችን ና ጥንካሬችን የት ደረሰ? ምእራባዊያንና አሜሪካውያን ትኩረት ና ክትትል ማድረግ የቻሉት እኛ ኢትዪጵውያን በውጭ ሀገር ከልጅ እስከደቂቅ ወጣት ሽማግሌ ፣ሴት ወንድ እስላም ክርስትያን ሁላችን በአንድነት ባደረግነው ትግል ውጤት አግኝተንብታል ታዲያ ዛሪ ያ ትግላችን የት ገባ በየስቲቱ ህዝቡን በፀረ ወያኔ አላማ ያስተባብሩ፣ያታግሉና ለተቃውሞ እንስቃሴ ሰልፍ ከፊት ሁነው ያታግሉ  የነበሩ መሪዎች ለምን ከትግሉ ሜዳ ወጡ ? ፓለቲካችን በመርህ ላይ ተመስርቶየሀሳብ ልዩነትን በማስተናገድ አቅጣጫ ያለው ትግል ከማድረግ ይልቅ ልዩነታችን በማግዘፍ በሀሳብ የበላይነት ከማመን የግለሰቦችን ሰብእና የሚዋርድ ሀገራዊ ራእይ የለለቸው ለራሳቸው ክብር የማይሰጡ የተቃውሞውን ኃይል ስለወረሩት ብዙ አንቱ የምንላቸው ሰዎች አጠናል። በዚህም የተነሣ ህዋት ኢህአደግ ሀገር ቤት ያለውን ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ህዝቡን በኃይልና በጠበንጃ ረግጠው ሲገዙ በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን ከእኛ በላይ ሥርዐቱን እያወገዙ በኮሚኒቴወችና በፓለቲካ ድርጅቶች ሰርገው በመግባት በኢትዮጵያውያን ድርጅቶችና ኢትዮጵያውነትን በሚቀነቅኑ ግለሰቦች ላይ የማጥላላትና ሰብእናን የሚነካ ጋጠ ወጥ ስድብ አየሩን በመሙላታቸው ይህንን እሳፋሪ እካሄድ አንዳንድ የፓለቲካ ድርጅቶች ለጊዜዊ የፓለቲካ ፍጆታ ስለ ፈለጉት ብዙ ኢትዩጵያውያን ሙህራንን አጠናል ፍሪ ያለው ትግል እንድናደርግ የኢትዮጵያውያን ሙሀራን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ከቆሻሻ ስሜትና አካሄድ ወጠን የፓለቲካ ባህላችንን ከፍ አድርገን አገርና ህዝብን የሚመጥን ሥራ እንዲሰራ አደራ ብሎል። ጋዜጠኛ አበበ በለው ከህዝብ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ በእኔ አመለካከት። በሚል ሰጥቶል ከቀረበው ጥያቄ አንድ የኤርትራ መንግስት ሻቢያ የኢትዮጵውያን የፓለቲካ ድርጅቶችን እያስታጠኩና እያሰለጠንኩ ነው ይላል ነገር ግን አርበኞች ግንባር ጨምሮ አስራ ስድስት አመት ሲቀመጥ አንድም ጊዜ ወታደሬዊ ኦፕሬሽን አድርጎ አያውቅም ይልቁንም ደርሰው የሚመለሱ ሰዎች እንደሚስረድት አርበኛው ለሻቢያ በጉልበት ስራ ተጠምዶ እንዳለ እዲሁም ብዙ የአርበኞች ግንባር መሪዎች ወታደራዊ እንቅስቃሴ እናድርግ ስለ አሉ እንደተገደሉና አድራሻቸው እንደጠፋ ይነገራል አንተ እንደ ጋዜጠያነትህ እንዴት ታየዋለህ? ሁለተኛው የቀረበ ጥያቄ በእሳት ጋዜጠኞች የቀረበው የፕሪዘርዳንት ኢሳያስ የቀረበው ቃለ መጠየቅ እንዲት አየኽው? በተለይ የእሳት ዘጋቤዎች ፕሪዘርዳንቱን የኢትዪጵያ ህዝብ ከሚውቃቸውና ከሚረዳቸው በላይ አሳምሮና ቀብቶ ያቀረባቸው ይመላል እውን ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ ኢትዮጵያ ሰላም፣ የግዛት ሉዑላዊነት ና የዲሞክራሲ እጦት ይጨነቃሉ? ሦስተኛው ጥያቄ ተስፋ የተጣለበት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ከህብረ ድርጅቶች ጋር ከመስራት ይልቅ በኢትዮጵያ  ቅኝ ተግዝተናል ከሚሉ ነፃ አውጭ ነን ብለው ከሚጠሩ ጋር እየሰሩ ነው እዲደውም ነፃ አውጭ ነን ከሚሉትና ከሚከሱት በላይ ግንቦት ሰባት ብሔራዊ ድርጅቶችን ሲጣጥልና ሲንቅ ይታያል ይህ አካሄድ ምን ይመስልሀል? የሚልና ሌሎች ጥያቄዎች ተጠይቆ መልስ ሰጠውባቸዋል። አበበ ስለ ኤርትራና ሻቢያ ማውራት ወያኔ እያሰኘ ነው ሲል ህዝቡ በጣም ይስቃል አዎ! አዎ አለ አበበ ማንም የፖለቲካል ድርጅት ለሚካሔደው የትጥቅ ትግል ከየት ነው መነሻህ ማን ነው የሚረድህ ምን አስቦና አልሞ የሚረዳህ ወዘተ ብየ ድርጅቱና የድርጅቱ ልሳና ራዲዮ ቢዘግብ አልጥይቅም ነገር ግን በሌላ ሚድያ እንደ እሳት ገለልተኛ የሆነ የህዝብ ዐይንና ጀሮ ተብሎ በተቅቐመ የሜዲያ ተቕም ሲነገር ግን ለህዝብ ውይይትና ክርክር እንዲቀርብ ታስቦል ማለት ነው ባለፈው ያቀረብኩት ቃለ መጠይቅ አሁንም ለወደፊትም የምናገረው የሁላችን  አይና ጀሮ በእሳት ራዲዮና ቴሌብጅን ለህዝብ ሲቀርብ ነው። እሳትእኔ የምላችሁን እመኑ፤ አትጠርይቁ አትመራመሩ አይልም ወይም አዳም ከዚች እጸ በለስ በቀር ሌላውን ብላ ተብሎ ትእዛዝ እንደተጠው እኛም ከኤርትራ፣ ከሻቤያና ከወዴ አፈወርቂ ሌላ አውሩ የሚል ትእዛዝ የሚሰጥ ከሆነ እንጠብቃለን ። እስከእዛ አወራለሁ በማለት አስቆናል። ኢሳያስ አፈወርቂ ና ሻብያ ወደድነም ጠላንም የሚታወቁበት የኤርትራን ጥቅም ለማስቀድም በሁለገብ ትግል ከእኛ ቀድመው እኛውን መሳሪያ አድርገው እኛ ኢትዮጵያውያን ታግለንላቸው ና ሙተንላቸዋል በብሄር ብሄረሰብ ነጻነት እሰከ መገንጠል በሚል እኛን ኢንተርናሽናል እያዘመሩ እነርሱ በመንደር ነጻነት እኛን አደንዝዘው ሀገር መስርተዋል ።በትግል ዘመን ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችን ከህውት ጋር በመሆን አጥፍተዋል ሻቢያ በራሱ ታጋዮች ኢትዪጵያን በመልካም ጎን ያነሳ አፍቃሪ አምሀሮይ አባይ እየተባለ ተረሽኖአል።የአንድ የሻቢያ ታጋይ መንፈሰ ጠንካራ ተብሎ የሚለካው በኢትዮጵያዊ በተለይ በአማራው ህዝብ ባለው ጭካኔና የጥላቻ ልክ ነው። የዚህ ሁሉ አመለካከት መሀንዲሲ ደግሞ ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው የኤርትራን በርሀ በደም ያጨቀዩ ሰው ናቸው ።ኢሳያስ አፈወርቂ  ለምን ብለው ነው እኛን የሚፈልጉ ለኤርትራ ነጻነት ደሙን ያፈሰሰው አጥንቱን የከሰከሰው ነገ ኤርትራ ላይ ጥቃት ቢሰነዘር ቀድመን ለኤርትራ ህልውና እንሞታለን የሚለው ህዋት ተቀምጦ የኤርትራን ነጻነት ያረጋገጠ ኢትዪጵያን ያለ ወደብ ያስቀረ ለኤርትራ ሙሉ ካሳ የከፈለ ይህን ድርጅት ትቶ በምን ሒሳብና ስሌት ነው ሊላ ቡድን ጋር የሚሻረክ ወይም ህዋት ያልፈቀደለት ተቃዋሚወች ለድል ከበቃን እናደርልሀለን ያሉት ውል ከለለ ይህ ውል ደግሞ ኢትዪጵያን ህልውናዋን አጥፍቶ ለወደፊት ኢትዪጵያ የምትባል ሀገር ኑራ ስጋት በማትሆን ድረጃ ካልተሰራ። ወዲ አፈዎርቂ ያለምንም ጥቅም የሚተባበሩት የለም ለበለጠ ጥቅም ይተባበራሉ ያ ይነገረን ህዋት ከሻቢያ ጋር ሲተባበር የኤርትራን ነጻነት አምኘተባብሬለሁ ለዚህም ዋጋ ሊከፍሉንና ልንከፍል በደም የተሳሰረ ቃል ተጋብተናል ብሎ በግልፅ እየነገረን ነው መንግስት የሆኑት ወዱ አፈወርቂ ከእናንተ ምን ለማግኘት እንደፈለገ በይፋ ይነገርን። ሁለተኛው ጥያቄ በእሳት ጋዜጠኞች ስለ ፕረዘርዳንት ኢሳያስ ተክለ ሰውነት፣ ለኢትዪጵያ ና ለአፍሪካ ሰላም መረጋጋት ሩቅ አሳቢነታቸው ተብሎ የቀረበውና ይህንም። በኢትዮጵያ ህዝብ ስነ ልቦና ተፅእኖ ለመፍጠር በእሳት ጋዜጠኞች። የተደረገው አካሄድ አሳዝኖኛል። ሙተን ሳናልቅ በአሁኑ ሰአት ለትግል ብለው ኤርትራ በርሃ ላይ በግፍ እየተገደሉ ያሉትን ሳስብ ፣ በባርነት ነፃ የጉልበት ሰራ የሚሰሩትን ና በበረሃ በእስርየሚሰቃዩ በደርግ የመጨረሻ ጊዜ እጃቸውን በሰላም ሰጠው በመትረየስና ላውንቸር የኢትዪጵያን የሠራዊት አባል ሳስብ ያ ቃለ መጠይቅ ያማል በሚል ዘሎታል ያማል። ሦስተኛው ጥያቄ ተስፋ የተጣለበት ግንቦት ሰባት ከህብረ ድርጅቶች ይልቅ ከኢትዪጵያ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ከሚሉ ጋር ይስርሉ ይህን አካሔድ እንዴት ታየዋለህ? ይህ ጥያቄ ለእኔ ሳይሆን ለግንቦት ሰባት መሪዎች የሚጠይቅ ነበር ሆኖም ድርጅቱ በሀሳብ ትችት ያምናል ብየ ስለማስብ የበኩሌን አስተያየት እሰጣለሁ። ጥያቄው የኔም ጥያቄ ነው ።  ግንቦት ሰባት የኢትዪጵያውን ህዝብ ከወያኔ አምባገነንነት ነፃ ለማውጣት የሚታገል ድርጅት ነው ብዪ አስባለሁ ነገር ግን ከኢትዪጵያነፃ እናወጣለን የሚሉ ድርጅቶች ዛሪ አብረው ታግለው ነገ ነጻ  ቢወጡን ከዚያ ምን እንደሚደርጉ ግልጽ አይደለም ነገ አንድ ኢትዮጵያን መስርተን በዲሞክራሲ ስርአት ለሁሉም ህዝብ እኩል የሆነች ሀገር መስርተን እኖራለን የሚሉ ከሆነ ዛሪ የነፃ አውጭ ድርጅቶች በኢትዮጵያዊነታቸው አምነውና ተቀብለው የሚደርጉት የፕሮግራም ለውጥ ይወስነዋል ያኔ በአንድ ልብ እንታገላለን። ይህን ሳይደረግ ከኤርትራ የሚነሳው የግንቦት ሰባትና የነፃ አውጭ ድርጅቶች ንቅናቄ ለድል ቢበቃ እኮ ሀገራችን  ከነ ሙሉ ሉአላዊነቶ መቀጦሎ አጠያያቂም አስፈሪ ነው። ግልጽና አስተማማኝ የሆነ በአገራችን ህልውናና ቀጣይነት ስምምነት ከለለ ከዚያ በኃላ የጠበንጃ ኃይልና ጥንካሬ ያለው ድርጅት ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ይመረዋል እነ ኦነግ፣ኦጋዴን ነፃ አውጭ ድርጅት ወዘተ ዘጠኝ የነፃነት ድርጅት በአንድ አገር አቀፍ ኢትዪጵያ በምትባል ሀገር በደምና በአጥንት በተመሰረተች ሀገር ማእቀፍ ስር ስለመኖራቸው ሳይሆን ያለው ምልክት ና ተጨባጬ ጉዳይ የሚሳየው ነፃነት ለማወጅ መዘጋጀታቸውን ነው ። ይህ ከሆነ ግንቦት ሰባት ፈቃደኛ ምርኮኛ በመሆን የ ኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ለመጣል ተባባሪ ሁኖአል ማለት ነው።ሻቢያ ደግሞ ነፃ አውጭ ድርጅቶችንየበለጠ የሚፈልግበት አንድ ምክንያት ዳግም ለኤርትራ ስጋት የማትፈጥር፤ አቅመ ደካማ አገር በመገንባት ኤርትራ ተፅእኖ ፈጣሪ ሀገር ለማድረግ የተከፋፈለች የተበታተነች ሀገር መፍጠር የሻቢያ ስትራቲጅክ አላማ መሆኑን የግንቦት ሰባት መሪዎች ይርዳሉ ያውቃሉ ነገር ግን አሁን ካሉበት ማጥ ለመውጣት በለለ ኃይልና አቅም በውሽት ፕሮፕጋንዳ ራሳችውን አሳብጠው ለዓመታት የተሰራ ድራማ በይፋ ሊጋለጥ ሲል ሻቢያ የፓለቲካ ህልውና እስትንፋስ በመስጠት አንዴ ከአርበኞች ግንባር ሌላ ጊዜ ከኦነግ ከዚያ ከትህዲን እያለ የጆከር ጨዋታ በማጫወት የፕሮፓጋንዳ ሥራ በማሰራት ሻቢያ ግንቦት ሰባትን መጠቀሚያ። እያደረገው ነው። የአበበው በለው  ንግግር ያስከተለው አብዩትና የኃይል አሠላለፍ ጋዜጠኛ አበበ በለው በአዲስ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በእሳት ራዲዮና ቴሌብጅን ስለ ፕሪዘርዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ሻቢያ የተደረገው ዘገባ መሰረት በማድረግ ኤርትራ በመመመላለስ ተመክሮ ያላቸው ወንድሞችን ባደረገው ቃለ መጠይቅ ሁለት ባላንጣዎችን ፈጠረ አንደኛው ስለ መሪችን፣ስለመሪ ድርጅታችን ሻቢያና ስለ ወደፊት የኤርትራ ጥቅም ላይ አደገኛ ቃለ መጠይቅ አድርጎል በሚል መሀል ሀገር ኢትዪጵያ የተወለድ ኤርትራውያን በማስተባበር  የተነሳው የሻቢያ ቡድን ነው። የዚህ ቡድን ካድሪዎች ባእድ መሆናቸው በእርግጥም ለሀገራቸው ጥቅም የቆሙና ማድረግ የሚገባቸው ስራ በመሆኑ አያስደንቅም። አደጋኛነቱ ግን እኛ ኢትዮጵያውያን መስለው የእኛን ቆንቆ እያወሩ የኢትዪጵያ በተለይ የግንቦት ሰባት ተቆርቆሪ መስለው ውይይቱን ለማስቆምና አበበ በለውን ለመዋጋት እያደረጉት ያለውን ዘመቻ በነ ተስፋየ ገ/አብ የሚመራው ግብረ ኃይል አንድ ክንፍ ነው። ሌላው በጋዜጠኛ አበበ በለው ነፃ ቃለ መጠይቅ ና ንግግር ከግንቦት ሰባት ሰዎች ጋር የተፈጠረውን የአካሄድና የአመለካከት ልዩነትና ክፍተት በምጠቀም በሁለቱ በኩል ያለውን የኃይል ሚዛን በመጠቀም ኃይላቸው ከተደራጀ ግንቦት ሰባትን ከማጥቃት ይልቅ ግለሰቡን አበበ በለውን በእርሱ ላይ ከተነሱት ጋር ማጥቃት ይቀላል በሚል በነ ዳዊት ከበደ የሚመራው የወያኔ ህዋት ግብረ ኃይል ነው። ይህም ኃይል የግንቦት ሰባት ተቆርቆሪ በኤርትራ ላለው ንቅንልቂ ደጋፊ በመምሰል ጋዜጠኛአበበ በለውን ለመዋጋት የተሰለፈው የወያኔ ኢህአደግ ኃይል ነው። ሌላውና ዋነኛው የጉዳዩ ባለቤት ራሱን እንደ ስደተ አምባገነን መንግሥት ቆጥሮ በሀገራችን የፓለቲካ ጉዳይ ፣ አሁን ባለው የፓለቲካ ድርጅቶች አካሄድ ላይ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ድርቶች በተለይ ኤርትራ አሉ በሚባሉ ጉዳዮች ና ፕረዘርዳንት ኢሳያስ በእሳት ራዲዮና ቴሌብጅን ስለ ሰጡት ቃለ መጠይቅ አትናገሩ ፣አትተቹና አትወያዩ የሚሉ እራሳችን የፈጠርናቸው ፀረ ዲሞክራሲ የሆነው የግንቦት ሰባት ኃይል ነው። ይህ ኃይል ሾላ በድፍን ኢሳያስ ለኢትዪጵያ አሳቤና ተጨናቄ ናቸው ስለ ሀገራችን ሰላም ፤ዲሞክራሲና አንድነት ያስባሉ በሚል ከነፃ ሜድያነት ወደ ድርጅት ልሣንነት እየተቀየረ በመጣው በእሳት ራዴዮና ቴሌብጅን የፕሮፓጋንዳ ሥራ ከአሰሩ በኃላ የህዝብን ትችት ካለመስማታቸው በላይ በዚህ ጉዳይ የሚወያዩ ጋዜጠኞችን ፀሐፊዎችን ይህን የሚስተነግዱ ወብ ሳይቶችን፤ራዲዮ ጣቢያዎችን ና የፓልቶክ ሩሞችን የሚሳደቡ፣የሚዋክቡ በጣም በወረደናሰብእናን በሚነካ ደረጃ የሚተናኮሉ የአጋዜና የፊደራል ተሳዴቢዋችን በመመደብ በአርበኞ ንአምን አመካኝነት በጋዜጠኛ አበበ በለው ላይ ዘመቻ ተከፈተበት ።ስለዚህ ጋዜጠኛ አቤ በሦስት ግንባር ማለትም ሻቢያ፣ ወያኔና የግንቦት ሰባት የጋጠወጥ ቡድን የከፈቱበት ጦርነት ሀሳቡን ባመኑ፣የመናገር የመተችት መብት በግንቦትሰባት ጋጠ ወጥ ቡድን፤በወያኔ ባንዳዎችና በሻቢያ አይቆምም በማለት ለአበበ ሺዎች እየደገፍት ሲሆን። የአበበ በለው ንግግርና እምነት ለተከታታይ ሦስት ሳምንት ርእስ ሁኖ በቀን ሀያ አራት ሰዐት እያነጋገረ ነው ከዚህ በኃላ ቀዳሚ ርእስ ሁኖ ለስንት ግዜ እንደሚቀጥል አይታወቅም። እውነተኛው ጉዳይ የሦስቱ ጥምረት መሪዎችን ሥራና መጨናነቅ አብዝቶባቸዋል። ከጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት በኃላ በቅድሚያ ርእስ ሆኖ ይህን ያህል ያወያየ ጉዳይ የለም።ብዙ ሙሀራን ፤ ለውጥ ፈላጊ የግንቦት ሰባት አባላት ና ኢትዪጵያውያን ወደዉታል፣ አወያይታልግንዛቤ ሰጥቶል ግንቦት ሰባት የማይሸሸው ህዝባዊ ጥያቄ ቀርቦለታል መሪዎች እጥቄ ተሳዳቤ ግብረ ኃይል ከሚልኩና የውይይትና የዲሞክራሲን ገፅታ ከሚጠፍ መልስ ይስጡ። 

- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/7956#sthash.yQR06ndd.dpuf

wanted officials