Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 27, 2015

የኢህአዴግ መንግስት በረመዳን ጾም ተቃውሞ ሊያይልብኛል ይችላል በሚል ፍርሃት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው

የኢህአዴግ መንግስት በረመዳን ጾም ተቃውሞ ሊያይልብኛል ይችላል በሚል ፍርሃት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው
ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት የሮመዳንን ጾም ተከትሎ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት፣ 53 ሚሊየን ብር በጀት በመመደብ የመስጊድ ኢማሞችን በአክራሪነት ዙሪያ የማሰልጠን እና የማግባባት ስራውን እያከናወነ ነው፡፡
አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ ሲል የሚታየው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሁንም መንግስትን እንቅልፍ እንደነሳው ነው፡፡
በሁሉም ክልልች ለሚገኙ የእስልምና የሃይማኖት አባቶች ህገመንግስቱ እና አክራሪነት በሚል ስልጠና ለመስጠት ሙሉ ለሙሉ የገንዘብ በጀቱን አፅድቆ ለክልል የአሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮዎች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡በቅርቡ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የደህንነት ሰራተኞች እና አንዳንድ የሙስሊም መሪዎች በዝግ ስብሰባ ያደረጉትን ውይይት ኢሳት በተከታታይ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በሌላ በኩል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ያላቸውን ድጋፍ ዛሬ ገልጸዋል።
በታላቁ አንዋር መስጊድ ሙስሊም በተካሄደው ተቃውሞ “የተከሰስነው እኛ ነን ፣ ኮሚቴው ነጻ ነው፣ ከማናምንበት ውጪ ፍርድ አንቀበልም” የሚሉ መፈክሮችን በማሳየት ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials