የኢሳት 5ኛ ዓመት ክብረ በዓል፥ ቅዳሜ ጁን 13 2015 ዓ ም፥ በቶሮንቶ ካናዳ በከፍተኛ ድምቀት ተከበረ፥
ተጋባዥ የክብር እንግዶች ተወዳጁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ፥ እና የመለስ ትሩፋት ጸሓፊ፣ የቀድሞው ሚኒስቴር ዲኤታ፣ ኤርምያስ ለገሰ በተገኙበት፥ ብዙ የቶሮንቶና የዓካባቢው ታዳሚዎች፥ ከኦታዋ፣ ከኪችነር እና ከሮቸስተርና ከባፋሎ ኒውዮርክ ድረስ ተጉዘው ከተሰባሰቡ ኢትዮጵያን ጋር የኢሳት 5ኛ ዓመት ክብረ በዓል በከፍትኛ ድምቀት ተከብሮ ውሏል::
በዕለቱም የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታና በዓገራችን የተከሰተውን ቅጥ ያጣ የወያኔ የጥፋት ዘመቻ፥ በተጨባጭ ማስረጃ ዓስደግፎ ጠለቅ ባለ መልኩ ለጉባኤው በመተንተን፥
ዓቶ ኤርምያስ ለገሰ ወያኔዎች የኢትዮጵያን የፖለቲካ ጉዳይና የዓገሪቱን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት ለመቆጣር ዓልመው እንደተነሱ በማስገንዘብ፥ የወያኔን መንግሥት ሕዝብ በታላቅ ቁጭት ሊታገለው የሚገባ ከፋፋይና መርዛማ የጎሰኛ ሥርዓት መሆኑን ዘርዘር ባለ ሁኔታ ለጉኤው ዓስረድቷል፥

ዓቶ ታማኝ በየነ ደግሞ ኢሳት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ የመረጃን ክፍተት በመሙላትና በኢትዮጵያ በሚደረገው የለውጥ ሂደት ላይ እያበረከተ ያለውን መልካም ስራ በሰፊው በማብራራት፥ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ከሰሩት ትልቅ ቁምነገር ዓንዱ የኢሳት መመስረት መሆኑን ጠቁሞ፥ በካናዳ የሚገኙ የኢሳት ደጋፊ ኢትዮጵያውያንም የዚህ ዓካል በመሆናቸው ላደረጉት ዓስተዋጽኦ ታላቅ ምስጋናውን በመግለጽ፥ በኢሳት የተጀመረው ስራ እንዳይቆም ድጋፋቸውን ዓጠናክረው እንዲቀጥሉ ዓበረታትቷል፥
በትግራይ ነጻ ዓውጭ ስም ታግሎ፥ የኢትዮጵያን በትረ መንግሥት ድንገት በተረከበው ወያኔ የተበላሸውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለማስተካከል እንዲቻል ወያኔን ዓስወግደን በእኩልነትና በመከባበር በነጻነት የምንኖርባት ኢትዮጵያን ለማስመለስ ወያኔን በጽኑ መታገል እንዳለብን በማሳሰብ፥ በዚህ እረገድ ኢሳት ለዓንድነት ትግሉ የሚያበረክተው ታላቅ በመሆኑ ኢሳትን ለመደገፍ ጉባኤው በቁጭት እንዲነሳሳ ከሚያዝናኑ ቁምነገሮች ጋር እያዋዛ ዓጥብቆ ተናግሮበታል፥
በመጨረሻም የዓንጋፋው ሰዓሊ የዓፈወርቅ ተክሌ የዓርበኛ ስዕል በከፍተኛ ውድድር ተጫርቶ በዓርበኞች ግንቦት 7 ስም የተወዳደረ ዓንድ ወንድም ጨረታውን በማሸነፍ የቀረበውን የዓርበኛ ምስል ዓሸንፎ ወስዶታል፥

ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይንና ጆሮ ነው፥
ኢሳት የእኔ ነው፥
ኢሳት የእኔ ነው፥
No comments:
Post a Comment