Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 25, 2015

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሊያ ህይወት አዳነ




(አድማስ ዜና) ባህሬን ፦ አሲያ አብዱ ትባላለች፣ ባህሬን ከመጣች ሁለት ሳምንት ቢሆናት ነው፣ እሷ እንደምትለው ፣ የመጣችው ለደላላ 8ሺ ብር ከፍላ ሲሆን፣ የልብ ህመም አለባት፣ እናም ከመጣች በኋላ መስራት አልቻለችም። ስለዚህ አስሪዎቿን መስራት እንዳቃታትና ወደ አገሯ መመለስ እንደምትፈልግ ትነግራቸዋለች።

እነሱ ግን ፣ ያወጣነውን ወጪ መልሰሽ፣ ከዚያም የራስሽን ትኬት ገዝተሽ ነው እንጂ፣ እንዲሁ አንለቅሽም ይሏታል። ከዚያም ለአራት ቀናት ያህል በአንድ ክፍል ውስጥ ዘግተውባት ስታለቅስ ትከርማለች፣ ታዲያ በመካከል ከነበረችበት አራተኛ ፎቅ መስኮት ከፍታ ለመወርወር ስትዘጋጅ፣ ድንገት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሊያ የለበሰ ወጣት ሲያልፍ በመመልከቷ በጩኸት ድረስልኝ ትላለች። ልጁም ያለችበት ተጠግቶ፣ …ክፎቅ ላይ እንዳትወድቅ በመለመን አሳምኖ፣ እዚያው እንደቆመ፣ ለባህሬን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እና ለፖሊስ ይደውላል።


የኮሚኒቲው ተወካይ ከቦታው ደርሶም ጉዳዩን ካየ በኋላ፣ ፖሊስ እስኪመጣ ድረስ ከውጭው ከባድ ሙቀት ለመራቅ ጥግ ይዞ ሳለ፣ ከልጅቷ ቤት ጩኸት ይሰማል፣ ሮጦ ፎቁ ላይ በመውጣት ሲገባም፣ አስሪዋ ልጅቷን ማሰቃየቱና ጨለማ ቤት ማስቀመጡ እንዳይታወቅበት፣ በጓሮ ይዟት ሊወጣ ሲጎትታት ይደርሳል፣ ያን ጊዜ እሷን አስጥሎ፣ ወዲያውም ርዳታው ደርሶ ልጅቷ በህይወት ተርፋ የባህሬ ኮሚኒቲ ጽህፈት ቤት በአሁኑ ሰአት እንደምትገኝ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials