በዳላስ ፎርትወርዝ የኢትዩጵያውያን የዉውይይት ፎረም በ6/07/15 በጠራው ስብሰባ ተገይቼ ነበር ። የሁለት ተጋባዥ እንግዶች ማለትም የታሪክ ሙሁርና ተማራማሪ ዶክተር ፍቅሪ ቶሎሳና ታዋቂው ጋዜጠኛ አበበ በለው ያደረጉት ንግግር ሰሞኑን አነጋጋሪና አከራካሪ ሁኖአል ። ዶ/ር ፍቅሪ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሑፍ አገራችን የረጅም አመታት ታሪክ እንዳላት ታሪካዊ ማስረጃውችን በማቅረብ የዚችን ጥንታዊ ሀገር ታሪክ በመበረዝ የለለ ታሪክ በመፍጠር በዘረኝነትናበጎጠኝነት ሰም የሚደረገው ሀገርን ለመበተን የሚደረገው ንቅናቄ የታሪክ መሰረት የለላቸው በጭፍንና ታሪክን በመበረዝ ላይ የተመሰረተ መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል። ታሪካችን የብዙ ሺህ ዓመታት መሆኑን ህዝቡ ተፋቅሮና ተቻችሎ የኖረናለአንድነቱ፤ለነጻነቱናለሀገሩ ሉዐላዊነቱን ደሙን አፍሶና አጥንቱን ከስክሶ ያቆማትና ያቆያት ሀገር መሆኖን ዶክተር ፍቅሪ አስተምረዋል ትምህርቱ ቀርቶ ለብሔርተኛው ና ለፅንፈኛው. የአንድነት ኃይሉ ይበልጥ የረጅም ዘመን ታሪኩን በመማር ኢትጵያዊነቱን ይበልጥ በማረጋገጥ በታሪኩና በማንነቱ የኮራንበት ትምህርት ነው። ሌላው ተጋባዥ እንግዳና ተናጋሪ ተዋቂው ጋዜጠኛ የወያኔን ስርአት በማጋለጥና በመተቸት የሚታወቀው በዚህ ተግባሩ ስርአቱ አስራ ሰባት አመት የፈረደበት በፅናቱ፤ በበሳልናበሰላ ሒሱ አመለካከቱ የሚወደደው አበበ በለው ነበር። እንደሰማሁት የአበበ በለው በተናጋሪ እንግድነት ወደዳላስ ቲክሳስመምጣት ያልወደዱትና ስብሰባው እንዳይሳካ እንቅስቃሴ ያደረጉ ስብስቦች ነበሩ እነሱም በግንቦት ሰባት የሰረገ የወያኔ ደህንነቶች፣አፍቃሪ ሻቢያዎችና አበበ የበለጠ ጠላት ነው ብለው የፈረጅ የወያኔ ደጋፊወች ናቸው። ምክንያታቸው የእሳት ራዲዪናቴሌብጅን ጋዜጠኞች ኤርትራ ምድር በመጎዝ ግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር መፍጠራቸውን ሲዘግቡ ስለ ኤርትራው ፕሪዘርዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ እንደ ብዙ ህዝብ አዲስ ድምፅ ራዲዮ ብዥታ ስለነበረው ያ የምናውቃቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ሀገራችን አሁን ላለችበትና ለደረሰችበት የቁልቁለት ጉዞና ቀውስ ዋነኛ መሀንዱስና መሪ ተዋናይ የነበሩ ሀገራችን እንደ ሀገር እንዳትቀጥል ከሀገራችን መሰረታዊናታሪካዊ ጠላታቶች ጋር አብረው የሰሩ ከህዝባዊ ወያኔ ትግራይ ነጻአውጭ ድርጅት ጀምሮ ሊሎችም ከዘጠኝ የበለጡ በነፃ አውጭ ድርጅት ስም ድርጅቶችን ጠፍጥፎ በመፍጠር ኢትዮጵያን ለመበተን የሰሩት ኢስያስ አፍወርቂን የእሳት ራዲዪ ዘጋቤዎች የእኒህን ሰው ተክለ ሰውነት ከፍ ከፍ በማድረግ ፕረዘርዳንት ኢሳያስ የኢትዪጵያ አንድነት ፣ሰላምና አለመረጋጋት እንደሚሳስባቸው በዚች ሀገር በጉልበትናበጠበንጃ ኅይል በሥልጣን ተቀምጦ ያለውን የህዋት ነፃ አውጭ ድርጅትን በማስወገድ ሰላም የተረጋገጠ አንድ ዲሞክራሲን ኢትዮጵያ ለመመስረት ከአንድ ብሔራዊ ግንባርና ከዘጠኝ የነፃ አውጭ ድርጅቶች ጋር አብረን እየሰራን ነው ያለትን በመቀጠል ቀድሞም ቢሆን ህዋቶች አልሰማም አሉን እንጅ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፣ሰላምና መረጋጋት ብዙ መክረናቸው ባለመስማታቸው ይህች ታርካዊና ጥንታዊ ሀገር በሚሳዝን ሆላቀርነትና አደጋ ወድቃለች ይህን ለመለወጥ አብረን እንሰራለን የሚል የፕሪዘርዳንት ኢሳያስ ቃለመጠይቅ በታወቁት የእሳትና የራዲዮ ጋዜጠኞች ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በተዋበ ድምፁ ባማረ ቅንብረ ጠፍቶ እንደተገኘ ልጅ በአድናቆትና በስሜት የቀረበ ቃለ~መጠይቅና ዜና መሰረትያደረገ ቃለ መጠየቅ መሰረት ያደረገ ነበር። ይህን ታሪክዊ የተባለናየሀገራችን እጣ ፈንታ ይውስናል የተባለ ቃለ መጠይቅ አንደ አስርቱ ትእዛዛት ማመንና መቀበል ብቻ ሳይሃን ህዝብ ሊወያይበትና ሊመክርበት ይገባል። በተለይ የቃለ መጠይቁ ባለቤት ሻቢያ፤ ኤርትራናኢሳያስ አፈወርቂ በመሆናቸው ይህን የአዱስ ድምፅ ራዱዪ አዘጋጅ አበበ በለው እንደ ብዙሀን ኢትዪጵያዊ ብሽታ ስለ ነበረው ለውይይት አቀረበው ። ለውይይት መደርደሪያ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራ በርሀ ድረስ በመሄድከኢትዩጵያ አርበኞች ግንባር መሪወች፣ከኤርትራ ባለ ሥልጣናትና ከፕሪዘርዳንት ኤሳያስ አፈወርቂ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ወንድሞችን በማቅረብ ጋዜጠኛ አበበ በለው አነጋገረ እንግዶችም አንደኛ ግንባር ላይ ያ እነርሱ የሚውቂት ሠራዊት ካለ በማመስገን፣ ለሀገራችን ነፃነት ብለው ብረት ያነሱ ወንድምችን በማድነቅ የእሳት ጋዝልጠኞችም ስለእደረጉት የኤርትራ ጉዞና ዘገባ አመስግነው በጥቅሉ ወዲ አፈወርቂ ወያኔን ለማስወገድ መነሻው ኤርትራ ያደረገው የአርበኞች ግንባር ለአሰራ ስድስት አመት ምንም እንቅስቃሴ እንዲደረግ በኤርትራ መንግስት ስላልተፈቀደለት በግዞትና በጉልበት ሥራ ብቻ እንዳለ ይህን ያልፈቀድና የታገሉ የአርበኞች ግንባር መሪዎችና አባላት በኤርትራ ባለስልጣናትናደህንነቶች እየተያዙ የተገደሉትንና መዳረሻቸው ያልታወቀ አርበኞች በማስረጃ አቅርበዋል ። ይህንን ውይይት ያልፈቀድና ያልወደድና በእሳት ጋዜጠኞች የቀረበ ድብቅና አስመሳይ የኢትዪጵያን ህዝብ የእውቀት ግንዛቤ የናቀ ዘገባ በጭፍንና በመጫን ያለ ምንም ውይይት ህዝቡ እንዱቀበለውና እንዲምንበት የፈለጉ የግንቦት ሰባት ሰወች፣ የፕረዘርዳንት ኢሳያስና የሻቢያ አፍቃሪዎች በአዲስ ድምዕ አዘጋጅ በአበበው በለው ላይ የማጥላላት ዘመቻ ላይ ማድረግ ጀመሩ በሆላም ግንቦት ሰባት በላይ ጠንቀኛ ጠላታችን አበበው በለው ስለሆነ በዚህ ዘመቻ እንድንሳተፍ በማለት የወያኔ ካድሬዎችከግንቦት ሰባት ደጋፊወች ጋር ተቀላቀሉ ሰለዚህ በአዲስ ድምፅ አዘጋጅ በአበበ በለው ሦስት ለአመታት የማይነጋጋሩ ፣ በደምና በጦርነትየሚፈላለጉ ኃይሎች ግንባር ፈጥረው በታዋቂው ኢትዪጵያዊ ጋዜጠኛና አክትቢስት አበበ በለው ላይ ጦርነት ከፈቱ። እንደሰማሁት የዳላስ ግንቦት ሰባት ቻፕተር በአበበ በለው በእንግድነት ና በተጋብዥነት በተገኘበት ሰብሰባ ከአጋር ኃይሎች ጋር ያለመሳተፍና ስብሰባው እንዳይሳካ ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል እነ እሰየ አብረሀ ለነ ዳዊት ከበደ መድረክ ያዘጋጀ እነ ተስፋገ/አብን በተጋባዥ እንግድነት ጠርቶ የነበር የግንቦት ሰባት ፎረም የራሳቸውን ወዳጅ እሳትን ካቆቆሙትና ከመሰረቱት አንድ የሆነ ለእሳት መጠናከር በየአገሩ በመዛወር በሰው ፊት እየተገረፈ ፈንድረይዚግ ያስደረገ ፤ እነ ብርሀኑን ነጋ ከቅንጅት መፍረስና ከእስር በሆላ ፕረሞት በማድረግ በየስቲቱ ይዞ በመዛወር አሁን ላሉበት ቀጣይ ትግል ያበቃ አበበ በለው ስለ ኤሳያስ አፈወርቅ ቃለ መጠይቅ አደረክህ ተብሎ ማእቀብ ተደረገበት የመጀረያው ተፈጠረ የተባለው ግንባር ሌሎች አጋር ኃይሎችን በመጨመር በአበበ በለው ላይ ጦርነት ከፈቱ። የሀሳብ ልዩነቴን ተቀብለው የትግል ጎደኝነታችን ይቀጥላል ብሎ የሚምናቸው ወዳጆቹ በተፋየ ገ/አብ ከሚመራው የሻቢያ ዲስፓራና በዳዊት ከበደ ማኔጅመንት የህዋት የዳይስፓራ ካድሪዎች ጋር በማወቅ ሆነ ባለማወቅ ተጣመሩ።ይህ ሁሉ ሁኖ ቀላል የማይባል ህዝብመጣ ስብሰባው በቀጥታ በአዲስ ድምፅና በፕልቶክ ሩሞች በተለይ በታወቀው፣ በድፍረቱና በሀርድ ቶክ ትንታኔው ተሰሚነት ያለው የአባ መላ ክፍል ኢትዮ ስብሊቲ መተላለፍ የስብሰባው መልእክት በሁሉም አለም ተሰማ። ከታሪኩ ምሁር ከዶ/ር ፍቅሪ ቶሎሳ በኃላ የመድረኩ አስተዋዋቁ ባልሳሳት ዶ/ ስሜነህ ሲናገሩ ጋዜጠኛ አበበ በለው እንዲቀርብ የተሰጠው ርእስ ባለፍት ሀያ አራት አመት የተቃዋሚ ድርጅቶች ትግሉን ምን ደረጃ አደረሱት? ምን ተግባር ሰርተው ምን ተሳካላቸው? ገዥው ሥርአት ወያኔ ኢህአደግ አገዛዙ በተራዘመ ቁጥር በኢትዮጵያ ህዝብ እያደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የመብት ገፈፋ፣የዘረኝነት አድለዎ በአጠቃላይ አገዛዙ ግፈኝነቱ በደሉ አየጨመረና እየጠጠረ ህዝቡ ሊሽከመውና ሊስተናግደው በማይችልበት የመከራውና የዘረኝነት ጽዋው በዝቶበታል።ከግፈኞችና ከአድርባይ ሆዳሞች ንሮ በታች ከሞቱት በላይ ሁኖ በተፋጠጠበት ሰአት ተቃሚ ድርጅቶች ይህን የተገፋ ህዝብ አደራጅቶ ና አቀናጅቶ ሥርዐቱን ለመለወጥ የሚደረገው ትግል ዳር ያለመድረስ ችግሩ ምንድን ነው?የሚልና እኛ ኢትዮጵውያን (ዲያስፖራ) ለሥርዐት ለውጥ የምናደርገው ትግል ምን ደረጃ ደርሶል የሚል ነው። ጋዜጠኛ አበበ ንግግሩን እንደሰማሁት የፖለቲካ እውቀቱን ናግንዛቤውን ብቻ ሳይሆን ይህን የግፈኝነት አስተዳደር ለመለወጥ ያለውን ቁርጠኝነትና ብርታት እጅግ የሚደነቅ ነው።አበበ ንግግሩን ሲጀምር ያለው ህዋትን በማውገዝና በማልቀስ ብቻ የትም አይደረስም የሰው ልጅ ይፈጽመዋል ተብሎ የማይታሰብ ወንጀል በወገኖቻችን ላይ ተፈጽሞብናል በዘርናበኃይማኖት ከፋፍለው አፋጅተውናል የሞትና የውርደት ሽማ አልብስርውናል።በአለም ፊት የተዋረድና የረክስን ዜጎች አድርገውልናል። ይህን ብሶት ሀያ አራት አመት ደግመን ደጋግመን አወራን አለቀስን ከዚህ በኃላ መጠየቅ፣መተቸትና መታገልም ያለብን የተቃዋሜ ድርጅቶችን ነው። ለምንድን ትግሉን ወደተሻለ ደረጃ ያላሻገሩት? ለምንድን ነው የህዝብን ተደጋጋሚ ጥሪ ተቀብለው አንድነት የማይፈጥሩት? ከኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣትና የራሴን አገር እመሰርታለሁ ከሚል ብሄርተኛ ድርጅት ጋር ግንባር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅት ለምንድን ነው ከኢትዮያውያንህብረ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ችግሩ ምንድነው? በቅንጅት ጊዜ የነበረው የዲስፓራው ህብረትና የተቀናጀ ትግል መሪት አንቀጥቅጥ የሆነ ሰላማዊ ስልፍ በማድረግ መሪዎቻችን ከእስር እስከ ማስፈታት ያደረሰው ህብረታችን ና ጥንካሬችን የት ደረሰ? ምእራባዊያንና አሜሪካውያን ትኩረት ና ክትትል ማድረግ የቻሉት እኛ ኢትዪጵውያን በውጭ ሀገር ከልጅ እስከደቂቅ ወጣት ሽማግሌ ፣ሴት ወንድ እስላም ክርስትያን ሁላችን በአንድነት ባደረግነው ትግል ውጤት አግኝተንብታል ታዲያ ዛሪ ያ ትግላችን የት ገባ በየስቲቱ ህዝቡን በፀረ ወያኔ አላማ ያስተባብሩ፣ያታግሉና ለተቃውሞ እንስቃሴ ሰልፍ ከፊት ሁነው ያታግሉ የነበሩ መሪዎች ለምን ከትግሉ ሜዳ ወጡ ? ፓለቲካችን በመርህ ላይ ተመስርቶየሀሳብ ልዩነትን በማስተናገድ አቅጣጫ ያለው ትግል ከማድረግ ይልቅ ልዩነታችን በማግዘፍ በሀሳብ የበላይነት ከማመን የግለሰቦችን ሰብእና የሚዋርድ ሀገራዊ ራእይ የለለቸው ለራሳቸው ክብር የማይሰጡ የተቃውሞውን ኃይል ስለወረሩት ብዙ አንቱ የምንላቸው ሰዎች አጠናል። በዚህም የተነሣ ህዋት ኢህአደግ ሀገር ቤት ያለውን ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ህዝቡን በኃይልና በጠበንጃ ረግጠው ሲገዙ በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን ከእኛ በላይ ሥርዐቱን እያወገዙ በኮሚኒቴወችና በፓለቲካ ድርጅቶች ሰርገው በመግባት በኢትዮጵያውያን ድርጅቶችና ኢትዮጵያውነትን በሚቀነቅኑ ግለሰቦች ላይ የማጥላላትና ሰብእናን የሚነካ ጋጠ ወጥ ስድብ አየሩን በመሙላታቸው ይህንን እሳፋሪ እካሄድ አንዳንድ የፓለቲካ ድርጅቶች ለጊዜዊ የፓለቲካ ፍጆታ ስለ ፈለጉት ብዙ ኢትዩጵያውያን ሙህራንን አጠናል ፍሪ ያለው ትግል እንድናደርግ የኢትዮጵያውያን ሙሀራን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ከቆሻሻ ስሜትና አካሄድ ወጠን የፓለቲካ ባህላችንን ከፍ አድርገን አገርና ህዝብን የሚመጥን ሥራ እንዲሰራ አደራ ብሎል። ጋዜጠኛ አበበ በለው ከህዝብ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ በእኔ አመለካከት። በሚል ሰጥቶል ከቀረበው ጥያቄ አንድ የኤርትራ መንግስት ሻቢያ የኢትዮጵውያን የፓለቲካ ድርጅቶችን እያስታጠኩና እያሰለጠንኩ ነው ይላል ነገር ግን አርበኞች ግንባር ጨምሮ አስራ ስድስት አመት ሲቀመጥ አንድም ጊዜ ወታደሬዊ ኦፕሬሽን አድርጎ አያውቅም ይልቁንም ደርሰው የሚመለሱ ሰዎች እንደሚስረድት አርበኛው ለሻቢያ በጉልበት ስራ ተጠምዶ እንዳለ እዲሁም ብዙ የአርበኞች ግንባር መሪዎች ወታደራዊ እንቅስቃሴ እናድርግ ስለ አሉ እንደተገደሉና አድራሻቸው እንደጠፋ ይነገራል አንተ እንደ ጋዜጠያነትህ እንዴት ታየዋለህ? ሁለተኛው የቀረበ ጥያቄ በእሳት ጋዜጠኞች የቀረበው የፕሪዘርዳንት ኢሳያስ የቀረበው ቃለ መጠየቅ እንዲት አየኽው? በተለይ የእሳት ዘጋቤዎች ፕሪዘርዳንቱን የኢትዪጵያ ህዝብ ከሚውቃቸውና ከሚረዳቸው በላይ አሳምሮና ቀብቶ ያቀረባቸው ይመላል እውን ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ ኢትዮጵያ ሰላም፣ የግዛት ሉዑላዊነት ና የዲሞክራሲ እጦት ይጨነቃሉ? ሦስተኛው ጥያቄ ተስፋ የተጣለበት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ከህብረ ድርጅቶች ጋር ከመስራት ይልቅ በኢትዮጵያ ቅኝ ተግዝተናል ከሚሉ ነፃ አውጭ ነን ብለው ከሚጠሩ ጋር እየሰሩ ነው እዲደውም ነፃ አውጭ ነን ከሚሉትና ከሚከሱት በላይ ግንቦት ሰባት ብሔራዊ ድርጅቶችን ሲጣጥልና ሲንቅ ይታያል ይህ አካሄድ ምን ይመስልሀል? የሚልና ሌሎች ጥያቄዎች ተጠይቆ መልስ ሰጠውባቸዋል። አበበ ስለ ኤርትራና ሻቢያ ማውራት ወያኔ እያሰኘ ነው ሲል ህዝቡ በጣም ይስቃል አዎ! አዎ አለ አበበ ማንም የፖለቲካል ድርጅት ለሚካሔደው የትጥቅ ትግል ከየት ነው መነሻህ ማን ነው የሚረድህ ምን አስቦና አልሞ የሚረዳህ ወዘተ ብየ ድርጅቱና የድርጅቱ ልሳና ራዲዮ ቢዘግብ አልጥይቅም ነገር ግን በሌላ ሚድያ እንደ እሳት ገለልተኛ የሆነ የህዝብ ዐይንና ጀሮ ተብሎ በተቅቐመ የሜዲያ ተቕም ሲነገር ግን ለህዝብ ውይይትና ክርክር እንዲቀርብ ታስቦል ማለት ነው ባለፈው ያቀረብኩት ቃለ መጠይቅ አሁንም ለወደፊትም የምናገረው የሁላችን አይና ጀሮ በእሳት ራዲዮና ቴሌብጅን ለህዝብ ሲቀርብ ነው። እሳትእኔ የምላችሁን እመኑ፤ አትጠርይቁ አትመራመሩ አይልም ወይም አዳም ከዚች እጸ በለስ በቀር ሌላውን ብላ ተብሎ ትእዛዝ እንደተጠው እኛም ከኤርትራ፣ ከሻቤያና ከወዴ አፈወርቂ ሌላ አውሩ የሚል ትእዛዝ የሚሰጥ ከሆነ እንጠብቃለን ። እስከእዛ አወራለሁ በማለት አስቆናል። ኢሳያስ አፈወርቂ ና ሻብያ ወደድነም ጠላንም የሚታወቁበት የኤርትራን ጥቅም ለማስቀድም በሁለገብ ትግል ከእኛ ቀድመው እኛውን መሳሪያ አድርገው እኛ ኢትዮጵያውያን ታግለንላቸው ና ሙተንላቸዋል በብሄር ብሄረሰብ ነጻነት እሰከ መገንጠል በሚል እኛን ኢንተርናሽናል እያዘመሩ እነርሱ በመንደር ነጻነት እኛን አደንዝዘው ሀገር መስርተዋል ።በትግል ዘመን ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችን ከህውት ጋር በመሆን አጥፍተዋል ሻቢያ በራሱ ታጋዮች ኢትዪጵያን በመልካም ጎን ያነሳ አፍቃሪ አምሀሮይ አባይ እየተባለ ተረሽኖአል።የአንድ የሻቢያ ታጋይ መንፈሰ ጠንካራ ተብሎ የሚለካው በኢትዮጵያዊ በተለይ በአማራው ህዝብ ባለው ጭካኔና የጥላቻ ልክ ነው። የዚህ ሁሉ አመለካከት መሀንዲሲ ደግሞ ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው የኤርትራን በርሀ በደም ያጨቀዩ ሰው ናቸው ።ኢሳያስ አፈወርቂ ለምን ብለው ነው እኛን የሚፈልጉ ለኤርትራ ነጻነት ደሙን ያፈሰሰው አጥንቱን የከሰከሰው ነገ ኤርትራ ላይ ጥቃት ቢሰነዘር ቀድመን ለኤርትራ ህልውና እንሞታለን የሚለው ህዋት ተቀምጦ የኤርትራን ነጻነት ያረጋገጠ ኢትዪጵያን ያለ ወደብ ያስቀረ ለኤርትራ ሙሉ ካሳ የከፈለ ይህን ድርጅት ትቶ በምን ሒሳብና ስሌት ነው ሊላ ቡድን ጋር የሚሻረክ ወይም ህዋት ያልፈቀደለት ተቃዋሚወች ለድል ከበቃን እናደርልሀለን ያሉት ውል ከለለ ይህ ውል ደግሞ ኢትዪጵያን ህልውናዋን አጥፍቶ ለወደፊት ኢትዪጵያ የምትባል ሀገር ኑራ ስጋት በማትሆን ድረጃ ካልተሰራ። ወዲ አፈዎርቂ ያለምንም ጥቅም የሚተባበሩት የለም ለበለጠ ጥቅም ይተባበራሉ ያ ይነገረን ህዋት ከሻቢያ ጋር ሲተባበር የኤርትራን ነጻነት አምኘተባብሬለሁ ለዚህም ዋጋ ሊከፍሉንና ልንከፍል በደም የተሳሰረ ቃል ተጋብተናል ብሎ በግልፅ እየነገረን ነው መንግስት የሆኑት ወዱ አፈወርቂ ከእናንተ ምን ለማግኘት እንደፈለገ በይፋ ይነገርን። ሁለተኛው ጥያቄ በእሳት ጋዜጠኞች ስለ ፕረዘርዳንት ኢሳያስ ተክለ ሰውነት፣ ለኢትዪጵያ ና ለአፍሪካ ሰላም መረጋጋት ሩቅ አሳቢነታቸው ተብሎ የቀረበውና ይህንም። በኢትዮጵያ ህዝብ ስነ ልቦና ተፅእኖ ለመፍጠር በእሳት ጋዜጠኞች። የተደረገው አካሄድ አሳዝኖኛል። ሙተን ሳናልቅ በአሁኑ ሰአት ለትግል ብለው ኤርትራ በርሃ ላይ በግፍ እየተገደሉ ያሉትን ሳስብ ፣ በባርነት ነፃ የጉልበት ሰራ የሚሰሩትን ና በበረሃ በእስርየሚሰቃዩ በደርግ የመጨረሻ ጊዜ እጃቸውን በሰላም ሰጠው በመትረየስና ላውንቸር የኢትዪጵያን የሠራዊት አባል ሳስብ ያ ቃለ መጠይቅ ያማል በሚል ዘሎታል ያማል። ሦስተኛው ጥያቄ ተስፋ የተጣለበት ግንቦት ሰባት ከህብረ ድርጅቶች ይልቅ ከኢትዪጵያ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ከሚሉ ጋር ይስርሉ ይህን አካሔድ እንዴት ታየዋለህ? ይህ ጥያቄ ለእኔ ሳይሆን ለግንቦት ሰባት መሪዎች የሚጠይቅ ነበር ሆኖም ድርጅቱ በሀሳብ ትችት ያምናል ብየ ስለማስብ የበኩሌን አስተያየት እሰጣለሁ። ጥያቄው የኔም ጥያቄ ነው ። ግንቦት ሰባት የኢትዪጵያውን ህዝብ ከወያኔ አምባገነንነት ነፃ ለማውጣት የሚታገል ድርጅት ነው ብዪ አስባለሁ ነገር ግን ከኢትዪጵያነፃ እናወጣለን የሚሉ ድርጅቶች ዛሪ አብረው ታግለው ነገ ነጻ ቢወጡን ከዚያ ምን እንደሚደርጉ ግልጽ አይደለም ነገ አንድ ኢትዮጵያን መስርተን በዲሞክራሲ ስርአት ለሁሉም ህዝብ እኩል የሆነች ሀገር መስርተን እኖራለን የሚሉ ከሆነ ዛሪ የነፃ አውጭ ድርጅቶች በኢትዮጵያዊነታቸው አምነውና ተቀብለው የሚደርጉት የፕሮግራም ለውጥ ይወስነዋል ያኔ በአንድ ልብ እንታገላለን። ይህን ሳይደረግ ከኤርትራ የሚነሳው የግንቦት ሰባትና የነፃ አውጭ ድርጅቶች ንቅናቄ ለድል ቢበቃ እኮ ሀገራችን ከነ ሙሉ ሉአላዊነቶ መቀጦሎ አጠያያቂም አስፈሪ ነው። ግልጽና አስተማማኝ የሆነ በአገራችን ህልውናና ቀጣይነት ስምምነት ከለለ ከዚያ በኃላ የጠበንጃ ኃይልና ጥንካሬ ያለው ድርጅት ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ይመረዋል እነ ኦነግ፣ኦጋዴን ነፃ አውጭ ድርጅት ወዘተ ዘጠኝ የነፃነት ድርጅት በአንድ አገር አቀፍ ኢትዪጵያ በምትባል ሀገር በደምና በአጥንት በተመሰረተች ሀገር ማእቀፍ ስር ስለመኖራቸው ሳይሆን ያለው ምልክት ና ተጨባጬ ጉዳይ የሚሳየው ነፃነት ለማወጅ መዘጋጀታቸውን ነው ። ይህ ከሆነ ግንቦት ሰባት ፈቃደኛ ምርኮኛ በመሆን የ ኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ለመጣል ተባባሪ ሁኖአል ማለት ነው።ሻቢያ ደግሞ ነፃ አውጭ ድርጅቶችንየበለጠ የሚፈልግበት አንድ ምክንያት ዳግም ለኤርትራ ስጋት የማትፈጥር፤ አቅመ ደካማ አገር በመገንባት ኤርትራ ተፅእኖ ፈጣሪ ሀገር ለማድረግ የተከፋፈለች የተበታተነች ሀገር መፍጠር የሻቢያ ስትራቲጅክ አላማ መሆኑን የግንቦት ሰባት መሪዎች ይርዳሉ ያውቃሉ ነገር ግን አሁን ካሉበት ማጥ ለመውጣት በለለ ኃይልና አቅም በውሽት ፕሮፕጋንዳ ራሳችውን አሳብጠው ለዓመታት የተሰራ ድራማ በይፋ ሊጋለጥ ሲል ሻቢያ የፓለቲካ ህልውና እስትንፋስ በመስጠት አንዴ ከአርበኞች ግንባር ሌላ ጊዜ ከኦነግ ከዚያ ከትህዲን እያለ የጆከር ጨዋታ በማጫወት የፕሮፓጋንዳ ሥራ በማሰራት ሻቢያ ግንቦት ሰባትን መጠቀሚያ። እያደረገው ነው። የአበበው በለው ንግግር ያስከተለው አብዩትና የኃይል አሠላለፍ ጋዜጠኛ አበበ በለው በአዲስ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በእሳት ራዲዮና ቴሌብጅን ስለ ፕሪዘርዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ሻቢያ የተደረገው ዘገባ መሰረት በማድረግ ኤርትራ በመመመላለስ ተመክሮ ያላቸው ወንድሞችን ባደረገው ቃለ መጠይቅ ሁለት ባላንጣዎችን ፈጠረ አንደኛው ስለ መሪችን፣ስለመሪ ድርጅታችን ሻቢያና ስለ ወደፊት የኤርትራ ጥቅም ላይ አደገኛ ቃለ መጠይቅ አድርጎል በሚል መሀል ሀገር ኢትዪጵያ የተወለድ ኤርትራውያን በማስተባበር የተነሳው የሻቢያ ቡድን ነው። የዚህ ቡድን ካድሪዎች ባእድ መሆናቸው በእርግጥም ለሀገራቸው ጥቅም የቆሙና ማድረግ የሚገባቸው ስራ በመሆኑ አያስደንቅም። አደጋኛነቱ ግን እኛ ኢትዮጵያውያን መስለው የእኛን ቆንቆ እያወሩ የኢትዪጵያ በተለይ የግንቦት ሰባት ተቆርቆሪ መስለው ውይይቱን ለማስቆምና አበበ በለውን ለመዋጋት እያደረጉት ያለውን ዘመቻ በነ ተስፋየ ገ/አብ የሚመራው ግብረ ኃይል አንድ ክንፍ ነው። ሌላው በጋዜጠኛ አበበ በለው ነፃ ቃለ መጠይቅ ና ንግግር ከግንቦት ሰባት ሰዎች ጋር የተፈጠረውን የአካሄድና የአመለካከት ልዩነትና ክፍተት በምጠቀም በሁለቱ በኩል ያለውን የኃይል ሚዛን በመጠቀም ኃይላቸው ከተደራጀ ግንቦት ሰባትን ከማጥቃት ይልቅ ግለሰቡን አበበ በለውን በእርሱ ላይ ከተነሱት ጋር ማጥቃት ይቀላል በሚል በነ ዳዊት ከበደ የሚመራው የወያኔ ህዋት ግብረ ኃይል ነው። ይህም ኃይል የግንቦት ሰባት ተቆርቆሪ በኤርትራ ላለው ንቅንልቂ ደጋፊ በመምሰል ጋዜጠኛአበበ በለውን ለመዋጋት የተሰለፈው የወያኔ ኢህአደግ ኃይል ነው። ሌላውና ዋነኛው የጉዳዩ ባለቤት ራሱን እንደ ስደተ አምባገነን መንግሥት ቆጥሮ በሀገራችን የፓለቲካ ጉዳይ ፣ አሁን ባለው የፓለቲካ ድርጅቶች አካሄድ ላይ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ድርቶች በተለይ ኤርትራ አሉ በሚባሉ ጉዳዮች ና ፕረዘርዳንት ኢሳያስ በእሳት ራዲዮና ቴሌብጅን ስለ ሰጡት ቃለ መጠይቅ አትናገሩ ፣አትተቹና አትወያዩ የሚሉ እራሳችን የፈጠርናቸው ፀረ ዲሞክራሲ የሆነው የግንቦት ሰባት ኃይል ነው። ይህ ኃይል ሾላ በድፍን ኢሳያስ ለኢትዪጵያ አሳቤና ተጨናቄ ናቸው ስለ ሀገራችን ሰላም ፤ዲሞክራሲና አንድነት ያስባሉ በሚል ከነፃ ሜድያነት ወደ ድርጅት ልሣንነት እየተቀየረ በመጣው በእሳት ራዴዮና ቴሌብጅን የፕሮፓጋንዳ ሥራ ከአሰሩ በኃላ የህዝብን ትችት ካለመስማታቸው በላይ በዚህ ጉዳይ የሚወያዩ ጋዜጠኞችን ፀሐፊዎችን ይህን የሚስተነግዱ ወብ ሳይቶችን፤ራዲዮ ጣቢያዎችን ና የፓልቶክ ሩሞችን የሚሳደቡ፣የሚዋክቡ በጣም በወረደናሰብእናን በሚነካ ደረጃ የሚተናኮሉ የአጋዜና የፊደራል ተሳዴቢዋችን በመመደብ በአርበኞ ንአምን አመካኝነት በጋዜጠኛ አበበ በለው ላይ ዘመቻ ተከፈተበት ።ስለዚህ ጋዜጠኛ አቤ በሦስት ግንባር ማለትም ሻቢያ፣ ወያኔና የግንቦት ሰባት የጋጠወጥ ቡድን የከፈቱበት ጦርነት ሀሳቡን ባመኑ፣የመናገር የመተችት መብት በግንቦትሰባት ጋጠ ወጥ ቡድን፤በወያኔ ባንዳዎችና በሻቢያ አይቆምም በማለት ለአበበ ሺዎች እየደገፍት ሲሆን። የአበበ በለው ንግግርና እምነት ለተከታታይ ሦስት ሳምንት ርእስ ሁኖ በቀን ሀያ አራት ሰዐት እያነጋገረ ነው ከዚህ በኃላ ቀዳሚ ርእስ ሁኖ ለስንት ግዜ እንደሚቀጥል አይታወቅም። እውነተኛው ጉዳይ የሦስቱ ጥምረት መሪዎችን ሥራና መጨናነቅ አብዝቶባቸዋል። ከጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት በኃላ በቅድሚያ ርእስ ሆኖ ይህን ያህል ያወያየ ጉዳይ የለም።ብዙ ሙሀራን ፤ ለውጥ ፈላጊ የግንቦት ሰባት አባላት ና ኢትዪጵያውያን ወደዉታል፣ አወያይታልግንዛቤ ሰጥቶል ግንቦት ሰባት የማይሸሸው ህዝባዊ ጥያቄ ቀርቦለታል መሪዎች እጥቄ ተሳዳቤ ግብረ ኃይል ከሚልኩና የውይይትና የዲሞክራሲን ገፅታ ከሚጠፍ መልስ ይስጡ።
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/7956#sthash.yQR06ndd.dpuf
No comments:
Post a Comment