በዛሬው እለት አዲስ አበባ በሚገኘው በታላቁ አንዋር መስጅድ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ!
ትናትም ዛሬም “ኮሚቴው ነፃ ነው.. በነፃ ይሰናበት” እያሉ ፍትህን የሚጠይቁ ሙስሊሞች በአንዋር መስጊድ ደማቅ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ:: በተያዘው የረመዳን ጾም የሕወሓት መንግስት ካንጋሮው ፍርድ ቤት እስር ቤት ባሉት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ፍርድ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ መዘገቡ ይታወሳል:: ዛሬ በአንዋር መስጊድ እና በተመረጡ የክልል ከተሞች በተደረገው በዚሁ የድምፃችን ይሰማ ተቃውሞ ሕዝቡ መፈክሩን በመያዝ በየመስጊዱ ኮሚቴውን በነጻ ከመልቀቅ የተሻለ አማራጭ የለም ሲል በአንድ ድምጽ ሲያሰማ ውሏል:: “የተከሰሰነው ነው እኛ ነን:: በነፃ ከማሰናበት ውጭ ያነሰን ብይን ያለ አማራጭ አንቀበልም” ያሉት ሕዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት መንግስትን አሁንም በሰላማዊ መንገድ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል::
ይህንን የበከተ በዴሞክራሲናፍትሕ ላይ የሚቀልድ ነዉረኛ ስርዓት ከዚህ በኋላ ባመጽ መንገድ አሽቀንጥሮ ለመጣል የንደዚህ አይነቱ ቁርጠኛና አይበገሬ ትግል ወሳኝም ታሪካዊም ነዉ፥ሁሉም ወገን በየፊናው ድምጹን ያሰማ !



No comments:
Post a Comment