Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 6, 2015

የመኢአዱ ጀግና መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን እና ተስፋየ ታሪኩ ሌሎች 16 የመኢአድ የቁርጥቀን ልጆች ልደታ ፍርድቤት 19ኛው ቀረቡ 28 /9/07



የመኢአዱ ጀግና መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን እና ተስፋየ ታሪኩ
ሌሎች 16 የመኢአድ የቁርጥቀን ልጆች ልደታ ፍርድቤት 19ኛው የወንጀል ችሎት ቀረቡ
28 /9/07
መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን የደረሰበትን አስከፊ ወንጀል ለዳኛው ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም
አቶ ተስፋየ ታሪኩ እሱም እየተፈፀመበት ያለውን ግፍ ለመናገር ቢያስፈቅድም ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ዳኛው አስቁሞታል
ዳኛው የናንተ ጉዳይ ወደ እኛ ከመጣ በኋላ የተፈፀመውን ለማስተካከል እንሞክራለን
ማእከላዊ በነበራችሁበት ወቅት የተፈፀመውን የማየት ስልጣን የለንም ብለዋል
በመቶ አለቃ ጌታቸው ላይ የተፈፀመው ወንጀል እግሩን በመስበር አማራን ማጥፋት አለብን በማለት የዘር ፍሬውን በማኮላሸት እራሱን እንዳይተካ (እናዳይወልድ) ተደርጓል እክምናም እንዳያገኝ ተደርጓል
አንድ ተከሳሺ ስሙን አላውቀውም ሁለት አይኑን ታሟል እክምና አገርውስጥ የለውም እክምናው በውጭ አገር ነው ስለዚህ ሲሆን የምታከምበት ቢመቻችልኝ ሳይሆን ግን አመቺ የሆነቦታ ይመቻችልኝ ብሎ ጠየቀ
አቶ ተስፋየ ታሬኩ ያቀረብነው አቤቱታ የማይሰማ ከሆነ ምንም ጠበቃ አያስፈልገንም ለፀረ ሺብር ህጉም ሆነ ለዚህ ፍርድቤት እውቅና አንሰጥም
ያሰረንም ያሳሰረንም የደበደበንም የሚያስደበድብንም የሚመሰክርብንም የሚያስመሰክርብንም የሚፈርድብንም ወያኔ ነው
እኛ ለግንቦት 7 እና ላርበኞች ግንባር ያደረግነው ነገር የለም
እነሱም የሳላማዊ ትግሉ ሲዘጋ ነው ወደትግል የገቡት ብሎአል
ሁሉም የመኢአድ አመራሮች እና አባሎች
16ቱም የተከሰሱበት ክስ ግንቦት 7 አርበኞች ግንባር እና ያማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ አባሎች ናችሁ የሚል ነው።
ቀጠሮ ከሐምሌ 1 ተወስኖአል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials