በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት የሆኑት ወታደሮች በአገልግሎት ማብቂያ በሚል ምክንያት ያልተፈለጉትን ለማሰናበት ተብሎ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ብዛት ያላቸው ወታደሮች አገልግሎታችን ግዜ ያበቃ በመሆኑ መሰናበት አለብን በማለታቸው የተነሳ ስብሰባው እንደተቋረጠ ታወቀ።
ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት- በሰሜን እዝ በክፈለ ጦሩ አዛዦች ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለና ብርጋዴር ጀነራል ማዓሾ በየነ የተመራው ስብሰባ ግንቦት 21 2007 ዓ/ም የተካሄደ ሲሆን። እንደ አጀንዳ ያቀረቡት ደግሞ ከአስርና ከስባት አመት በላይ ካገለገሉት መካከል የተወሰኑትን ለማሰናበት በሚል ቢነጋገሩም ብዛት ያላቸው የሰራዊቱ አባላት ግን ከተባለው የአገልግሎት እድሜ በላይ ያገለገሉ ስለሆኑና። ላቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ በመቃወም“ ግዳጃችን ስለፈፀምን የሚገባንን ሰጥታችሁ ሸኙን” በሚል በአንድ ድምፅ ስለተቃወሙ ስብሰባውን እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በማከል እንዳስረዳው- በአገልግሎት ስም የተወሰኑት ልንሸኝ ነው የሚለውን ሃሳብ እንደ ሽፋን እንጂ ዋናው አላማው ግን በወታደሩ ውስጥ በተካሄደው የግንቦት 16/ 2007ዓ/ም ምርጫ በረከት ያለ ድምፅ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሰጥቶ በመገኘቱ የተነሳ ይህ ደግሞ ለሰራዊቱ አዛዦች የራስ ምታት ስለሆነባቸው በምርጫ ጊዜ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መርጠው ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉት ወታደሮች ለመቀነስ የታለመ ሴራ ቢሆንም ነገር ግን ሳያስቡት ግርግር በመከሰቱ አጀንዳውን እንዳስቆሙት መረጃው ጨምሮ አስረድታል
No comments:
Post a Comment