Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, June 19, 2015

በሼኽ አላሙዲን ጉዳይ… ማህደር አሰፋ ምላሽ ሰጠች

 ሰሞኑን አንድ አነጋጋሪ ጉዳይ ተፈጥሯል። አርቲስት መሃሙድ ሙዚቃ የጀመረበት 50ኛ አመት ኢከበር፤ ሼኽ አላሙዲን በስፍራው ተገኝተው ነበር። ሼኽ አላሙዲን በዚህ ምሽት በፊልም ሙያ ከምትታወቀው ማህደር አሰፋ ጋር ሲደንሱ፤ በፎቶ እና በቪዲዮ የተነሱት ምስል፤ በተለይ በማህበራዊ ድረ ገጾች ተሰራጩ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሼኽ አላሙዲን ከዚህ በፊት አብረዋት የተነኡት ፎቶ ጭምር እንደአዲስ መሰራጨት ጀመረ። ይህን በተመለከተ ሰዎች የየራሳቸውን አስተያየት ሰጥተዋል። አንዳንዶች ድርጊቱን ሲያወግዙ ሌሎች ደግሞ የማህደር ደጋፊዎች በመሆን ድምጻቸውን ሲያሰሙ ነበር።
"ጥበብን በጥበብነቷ ዳኝታቹህ ከራስ ማንነት ግላዊ ህይወት ጋር ሳታደባልቁ ለምታዩት ለናንተ የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳቹህ።” ማህደር አሰፋ
“ጥበብን በጥበብነቷ ዳኝታቹህ ከራስ ማንነት ግላዊ ህይወት ጋር ሳታደባልቁ ለምታዩት ለናንተ የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳቹህ።” ማህደር አሰፋ
የግራ እና ቀኙ አስተያየት እንዳለ ሆኖ፤ “የጉዳዩ ባለቤት የሆነችው እራሷ ማህደር ምን ትላለች?” የሚለው ጥያቄ በብዙዎች ዘንድ ሲጉላላ ቆይቷል። ኢ.ኤም.ኤፍ ዛሬ የሚያቀርብላቹህ ስሜታዊ በሆነ መልኩ የተባለ ቢሆንም፤ እራሷ አርቲስት ማህደር ያለችውን ለማቅረብ ወደድን። “ለሚተቹኝ፣ ለሚተባበሩኝ፣ ለሁላችሁም አመሰግናለሁ።” ብላ ነው የጀመረችው ማህደር።
ከዚያም ቤቀጠል፤ “ግን አንዳንድ ሰዎች ድንበር አልፈው በማያገባቸው ሲዘባርቁ ይገርመኛል። እኔ የምኖረው የራሴን ህይወት ነው። እናንተም እንደዛው። ነገር ግን በምንም ይሁን በሚያገናኘን ነገር ካለ በሱ ብቻ ዳኙኝ። ከዚህ አልፋቹህ ብዙ ለምታወሩ እና ለምትሉ ቦታ የለኝም። በተለይ ሰሞኑን ብዙ ብላችኋል። ታላላቅ የሚባሉት ሚዲያዎች ሳይቀሩ ስለኔ መቃዠት ከጀመሩ ሰነበቱ። ተመልካች ወይም ትርፍ ካስገኘላቹህ አሪፍ ነው። ከዚያ ውጪ ግን በሰው ህይወት ገብቶ መፈትፈት የሚፈጥረው ፋይዳ የለም። ብታወሩም ባታወሩም ለውጥ የለውም። ምክንያቱም ስለምኑም አታውቁምና። ስለዚህ መሳደብ የምትፈልጉ ቀጥሉበት – አእምሯቹህ ማመንጨት የሚችለው እሱን ብቻ ነውና።”
በሌላ በኩል ደግሞ፤ ሲደግፏት ለቆዩት “ይህ መልዕክት ግን በማንኛውም ግዜ ከጎኔ ለሆናችሁት፤ አሁንም አብራችሁኝ ለሆናቹህ ከሰው ማንነት ከፍ ብሎ በማስተዋል ላይ የሚያስብ አእምሮ ባለቤቶች፤ ጥበብን በጥበብነቷ ዳኝታቹህ ከራስ ማንነት ግላዊ ህይወት ጋር ሳታደባልቁ ለምታዩት ለናንተ የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳቹህ።” ብላለች።
በማጠቃለያዋም “ግን ያው የመናገር፣ የመጻፍ የመሳደብም ሆነ ከመጥፎ ነገር ውጪ አእምሯቹህ ማሰብ ለማይችለውም ሁሉ የመሰላችሁትን ነው ያላችሁት። አመሰግናለሁ።” በማለት ምላሿን ሰጥታለች።

No comments:

Post a Comment

wanted officials