ባለፈዉ ሃሙስ ሌሊት፥ አርብ ንጋት ላይ የቴፒ ወህኒ ቤትን ሰብረው ፖሊሶችን ገድለው እስረኛ ያስለቀቁት ታጣቂዎች የፍትህና የነጻነት ጥያቄ አንግበው መነሳታቸውን የእንቅስቃሴው መሪ ካለበት ለኢሳት በሰጠዉ ቃለምልልስ ገልጸ።
ጥቃቱት ተከትሎ በእነሱ ወገን ሁለት ሰዎች መገደላቸዉን ያመነ ሲሆን፥ አንደኛው የንቅናቄው መስራች፥ ሌላኛዉ ሟች ቡድኑን በቅርቡ የተቀላቀለ መሆኑን አመልክቷል።
ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገው የእንቅስቃሴው መሪ፥ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ጥቃቶች ሲፈጽሙ መቆየታቸውን ገልጿል። የመንግስት ሃይሎች በከባድ መሳሪያ ሊያጠፏቸው ሞክረው እንዳልተሳካላቸዉም አብራርቷል።
በህዝብ ላይ የሚደርሰዉ በደልና ምሬት ወደትግል እንደገፋቸው የገለጸዉ ይህ ወጣት፥ አሁን በርካቶች ትግሉን የመቀላቀል ፍላጎት ቢኖራቸዉም የአቅርቦት ችግር ቁጥራቸውን ይበልጥ ለማሳደግ እንዳላስቻላቸው ገልጿል።
አርብ ሊነጋ ሲል በተፈጸመዉ ጥቃት እስር ቤት ሰብረው ከመቶ በላይ እስረኞች ባስለቀቁበት ወቅት፥ የፖሊስ አዛዡን ጨምሮ ሶስት ፖሊሶች መግደላቸውንና መሳሪያ ነጥቀው መሰወራቸውን የአማጺያኑ መሪ ለኢሳት ገልጿል።

Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment