Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 25, 2015

መንግስት አሁንም በእስልምና እምነት ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደቀጠለበት ይገኛል


Shimeles Kemal
<<ሰለፊስቶች ባሉበት ሁሉ ጦርነት፣ሁከት፣ብጥብጥ ይኖራል>> አቶ ሽመልስ ከማል ከተናገሩት! አቡበከር አህመድ መንግስት በእስልምና እምነት ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደቀጠለ ሲሆን ከምርጫ ማግስት በአዳማው ቲታስ ሆቴል በተካሄደውና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴንና በተለይ ምክትላቸው አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት አሁንም በእስልምና እምነት ዘልቆ መግባቱን የሚያስረዱ ንግግሮችን አድርገዋል። አቶ ሬድዋን ሁሴን በዋናነት ሽብርተኝነት በተመለከተ በምዕራባውያን እይታና በኢትዮጵያ መንግስት እይታ መካከል ያለውን ልዩነት አብራርተዋል። ምክትላቸው አቶ ሽመልስ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በእስልምና እምነት ስር ሰለፊዝም በሚባለው አስተምህሮት አማካኝነት ወደሽብር እየገባች እንደሆነ ያስረዱ ሲሆን በንግግራቸውም <<ሰለፊዝም ባለበት ቦታ ሁሉ ጦርነት አለ የሰለፊዝም አስተሳሰብ የሚያራምዱ አካላት ሁሉ ዓለማዊ መንግስት አይቀበሉም በሸሪዓዊ ስርዓት ብቻ ነው የሚያምኑት የሀገርን ህልውና ያፈራርሳሉ ለምሳሌ አይኤስአይኤስ (ISIS) የተባለውም ቡድን ይሄ ነው አላማው በሀገራችንም እነዚህ አካላት እራሳቸውን ማጠናከር ጀምረው እስከሚኖሩበት አከባቢም መነጠል ጀምረዋል ለምሳሌ ኮልፌና አየር ጤና ይሄንን አስተሳሰብ ልንከላከለው ይገባል ከዚህ ቀደም በሀገራችን የነበረው የሱፊዝም እስልምና ተከታዮች ከህብረተሰቡ ጋር አብረው መኖር ይችላሉ። አሁን የዚህ ተከታዮች እየጠፉ ነው አስተማሪዎቻቸውም እንዲጠፉ እየተደረገ ይገኛል ይሄንን አስተምህሮት ልንደግፈው ይገባል ለዚህ ትልቁን ድርሻ እየተወጣ ያለው አንዱ የሰለፊዝም አካል ወሀቢዝም የሚባለው አስተምህሮት ነው። በሀገራችን ከ2004 ጀምሮ የተከሰተው የእምነት ችግር ከዚሁ ጋር ይያያዛል በወቅቱ ለዚህ ተጠያቂዎቹ አሁን በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ ወሀብዮችና ሰለፊስቶች አንድ ናቸው በአካሄድ ብቻ ልዩነት አላቸው እነዚህ አካላት ከዚህ በላይ ከተጠናከሩ እንደ ናይጄሪያ ትልቅ ቀውስ ማስከተላቸው አይቀርም በገንዘብ አቅም በኩል ጎልበተዋል በቴክኖሎጂም ሚፈልጉትን የሚፈፅሙበት ላይ ይገኛሉ>> በማለት በጥቅሉ መንግስት አሁንም በእስልምና ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደሚቀጥል የሚያረጋግጥ ንግግር አድርገዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች የተጠየቁ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ፓሊስ በህግ ስር ታራሚዎችን የሚይዝበት መንገድ አግባብነት፣ የፕሬስ ነፃነትና የመሳሰሉት ይገኙበታል። ምንጭ: ሪፓርተር 

No comments:

Post a Comment

wanted officials