አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ሪፕሪቭ ዘመቻ ጀመረ
ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝ አገር የሚገኘው ሪፕሪቭ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስቲር ዴቪድ ካሜሩን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል። አቶ አንዳርጋቸው ለአንድ ሳምንት መታሰራቸው ረጅም መሆኑ ሳያንስ ለአንድ አመት ታስረው መቆየታቸው ለማሰብም የሚከብድ ነው ሲል የህግ ድጋፍ በመስጠት የሚታወቀው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገልጿል። በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሪፐሪቭ ዌብሳይት በመግባት በፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻው እንዲሳተፉ ጠይቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በግፍ የታሰሩበትን አንደኛ አመት በማስመልከት በቤልቦርን ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
ኢትዮጵያውያኑ የእንግሊዝ መንግስት እስካሁን ጉዳዩን ችላ ማለቱን በመቃወም እና አሁንም አቶ አንዳእጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግ በማሳሳብ የተዘጋጀውን ደብዳቤ ለኢምባሲው ተወካይ ሰጥተዋል።
በጀርመን አገር በዱስልዶርፍ እንዲሁም በሙኒክ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መደረጋቸውን ዘገይቶ የደረሰን ዜና ያመለክታል። በዱስልዶርፍ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞቸውን በእንግሊዝ ቆንስላ ፊት ለፊት አካሂደዋል።

No comments:
Post a Comment