ጋዜጠኛ ዳሪዮስ ሞዲ ከዚህ አለም በሞት ተለየ:-ዳሪዮስ ሞዲ በ1940 ዓ/ም አዲስ አበባ ከተማ ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ ተወለደ:: አባቱ የፓሪሲ (የጥንታዊቷ ኢራን) ደም ያላቸው ህንዳዊያን ተወላጅ ሲሆኑ ለልጃቸው ዳሪዮስ የሚለውን ስም የሠጡት “ዳሪዮስ” የሚባለውን ዝነኛ የፋርስ ንጉሰ ነገስት ለማሥታወስ ነው በዜግነታቸው እንግሊዛዊ የነበሩት እኝህ ሠው የዳሪዮስ አባት የቤተ መንግስት ፎቶ አንሺ ነበሩ:: በሁላ ላይም በሀገራችን የመጀመሪያውን ፎቶ ቤት አራት ኪሎ በሚገኘው የአርመን ቤተክርስቲያን አካባቢ ከፍተዋል:: ዳሪዮስ ለአባቱ ብቸኛ ልጅ ነው በሥተርጅና የተገኘ ልጅ በመሆኑ አባቱ በጣም አቀማጥለው ነው ያሣደጉት ኢትዮዽያዊት የነበረች እናቱ ግን ከዳሪዮስ በሁዋላ ሌላ ሶስት ልጆችን ወልዳለች ዳሪዮስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በሁዋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ገባ ይሁን እንጂ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ዩኒቨርስቲውን ለመሠናበት ተገደደ ለዚህም ያበቃው የተማሪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት የእሱ የቅርብ ጉዋደኛ የነበረው የጥላሁን ግዛው መገደል ነው ዳሪዮስ 1964 በቀድሞው ብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ ተቀጠረ አብዮቱ ሲመጣ ደግሞ ወደ ኢትዮዽያ ሬዲዮ በመዛወር እስከ 1985 ድረስ አገለገለ ከ1985 አጋማሽ በሁዋላ በሀላፊነት ወደ ኢትዮዽያ ዜና አገልግሎት ተወሠደ በዚያ መ/ቤት እስከ 1999 ካገለገለ በሁዋላ ከስስራው በጡረታ ተሰናብቷል ተወዳጁ ጋዜጠኛ ዳሪዮስ ሞዲ ዛሬ ይህችን አለም እስከመጨረሻው ተሠናብቷል ለቤተሠቡ መፅናናትን እንመኛለን!!
No comments:
Post a Comment