Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 6, 2015

በኢትዮጵያና ሱማሊያ ድንበር ውጥረቱ አይሏል * በትናንትና ዛሬ ጠዋት ጦርነት 19 ሰዎች ሞቱ


በኢትዮጵያና ሱማሊያ ድንበር ውጥረቱ አይሏል * በትናንትና ዛሬ ጠዋት ጦርነት 19 ሰዎች ሞቱ


(ዘ-ሐበሻ) 2ኛ ሳምንቱን የያዘውና በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር ባሉ መንደሮች አካባቢ በተነሳ ጦርነት ትናንት ረቡዕ እና ዛሬ ሐሙስ በተደረጉ ውጊያዎች የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ቁስለኛ መሆናቸውን ዘ-ሐበሻ ከስፍራው ያገኘችው መረጃ አመለከተ::



በድንበሩ አካባቢ ትናንትና ዛሬ በ3 መንደሮች አካባቢ 2 ውጊያዎች መደረጋቸውን ያስታወቁት የአካባቢው የዜና ምንጮች በዚህ ውጊያ ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ንብረታቸውን እና ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ በቅተዋል::

በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ባሉት መንደሮች አካባቢ የተነሳው ጦርነት እስካሁን ግልጽ አለመሆናቸውን የሚጠቁሙት የዜና ምንጮች በደፈናው የዘር ግጭት ነው ሲሉት ይገልጹታል:: በዚህ ጦርነት ዙሪያ የሶማሊያም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ለማርገብ ምንም አይነት ንግግር አለማድረጋቸውም ተዘግቧል::

በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር ባሉ መንደሮች ላለፉት ዓመታት በዘር ግጭት የተለያዩ ጦርነቶች ሲደረጉ የቆዩ መሆናቸውን የሚጠቁሙት የዜና ምንጮቹ የኢትዮጵያም ሆነ የሱማሊያ መንግስታት ዜጎቻቸው እየተላለቁባቸው ጉዳዩን በዝምታ ማለፋቸው በጣም አሳፋሪ ነው ብለውታል::በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት ጦሩን ወደዚያ ከማስጠጋት ውጪ ጉዳዩን ለማረጋጋት ያደረገው ይኸ ነው የሚባል ሥራ አለመስራቱ እየተተቸ ነው::

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44038#sthash.8ngkEfa8.dpuf

No comments:

Post a Comment

wanted officials