Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 11, 2015

ዋጋ እየከፈሉ ካሉ ወገኖቻችችን ጎን እንቁም - የሚሊዮኖች ድምጽ

Millions of voices for freedom - UDJ
ዋጋ እየከፈሉ ካሉ ወገኖቻችችን ጎን እንቁም - የሚሊዮኖች ድምጽ
የሰላማዊ ትግል ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል ነው። በዚህ ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን እየታሰሩ ነው። አገዛዙ ለመብት የቆሙትን በሚያስርበት ጊዜ የእስረኞች ቤተሰቦችንም ነው በጭካኔ የሚቀጣው። ልጆቻቸዉን እያስራበ።
የታሰሩ ወገኖቻችን ቁጥር እጅግ በጣም ብዙ በመሆኑ፣ ሁሉንም መደገፍ ባይቻልም፣ ቤተሰቦቻቸው በጣም ችግር ላይ ያሉትን ለመደገፍ፣ በሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር አስተባባሪነት አንዳንድ ስራዎች እየተሠሩ ነው። በመጠኑና በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም፣ የጋዜጠኖች ፣ የመድረክ፣ የሰማያዊ፣ የመኢአድ እና የአንድነት አባላት እስረኞችን ለመደገፍ ተሞክሯል። ይህ ሥራ ቀጣይነት እንዲኖረውና ሌሎች ያልተካተቱ እስረኞችን ለማካታት፣ የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል።
አምስት ሆነን አንድ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ብንሄድ ቢያንስ ከ50 እስከ 100 ዶላር በአንድ ምሽት እናወጣለን። ያ ለአንድ ወር አንድ ቤተሰብ ሊደገፍ ይችላል። በተለይም በዉጭ ያለን ወገኖች አቅሙ አለን። ብዙ ልናደርግ እንችላለን። አቅም ያለው ወገን እያላቸው ለአገርና ለሕዝብ የታገሉ ወገኖቻችን ቤተሰቦች የሚራቡበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይገባም።
በግለሰብ ደረጃ የእስረኞች ቤተሰብን ስፖንሰር ለማድረግ ወይንም ለመደገፍ በሚከተለው ድህረ ገጽ በመሄድ በፔይ ፓል የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል። በሚከተለው የድህረ ገፅ ሊንክ በመሄድ PAYPAL የሚለውን ቢጫ ሳጥን በመጫን ገንዝበ መላክ ይችላሉ።

http://www.finotenetsanet.org/
በቀጥታም ከእስረኞች ቤተሰቦች ጋር በመገናኘት መርዳት ካስፈለገም፣ ሁኔታዉን እንደምናመቻች ለመግልጽ እንወዳለን።በሚከተለው ኤሜል አድራሻ ያሳዉቁን።
millionsforethiopia@gmail.com

No comments:

Post a Comment

wanted officials