Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, June 22, 2015

እነ ወይንሸት ሞላ እንዲፈቱ ተወሰነ

እነ ወይንሸት ሞላ እንዲፈቱ ተወሰነ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ዛሬ ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ቀርበው እንዲፈቱ ተወስኗል፡፡ አቃቤ ህግ እነ ወይንሸት ሞላ አንድ ላይ ሆነው ፈጽመውታል ያለውን ክስ ማስረዳት እንዳልቻለ የገለጸው ፍርድ ቤቱ ከተከሳሾቹ መካከል የኤርሚያስ ፀጋዬ መከላከያ ምስክሮች በቦታው እንዳልነበረ እንዳስረዱ ገልጾ በነጻ እንዲለቀቅ ወስኗል፡፡
የወንይሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ የመከላከያ ምስክሮች ተከሳሾቹ በቦታው እንዳልነበሩና ወንጀሉን እንዳልፈፀሙ አላስረዱም በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ የተከሰሱበት ወንጀል እስከ 6 ወር እንደሚያስቀጣ የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ላይ የሁለት ወር እስር የፈረደባቸው ሲሆን ከሚያዝያ 14/ 2007 ጀምሮ ሁለት ወር ከአንድ ቀን የታሰሩ በመሆኑ ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል፡፡
በሌላ በኩል 3ኛ ተከሳሽ የሆነው ማስተዋል ፈቃዱ ‹‹የተከሰስኩት በፖለቲካ አመለካከቴ ነው›› በማለቱ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ተቃውመሃል በሚል 3 ወር እስራት ፈርዶበታል፡፡ ከሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት ወር በእስር ላይ የቆየ በመሆኑም ለአንድ ወር በእስር እንደሚቆይ ይታመናል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials