Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 25, 2017

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ - “በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ከነፃነት ኃይሎች ጋር የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት የክብር አቀባበል ይደረጋል።"

የአርበኞች ግንቦት 7 ግንባር መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ !!
ለመከላከያ ሰራዊቱ ወሳኝ የሆነ ጥሪ ዳግም አቅርበዋል ።
-
“በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ከነፃነት ኃይሎች ጋር የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት የክብር አቀባበል ይደረጋል።
ሠራዊቱን የሚቀበሉ የሚያስተናግዱ፣ የሚያቋቁሙ ቡድኖችን በየቦታው አደራጅተናል።
ሕዝብ በህወሓት አገዛዝ ላይ እንጂ በአንተ በሠራዊቱ አባል ላይ የያዘው ቂም የለም።
እንዲያውም አንተ ራስህ ትግሉን እንድትቀላቀል ይፈልጋል። በሕዝብና በአገር ላይ በደል ሲፈጽም የኖረው የህወሓት አገዛዝ ፍፃሜ ለማፍጠን በሚደረገው ትግል የአንተ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
በኢትዮጵያችን ውስጥ እንዲኖር የምንፈልገው ሠራዊት ታማኝነቱ ለፓርቲ ሳይሆን ለሀገር የሆነ፤ ድንበሯን ከጠላት የሚከላከል፤ በሀገር ፍቅር ስሜት የነደደ፤ ሕዝብ የሚወደውና የሚያከብረው ሠራዊት ነው ይህ ሠራዊት የሚገነባው በአንተው ነው። .
የህወሓት ወንበዴዎች ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሠራዊቱን የመበተን ዓላማም ሆነ ፍላጎት ያላቸው የነፃነት ኃይሎች የሉም።
እነኝህ ብልሹ መሪዎቹ ተወግደውለት መዋቅሩ እንደተጠበቀ፤ ሹመትና የደሞዝ ጭማሪ በችሎታና ባደረገው አስተዋጽኦ ብቻ እንጂ ለአንድ ድርጅት ባለው ድጋፍ ወይም በዘውግ ማንነቱ ያልሆነ፤ ሙያውና ተጋድሎው ሀገሩን ከጠላት መጠበቅና የህዝቡን ደህንነት ማረጋገጥ የሆነ፤ በተልዕኮ ላይ ቢሰዋ ህዝቡ እንደጀግና የሚቀብረው፤ አካለ ስንኩል ቢሆን ህዝቡ በአክብሮት እስከ እድሜ ልኩ የሚጦረው፤ መለዮ ለብሶ በህዝቡ ውስጥ ሲገኝ ወጣቱ እንደሱ ለመሆን የሚመኘው አኩሪ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆኖ እንዲቀጥል ነው ፍላጎታችን። ይህ ምኞት እንዲሳካ ግን ዛሬ የምትፈጽፈው ተግባር ወሳኝ ነው።
Image may contain: 3 people, outdoor

በአቶ ደመቀ መኮንንና በዶ/ር ደብረጺዮን መካከል የተጀመረው ጥል ወደ ሃይል እርምጃ ተሸጋገረ

በአቶ ደመቀ መኮንንና በዶ/ር ደብረጺዮን መካከል የተጀመረው ጥል ወደ ሃይል እርምጃ ተሸጋገረ
በም/ል ጠ/ሚኒስትርና የብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮንን እና በህወሃቱ ም/ል ሊቀመንበርና የኮሚኒኬሽንና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ያለው አለመግባባት ወደ ሃይል እርምጃ ማምራቱን የኢሳት ምንጮች ገልጻዋል።
ባለፈው ሰኞ አቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በአቶ ደመቀ መኮንን ቢሮ ተገኝተው በነበረበት ወቅት
“ዶ/ር ደብረጺዮን እኔን አያዘኝም ብለህ ለአቶ ሽፈራው ተናግረሃል፣ እንዴት እንዲህ ትላለህ?” ብሎ ዶ/ር ደብረጺዮን ጥያቄ ሲያቀርብ፣
አቶ ደመቀም፣ “ አዎ ብያለሁ። እኔ እኮ ም/ል ጠ/ሚኒስትር ነኝ፣ መዋቅሩን አታውቀውም እንዴ? ” በማለት መልስ ሲሰጠው ፣ ጭቅጭቁና ንትረኩ እየጨመረ መምጣቱን ፣ በመሃሉ ዶ/ር ደብረጺዮን በስሜት ሆኖ ከመቀመጫው ተነስቶ በአቶ ደመቀ ላይ እጁን መሰንዘሩን ፣ አቶ ደመቀም ራሱን ለመከላከልና መልሶ ለማጥቃት ሲሞክር አቶ በረከትና አቶ ሽፈራው መሃል ላይ በመግባት መገላገላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
በዶ/ር ደብረጺዮን ድርጊት የተበሳጨው አቶ ደመቀ “ አሁንም፣ ወደፊትም አንተ አዘኸኝ የምሰራው ምንም ስራ የለም፣ አይኖርምም ” በማለት ደጋግሞ የተናገረ ሲሆን ፣ እነ አቶ በረከት ገላግለው ሁለቱ ባለስልጣናት እንዲለያዩ አድርገዋል።
የህወሃት እና የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ግጭት በህወሃትና በብአዴን መካከለኛ አመራሮች መካከል የሚታየው ልዩነት ወደ ከፍተኛ ባለስልጣናቱም እየተሸጋገረ መምጣቱን የሚያመላክት ተደርጎ ተወስዷል።

አውሮፓውያን በኤርትራ ላይ የያዙትን አቋም ማለሳለስ መጀመራቸው ህወሃትን ስጋት ላይ ጥሎታል

አውሮፓውያን በኤርትራ ላይ የያዙትን አቋም ማለሳለስ መጀመራቸው ህወሃትን ስጋት ላይ ጥሎታል
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 19/2009)
ከባድመ ጦርነት ጋር በተያያዘም ይሁን የኢትዮጵያን የነጻነት ሃይሎች ትደግፋለች በሚል ምክንያት ህወሃት በብቸኝነት የያዘው የኤርትራ ፖሊሲ እየከሸፈበት መምጣቱ ግራ እንዳጋባው በኒዮርክ የኢትዮጵያ የተመድ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚሰሩ ምንጮቻችን የላኩን መረጃና ሰነድ ማስረጃዎች ያመለክታሉ።
የሌሎችን ብሄር ተወላጆች ባለማመን በህወሃቱ አባልና በቀድሞው የአለማቀፍ ድርጅቶች ዳይሬክተር ጄኔራል በአዲሱ ሹመታቸው የሱዳን አምባሳደር በሆኑት አቶ ሙሉጌታ ዘውዴ እና በጥቂት የህወሃት ባለስልጣናትና ምሁራን የተረቀቀው የኤርትራ ባለስልጣናትን በአለማቀፍ ፍርድ ቤት የማቆም እንዲሁም በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የሚቀጥልበትንና አጠቃላይ አለማቀፉ ማህበረሰብ በኤርትራ ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንዲያጠናክር የተነደፈው ፖሊሲ ውጤት አልባ እየሆነ ነው።
ለፖሊሲው መክሸፍ ደግሞ ህወሃት በተለይ የተወሰኑ አውሮፓ አገራትን ተጠያቂ እያደረገ ነው። ጄኔቭ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኔ፣ 2008 ዓም በኤርትራ የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን የቀረበው ምክረ ሃሳብ ተግባራዊ እንዲሆን ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ ዘመቻ ያካሄደው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት፣ ከአውሮፓ አገራት ውስጥ ኖርዌይ፣ ጀርመንና ስዊዘርላንድ ከኤርትራ ጋር ስደተኞችን በተመለከተ በጋራ መስራት በመጀመራቸው የአውሮፓ ህብረት ቀደም ብሎ የያዘውን አቋም እንዲያለሰልስ ግፊት ማድረጋቸው ራስ ምታት ሆኖበታል። የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ በኤርትራ ውስጥ የሚሰሩ ባለሀብቶች የኤርትራውያንን ጉልበት እንደሚበዘብዙ ያወጣው ሪፖርት እንዲሁም ግለሰቦኡ በቡድንም ሆነ በተናጠል ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ ያስቀመጠው ምክረ ሃሳብ የአውሮፓ ህብረት አባላትን ባለማስደሰቱ ፣ ህብረቱ በኤርትራ ላይ በሚወሰደው እርምጃ ላይ የተቀዛቀዘ ስሜት እንዲይዝ እያደረገው ነው።
ከአውሮፓ አገራት በተጨማሪ የአረብ አገራት፣ ቻይና እንዲሁም የተወሰኑ የላቲን አሜሪካ አገራት፣ ከአፍሪካ ግብጽ እና በከፊል ሱዳን ለኤርትራ ድጋፍ በመስጠት በምክር ቤቱ ውስጥ ጉዳዩ እንዲቀዛቀዝ ማድረጋቸው የህወሃትን ባለስልጣናት በእጅጉ አስቆጥቷል።
ህወሃት መራሹ መንግስት በዚህ አመት ጅቡቲና ሶማሊያን በተዘዋዋሪ መንገድ በመጠቀምና ለእነሱ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ተመድ በኤርትራ ላይ ጠንካራ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም። ይህንን የ2017 የተመድ የውሳኔ ሃሳብ የደገፉት አገራት ኔዘርላንድስ ፣ ክሮሺያ፣ ቤልጂየም፣ ኦስትሪያ፣ ካናዳ ፣ ፖላንድ፣ ግሪክ፣ አየርላንድ እና ሮማኒያ ብቻ ሲሆኑ፣ ተመድ በ2016 ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ከደገፉት አገራት ጋር ሲነጻጻር በእጅጉ አንሶ ተገኝቷል። በ2016 በተላለፈው ውሳኔ 2 ዋና ስፖንሰሮችና 19 ተባባሪ ስፖንሰሮች የነበሩ ሲሆን፣ በ2015 ውሳኔ ደግሞ 7 ዋና ስፖንሰሮችና 16 ተባባሪ ስፖንሰሮች ነበሩ። በአጠቃላይ የአለም አገራት በተለይም አውሮፓውያን በኤርትራ ላይ የያዙትን አቋም እያለሳለሱ መምጣታቸውን የሚያሳይ ሲሆን፣ በዚህ የተበሳጨው ህወሃት ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ህብረት በመውሰድና የአፍሪካ ህብረት የኤርትራ መንግስት ተጠያቂ የሚሆንበትን አሰራር ለመንደፍ ላይ ታች እያለ ነው።
የህወሃት ዋና ግብ የኤርትራ ጉዳይ ወደ ተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ተመርቶ ከዚያም ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ( ICC) እንዲሄድ በማድረግ የኤርትራ ባለስልጣናት በወንጀል ተጠያቄ እንዲሆኑ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር አብረው ይሰራሉ በሚላቸው የኢትዮጰያን ተቃዋሚ ሃይሎች ላይ እርምጃ ማስወሰድ ነው።
ህወሃት የአውሮፓ አገራት የያዙትን አቋም መልሰው እንዲቀይሩ አሁንም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።

ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እስከ ሰኞ ድረስ እንደማይሰሩ አስታውቀዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እስከ ሰኞ ድረስ እንደማይሰሩ አስታውቀዋል። 
ከአዲስ አበባ ወደ አራቱም የአገሪቱ ማዕዘናት የሚደረገው የትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ጉዞቸውን እንዲሰርዙ ተገደዋል። ለስራ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ የሄዱና መመለስ ያልቻሉ የመንግስት ሰራተኞች በአዲስ አበባ ለሚቆዩባቸው ለ5 ቀናት ወጪ መሸፈኛ የሚሆን አበል መስሪያ ቤቶቻቸውን እየጠየቁ ነው።
Image may contain: sky, outdoor and nature

ህዝብ የጠራውን አድማ ጥሶ ሲሄድ የነበረ የአንበሳ አውቶብስ ከጋራ ሙላታ ወደ ጅጅጋ ስጓዝ የነበረ መኪና

Image may contain: outdoor and nature
 ከጋራ ሙላታ ወደ ጅጅጋ ስጓዝ የነበረ መኪና አወዳይ ከተማ ላይ ቄሮዎች በወሰዱበት እርምጃ ደንግጦ ሹፌሩ ልያመልጥ ሲሮጥ መንገድ ስቶ የሰው ቤት ደርምሶ ገብቶል። ሹፌሩም ክፉኛ ተጎድቷል።
Image may contain: plant, outdoor and nature
አብዛኛው የኦሮምያ አከባቢ አድማውን ጀምሯል ።
ከትራንስፖርት ጀምሮ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ሱቆችን ጨምሮ ዝግ ሆነዋል !!
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዚህ አድማ ተሳታፊ ሊሆን ይገባል !!
ህዝብ ያሸንፋል ወያኔ ይወድቃል ትግሉ እስከ ምኒሊክ ቤተ መንግስት ዳጃፍ ድረስ ይቀጥላል ።
Holota ህዝብ የጠራውን አድማ ጥሶ ሲሄድ የነበረ የአንበሳ አውቶብስ ለነጻነታቸው በሚታገሉ ቆራጥ የኦሮሞ ልጆች ጥቃት ደርሶበታል !!

በሩሲያ ሶሺ ባህር ዳርቻ ላይ 12 ዶልፊኖች ያመጡት እመቤታችንን_ስዕለ_አድኅኖ



በሩሲያ ሶሺ ባህር ዳርቻ ላይ ይዝናኑ የነበሩ ባልና ሚስት 12 ዶልፊኖች ከባህሩ ውስጥ አንድ ነገር ተሸክመው አምጥተው ባህሩ ዳር ላይ አስቀምጠውት ሲመለሱ ይመለከታሉ።
ሚስትም ባሏን ባክህ ምን እንደሆነ እንየው ትለዋለች ባልየውም እሺ በማለት ወደ ዛ ከባህር ወደወጣው ሄደው ሲመልከቱት አራት መዓዘን የሆን በጭቃ የተሸፈነ ነገር ነበር
ጭቃውን ሲያራግፉት ግን ያዩትን ነገር ማመን ከበዳቸው በጣምም ተገረሙ። ለካስ እነዛ ግዑዝን ፍጥረታት 12 ሆነው ተሸክመው ያመጡት #የእመቤታችንን_ስዕለ_አድኅኖ_ኖሯል
ሰዎቹም ስዕሉን ለሩስያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ ቄርሎስ( Kirill) ለማስረረከብ ወደ ዋና ከተማዋ ሞስኮ አምርተዋል ተብሏል።
ኦ ሰአሪተ መርገሙ ለአዳም እግዝእትነ ማርያም ሰአሊ ለነ ሀበ እግዚእነ ወመድኅኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ያጽንአነ በርትዕት ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ውስተ አሚነ ዚአሁ ወዘአቡሁ ወዘቅዱስ መንፈሱ አሜን!!!Image may contain: 1 person

በመላ ኦሮሚያ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።

በመላ ኦሮሚያ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
ሱቆቹ ፣ የገበያ ማዕከሎች፣ መደብሮች ፣ የግል የንግድ ባንኮች ሁሉም ዝግ ናቸው። ምንም አይነት የትራንስፓርት እንቅስቃሴ የለም ማንኛውም ተሽከርካሪ ቁሟል።
ወደ ኦሮሚያ የሚገቡ ሆነ የሚያልፉ ፣ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱ ተሽከርካሪወች በወታደራዊ አጀብ ማለፋ ያልቻሉት በየመንገዱ ቁመው ምሽቱን እየጠበቁ ይገኛል።
አባይን ተሻግሮ ያሉ የአማራ ከተሞች በሁለት አበይት አቅጣጫወች የነፃነት ትግሉን ለመቀላቀል ተዘጋጂተዋል። ምንም አይነት የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የማይችለው እብሪተኛው የህውሓት ወያኔ ቡድን በህዝባዊ አመፅ እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ስርዓቱን የቆመበትን የህዝብ ጭንቃ ላይ ለማውረድ ማሽመድመድ እንደሚቻላ በጥቂት አመት ውስጥ ያየነው እውነት ነው። የወያኔ አምባገነን ስርዓት ለኢትዩጲያ ህዝብ አያስፈልግም። የስርዓት ለውጥ ይፈልጋል ይሄም በተግባር እምቢ በማለት ከአፈሙዝ ታጣቂወች ጋር እየተፋለመ ይገኛል ። እጂግ ብዙ ምክንያቶች የስራ ማቆም አድማ እንድናደርግ በቂ ናቸው።
እንዳጠቃላይ የስርዓቱን እድሜ ለማሳጠር ሁሉም በጋራ እንዲነሳ ዛሬም ባለመሰልቸት የትግላችን አካል እንሁን።
ነፃነት በነፃ አይገኝም !!
አንድነት ለአንድ ወያኔ ጠላት!!

Thursday, August 17, 2017

ሕወሃት የአፓርታይድ ስርአትን በኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገ ነው ተባለ


ESAT
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስልጣኑን የያዘው የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ/ሕወሃት/ቡድን የአፓርታይድ ስርአትን በመገልበጥና በኢትዮጵያ ተግባራዊ በማድረግ ኢትዮጵያውያንን እየጨቆነና እየመዘበረ መሆኑን አንድ አሜሪካዊ የሕዝባዊ ንቅናቄ ኤክስፐርት ገለጹ።
አሜሪካዊው ኢኮኖሚስትና የህዝባዊ ንቅናቄ ኤክስፐርት ዴቪድ ስቴማን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ የአፓርታይድ ስርአት በሚገባ ተጠንቶ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ብዙሃኑ እየተገፋ መሆኑን ተናግረዋል።
አሜሪካዊው ኢኮኖሚስትና የህዝባዊ ንቅናቄ ኤክስፐርት ዴቪድ ስቴማን ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አናሳዎች የፖለቲካ ስልጣን ሲይዙ የብዙሃኑን ሀብት በመበዝበዝ ስራ ላይ ይጠመዳሉ ሲሉ ነው የተናገሩት።
በዚህ ረገድ የደቡብ አፍሪካን አፓርታይድ ስርአት ከኢትዮጵያው የሕወሃት አገዛዝ ጋር በማነጻጸርም ተመልክተውታል።በደቡብ አፍሪካ የነጮች የአናሳ አገዛዝ ከብዙሃኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊ ላይ የሚፈጽመውን ዘረፋ ፍትሃዊ ተግባር እንደሆነ ለማሳየት ያደረገው ጥረት በኢትዮጵያ ሲደገም መታየቱ የአጋጣሚ ጉዳይ አይመስለኝም ያሉት አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት ዴቪድ ስቲማን የአፓርታይድ ስርአት በሚገባ ተጠንቶ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ብዙሃኑ እየተገፋ መሆኑን አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ እየታየ ነው በሚባለው የኢኮኖሚ እድገት ላይ ጥያቄ ያነሱትና ይልቁንም የሀገሪቱ መሪዎች በዘረፋ ላይ መጠመዳቸውን ያወሱት ኢኮኖሚስቱ ዴቪድ ስቴማን የኢኮኖሚ እድገት ከፖለቲካ ምህዳሩ ጤናማነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ አስረድተዋል።
ሰብአዊ መብት በማይከበርበትና የህግ የበላይነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገት እንደማይኖር ተናግረዋል።
የሕወሃት ሰዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት መጨረሻው አስከፊ እንደሚሆንም አሳስበዋል።
ለዚህ ችግር ግንባር ቀደሙ ተጣያቂ ሟቹ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ናቸው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዲሞክራሲና የህግ የበላይነትን አሰፍናለሁ ብሎ ቃል ገብቶ ዘራፊና ጨቋኝ ስርአት ጥሎ ሔዷል በማለት መለስ ዜናዊን ተጠያቂ አድርገዋል።
ታማኝ የመረጃ ምንጮችን ዋቢ በማድረግም የሀገሪቱ መሪዎች ወደ 30 ቢሊየን ዶላር መዝረፋቸውን የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሀብት ደግሞ 3 ቢሊየን ዶላር መድረሱን አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት ገልጸዋል።
ሴሌብሪቲ ኔት ዎርዝ የአቶ መለስ ዜናዊ ሀብት 3 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ሲገልጽም የተጠኑ የምርመራ ዘዴዎችንና የታመኑ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ነው።

Wednesday, August 16, 2017

በዶ/ር ደብረጺዮንና ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን መደባደባቸው ተነገረ






በም/ል ጠ/ሚኒስትርና የብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮንን እና በህወሃቱ ም/ል ሊቀመንበርና የኮሚኒኬሽንና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ያለው አለመግባባት ወደ ሃይል እርምጃ ማምራቱን የኢሳት ምንጮች ገልጻዋል።

ባለፈው ሰኞ አቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በአቶ ደመቀ መኮንን ቢሮ ተገኝተው በነበረበት ወቅት፣ “ዶ/ር ደብረጺዮን እኔን አያዘኝም ብለህ ለአቶ ሽፈራው ተናግረሃል፣ እንዴት እንዲህ ትላለህ?” ብሎ ዶ/ር ደብረጺዮን ጥያቄ ሲያቀርብ፣ አቶ ደመቀም፣ “ አዎ ብያለሁ።

እኔ እኮ ም/ል ጠ/ሚኒስትር ነኝ፣ መዋቅሩን አታውቀውም እንዴ? ” በማለት መልስ ሲሰጠው፣ ጭቅጭቁና ንትረኩ እየጨመረ መምጣቱን፣ በመሃሉ ዶ/ር ደብረጺዮን በስሜት ሆኖ ከመቀመጫው ተነስቶ በአቶ ደመቀ ላይ እጁን መሰንዘሩን፣ አቶ ደመቀም ራሱን ለመከላከልና መልሶ ለማጥቃት ሲሞክር አቶ በረከትና አቶ ሽፈራው መሃል ላይ በመግባት መገላገላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።


በዶ/ር ደብረጺዮን ድርጊት የተበሳጨው አቶ ደመቀ “ አሁንም፣ ወደፊትም አንተ አዘኸኝ የምሰራው ምንም ስራ የለም፣ አይኖርምም” በማለት ደጋግሞ የተናገረ ሲሆን፣ እነ አቶ በረከት ገላግለው ሁለቱ ባለስልጣናት እንዲለያዩ አድርገዋል።

የህወሃት እና የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ግጭት በህወሃትና በብአዴን መካከለኛ አመራሮች መካከል የሚታየው ልዩነት ወደ ከፍተኛ ባለስልጣናቱም እየተሸጋገረ መምጣቱን የሚያመላክት ተደርጎ ተወስዷል።

Ethiopia: Court denies bail to Bekele Gerba


ESAT News (August 10, 2017)
The 4th criminal bench of the federal high court in Addis Ababa on Thursday denied bail to a prominent Ethiopian opposition leader while the 2nd bench gave additional time to police investigating the cases of individuals accused of corruption.
Bekele Gerba, first secretary general of the Oromo Federalist Congress was initially accused of terrorism but the charges were later reduced to criminal offences. As soon as the charges were reduced, Gerba’s lawyers requested bail for their client. The court in today’s session rejected the request saying Gerba “could incite violence” if released. Gerba, among other charges, was accused of igniting the unrest in the Oromo region last year.
Gerba responded to the court saying he expected no justice from the court and that he was not surprised at all. Gerba said that was not the first time an Ethiopian court made such a decision.
Bekele Gerba a linguist who taught at the Addis Ababa University for nearly three decades is also a vocal opposition figure in Ethiopia. Gerba had previously served 4 years on trumped up charges of terrorism. No sooner had he been released upon serving his four years sentence than he was arrested again in December 2016.
Meanwhile the 2nd bench of the court gave police additional 14 days in the case 16 individuals recently detained on suspicion of high level corruption. The individuals, including the former bosses of the Addis Ababa Roads Authority, were arrested a week ago as part of the crackdown against corruption by the regime. Critics say the campaign has left untouched high level officials who are accused of squandering billions of dollars.

Tuesday, August 15, 2017

American expert accuses TPLF of reviving apartheid in Ethiopia, embezzling billions of dollars


David Steinman
ESAT News (August 9, 2017)
An American economist and civil resistance expert has accused the TPLF of copying the policies of the defunct apartheid regime in South Africa to oppress and exploit the poor people of Ethiopia.
In an exclusive interview with ESAT, David Steinman, who advises pro-democracy movements around the world, said the minority regime is draining all the economic resources away from the majority.
He claims that there is a good reason to conclude that Zenawi embezzled over $3 billion during his reign of terror. He mentioned Celebrity Net Worth as a pretty accurate source that uses financial investigative methods before arriving at such a conclusion.
According to him, there is ample evidence that shows that the TPLF regime has embezzled over 30 billion US dollars. The Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT) is a major force in the massive scale looting of Ethiopia, according to Steinman.
According to Steinman, the structure of apartheid was deliberately revised and imposed in Ethiopia. “This doesn’t appear coincidence to me,” he said.
“In South Africa apartheid was used to justify the exploitation of the majority by minority whites. I don’t think it is a coincidence that you see in Ethiopia the exact same dynamic. You have a small ethnic minority that is pushing on other people this ethnic tribalism,” he said.
He noted that there is already a history going back the last 26 years of ethnicity being disastrous for Ethiopia. “The signs are that it is not going to get any better. I think Africa has already experienced the struggle to get rid of one apartheid regime. Another apartheid regime does not strike me as exactly one that Africa needs at this point in history.”
He also claimed that the economic development that the TPLF is trying to promote is fake as the major beneficiaries of any economic gains are corrupt TPLF officials and their cronies. He argued that there is a direct connection between economic development and enabling political environments such as respect for human rights, rule of law and human rights.
“Ethiopian can only prosper by the efforts of millions of Ethiopians aspiring to improve their own life. The power of the individual must be unleashed in Ethiopia.”
Steiman further pointed out that the domination of the economy and political space by the TPLF is dangerous that will only end up in disaster. He blamed former tyrant Meles Zenawi for instituting such a corrupt and oppressive regime after promises to bring about justice, rule of law and democracy.
Steinman urged Ethiopians to unify against the TPLF regime which is using ethnicity as a tool of implementing its divide and rule policy.

INSIGHT’s interview with David Steinman [Full]

160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመን ባህር ውስጥ በግዴታ መወርወራቸው ተሰማ


160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመን ባህር ውስጥ በግዴታ መወርወራቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይ ኦ ኤም አስታወቀ።
ድርጊቱ የተፈጸመው በግዴታ ወደ ባህር ከተወረወሩት ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን ስደተኞች 50 ዎቹ መሞታቸው በተነገረ በ24 ሰአት ጊዜ ውስጥ ነው።
ተቋሙ እንዲህ አይነቱ ድርጊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊገታና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በተሰማሩት አካላት ላይም በተግባር የተደገፈ ርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲል አስጠንቅቋል።
እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይ ኦ ኤም መረጃ ከሆነ በየመን የባህር ዳርቻ ሻብዋ በሁለት ቀናት ብቻ 280 ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን ስደተኞች በግዴታ ወደ ባህር ተወርውረዋል።
160 የሚሆኑት ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል።
የነዚህ ኢትዮጵያውን ወደ ባህር መወርወር የተሰማው ደግሞ ከ24 ሰአት በፊት ወደ ባህር በግዴታ ከተወረወሩት 120 ስደተኞች የ50ዎቹ ህይወት ማለፉ ከተሰማ በኋላ ነው።
ወደ ባህር ከተወረወሩት 160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችም የ2 ወንዶችና የ4 ሴቶች አስከሬን መገኘቱን ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።
እስካሁን 13 ኢትዮጵያውያን የደረሱበት አልታወቀም።በህይወት ለተረፉት 57 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችም አስቸኳይ የህክምናና የምግብ እርዳታ በማድረግ ላይ ይገኛል።
እንደ መረጃው ከሆነ ከ24 ሰአት በፊት ወደ ባህር የተወረወሩትን ስደተኞች ጨምሮ 84 ስደተኞች የተቋሙ ሰራተኞች ወደ ስፍራው ከመድረሳቸው በፊት ባህር ዳርቻውን ጥለው መሄዳቸው ታውቋል።እጣ ፋንታቸው ምን እንደሆነ ባይታወቅም እንኳን ብሏል ተቋሙ።
በሁለት ቀናቱ አሳዛኛና ሰብአዊነት በጎደለው ድርጊት ህይወታቸውን ያጡ ስደተኞች ቁጥር 70 ደርሷል ያላል ሪፖርቱ።ምናልባትም ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ ይችላል በማለት።
በህይወት የተረፉት ሰደተኞችም አሰቃቂ የሚባልውን ጉዟቸውን ለተቋሙ ሰራተኞች በዝርዝር ነግረዋቸዋል።
እንደነሱ አባባል ከሆነም አንድም ስደተኛ ወደ ጀልባዋ ከገባ በኋላ መንቀሳቀስ የሚባል ነገር አይፈቀድለትም።
በጉዟቸው ወቅት አንዳንድ ችግሮች ቢፈጠሩና ስደተኞቹ ሮጠው አልያም በዋና ሊያመልጡ ቢሞክሩ በሚል እጃቸውና እግራቸው በህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ እንደሚታሰርም ይናገራሉ።
ይሄ ሁሉ ሆኖ ደግሞ ከመካከለቻው በድንገት አንዱ ለመንቀሳቀስ ቢሞክር ከፋ ያለ ዱላ አልያም ህይወቱን እስከማጣት ሊደርስ ይችላል።
ከ24 እስከ 36 ሰአታትን በሚፈጀው የባህር ላይ ጉዞም በቂ የሚባል ምግብም ሆነ ውሃ እንዲወስዱ አይፈቀድላቸውም።
በህይወት የተረፉት ስደተኞች ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ በባህር ዳርቻው ያለው የጸጥታ ሃይል በቁጥጥር ስር ያውለናል በሚል ፍራቻ በግዴታ ወደ ባህር እንደወረወሯቸው ይናገራሉ።
በሻብዋ የአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይ ኦ ኤም የአደጋ መከላከል ኦፊሰር ሊና ኮሳ ይሄ ድርጊት በፍጹም ሊገታ ይገባል ይላሉ።
የእነዚህ ታዳጊዎችን ህይወት ልንታደግ ይገባል።መመሪያ በማስቀመጥ ሳይሆን በድርጊት በማሳየት ጭምር ይላሉ ሊና ኮሳ።
የህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሰንሰለት መበጣጠ ቅድሚያ የሚሰጠው ተገባር ነው ሲሉም አሳስበዋል።
እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ በተያዘው የፈረንጆቹ 2017 ብቻ በየመን የባህር ዳርቻ 114 ስደተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል።

Monday, August 14, 2017

በኢትዮጵያ 16 የጥጥ እርሻ ልማት ድርጅቶች ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ተጭበረበርን አሉ


(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009) 
በኢትዮጵያ 16 የጥጥ እርሻ ልማት ድርጅቶች በአንድ የቱርክ ኩባንያ ከ21 ሚሊየን ብር በላይ መጭበርበራቸውን አመለከቱ።
የጥጥ ልማት ድርጅቶቹ በደረቅ ቼክ የተጭበረበሩት ኤልሴ አዲስ በተባለ የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ነው።
የቱርኩን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኩባንያው ባለቤት 1 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ብር ተበድሮ መጥፋቱን አስታውቋል።
ኢትዮጵያውያኑ የጥጥ አምራቾች በጠራራ ጸሃይ በኢንቨስትመንት ስም በመጣ የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ 21 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በደረቅ ቼክ ተጭበርብረናል ይላሉ።
ፋብሪካው የጥጥ ምርታቸውን ከገዛ በኋላ በምትኩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደረቅ ቼክ ሰጥቶአቸዋል።
ወደ ባንኩ ብሩን ለማምጣት ሲሄዱ ግን የተባለው ገንዘብ አለመኖሩ ተነግሯቸዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በበኩሉ ኤልሴ አዲስ የተባለው የቱርክ ኩባንያ ባለቤት 1 ቢሊየን የሚጠጋ ብር ተበድሮ ከሀገር መሰወሩን ይፋ አድርጓል።
እናም ባንኩ ፋብሪካውን ወርሶ ለመሸጥ ቢሞክርም ገዢ ማጣቱን ነው የገለጸው።
በደረቅ ቼክ የተጭበረበሩት የጥጥ አምራች ባለቤቶች ልማት ባንክ ፋብሪካውን እያስተዳደረ ስለሆነ ገንዘባችን ሊከፈለን ይገባል ይላሉ።
ባንኩ ግን ፋብሪካው 800 ሚሊየን ቢሸጥ እንኳ ከቱርኩ ባለሃብት የምፈልገው 1መቶ ሚሊየን ብር ይቀረኛል በማለት የጥጥ አምራቾቹን ጥያቄ ለመመለስ እንደማይችል ገልጿል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ልማት ባንክ በብድር አመላለስ አሰራሩ ላይ በመያዣ ላይ ከመወሰን ይልቅ ክትትል ማድረግም ይኖርበታል።
ባለሃብቱ ገንዘብ ሳይኖረው ለምን የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠው ለሚለው ግን ምላሽ አልሰጡም።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከቱርኩ ባለሃብት የባከነበት ገንዘብ እንዳለ ሆኖ በተያዘው የበጀት አመት የተበላሸ ብድር ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የመንግስት ፋይናንስ ኤጀንሲ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ኤጀንሲው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበላሸ ብድር ከ5 እስከ 10 በመቶ መብለጥ ባይኖርበትም 25 በመቶ መድረሱ እጅግ የሚያሳስብ ሆኗል።
የተበላሸ ብድር ከተባሉት ደግሞ ኢፈርትና የህወሃት ድርጅቶች ወስደው ያልመለሱት እንደሚበዛ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ።

አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ አምስት አምባሳደሮች ወደ ሀገር ቤት ተጠሩ


(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009)አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ አምስት አምባሳደሮች ወደ ሀገር ቤት መጠራታቸው ተዘገበ።
በተጠሩት አምባሳደሮች ምትክ አዳዲስ ግለሰቦች እንደሚሾሙም ተመልክቷል።
በማይታወቅ የገንዘብ ምንጭ በተለያዩ የንግድ ተቋማት ውስጥ ባለድርሻ መሆናቸው የሚገለጸው አምባሳደር ግርማ ብሩ የጸረ መስናው ዘመቻ እስኪያቆም በሕክምና አሳበው ሊዘገዩ እንደሚችሉም የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ።
በዩ ኤስ አሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ከአቶ ግርማ ብሩ በተጨማሪ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ስዩም መስፍን በተመሳሳይ ወደ አዲስ አበባ ተጠርተዋል።
ሪፖርተር የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሁለቱ ነባር የኢህአዴግ አባላት በተጨማሪ በቤልጂየም፣በፈረንሳይና በአየርላንድ በአምባሳደርነት የሚያገለግሉት አቶ ተሾመ ቶጋ፣አቶ ነጋ ጸጋዬና አቶ ሬድዋን ሁሴን በተመሳሳይ ወደ ሀገር ቤት ተጠርተዋል።
የተጠሩትን አምባሳደሮች የሚተኩ ሌሎች አምባሳደሮች ሐምሌ 19/2009 መመረጣቸውና መሾማቸውም ይታወሳል።
ላለፉት 6 አመታት በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን የሕወሃቱን አቶ ስዩም መስፍንን የሚተኩት ሌላው የሕወሃት ታጋይ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ።
ላለፉት 26 አመታት በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደርነት ቦታን ከሕወሃት ሰዎች ውጪ ለሌሎች የማይሰጥበት ምክንያት እንቆቅልሽ ሆኖ ቀጥሏል።
ከአቶ ስዩም መስፍን በፊት የሕዋሃቶቹ አቶ ሃይለኪሮስ ገሰሰ ነበሩ።ከርሳቸው በፊት ደግሞ ዶክተር አዲስአለም ባሌማ በአምባሳደርነት ቆይተዋል።
በዩ ኤስ አሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ብሩን የሚተኩት የብአዴኑ አቶ ካሳ ተክለብርሃን መሆናቸውን የሚገልጹት ምንጮች የተነሱት አምባሳደሮች ወዴት እንደሚወሰዱ በዝርዝር ያስታወቁት ነገር የለም።ነገር ግን በሚኒስትር ደረጃ የሚሾሙ እንደሚኖሩ ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ከፈረንሳይ ፣ቤልጂየምና አየርላንድ የተነሱት አቶ ተሾመ ቶጋ፣አቶ ነጋ ጸጋዬና አቶ ሬድዋን ሁሴን በመጪው ጥቅምት የሚኒስትርነት ቦታ እንደሚሰጣቸው ሲገመት አቶ ስዩም መስፍን ከጤና ጋር ተያይዞ በጡረታ እንደሚገለሉ ይጠበቃል።
አምባሳደር ግርማ ብሩ በአቶ አባይ ጸሃዬ ወደሚመራው የፖሊሲ ምርምርና ጥናት ተቋም ውስጥ ይመደባሉ የሚል እምነት እንዳለም መረጃው አመልክቷል።
አሁን በሙስና ስም ተጠርጣሪ ሌቦችን የማሰሩ ርምጃ ከቀጠለ ከልዩ ልዩ ተቋማት፣ፋብሪካዎችና ህንጻዎች ጋር በተያያዘ ስማቸው የሚነሳው አቶ ግርማ ብሩ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸው አጠራጣሪ ሆኗል።
ሁኔታዎች እስኪረጋጉ በሕክምና ሰበብ አሜሪካ ሊቆዩ እንደሚችሉ ይጠበቃል።

Sunday, August 13, 2017

About 180 migrants forced from boat, a day after 50 Somalis, Ethiopians drowned by smugglers


IOM staff tend to the remains of a deceased migrant on a beach in Yemen. Photo: UN Migration Agency (IOM) 2017
ESAT News 
Another 180 migrants were forced from a boat today, a day after 50 Somalis and Ethiopians were drowned by smugglers off the coast of Yemen, the International Organization for Migration (IOM) said in a statement Thursday.
“Up to 180 migrants are reported to have been forced from a boat by smugglers off the coast of Yemen. Five bodies have been recovered so far and around 50 are reported missing. This latest incident comes barely 24 hours after smugglers forced more than 120 Somali and Ethiopian migrants into the sea as they approached the coast of Shabwa, a Yemeni Governorate along the Arabian Sea resulting in the drowning of around 50 migrants,” said the statement from the IOM
The migrants had been hoping to reach countries in the Gulf via war-torn Yemen, the IOM further said.
The staff from the IOM also found shallow graves of 29 migrants on a beach in Shabwa, during a routine patrol. The dead had been quickly buried by those who survived the smuggler’s deadly actions, according to the Organization.
The approximate average age of the passengers on the boat was 16.
“The survivors told our colleagues on the beach that the smuggler pushed them to the sea, when he saw some ‘authority types’ near the coast,” explained Laurent de Boeck, the IOM Yemen Chief of Mission. “They also told us that the smuggler has already returned to Somalia to continue his business and pick up more migrants to bring to Yemen on the same route. This is shocking and inhumane. The suffering of migrants on this migration route is enormous. Too many young people pay smugglers with the false hope of a better future,” de Boeck further said.
Since January 2017 to date, the IOM estimated that around 55,000 migrants left the Horn of Africa to come to Yemen, most with the aim of trying to find better opportunities in the Gulf countries. More than 30,000 of those migrants are under the age of 18 from Somalia and Ethiopia, while a third are estimated to be female.

በባህር ዳር ከደረሰው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ በመንግስት ዘጋቢ ፊልም በመዘጋጀት ላይ መሆኑ ታወቀ


(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009) 
ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር ከደረሰው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ በመንግስት በኩል ዘጋቢ ፊልም በመዘጋጀት ላይ መሆኑ ታወቀ።
ቦምቡን ያፈነዱትና በቁጥጥር ስር የሚገኙት ተጠርጣሪዎች ከደቡብ ጎንደር ዕብናት የመጡ ናቸው የሚል መልዕክት የሚያስተላልፈው ዘጋቢ ፊልም ቀረጻው እየተካሄደ ሲሆን በቅርቡ እንደሚለቀቅ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የግብር ጭማሪውን በመቃወም በምስራቅ ጎጃም በተለያዩ ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ መቀጠሉ ታውቋል።
በባህርዳር ከ100 በላይ የባጃጅ ታክሲዎች ታስረዋል። በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሀረርጌ፡ በቄሌም ወለጋ፡ በጊምቢ ሱቆች ተዘግተዋል። የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል።
በ1ዓመት ውስጥ በትንሹ ለ7ጊዜያት ተፈጽሟል። ነሀሴ 1/2008 በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መንግስት ጥይት ከ50 በላይ ወጣቶቿን የተነጠቀችው ባህርዳር ከዛን ጊዜ ወዲህ የቦምብ ፍንዳታ በተደጋጋሚ ሲፈጸምባት ቆይቷል። የቅዳሜው ደግሞ የተለየ ነበር።
በሰሞንኛው አድማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በፈሰሰባት፡ ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር ባልተለያት ባህርዳር ሁለት ተከታታይ የቦምብ ፍንዳታ መፈጸሙ የስርዓቱን አቅም የተፈታተነ መሆኑ ታምኖበታል።
በአማራ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው መሪነት በህወሃት ባለስልጣናት አዘጋጅነት በጎንደር እየተደረገ ያለው ስብሰባም ይህን ለስርዓቱ አስደንጋጭ የተባለውን ክፍተት ለመነጋገር ነው ተብሏል።
ቅዳሜ ዕለት የፈነዳው ቦምብ በነሀሴ አንዱ ሰማዕታትን የማሰቡ ዘመቻ ላይ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው የንግድ ቤታቸውን ክፍት ባደረጉ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። በፍንዳታው ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ይህን አደጋ ያደረሱትን ይዣለሁ ብሏል።
ሊቦ ከመከም ላይ ተያዙ የተባሉት ግለሰቦች ከደቡብ ጎንደር ዕብናት የመጡ ናቸው በሚል ዘጋቢ ፊልም እየተዘጋጀባቸው እንደሆነ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። እንደ ምንጮቹ ከሆነ የህወሃት መንግስት ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሰዎች በመያዝ፡ የሚያመልጠን የለም ዓይነት መልዕክት በማስተላለፍ ፍርሃት ለመፍጠር በሚል የተሰራ ቲያትር እንደሆነ ነው ለመረዳት የተቻለው።
በዕለቱ አካባቢውን የሚጠብቁት የማህበረሰብ ፖሊስ አባላት በሌሎች በአካባቢው ምድብተኛ ባልሆኑ የጸጥታ ሃይሎች እንዲተኩ መደረጋቸው በባለስልጣናቱ ዘንድ የእርስ በእርስ ውዝግብን ፈጥሯል።
እነዚህ የማህበረሰብ ፖሊስ አባላት እንዲቀየሩ በተደረገበት ምሽት የቦምብ አደጋው መፈጸሙ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል። ቦምቡ በፈነዳበት ምሽት በርካታ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን እስካሁን አለመለቀቃቸው ታውቋል።
ባህርዳር ከ1ሳምንት በኋላም በርካታ ሱቆች እንደተዘጉ ናችው። የሆቴል ባለቤቶች፡ ከፍተኛ ነጋዴዎች በአፈሳ ተይዘው እስር ቤት የገቡ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል።
ከ100 በላይ ሚኒባስና የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በአድማው ተሳትፋችኋል ተብለው መታሰራቸውንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የዛሬ ሳምንት በስራ ማቆም አድማ የጀመረችው ደብረታቦር እስከዛሬ ሱቆቹ እና መደብሮቹ ታሽጓል የሚል ወረቀት የተለጠፈባቸው ዛሬ ድረስ ዝግ እንደሆኑ ናቸው።
የከተማዋ አጠቃላይ እንቅስቃሴ የተገደበ ሆኗል። የስራ ማቆም አድማውን አስተባብረዋል ፣ተሳትፈዋል በሚል የሀገር ሽማግሌወችን ፣ታዋቂ ሰዎችን፣ እንዲሁም ወጣቶች ታፍነው ተወስደዋል።
በስራ ማቆም አድማው ተሳትፋችኋል በሚል ሰሌዳቸው የተወሰደባቸው ባለባጃጆች ቅጣት አምስት መቶ ብር እና ግብር ሁለት ሺ አምስት መቶ ብር ካልከፈሉ እንደማይሰጣቸው የከተማው አስተዳደር መወሰኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በተያያዘ ዜና በምስራቅ ጎጃም አድማ በተጀመረባቸው ከተሞች አሁን ድረስ ወደ ስራ ያልገቡ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
ሱቆችና መደብሮች ተዘግተው ሁለተኛ ሳምንታቸውን እየተሻገሩ ሲሆን ግብር አንከፍልም የሚል አቋም የያዙት ነጋዴዎች ላይ እስራትና አፈና እየተፈጸመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በሰሜን ጎንደር በመተማና በሌሎች አካባቢዎች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ሱቆችና መደብሮች ዝግ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በኦሮሚያም በተመሳሳይ አድማ ላይ የሰነበቱ አካባቢዎች እስካሁን ወደ እንቅስቃሴ እንዳልገቡ ታውቋል።
ከግብር ጭማሪው ጋር በተያያዘና በፖለቲካ እስረኞች ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃና ኢሰብአዊ አያያዝ በመቃወም እየተካሄደ ያለው አድማ በተለይ በምዕራብ ሀረርጌና በወለጋ በስፋት ቀጥሏል።
በጊምቢ ሙሉ በሙሉ ሱቆችና መደብሮች ተዘግተው የዋሉ ሲሆን በአጋሮም የንግድ እንቅስቃሴው በአድማው ምክንያት መቆሙን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የአድማ ጥሪ የተበተነ በመሆኑ በቀጣዮቹ ቀናት ተመሳሳይ እርምጃዎች ይጠበቃሉ ተብሏል።

Saturday, August 12, 2017

Advocacy group demand British prosecutors to drop charges against Ethiopian pro-democracy activist

Advocacy group demand British prosecutors to drop charges against Ethiopian pro-democracy activist

Dr. Tadesse Biru Kersmo
ESAT News (August 9, 2017)
The Ethiopian Advocacy Network (EAN) demand British prosecutors to drop what it called politically motivated charges against Dr. Tadesse Biru Kersmo, well-known dissident and pro-democracy activist who was briefly detained by UK authorities on terrorism charges.
“Dr. Kersmo, a scholar, researcher, and God-fearing Christian believes only a genuine democratic system will bring peace and stability in Ethiopia and the Horn of Africa. Dr. Kersmo is a passionate defender of human rights and a dedicated advocate for social justice. His well-known activism has made him an implacable enemy and a prime target of the Ethiopian regime,” said EAN in an open letter to Alison Saunders,
Director Public Prosecution with Crown Prosecution Service.
Last month Dr. Kersmo, a leading voice of dissent against the Ethiopian tyrannical regime who lives in exile in U.K. was granted bail after Scotland Yard charged him with terrorism offenses. Released on bail, his case was declared not suitable for a magistrate and was sent to a jury trial.
British authorities found articles about security, intelligence and urban guerrilla tactics on the computer of Dr. Kersmo, who is a researcher and frequent media analyst on the issues. He argues those articles were solely for research purposes.
A judge concluded the case not suitable for trial before a magistrate and sent it to a jury trial.
Tadesse Biru Kersmo is a pro-democracy advocate who writes and speaks against the Ethiopian brutal regime and teaches his people about how to stand up against tyranny. His computer was found to have been hacked by the Ethiopian regime, which led to a legal case against a regime known for using spyware, wiretapping and surveillance against pro-democracy activists and critical journalists.
“We strongly believe that the charges brought against Dr. Kersmo by UK government, a very strong supporter and major financier of the Ethiopian regime, is a politically motivated witch hunt that charts a frightening future for freedom of speech and privacy in the UK,” said EAN
Kersmo escaped persecution by the Ethiopian regime and has lived in U.K. since 2009.
The Network also used the opportunity to “urge the UK to use its leverage to pressure the Ethiopian regime to open the political space, respect universally guaranteed human rights and release all political prisoners including Mr. Andargachew Tsege, a British citizen who was secretly kidnapped in Yemen and renditioned to Ethiopia where he had been sentenced to death, in absentia, in 2009.”

Friday, August 11, 2017

የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደረገ

) የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደረገ።
በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት የቀረቡትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዋስትና የተከለከሉት ለ5 ጊዜያት ያህል በጉዳዩ ላይ ፍርድ ቤት ከተመላለሱ በኋላ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ከተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ የታሰሩትና በአሸባሪነት የተከሰሱት አቶ በቀለ ገርባ ከወር በፊት ክሳቸው ከአሸባሪነት ወደ ወንጀል ክስ ተደርጎ በፍርድ ቤት መበየኑ ይታወሳል።
የፍርድ ቤቱን ብይን ተከትሎ በጠበቆቻቸው አማካኝነት የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡት አቶ በቀለ ገርባ የተለያዩ ምክንያቶች እየተሰጡ የዋስትና ጥያቄያቸው ውሳኔ ሳያገኝ 5 ቀጠሮዎችን አሳልፏል።
አንዴ ዳኞች አልተሟሉም በሌላ ጊዜ አንዱ ዳኛ ታሟል በሚል ሲገፋ የቆየው የዋስትና ጥያቄ ነሀሴ 4/2009 ውሳኔ አግኝቷል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ አቶ በቀለ ቢፈቱ አመጽ ያነሳሳሉ በሚል ዋስትና ከልክሏቸው ወደ ወህኒ ቤት እንዲመለሱ ወስኗል።
አቶ በቀለ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለመከታተል ከወህኒ ወደ እስር ቤት ሲወሰዱ እንዲሁም ከፍርድ ቤት ወደ ወህኒ ሲመለሱ ሁለት እጃቸውን በካቴና ታስረው ታይተዋል።
ከሳምንት በፊት የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና በተመሳሳይ ሁለት እጃቸውን በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል።
አቶ በቀለ ሁለት እጃቸውን ወደፊት አድርገው በካቴና ሲታሰሩ ዶክተር መረራ ደግሞ ሁለት እጃቸውን ወደ ወደ ኋላ መታሰራቸው ይታወሳል።
በሌብነት፣ በነፍስ ማጥፋት፣ በዘረፋ ወዘተ የሚታሰሩ ግለሰቦች ማጅራት መቺዎች ጭምር በካቴና በማይታሰሩበት ሁኔታ ውስጥ እነዚህ ሁለት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች በካቴና ታስረው መታየታቸው ኢትዮጵያውያንን ማስቆጣቱን በማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚሰጡ አስተያየቶች መረዳት ተችሏል።
የዶክተር መረራ በካቴና ታስሮ መታየት በአምቦ፣ወሊሶ በኋላም በጊንጪና ጉደር ተቃውሞ መቀስቀሱ በግልጽ በታየበት አቶ በቀለ ገርባን በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ፍርድ ቤት መውሰድ አነጋጋሪ ሆኗል።

Thursday, August 10, 2017

Reports of fighting in eastern Ethiopia, highway to Jijiga blocked


ESAT News 
There has been reports of fighting in the area between the cities of Harar and Babile on the way to the country’s eastern commercial town of Jijiga. The highway connecting the capital Addis Ababa to Jijiga has been blocked, according a security alert by the U.S. Embassy in Addis Ababa.
Bloggers close officials in Addis Ababa said the fighting took place on the border between the Oromo and Somali regions, hinting that the fighting could be a continuation of conflict between the two ethnic groups. There has been no official statement from the government or the state run media in Addis Ababa.
The alert from the U.S. Embassy said regime’s army have already arrived in the area.
Clashes between the two ethnic groups early this year had turned deadly with the Oromos accusing that raids by the Somlais were backed by the regional special forces and have resulted in the death of several people, raiding of cattle and abduction of women and children.

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ህዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱ ተሰማ

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ህዝባዊ ቁጣ ተቀስቅሷል። በሰሜን ጎንደር በመተማ፡ በአይከል፡ አርባያ፡ በበለሳ ህዝባዊ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ ወደ ደብረማርቆስ የሚወስደው መንገድ በህዝቡ ተዘግቷል።
በምስራቅ ሀረርጌ በባቢሌ መስመር የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሷል።በርካታ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል።
በወልቃይት አዲረመጽ የህወሃት ታጣቂዎች ገብተው ህዝቡን እያሸበሩት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በወሊሶና ጊንጪ አድማው እንደቀጠለ ነው። በሀዋሳ በባጃጅ አሽከርካሪዎች ትላንት የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሏል።
በሰሜን ጎንደር በበርካታ አካባቢዎች አድማ ተጀምሯል።
በመተማ ወረዳ በመተማና ኮኪት ከተማ ወደ ህዝባዊ አመጽ የተሸጋገረ አድማ መጀመሩን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከጎንደር ወደ ሱዳን በሚወስደው ዋናው መንገድ ላይ ባሉ ከተሞች አድማው ዛሬ የተጀመረ ሲሆን በአንዳንድ ቦታዎች የተኩስ ድምጽ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
በጭልጋ አይከል፡ ነጋዴ ባህር፡ አይምባ በተባሉ ከተሞች የንግድ ድርጅቶች ተዘግተዋል። በበለሳ ወረዳ አርባያ ከተማም ሱቆችና መደብሮች ተዘግተው አድማውን ተቀላቅለዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ ከደብረ ማርቆስ ወደ ሰሜን አቅጣጫ በግምት 25 ኪ.ሜ ረዕቡ ገበያ የሚባል ስፍራ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ በህዝቡ ተዘግቷል። ብዛት ያለው የልዩ ሃይል እና መከላከያ በአካባቢው ሰፍሯል። ከረዕቡ ገበያ ወደ ደብረ ማርቆስ ምንም አይነት የትራንስፓርት እንቅስቃሴ የለም።
በባቢሌ መስመር ቆሬ እየተባለ በሚጠራው ቦታ የኦሮሞ ተወላጆች ከሶማሊያ ልዩ ሃይል ጋር ትንቅንቅ ውስጥ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ። ህዝቡ ባለው መሳሪያ ከልዩ ሃይሎች ጋር እየተዋጋ ነው።
የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። እንዲሁም በፉኛን ቢራና ጉርሱም ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ ተካሂዷል። ትላንት የአሜሪካን መንግስት በሀረርና በባቢሌ መሃል ያለው መንገድ በመዘጋቱ ዜጎቹ ከእንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ ይታወሳል። ዛሬ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ የአሜሪካን መንግስትን መረጃ አጣጥለዋል። በተጠቀሰው አካባቢ የተዘጋ መንገድም ሆነ የተደረገ የተኩስ ልውውጥ የለም ብለዋል-ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ።
በግብር ተመኑ የተነሳ ተቃውሞ በጀመሩ የኦሮሚያ ከተሞች አሁንም አድማው እንደቀጠለ ነው። በወሊሶና ጊንጪ ዛሬም አብዛኞቹ የንግድ ቦታዎች ከእንቅስቃሴ ውጪ ሆነው ውለዋል። በአምቦም ተመሳሳይ የአድማ እንቅስቃሴ እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማል።
በባህርዳር በነጋዴዎችና ባለሀብቶች ላይ የተጀመረው የእስር ዘመቻ የቀጠለሲሆን፡ ዛሬ ከ150 በላይ የሚሆኑ ታስረው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል። በደብረታቦር ዛሬም አድማ እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ። በምዕራብ ጎጃም ደምበጫም እንዲሁ ለተከታታይ ቀናት ሱቆችና መደብሮች ተዘግተዋል።
ሀዋሳ ትላንት የተጀመረው የባጃጅ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሏል። በአስፓልት መንገዶች ላይ አገልግሎት እንዲያቆሙ በመደረጋቸው የተቃወሙት የባጃጅ አሽከርካሪዎች በትላንትናው ዕለት ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውንና የመንግስት ተሽከርካሪዎችን ማጥቃታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ዛሬ ጥያቄ ይዘው ወደሚመለከተው አካል ቢሄዱም ተቀባይነት አላገኙም። በአድማው ቀጥለዋል። በሌላ በኩል በሀዋሳ አዲሱ ገበያ ዛሬ ሌሊቱን ከ20 በላይ ሱቆች በግሬደር መፍረሳቸውን ተከትሎ በአከባቢው መለስተኛ ውጥረት መፈጠሩ ተገልጿል።
ወደ ገበያው የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ እንደነበርና ሱቃቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ተቃውሞ እያሰሙ መሆኑንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በሌላ በኩል የህወሀት ወታደሮች ወደ ወልቃይት አዲረመጽ ከተማ በብዛት መግባታቸውን የኢሳት ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል። የአመጽ ጥሪ ተደርጓል በሚል ወደ ከተማዋ የገቡት ወታደሮች ነዋሪውን እያሸበሩት እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በከተማዋ መግቢያና መውጪያ ያሉ ኬላዎች በወታደሮቹ ተከበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በበለሳ የአርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄ ታጣቂዎች ከስርዓቱ ወታደሮች ጋር መዋጋታቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በበለሳ ወረዳ ልዩ ስሙ ቆላ ሀሙሲት ላይ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በመንግስት ወታደሮች ላይ የሞትና የመቁስል አደጋ የደረሰ መሆኑን ንቅናቄው ከላከው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ኢሳት ንቅናቄው አደረኩ ስላለው ጥቃት ከመንግስት በኩል ለማረጋገጥ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

Wednesday, August 9, 2017

ከአዲስ አበባ ወደ ጅጅጋ የሚወስደው መንገድ በባቢሌና በሃረር መካከል መዘጋቱን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ


(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 4/2009)
ከአዲስ አበባ ወደ ጅጅጋ የሚወስደው መንገድ በባቢሌና በሃረር መካከል መዘጋቱን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ።
በጦር መሳሪያየተደገፈ ከፍተኛ የተኩስ ለውውጥ እየተካሄ መሆኑንና መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው መንቀሳቀሱን ኤምባሲው ገልጿል። የአሜሪካ ዜጎች በባቢሌና ሃረር መካከል ባሉ ቦታዎች እንዳይጓዙ ኤምባሲው አስጠንቅቋል።
በባህርዳርም አፈሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሆቴል ባለቤቶችና ከፍተኛ ነጋዴዎችም እየታሰሩ ነው።
በሀዋሳ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ አድርገው ውለዋል። የመንግስት ተሽከርካሪዎችና የከተማ አውቶቡስ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል።በተለያዩ ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማም እንደቀጠለ ነው።
በባህርዳር ውጥረቱ ጨምሯል።
የአድማ በታኝ ዩኒፎርም የለበሱ የአጋዚ ወታደሮች ውርውር ይላሉ ፍተሻውም ፣ እስራቱም ቀጥሏል።
ነሃሴ 1 የሰማዕታት ቀን የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ የህወሓት/ብአዴን አባላት ሱቆቻቸው ታሽጎባቸዋል።
በቀበሌ 12 ከመናሃሪያው አካባቢ ጋሳ ሆቴል ጥግ የሚገኙት የፀጉር ቤት ኮንቲነሮች ፤ ትንንሽ ምግብ ቤቶች… ሰማዕታት የምትሏቸውን አስባችኋል፣ አድማ ተሳትፋችኋል በማለት ኮንቲነሮቻቸው የታሸገባቸው ሲሆን ወረቀቱን የሚቀድ ይቀጣል በማለት የግሽ አባይ ክ/ከተማ ካድሬዎች እና ፖሊሶች እያስፈራሩ ሲሆን ” ወረቀቱን አንሱል እና እንስራበት ” በማለት ሲጠይቁ ” ግንቦት 7 መጥቶ ያስከፍትላችሁ ” የሚል ምላሽ ነው በካድሬዎቹ የተነገራቸው። በቀበሌ 11 አባይ ማዶ በገበያው ዙሪያ አድማ አድርጋችኋል የተባሉ ” የህዝብ አገልግሎት ባለመስጠት ታሽጓል ” የሚል ወረቀት የተለጠፈባቸው ሲሆን ወደ ህዳር 11 ክ/ከተማ ሂደው ካድሬዎቹን ሲጠይቁ በፅ/ቤቱ በሰፈረው የልዩ ሃይል አድማ በታኝ ዩኒፎርም በለበሱ የአጋዚ ወታደሮች ታፍነው ታስረዋል። በጠዋት ለመጠየቅ ከሄዱት ውስጥ አንዱ ሊይዙት ሲሉ በማምለጡ መረጃው ለሁሉም ተዛምቷል። የተያዙ ከ5 የሚበልጡ ባለኮንቲነሮች ድብደባም እንደተፈፀመባቸው ለማወቅ ተችሏል። ከባህርዳር በሚያስወጡና በሚያስገቡ መንገዶች ላይ በሚገኙ ከተሞች ፍተሻው ከፍተኛ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ወደ ሀዋሳ ለኢትዮጵያ ታዳጊዎች ሻምፒዮን ለመሳተፍ እያመራ የነበረው የአማራ ክልል ታዳጊዎች ቡድን በመንገድ ላይ ባለው አለመረጋጋት የተነሳ በደጀን ለማደር መገደዱም ተሰምቷል።
በደብረታቦር አድማው ለአራተኛ ቀን ቀጥሏል። ሱቆችና መደብሮች እንደተዘጉ ናቸው። በምስራቅ ጎጃም በበርካታ አካባቢዎች ግብር አንከፍልም በሚል የተነሳው ተቃውሞና የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ እየተካሄደ ነው። በሸዋ ሮቢት ሳምንቱን ያለፈው አለመረጋጋት አሁንም አልበረደም። በርካታ ሱቆች እንደታሸጉ ናቸው።
በሀዋሳ ዛሬ የባጃጅ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ አድርገው መዋላቸው ታውቋል። ከአካባቢው የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው የባጃጅ ትራንስፖርት ከአስፓልት መንገዶች ውጭ እንዲሆኑ መወሰኑን በመቃወም የተካሄደው የስራ ማቆም አድማ ግጭት ያስከተለ ሲሆን ፖሊስ ሌባ በሚል ተጀምሮ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም መቀጠሉ ታውቋል። የከተማ አውቶብሶች መስታወታቸው መሰባብሩን የገለጹት ምንጮች የፌደራል ሃይል ተጨምሮ ማምሻውን ግጭቱ ቢበርድም ባጃጅ አሽከርካሪዎች ግን ስራ እንዳልጀመሩ ጠቅሰዋል።
የአሜሪካን ኤምባሲ ደግሞ ለዜጎቹ ማስጠንቀቂያ ማስተላልፉ ተሰምቷል። ኤምባሲው በድረገጹ ከበተነው የማስጠንቀቂያና የጥንቃቄ መልዕክት መረዳት እንደተቻለው፡ ከአዲስ አበባ ወደ ጅጅጋ የሚወስደው መንገድ ለደህንነንት አደጋ ስላለው የአሜሪካ ዜጎች በዚያ መስመር ጉዞ ካላቸው እንዳይንቀሳቀሱ አሳስቧል። ኤምባሲው እንዳለው አዲስ አበባ ጂጂጋ መስመር ባቢሌና ሀረር መሃል መንገድ ተዘግቷል። የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ነው። ኤምባሲው ማስጠንቀቂያውን ከመስጠት ባለፈ እየተካሄደ ነው ስለተባለው የተኩስ ልውውጥ ዝርዝር መረጃ አላቀረበም። በሌላ በኩል የአሜሪካን ኤምባሲ ለጤና አገልግልት እንዲውል በሚል በእርዳታ የሰጠውን ተሽከርካሪ ለፖሊስና ወታደራዊ ጠቀሜታ እንዲውል መደረጉን ተከትሎም ማብራራያ እንዲሰጠው ጠይቋል። ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄውን ያቀረበው ኤምባሲው በአሜሪካ ድጋፍ የተሰጠው ተሽከርካሪ ከታሰበለት ዓላማ ውጪ መዋሉን በተመለከተ ምርመራ እንዲደርግ አሳስቧል። በአምቦ በተመሳሳይ ወታደሮችን ሲያጓጉዝ በነበረ የጤና ቢሮ ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ መቃጠሉ የሚታወስ ነው።

አልማ ለገቢ ማስገኛ በሚል ያስገነባው ማተሚያ ቤት ከጥቅም ውጪ መሆኑ ተነገረ

Bildergebnis für አልማ

 የአማራ ልማት ማህበር/አልማ/ለገቢ ማስገኛ በሚል ያስገነባው ማተሚያ ቤት የህትመት ማሽኑን ሊያስገባ ባለመቻሉ 24 ሚሊየን ብር የወጣበት ግንባታ ከጥቅም ውጪ መሆኑ ተነገረ።
ባልተጠና የግንባታ ዲዛይን የተሰራው ማተሚያ ቤት ከጥቅም ውጪ ከሆነ በኋላ በሌላ ቦታ ግንባታ ለማከናወን የተገዛው ከ900 በላይ ከረጢት ሲሚንቶም ተበላሽቶ መጣሉ ተነግሯል።
በአያያዝ ችግር እንዲወገድ የተደረገው የአማራ ልማት ማህበር/አልማ/ ከ900 በላይ ከረጢት ሲሚንቶ ከ324 ሺ ብር በላይ ወጭ የተደረገበትና የባከነ ነው።
ከአመታት በፊት በአቶ ህላዊ ዮሴፍ ሲመራ የነበረው የአልማ ጽህፈር ቤት በከፍተኛ የኦዲት ጉድለት በመጠርጠሩ ህንጻው ሙሉ በሙሉ እንዲቃጠል ተደርጎ ማንም ሳይጠየቅ መቅረቱ ይታወሳል።
የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/በቴሌቶን አማካኝነት በገቢ ማሰባሰብ ከሕዝብ አግኝቻለሁ ያለውን ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ በምን ስራ ላይ እንዳዋለው በዝርዝር ሳይታወቅ ተንጠልጥሎ የቆየ ጉዳይ ነው።
የማህበሩ ወጪና ገቢ ታውቆ የኦዲት ሪፖርት ለሕዝብ ግልጽ ተደርጎ አያውቅም።አሁን ያገኘንው መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ የአልማ ጽህፈት ቤት ገቢ ለማግኘት በሚል ያሰራው የአባይ ማተሚያ ቤት ሕንጻ ትክክለኛ ባልሆነ ዲዛይን ሳቢያ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።
ከ24 ሚሊየን ብር በላይ የወጣበት ይህው ህንጻ የሕትመት ማሽኖችን ሊያስገባ አልቻለም በሚል ያለአገልግሎት በቁሙ ቀርቷል ነው የተባለው።
ይባስ ብሎ ደግሞ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ዘንዝልማ መውጫ ላይ ሌላ የማተሚያ ቤት ሕንጻ እንሰራለን በሚል ከ900 በላይ ከረጢት የደርባን ሲሚንቶ ከ324 ሺ ብር በላይ ወጪ ቢገዛም በአያያዝ ችግር መበላሸቱን የኢሳት ምንጮች በቪዲዮ አስደግፈው ጠቁመዋል።
የአባይ ማተሚያ ቤት መጀመሪያ ሲገነባ የአልማ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሰለሞን ታደሰና የማህበሩ የገቢ ማስገኛ ክፍል ሃላፊ የነበረው አቶ ታደሰ ጊዮን ድርጅቱን ቢለቁም ከብክነቱና በህንጻው ስም ለተበላው 24 ሚሊየን ብር ተጣያቂ መሆናቸው ተመልክቷል።
የአካባቢው ምንጮች የተበላሸና ሲሚንቶም ከቀበሌ 11 ወደ ቀበሌ 07 ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ፊት ለፊት ባለ ግቢ እንዲከማች ተደርጓል።
በአማራ ልማት ማህበር/አልማ/ከቴሌቶን ገቢ ለክልሉ ጤና ጣቢያዎች አምቡላንሶች ተገዝተው ብዙዎቹ ያለአገልግሎት ቆመው ሲቀሩ ተጠያቂ የተደረገ አካል የለም።
ከአመታት በፊትም አልማ በአቶ ህላዊ ዮሴፍ ሲመራ በነበረበት ጊዜ ከፍተኛ የኦዲት ጉድለት እንዳለ በመጠርጠሩ ጽህፈት ቤቱ ሙሉ በሙሉ እንዲቃጠል ተደርጎ ምክንያቱ ለሕዝብ ሳይገለጽ ጉዳዩ ተሸፋፍኖ ቀርቷል።
በአሁኑ ጊዜ የአማራ ልማት ማህበር በዋና ዳይሬክተር በወይዘሮ ብስራት ጠናጋሻው ቢመራም ሴትዬዋ መኖሪያቸው አዲስ አበባ በመሆኑ በሳምንት 2 ጊዜና 3 ጊዜ በአውሮፕላን ባህርዳር ስለሚመላለሱ የትራንስፖርት ወጪያቸው ብቻ ቀላል የማይባል ብክነት መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ።
እናም የባህርዳር ምንጮቻችን የአማራ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ይህን እያየ ዝም ማለቱ እስገራሚ ነው ባይ ናቸው።

Tuesday, August 8, 2017

የመብራትና ውሃ እጥረት በመላ ሃገሪቱ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑን ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ።

የመብራትና ውሃ እጥረት በመላ ሃገሪቱ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 27/2009) 
የመብራትና ውሃ እጥረት በመላ ሃገሪቱ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑን ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ።
በመዲናይቱ አዲስ አበባ የኤሌክትሪክና የውሃ እጥረት እየተባባሰ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ንጽህና የጎደለው ውሃ ከመጠቀም ባለፈ ዝናብ እየጠበቁ ውሃ ማጠራቀምና ለእለታዊ ፍጆታ ማዋል እየተለመደ መጥቷል።
በአማራ ክልልም የውሃና የኤሌክትሪክ እጥረቱ በህዝቡ ላይ የፈጠረው አደጋ እየከፋ መምጣቱ ተገልጿል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍልም በተለያዩ አካባቢዎች መብራትና ውሃ ከአንድ ወር በላይ እንደሚጠፋባቸው ወኪላችን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።የነዳጅ እጥረትም ተከስቷል።
በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሃይል መቆራረጥ እንጂ እጥረት የለም ይላል።
የኤሌክትሪክ ሽያጭ ከጎረቤት ሀገራት ባሻገር እስከ አውሮፓ ድረስ ሊቀርብ የሚያስችል አቅም እየፈጠርን ነው ይላል በሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት።
ጅቡቲ ሱዳንና ኬንያ መስመር ተዘርግቶላቸው ከኢትዮጵያ መብራት እያገኙ እንደሆነም በመንግስት በኩል በየጊዜው በስኬት ተመዝግቦ እየተገለጸ ይገኛል።
አዲስ አበባ በመብራት እጥረት የተነሳ ነዋሪው ከፍተኛ ችግር ላይ በመውደቁ ደግሞ ጉዳዩን ግራ የሚያጋባ አድርጎታል።
ሰሞኑን የታየው የመብራት እጥረት ከምንግዜውም በላይ የከፋ ሆኖ ህዝቡን ለተለያዩ ችግሮች እየዳረገው ነው ሲሉ የኢሳት ወኪል ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በመደበኛነት በሳምንት ሁለትና ሶስት ቀናት ለ24 ሰአት መብራት ሙሉ በሙሉ የሚጠፋ በመሆኑ ከኤሌክትሪክ ጋር በተያያዘ የንግድ ቤቶች ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ ናቸው።
መብራት በሚመጣባቸው የተቀሩት ቀናት ለሰአታት የሚዘልቅ የሃይል መቆራረጥ የሚከሰት በመሆኑ በአዲስ አበባ ነዋሪው የገጠመው ችግር የመኖር ህልውናውን እየተፈታተነው እንደሚገኝ ወኪላችን ገልጿል።
የኤሌክትሪክ እጥረቱ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በዋና ዋና የሀገሪቱ ከተሞች የተከሰተ መሆኑን ለኢሳት የደረሱት መረጃዎች ያሳያሉ።
ሀዋሳ፣ዲላ፣አዳማ፣ባህርዳር፣ጎንደር፣ደሴ፣ነቀምት፣ድሬደዋና ሀረር ተመሳሳይ በሆነ የኤሌክትሪክ እጥረት ነዋሪው ለከፋ ችግር ተጋልጦ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው።
በአዲስ አበባ በጸጉር ቤት ስራ ፣በአነስተኛ ማሽኖች የሚንቀሳቀሱ የንግድ ተቋማት፣ሆቴል ቤቶች በአጠቃላይ ኑሮአቸው በኤሌክትሪክ ሃይል ላይ የተመሰረተባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሰርተው መብላት እስከሚያቅታቸው እንደደረሱ ለማወቅ ተችሏል።
ችግሩ በአማራ ክልልም ጎልቶ የሚታይ ሲሆን ከአንድ ሳምንት በላይ መብራት የሚያጡ አካባቢዎች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም።በባህርዳር ያለው ሁኔታም ተመሳሳይ ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ በከፋ ዞን ቦንጋ ነጋዴዎች የቀን ገቢ ግብር አንከፍልም የሚል ተቃውሞ ሲያስነሱ በምክንያትነት ያስቀመጡት የመብራት እጥረትን ነው።
በአመት ከአንድ መቶ ቀናት በላይ መብራት እየጠፋ ሲመጣም እየተቆራረጠ መሆኑ በንግድ ስራቸው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተለ በመሆኑ የተጣለባቸውን የቀን ገቢ ግብር መክፈል እንደማይችሉ ነው ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ያስታወቁት።
የውሃ እጥረትም በተመሳሳይ የኢትዮጵያውያንን ኑሮ አደጋ ውስጥ ከቶታል።ከውሃ እጥረቱም በተጨማሪ ለጤና ጠንቅ የሆነ ድፍርስ ውሃ በቧንቧ እየመጣ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ አካባቢዎች እንዳሉ ተጠቁሟል።
ውሃ ለመቅዳት የሚያዙ ሰልፎች እየተለመዱ የመጡ ሲሆን አንድ ጀሪካን ውሃ ከ20 ብር በላይ እየተሸጠ እንደሆነም ተገልጿል።
በሀዋሳ መብራትና ውሃ የነዋሪው ብርቱ ችግር እየሆነ እንደመጣም ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ከሃይል መቆራረጥ ሌላ ለቀናት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማይኖር በመሆኑ ችግሩ አሳሳቢ ከሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሀዋሳ እስከ 15 ቀናት ድረስ ውሃ የሚጠፋ እንደሆነ የሚናገሩት ነዋሪዎች የታሸገ ውሃ በመግዛት ለመጠቀም እንደተገደዱም ይገልጻሉ።
በመላ ሀገሪቱ የተከሰተውን የመብራትና የውሃ እጥረት በተመለከተ በመንግስት በኩል መፍትሄ እየቀረበ እንዳልሆነ ይነገራል።
ከዚያ ይልቅ ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ሃይል በሽያጭ ለማቅረብ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።
የሀገር ውስጥ ፍላጎት ሳይሟላ ለውጭ ምንዛሪ በሚል የሃይል ሽያጭ መከናወኑ ህዝቡን እያስቆጣ እንደሆነም ለኢሳት የደረሱት ምረጃዎች አመልክተዋል።

wanted officials