በአፍሪካ ተራሮች ላይ ፍየል ከመጠበቅ እስከ የፈረንሳይ ትምህርት ሚኒስትርነት
………………………….
ይህች ጀግና ሴት ነጃት ቫሉድ ትባላለች ። በአፍሪካዊቷ ሞሮኮ ውስጥ በምትገኝ ናዶር የተባለች መንደር ተወልዳ የልጅነት ጊዜዋን ፍየል በመጠበቅ ያሳለፈች እረኛ ነበረች ።
ሆኖም ዘመንዋ በዚህ እንዲያልቅ አልተፈረደባትም ነበርና በኮንስትራክሽን ሙያ የሚሰራው አባቷ ቤተሰቡን ጠቅልሎ ወደ ፈረንሳይ ሲገባ የነጃትም የእረኝነት ዘመን በዚያው አበቃ ።
……………………….
የትምህርትን ሃሁ በፈረንሳይ የጀመረችው ነጃት ዩኒቨርስቲ ገብታ ስትወጣ በተቀላቀለችው የፈረንሳይ ሶሻሊስት ፓርቲ አማካኝነትም ከትናንሽ ስልጣን ጀምሮ
* የመንግስት ቃል አቀባይ
* የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር
* የሴቶች መብት ሚኒስትር
* የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ሚኒስትር
* እና የመጀመሪያዋ የፈረንሳይ የትምህርት ሚኒስትር የሆነች ጠንካራ ሴት ናት ።

No comments:
Post a Comment