160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመን ባህር ውስጥ በግዴታ መወርወራቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይ ኦ ኤም አስታወቀ።
ድርጊቱ የተፈጸመው በግዴታ ወደ ባህር ከተወረወሩት ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን ስደተኞች 50 ዎቹ መሞታቸው በተነገረ በ24 ሰአት ጊዜ ውስጥ ነው።
ተቋሙ እንዲህ አይነቱ ድርጊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊገታና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በተሰማሩት አካላት ላይም በተግባር የተደገፈ ርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲል አስጠንቅቋል።
እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይ ኦ ኤም መረጃ ከሆነ በየመን የባህር ዳርቻ ሻብዋ በሁለት ቀናት ብቻ 280 ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን ስደተኞች በግዴታ ወደ ባህር ተወርውረዋል።
160 የሚሆኑት ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል።
የነዚህ ኢትዮጵያውን ወደ ባህር መወርወር የተሰማው ደግሞ ከ24 ሰአት በፊት ወደ ባህር በግዴታ ከተወረወሩት 120 ስደተኞች የ50ዎቹ ህይወት ማለፉ ከተሰማ በኋላ ነው።
ወደ ባህር ከተወረወሩት 160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችም የ2 ወንዶችና የ4 ሴቶች አስከሬን መገኘቱን ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።
እስካሁን 13 ኢትዮጵያውያን የደረሱበት አልታወቀም።በህይወት ለተረፉት 57 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችም አስቸኳይ የህክምናና የምግብ እርዳታ በማድረግ ላይ ይገኛል።
እንደ መረጃው ከሆነ ከ24 ሰአት በፊት ወደ ባህር የተወረወሩትን ስደተኞች ጨምሮ 84 ስደተኞች የተቋሙ ሰራተኞች ወደ ስፍራው ከመድረሳቸው በፊት ባህር ዳርቻውን ጥለው መሄዳቸው ታውቋል።እጣ ፋንታቸው ምን እንደሆነ ባይታወቅም እንኳን ብሏል ተቋሙ።
በሁለት ቀናቱ አሳዛኛና ሰብአዊነት በጎደለው ድርጊት ህይወታቸውን ያጡ ስደተኞች ቁጥር 70 ደርሷል ያላል ሪፖርቱ።ምናልባትም ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ ይችላል በማለት።
በህይወት የተረፉት ሰደተኞችም አሰቃቂ የሚባልውን ጉዟቸውን ለተቋሙ ሰራተኞች በዝርዝር ነግረዋቸዋል።
እንደነሱ አባባል ከሆነም አንድም ስደተኛ ወደ ጀልባዋ ከገባ በኋላ መንቀሳቀስ የሚባል ነገር አይፈቀድለትም።
በጉዟቸው ወቅት አንዳንድ ችግሮች ቢፈጠሩና ስደተኞቹ ሮጠው አልያም በዋና ሊያመልጡ ቢሞክሩ በሚል እጃቸውና እግራቸው በህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ እንደሚታሰርም ይናገራሉ።
ይሄ ሁሉ ሆኖ ደግሞ ከመካከለቻው በድንገት አንዱ ለመንቀሳቀስ ቢሞክር ከፋ ያለ ዱላ አልያም ህይወቱን እስከማጣት ሊደርስ ይችላል።
ከ24 እስከ 36 ሰአታትን በሚፈጀው የባህር ላይ ጉዞም በቂ የሚባል ምግብም ሆነ ውሃ እንዲወስዱ አይፈቀድላቸውም።
በህይወት የተረፉት ስደተኞች ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ በባህር ዳርቻው ያለው የጸጥታ ሃይል በቁጥጥር ስር ያውለናል በሚል ፍራቻ በግዴታ ወደ ባህር እንደወረወሯቸው ይናገራሉ።
በሻብዋ የአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይ ኦ ኤም የአደጋ መከላከል ኦፊሰር ሊና ኮሳ ይሄ ድርጊት በፍጹም ሊገታ ይገባል ይላሉ።
የእነዚህ ታዳጊዎችን ህይወት ልንታደግ ይገባል።መመሪያ በማስቀመጥ ሳይሆን በድርጊት በማሳየት ጭምር ይላሉ ሊና ኮሳ።
የህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሰንሰለት መበጣጠ ቅድሚያ የሚሰጠው ተገባር ነው ሲሉም አሳስበዋል።
እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ በተያዘው የፈረንጆቹ 2017 ብቻ በየመን የባህር ዳርቻ 114 ስደተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል።
No comments:
Post a Comment