በላሊበላ ከተማ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ቀጥሏል!!
በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በዘፈቀደ የተጣለብንን ግብር አንከፍልም በማለት ዕለተ ዓርብ ሐምሌ 28 /2009 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የጀመረው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ሐምሌ 29 /2009ዓ.ም በከተማው ያሉ ሱቆች እና መደብሮች በመዝጋት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ በላሊበላ ከተማ የሚገኘው የቅዳሜ ገበያ በዙሪያ አካባቢው ከመጡ ያልሰሙ ገበያተኞች ውጭ ጭር ብሎ ውሏል። በገበያው የበርበሬ ተራ፣ የልብስ ተራ ፣ የሸቀጣ ሸቀጦች ተራ ነጋዴወች አይታዩባቸውም። የአካባቢው የህወሓት ካድሬወች የሀገር ሽማግሌ በመምረጥ ቤት ለቤት እየዞሩ የሀገር ገፅታ ግንባታ ታበላሻላችሁ ክፈቱ እያሉ ቢያስገድዱም ሁሉም በስራ ማቆም አድማው በመፅናት አልከፍትም ብለዋል።
በላሊበላ ከተማ በሮሃ ላልይበላ ውቅር አበያተክርስቲያናት ከፍተኛ የውጭ ሀገር እና የሀገር ውስጥ ጎብኝወች የሚጎርፉ ሲሆን ከአምናው የወያኔ ስርዓትን ካሽመደመደው ህዝባዊ እምቢተኝነት እና ህዝባዊ አመፅ ወዲህ የቱሪስቶች ፍሰት በጣም የቀዛቀዘ እንደሆነ ታውቋል።
በተያያዘ መረጃ በዘፈቀደ በካድሬወች የተጣለብንን የግብር ውሳኔ አንከፍልም በማለት ከላሊበላ ከተማ በ30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ብልባላ ከተማ የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ ከሳምንት በፊት የጀመሩት የስራ መቆም አድማ እንደቀጠለ ይገኛል። የአካባቢው ካድሬወች ነጋዴወቹን ስራ እንዲጀምሩ ቢያግባቡም ግብር አንከፍልም በማለት መሳሪያቸውን ወልውለው እንደተቀመጡ ታውቋል።
ግብር ለህወሓት ወያኔ አንከፍልም !!

No comments:
Post a Comment