Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 31, 2016

ጥሪ: ከዚህ ወር ጀምሮ ወደ ሃገር ቤት ለግንባታም ይሁን ለቤተሰብ ድጎማ የሚላከው የውጭ ምንዛሪ እንዳይላክ






የአስቸኳይ ጊዜ የዉጭ ምንዛሬ ማዕቀብ አዋጅ!

ውድ ኢትዮጵያዊያን፣


ሁላችንም በሚገባ እንደምናውቀው፤

ሀገራችን ኢትዮጵያ በሕወሓት መራሹ ዘረኛ የግፍ አገዛዝ ሥር ሆና ዜጎች እንደ እንስሳ እየተገደሉ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፣ አስከፊውን ስርዓት ከስሩ ነቅለን ሕዝባችንን እና ሀገራችንን ለመታደግ ዛሬ ነገ የማይባልበት አጣዳፊ ጊዜ ላይ የደረስን በመሆኑ፤
ጠላት ሌት ተቀን ሥልጣኑን ለማራዘም በሽዎች እያሰረ፣ እያሰቃየና እየገደለ ባለበት ወቅት፣ ዝም ብለን በመቀመጥ ወይንም ወያኔ በሚፈፅመው ግፍ በማዘን እና በመቆጨት ብቻ ተጠምደን እያንዳንዳችን የቻልነውን ያህል ጠጠር ከመወርወር ከተቆጠብን ፣ “ነገ ሀገር እና ሕዝብ የሚባል ይኖረናል ወይ?” ብለን የምንጠይቅበት ደረጃ ላይ የደረስን በመሆኑ፣
በሀገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን የእለት ጉሮሯቸውን ዘግተው እየተራቡ እና እየተጠሙ በሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ዐውድ የሚያደርጉትን የሞት ሽረት ትግል፤ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ወገን የበኩሉን እርምጃ በመውሰድ አጋርነቱን ማሳየቱ ትግሉን እንደሚያጎለብት የታመነበት በመሆኑ፣
ሀገራችን ኢትዮጵያን ለ25 ዓመታት በግፍ እንዲገዛ የኢኮኖሚው ጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለገለው ከውጭ ሀገራት በተለያዬ መንገድ እና ምክንያት የሚገባው የውጭ ምንዛሬ በመሆኑና ከዚህም ዉስጥ በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለግንባታ፣ ለንግድ እና ለዘመዶቻቸዉ በባንክ በኩል የሚልኩት ህዋላ (remittance) ከፍተኛ ድርሻ ያለዉ በመሆኑ፣
በህዝባዊ እምቢተኝነቱ መቀጣጠል ምክንያት ወያኔ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የገባ በመሆኑ እና ወደ ሀገር ቤት በተለያዬ ምክንያት በሚላከው የውጭ ምንዛሬ ላይ ውጤታማ ተአቅቦ ከተደረገ ሕወሓት መራሹን ዘረኛና ወንበዴያዊ አገዛዝ ውድቀት በእጅጉ የሚያፋጥነው በመሆኑ፣
እኛ ስማችን ከታች የተጠቀሰው የሲቪክ እና ፖለቲካ ድርጅቶች፤ ከላይ የተዘረዘሩቱን ወቅታዊ የሀገራችንን ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እና መነሻ በማድረግ፣ በውጭ የምንኖር፣ ፍትህ፣ እኩልነት እና ነፃነት ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ በሕወሓት መራሹ ዘረኛ አገዛዝ ላይ የዉጭ ምንዛሬ ማዕቀብ እንድናደርግ ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።

ከዚህ ‘ከዲሴምበር’ ወር ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ የኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ አዋጅ በማወጅ፣ ወደ ሃገር ቤት ለግንባታም ይሁን ለቤተሰብ ድጎማ የሚላከው የውጭ ምንዛሪ እንዳይላክ፣
የሦስት ወሩ አስቸኳይ የኢኮኖሚ ማእቀብ የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ፤ የስርዓቱን የገንዘብ አቅም የበለጠ ማሽመደመድ እንዲቻል፣ ቢያንስ ለስድስት ወር ያህል የሚላከው ገንዘብ በአንድ ሶስተኛ እንዲቀንስ ማድረግ። ይህም ማለት መቶ ዶላር የሚልክ ሰው ሰባ ዶላር እንዲልክ ወይም በአመት አምስት ጊዜ የሚልክ ሦስት ጊዜ ብቻ እንዲልክ ማድረግ፣
የማእቀቡ ጥሪ በተላለፈበት የጊዜ ገደብ ውስጥ የግድ ለቤተሰብም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ገንዘብ መላክ ካለበት፤ ገንዘቡ ለስርዓቱ ሊደርስ የማይችልበትን መንገድ በምንኖርበት ከተማ በማፈላለግ ገንዘቡን መላክ። ይህ ማለት ከባንኮች እና ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች እንዲሁም የወያኔ አባላት እና ደጋፊዎች ከሚቆጣሩት የአላላክ ዘዴ ውጭ የውጭ ምንዛሬውን መላክ።
ውድ ወገኖቻችን፣

ወያኔን የውጭ ምንዛሬ ማሳጣት በእጃችን ውስጥ ያለ የትግል መሳሪያ ስለሆነ ለተግባራዊ እርማጃ በመነሳት ኢትዮጵያዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ለነፃነቱ እና ለእኩልነቱ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ባለው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም እንጠይቃለን።

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ!!
western_union

Thursday, December 29, 2016

Groups call halt on remittance to punish the Ethiopian regime


ESAT News (December 27, 2016)
Civic and political organizations called on Ethiopians in the Diaspora to suspend sending remittances to the country to punish a regime which they said uses the money to oppress the people.
The seventeen civic and political organizations in a press release urged Ethiopians to halt sending money for three months. It also called for a reduction by one third for six months after the end of the three month halt.
Remittance accounts is a major foreign currency source for the regime. Data show Ethiopians in the Diaspora sent 3.7 billion dollars in 2015 and the 2016 estimate remittance is expected to be at least 4 billion dollars.
Earlier in the month, a U.S. based economist said in an interview with ESAT that remittances from Ethiopians abroad are the main source of the country’s foreign currency and any reduction would further cripple the economy already dominated by the ruling elite.
“It is a weapon in the hands of the Diaspora if they want to punish the regime,” Dr. Zelalem Teklu said. “A little reduction in what we send back home could have a serious impact on the economy.”
Investment, export and trade have shown a serious decline in the country while cost of living has risen dramatically posing a serious challenge to the country’s overall economy, according to the economist.
A year-long anti-government protest is having a negative impact on the country’s economy. Ethiopian regime claims that the Ethiopian economy is growing at the rate of 8 percent while the World Bank puts the rate at 6 percent.

Wednesday, December 28, 2016

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ በጽኑ ታሞ ባቱ ሆስፒታል ገባ

Image may contain: 1 person

 ኢሳት ዜና :- የሶስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት በዝዋይ እስር ቤት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታህሳስ18 ቀን 2009 ዓ.ም በፀና ታሞ በአንፑላንስ ተጭኖ ዝዋይ በሚገኘው ባቱ አጠቃላይ ሆስፒታል መግባቱ ታውቋል።
በተደጋጋሚ ጊዜያት ከቤተሰቦቹ እና ሕጋዊ ጠበቃው ጋር እንዳይገናኝ ሲደረግ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ የእስር ቤቱ ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ይዘውት በሚገቡበት ወቅት በአቅራቢያው የሚገኙትን ሰዎች እንዲርቁ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የተመስገን የሕመም ደረጃ ምን ያህል እና በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ እንዳልተቻለ ቤተሰቦቹ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቃሬዛ ተጭኖ ከገባበት ዝዋይ ባቱ ሆስፒታል ያልወጣ ሲሆን የሕመሙን ዓይነት ቤተሰቡ እንዲያውቁት አልተደረገም።
”የዛሬው የፈረቃ መሪ ሻለቃ ንጉሴ ጨምሮ ዝዋይ እስር ቤት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም እስከ ዛሬ በተመሰገን ላይ ለደረሰው እና ለሚደርሰው ነገር ሁሉ መንግስት ሙሉ ሃላፊነቱን ይወስዳል” ሲል የጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ ወንድም የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስነብቧል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከወራት በፊት የአመክሮ ጊዜውን ጨርሶ መፈታት ይገባው የነበረ ቢሆንም የእሱ መጽሐፍ እና ጹሁፎች አሁን ለተፈጠረው ሕዝባዊ እንቢተኝነት መቀስቀስ መንስዔዎች ናቸው በሚል ምክንያት ከሕግ አግባብ ውጪ በሕመም ላይ እያለ በኮማንድ ፖስቱ በእስር እንዲማቅቅ መደረጉ ይታወሳል።

Egypt warns Ethiopia . ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች።




#Egypt warns #Ethiopia . ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች።
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሀገር ውስጥ የተነሳውን ህዝባቂ አመጽን ተከትሎ በተደጋጋሚ የግብጽ መንግስት እጅ አለበት ሲሉ መደመጣቸው ይታወቃል። ለዚህም የግብጽ መንግስት ምላሽ ይስጠን ሲሉ የሰነበቱ ሲሆን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ምንም መረጃ ሳትይዝ የግብጽን ስም ማጥፋቱና ታቁም ብሏል።
በካይሮ የሚኖሩ ስደተኞችን ፎቶ እያቀረቡ ግብጽ የምትረዳቸው ብሎ መናገር የአለማቀፍ ህጎችን አለማክበር ነው ሲል ያተተው መግለጫው ስደተኞች በሚኖሩበት ሀገር የራሳቸውን ፖለቲካ የማንጸባረቅ ሙሉ መብታቸው ነው ብሏል።
ዝርዝሩን ይመልከቱ።
ዝርዝሩን http://mereja.com/network/post/648/egyptian-official-calls-on-addis-ababa-to-stop-accusing-cairo-of

የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር እሳዛኝ እና አስገራሚ ገድሎች | በታምሩ ገዳ



የማርሽ ቀያሪው ፥ለበርካታ አትሌቶች መንገድ ጠራጊው እና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር እሳዛኝ እና አስገራሚ ገድሎች(ዝክረ ምሩጽ ይፍጠር)በታምሩ ገዳ

Tuesday, December 27, 2016

ፈረንሳይ ከፀሀይ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጭ መንገድ ይፋ አደረገች

ፈረንሳይ ከፀሀይ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጭ መንገድ ይፋ አደረገች
 ፈረንሳይ በዓለም የመጀመሪያ የሆነውንና የፀሃይ ሀይልን ወደ ኤሌክትሪክ የሚቀይር የሶላር ፓኔል መንገድ ከፍታለች።
1 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሶላር ፓኔል መንገዱ ለጎዳና መብራቶች በቂ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ይችል ይሆን በሚለው ላይ ሙከራ እየተደረገበት ነው።
solar_road_2.jpg
መንደጉ 2 ሺህ 880 ሶላር ፓኔሎች በመገጣጠም የተሰራ ሲሆን፥ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥም 280 ሜጋ ዋት ኤኬልትሪክ ማመንጨት እንደሚችልም ነው የተነገረው።
ይህም በአካባቢው ላይ ለሚገኙ እና ለገረቤት ከተሞች የጎዳና ላይ መብራቶች በቂ ኤሌክትሪክ እንደሚሰጥ ተገምቷል።
በሙከራው ላይ ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይም የመንገዱ እድሜ መሆኑም ተነግሯል።
መንገዱ ልክ እንደ ሌሎች አስፓልት መንገዶች ሁሉ እድሜ ይኖረዋል የተባለ ሲሆን፥ በየእለቱም 2 ሺህ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም አለው ተብሏል። 
የፀሀይ ሀይልን ወደ ኤሌክትሪክ የሚቀይር የሶላር ፓኔል መንገድ ፕሮጀክት 5 ሚሊየን ዩሮ የፈጀ ሲሆን፥ ወጪውም በፈረንሳይ መንግስት መሸፈኑ ነው የተገለጸው።

የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን በጥቁር ባህር ላይ ተከሰከሰ


የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን በጥቁር ባህር ላይ ተከሰከሰ
ኢሳት (ታህሳስ 17 ፥ 2009)
ንብረትነቱ የሩሲያ የሆነ ወታደራዊ አውሮፕላን ዕሁድ በጥቁር ባህር ላይ ተከሰከሰ። የገቡበት ያልታወቀ ከ90 በላይ ሰዎችን ለማግኘት ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑን ሩሲያ አስታወቀች።
ይኸው ወደ ሶሪያ በማቅናት ላይ የነበረው አውሮፕላን ወታደሮችን፣ ሙዚቀኞችን፣ እንዲሁም ጋዜጠኞችና የበረራ ባለሙያዎችን ይዞ በማቅናት ላይ እንዳለ ሶቺ ተብላ ከምትጠራ የባህር ዳር አቅራቢያ ከተማ መከስከሱን የሩሲያ ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
የሃገሪቱ ወታደራዊ ባለስልጣናት ወታደራዊ አውሮፕላኑ 92 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበር ያስታወቁ ሲሆን፣ የመከስከስ አደጋው በምን ምክንያት የደረሰ እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን ተናግረዋል።
ከ100 የሚበልጡ ጥልቅ ዋናተኞችን ጨምሮ መርከቦች፣ አውሮፕላኖችና፣ ሄሊኮፕተሮች በነፍስ አድን እና አውሮፕላኑ ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆን፣ በእስካሁን ፍለጋ የ11 ሰዎች አስከሬን መገኘቱ ታውቋል።
መንገደኞቹን በነፍስ የማግኘቱ ዕድል ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ የሚናገሩት የነፍስ አድን ሰራተኞች ከአስራ አንዱ አስከሬን በተጨማሪ 154 የሚደርሱ የሰውነት ክፍሎች መገናኘታቸውንም ይፋ አድርገዋል።
የሩሲያ የመከላከከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ሜጀር ጄኔራል ኢጎር ካናሼንኮቭ የፍለጋው ዘመቻ ለ24 ሰዓት ያለማቋረጥ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በፍለጋው የተገኙ 10 አስከሬኖች እና 86 የሰውነት ክፍሎች ወደ ሞስኮ በመጓጓዝ ማንነታቸውን የመለየት ስራ እየተካሄደ መሆኑን ቃል-አቀባዩ አክለው አስታውቀዋል።
ቱፓልብ-154 የሚል መጠሪያ ያለው ይኸው ወታደራዊ አውሮፕላን ከሶቺ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ከተነሳ ከሁለት ደቂቃ በኋላ ከአየር ትራፊክ ጋር የነበረው ግንኙነት የተቋረጠ ሲሆን፣ አደጋው የሽብር ድርጊት እንደማይሆን ይታመናል ሲሉ የሩሲያ የትራንስፖርት ባለስልጣናት ለመገኛኛ ብዙሃን አስረድተዋል።
ባለስልጣኑ አደጋው ከሽብር ጋር እንደማይያያዝ ቢገልፁም ለአውሮፕላኑ መከስከስ የሰጡት ምክንያት አለመኖሩን ዘግቧል።
መነሻውን ከሞስኮ አድርጎ የነበረው ወታደራዊ አውሮፕላኑ በሶቺ ከተማ ነዳጅ ለመሙላት አርፎ እንደነበር የሚናገሩት ባለስልጣን መንገደኞቹ በሶሪያ ለሚገኙ የሩሲያ ወታደሮች የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ በማቅናት ላይ እንደነበሩ ገልጸዋል።
የአደጋው መድረስ ተከትሎ ሩሲያ ሰኞ የሃዘን ቀን እንዲሆን የደነገገች ሲሆን አደጋ የደረሰበት አውሮፕላን ላለፉት 33 አመታት ጥገናዎች እየተደረጉለት በአገልግሎት ላይ እንደነበር ታውቋል።
ሩሲያ አውሮፕላኑ ለሲቪል አገልግሎት የማትጠቀመው መሆኑም ተነግሯል። ይሁንና ቱፓልቭ-154 የተሰኙ 50 አውሮፕላኖች በአሁኑ ወቅት በሩሲያና በጥቂት ሃገራት ውስጥ አገልግሎት ላይ እንደሆኑ ለመረዳት ተችሏል።

ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን በሶማሌ ድንበር በኩል ከሃገር ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ



በሶማሌ ክልል ድንበር አቋርጠው ከሃገር ሊወጡ የነበሩ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ማክሰኞ ገለጸ።
የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት (IOM) በበኩሉ የመንን ጨምሮ ከተለያዩ የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት መውጫን አጥተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገር ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ እያለ ማክሰኞ ማለዳ በጭነት ተሽከርካሪዎች ተጭነው በሶማሌ ክልል ድንበርን አቋርጠው ለመውጣት የሞከሩ 105 ኢትዮጵያውያን በቁጥርር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የክልሉ ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጿል።
በጸጥታ ሃይሎች ከተያዙት መካከል 24ቱ ሴቶች ሲሆኑ ከሁለት የጭነት ተሽከርካሪ ሾፌሮች መካከል አንደኛው አምልጦ በፍለጋ ላይ መሆኑ ታዉቋል።
ከኢትዮጵያ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣትን ተከትሎ መንግስት በድንበር አካባቢ ጥብቅ የተባለ ቁጥጥር ተግባራዊ ማድረጉ ይታወሳል።
ይሁንና አሁንም ድረስ በጎረቤት ሶማሊያ ኬንያ እና ሱዳን በኩል ወደ ተለያዩ ሃገራት የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ ሲሆን፣ በተያዘው የፈረንጆች አመት ብቻ 90ሺ ኢትዮጵያውያን ጦርነት ዕልባት ወዳላገኘባት የመን መሰደዳቸውን የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
የስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጸው ድርጅቱ በማላዊ እስር ቤቶች ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ይገልጻል።
እንዲሁም ጦርነት ዕልባት ወዳላገኘባት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዕልባት ባለማግኘቱ ሳቢያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ችግሩን ለመቅረፍ በኢትዮጵያ ትምህርታዊ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በሞዛምቢክ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በጉዞ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን የትራፊክል አደጋ ደርሶባቸው ከ15 የሚበልጡት ህይወታቸው ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል።
ባለፈው አመት በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የቆየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች በመሰደድ ላይ መሆናቸውን የተለያዩ አካላት ይገልጻሉ።

ሕወሓት የአርበኛ ጎቤ መልኬ ቤተሰቦች ጋር የሚያሸማግሉትን ላከ


የጎንደር ሕብረት ዘጋቢ ዞብል ከጎንደር እንደዘገበው በአሁኑ ወቅት የሕወሓትን ሰራዊት እየተፋለመው የሚገኘው አርበኛ ጎቤ መልኬ ቤተሰቦች ጋር ሕወሓት አማላጅ በመላክ አስታርቁኝ አለ:: እንደ ዘጋቢው ገለጻ ከሆነ ከቤተሰቡ በኩል የተገኘው ምላሽ አያገባንም የሚል ነው::

ዞብል በዘገባው አርበኛ ጎቤ ሕወሃት የወልቃይት የአማራ ማንነት እና የነጻነት ጥያቄ ባነሱ ዜጎች ላይ በወሰደው ግድያ፣ እስራት እና ድብደባ ተማረው ሕወሃትን እስከወዲያኛው ለማስወገድ ቆርጠው በመነሳት ዱር ቤቴ ካሉት አርበኞች (የነጻነት ታጋዮች) መካከል አንዱ ናቸው። ሕወሃት በአርበኛ ጎቤ የሚመራውን እና ሌሎችም የነጻነት ሃይሎች እያደረጉ ያሉትን የአርበኝነት ተጋድሎ በእንጭጩ ለመቅጨት ሳያሰልስ ወደ ስፍራው ጦሩን እያሰማራ ባለበት ሁኔታ ነው እንደወትሮው ሁሉ የአርበኛ ጎቤን ቤተሰቦች በማስገደድ፣ በማስፈራራት እና በመለማመጥ “ከአርበኛ ጎቤ ጋር ሸምግሉኝ” በማለት ላይ የሚገኘው። እንደ ዞብል ዘገባ ከሆነ የአርበኛ ጎቤ ቤተሰቦች ለሕወሃት “አስታርቁኝ” ጎትጎታ የሰጡት ምላሽ፣ “…ስለ ጎቤ እኛ ሽምግልና መቀመጥ አንችልም እራሱን ወደአለበት ቦታ ሒዳችሁ እንደፈለጋችሁ አድርጉት” የሚል ነው።
ሃብትና ንብረቱን ጥሎ በረሃ በመግባት እየታገለ የሚገኘው አርበኛ ጎቤ መልኬና የሚመራው ጦር የኢትዮጵያን ሕዝብ ድጋፍ እንደሚፈልግ መግለጹ የሚታወስ ነው::
ይሁንና ሕወሃቶች ተስፋ ባለመቁረጥ የአርበኛ ጎቤ ቤተዘመዶችን ሁሉ እያፈላለጉ “ሂዱና ከመንግስት ጋር አሸማግሉት” በማለት ላይ ይገኛሉ። ሕወሃት ከዚህ ቀደም ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ በርካታ ነጻነታቸውን ለመቀናጀት ዱር ቤቴ ያሉ አርበኞችን በሽምግልና ስም ከመለሰ በኋላ ለእስርና ሞት እንደሚዳርጋቸው ይታወቃል።

በትግራይ ክልል መንግስት የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ቅርሶች መዘረፋቸውን እቃወማለሁ



Abraham Zerihun እባላለሁ ። ሰሞኑን የትግራይ ክልል መንግስት ለብአዴን ተላላኪዎቹ በጻፈው ደብዳቤ ላይ በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን በሙሉ ተሰብስብሰው ወደ ትግራይ እንዲላኩለት አዟል ። ከዚህ በፊት በርካታ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ቅርሶች መዘረፋቸውና ማንም ተጠያቂ ሳይኖረው መቅረቱ ይታወሳል ። አሁንም በብአዴን በኩል ሊሰበሰብ የታሰበው ታሪካዊ ቅርሶቻችን ወደ ትግራይ የመላክ ዘመቻ የአማራውን ህዝብ መብት የሚጋፋ በመሆኑ እነዚህ ቅርሶች ከነባር ቦታቸው መነሳት እንደሌለባቸው አምናለሁ ። ስለሆነም ይሄንን ህገ ወጥ የቅርስ ዘረፋ በጽኑ እቃወማለሁ ። የአማራ ህዝብ መብት ከቅርሶቻችን ጋር አብሮ ይከበር!!!
#Save_Our_Historical_Artifact
Image may contain: text

ዘ-ሐበሻ ጠቅላላ ዕውቀት: በ2016 ዓ.ም ሕይወታቸውን ያጡ 19 ታዋቂ ኢትዮጵያውያን



(ዘ-ሐበሻ) የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ሊጠናቀቀ የ2 ቀናት ዕድሜ ቀርቶታል:: ባሳለፍነው የ2016 ዓ.ም ሕወሓት በሚመራው መንግስት የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሕይወት አልፏል:: የእሬቻው ጭፍጨፋን ጨምሮ በበኦሮሚያ፣ ጎጃምና በጎንደር እንዲሁም በኮንሶ በተጨማሪም በዲላ ከተማ የተፈፈጸሙ የዘር ማጥፋቶችም ሳይጠቀሱ የማያልፉ ጠባሳዎቻችን ናቸው::
ይህን በሌላ ዝግጅት የምንመለስበት ይሁንና ለዛሬው የዘ-ሐበሻ የጠቅላላ ዕውቀት ዝግጅታችን ይዘን የቀረበነው በዚህ በተገባደደው 2016 ሕይወታቸውን ያጡ 19 ታዋቂ ኢትዮጵያውያንን ይሆናል:: የረሳናቸው ካሉ ቀድመን ይቅርታ እየጠየቅን እንድትመለከቱት እንጋብዛለን::

መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳ ኢንተርኔት በማቋረጡ 9 ሚ. ዶላር አጥቷል ተባለ



ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው  ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅና ከዚያ በፊት በነበረው ሁኔታ የኢንተርኔት መቆራረጥና መታገድ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ማድረሱ የተጠቀሰ ሲሆን  ባለፈው አንድ ዓመት አገሪቱን 9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማሣጣቱን የአሜሪካው ብሩኪንግ ኢንስቲቲዩት ይፋ ያደረገው ጥናት አመልክቷል። ዴልዮት የተባለው ዓለማቀፍ አማካሪ ተቋም በበኩሉ፤ የሞባይል ኢንተርኔት መዘጋት ሀገሪቱን በቀን 5 መቶ ሺህ ዶላር እያሳጣት ነው ብሏል፡፡
በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞና ግጭቶች መከሰታቸውን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቆራረጥ፣ ሃገሪቱን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ አሳጥቷል ብሏል- ዴልዮት፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎት መቃወስ የኢኮኖሚ እድገቱን እንዲቀዛቀዝ አድርጓል ያለው ‹‹አፍሪካን ቢዝነስ››፤ ፈጠራዎች እንዳይበረታቱ፣ የገቢ ታክሶች በአግባቡ እንዳይሰበሰቡና ነጋዴዎች በቴክኖሎጂው ላይ ያላቸው እምነት እንዲሸረሸር ማድረጉን… የብሩኪንግ ኢንስቲቲዩት ም/ፕሬዚዳንት ዳረል ዌስትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ዘመናዊ የኢኮኖሚ እድገት በኢንተርኔት ላይ ጥገኛ መሆኑን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ታዳጊ ሃገራት በአመታዊ ጠቅላላ አገራዊ ምርት እድገታቸው ላይ የ1.35 በመቶ ድርሻ እንዳለው ያመለክታል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀበት ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በተለይ የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ግንኙነት መቋረጡ፣ በመንግስት ገቢ ላይ ጉዳት ከማድረሱ በተጨማሪ የዕለት ተለት ስራቸው በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር ለተቆራኙ ነጋዴዎችም ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተለባቸው እንደቆየ ጠቁሟል፡፡
ከኢንተርኔት አገልግሎት ባሻገር ከፍተኛ ገቢ ከሚያስገኙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንዱ የሆነው የተለያዩ የተንቀሳቃሽ ስልኮች መተግበሪያ (Application) እየተገደበ መሆኑን ሪፖርቱ ይጠቁማል – ቫይበር፣ ዋትሳፕና ሜሴንጀር የመሳሰሉ የኢንተርኔት የግንኙነት አውታሮች በዚህ መንገድ እየተገደቡ መሆኑን በመጥቀስ፡፡
ባለፈው አመት በኢንተርኔት የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ላይ የተደረገው ጥናት፤ በአሜሪካ የኢንተርኔት አገልግሎት በአመት እስከ 966 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት፣ ከአጠቃላይ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ 6 በመቶ ድርሻ እንዳለው የተጠቆመ ሲሆን ሌሎች ሃገራት ግን ከዚህ ቴክኖሎጂ ማግኘት የሚገባቸውን ከፍተኛ ገቢ አገልግሎቱን በመገደብ እያጡ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የኢንተርኔት አገልግሎትን በመገደብ ከአፍሪካ በቀዳሚነት የተጠቀሰችው ሞሮኮ፤ በአመት 320 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷ የተጠቀሰ ሲሆን ኮንጎ 72 ሚሊዮን ዶላር፣ አልጄሪያ 20 ሚሊዮን ዶላር፣ በአመት አጥተዋል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ በበኩሏ፤ ባለፈው 1 ዓመት 9 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
ከአፍሪካ ሃገራት ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያና ግብፅ የተሻለ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳላቸው የተጠቆመ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ናሚቢያና ደቡብ ሱዳን የኢንተርኔት አገልግሎታቸው ዝቅተኛና አርኪ አለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤትም ሆነ ከኢትዮ-ቴሌኮም ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች “ስብሠባ ላይ ናቸው” ሳይሳካልን ቀርቷል።

አለማየሁ አንበሴ

ሰዎች የሞት አፋፍ ላይ ሲሆኑ ምን ያወራሉ…?

ሰዎች የሞት አፋፍ ላይ ሲሆኑ ምን ያወራሉ…?
 ሰዎች በሞት አፋፍ ላይ ሲሆኑ አጠገባቸው ላሉ ሰዎች ምን ያወራሉ የሚለው በርካቶችን ሊያነጋገርር ይችላል።
የስነ መለከቶት ተማሪ የነበረው እና በኋላ ላይ በሆስፒታል ውስጥ በማይድን በሽታ የተያዙ ሰዎችን የሚያማክር ቄስ የሆነው "የOn Living" መጽሃፍ ደራሲው ኬሪ ኤጋን ህይወታቸው ለማለፍ ከጫፍ ላይ የደረሱትን ሰዎች በማናገር በኩል ብዙ ልምድ አለው።
ኬሪ ኤጋን በዚህ ዘርፍ ላይ ከተማሪነት አንስቶ ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ ሲሆን፥ ከዚህ በመነሳትም የረጅም ጊዜ ልምዱን አካፍሏል።
ኬሪ ይናገራል፥ “ከ13 ዓመት በፊት ገና ተማሪ እያለሁም ይሁን አሁን ከሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎችን ሆስፒታል፣ መኖሪያ ቤት አልያም እንክብካቤ በሚደረግላቸው ቦታ በመሄድ አናግራለቸዋለሁ፤ ሰዎች ሊሞቱ ሲሉ ስለምን ማውራት ይፈልጋሉ ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እችላለው”።
“በርካቶቻችሁ ሰዎች ለመሞት ከጫፍ በሚደርሱበት ጊዜ ስለ ፈጣሪያቸው አልያም ንሰሃ ስለ መግባት ብቻ ነው የሚያወሩት ብላችሁ ልትገምቱ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አይደለም” ይለናል።
“ሰዎች ሰዎች የሞት አፋፍ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ በብዛት የሚያወሩት ስለ ቤተሰባቸው ነው፤ ስለ እናታቸው፣ አባታቸው፣ እህታቸው፣ ወንድማቸው፣ ልጆቻቸው፣ ስለ ትዳር አጋራቸው ነው የሚያወሩት” ሲልም ኬሪ ተናግሯል።
“በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎች በውስጣቸው ስላለ ፍቅር፣ ለሰዎች ስለሰጡት ፍቅር፣ ከሰዎች ስላጡት ፍቅር፣ በቅጡ ሳይጠቀሙበት ስለቀሩት ፍቅር፣ በጣም ከመጠን በላይ ስላፈቀሩት ሰው እና የመሳሰሉትን ማውራትም ምርጫቸው ነው” ሲል ኬሪ ይናገራል።
“ሰዎች ለመሞት የመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ ሲሆኑ ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዴት እንደተማሩ ማውራትን ይመርጣሉ” ያለው ኬሪ፥ ለመሞት በመጨረሻዋ ደቂቃ ምራቃቸውን አፋቸውን ሞልቶ ነገሮች አልታያቸው ሲል እንኳ እጃቸውን እያወራጩ እማማ፣ አባቴ፣ እናቴ እያሉ ቤተሰቦቻቸውን ይጣራሉ” ይላል።
“ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ያልገባኝ እና አሁን የተገለጸልኝ ነገር፤ ሰዎች ለመሞት ከጫፍ ላይ ሲደርሱ ስለ ፈጣሪ ሳይሆን ስለቤተሰቦቻቸው ነው ለቄሶች የሚናገሩት፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ሰዎች ስለ ፈጣሪያቸው በዚህ መልኩ ስለሚናገሩ ነው፤ ይህ ደግሞ የህይወትን ትርጉም የምንገልጽበት መንገድ ነው፤ የሰው ልጆች ስለመኖራቸው በሀይማኖታዊ መንገድ ለሚቀርበው ጥያቄም ምላሽ የሚሰጥ ነው” ሲልም ኬሪ ያብራራል።
“በስነ መለኮት እና እና በሌሎች ፅንሰ ሀሳቦች ላይ እንደተቀመጠው ኑሮን የምንኖረው በጭንቅላታችን ውስጥ አይደለም” የሚለው ኬሪ፥ “ኑሮን በተወለድንበት ቤተሰብ፣ በፈጠርነው ቤተሰብ፣ ጓደኞቻችን እንዲሆኑ ከመረጥናቸው ጓደኞቻችን ጋር በመሰረትነው ቤሰብ ውስጥ ነው የምንኖረው” ይላል።
“ይህ ቦታ ኑሮን የምንመሰርትበት ስፍራ ነው፣ ይህ የኑሮን ትርጉም የምናገኝበት ስፍራ ነው፣ ይህ ቦታ የምንኖርበት ምክንያት ግልጽ የሚሆንበት ስፍራ ነው” በመናለትም ኬሪ ስለቤተሰብ ያብራራል።
“ቤተሰብ ማለት ስለፍቅር መጀመሪያ ልምድ የምናገኝበት፣ ለጀመሪያ ጊዜ በሆነ ሰው የምንጎዳበት እንዲሁም ሁሉምን መገፋቶች ፍቅር እንደሚያሸንፍ የምንማርበት ነው፤ ይህ ፍቅርን የምንማርበት ስፍራ ሀይማኖታዊ ጥያቄዎችን ማቅረብ የምንጀምርበት ስፍራም ነው” ይላል ኬሪ።
“ሰዎች በመጨረሻዋ ሰዓት ቤተሰባዊ ፍቅራቸውን በተግባር ሲገልጹ አይቻለው” የሚለው ኬሪ፤ ባል ምንም የመኖር ተስፋ የሌላትን ሚስቱን ፊት በውሃ የራሰ ፎጣ በመጠቀም ሲጸዳዳ፣ ለረጅም ዓመታት በህመም ምክንያት በእናቷ የተረሳች ልጅ በእናቷ አፍ ላይ ተከድና ፍቅሯ ስታካፍል” ተመልክቻለው።
“ሚስት ከሞተው ባሏ ጭንቅላት ስር አንሶላ ስታስተካክል ከመመልከት በላይ ሰዎች ፍቅርን ሲገላለፁ ማየት የትም አይገኝም” ሲልም ኬሪ ይናገራል።
“የመኖርን ትርጉም በመወያየት ማግኘት እልችልም፤ የመኖርን ትርጉም ከመፅሀፍት፣ ከቤተክርስቲያን፣ ከመስጊድ አልያም ከተለያየ የአምልኮ ስፍራ ማግኘት አንችለም” ይላል ኬሪ።
“ፈጣሪ ፍቅር ነው ካልን እና እውነት መሆኑን ካመንበት፤ ስለ ፈጣሪ የምናውቀው ስለ ፍቅር ስናውቅ ነው፤ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው የፍቅር ትምህር ቤት ደግሞ ቤተሰብ ነው” ሲልም ኬሪ ያብራራል።
“አንዳንዴ ሁሉም የቤተሰብ ፍቅር ሙሉ ላይሆን ይችላል፣ ቤተሰብ በተለያዩ ምክንያቶች ተቃርኖ ውስጥ ገብተው ሊጋጩ ይችላሉ፣ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያሳለፉ ሰዎችንም ቢሆን አናግሬያለው” የሚለው ኬሪ፥ በቤተሰባቸው ውስጥ ፍቅርን የማያውቁ ሰዎች እንኳ ፍቅር ማግኘት እንደነበረባቸው ያውቃሉ ብሏል።
“እነዚህሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ምን እንደጎደለ እና ከልጅነታቸው አንስቶ ፍቅርን ማግኘት እንደበረባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ” ብሏል።
“ፍቅር ሙሉ በማይሆንበት ጊዜ ቤተሰብ ይበጣበጣል፤ በዚህ ጊዜም አንድ ነገር መለመድ አለበት የሚለው ኬሪ “ይህም ይቅርታ ማድረግ ነው” ሰዎች በእምነታቸው ውስጥ ይቅርታ ማድረግን መልመድ አለባቸው ሲልም ይናገራል።
“እኛ ለሞት ከተቃረቡ ሰዎች ጋር ስናወራ ስለ ፈጣሪ ለማውራት የሚያግዘንን ስነ መለኮታዊ ቃል አንጠቀምም” ያለው ኬሪ፥ “በሚሞቱበት ጊዜ እርስ በእርስ በመዋደድ እና ይቅርታ በመደራረግ ልጆቻቸውን ስለ ፈጣሪ ካስተማሩት ሰዎች መማር አልብን” ይላል።
ምንጭ፦ cnn.com/health
በሙለታ መንገሻ

በሱዳን በኩል ከአልቀዳሪፍ ለማጥቃት የተንቀሳቀሰው የህወሀት አንድ ሽምበል ኮማንድ ፓስት ተደመሰሰ::




በሱዳን በኩል ከአልቀዳሪፍ ለማጥቃት የተንቀሳቀሰው የህወሀት አንድ ሽምበል ኮማንድ ፓስት ተደመሰሰ::
አዘናግቶና አድብቶ ከጀርባ በመምታት የነፃነት ሐይሎችን ለመደምሰስ ከአል-ቀዳሪፍ ወደ ሁመራ እና አካባቢው የተነቃነቀው 400 የሚጠጋ የህወሀት ቅጥረኛ ሰራዊት መሽገው ከነበሩ የነፃነት ሀይሎች ጋር የገጠመውን ድንገተኛ ውርጅብኝ ለመመከት ባደረገው ማፈግፈግ ከሌላኛው የህወሀት የጦር ቀጠና በመግባቱ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ከ 24 ተኛ ክ/ጦር የውስጥ አርበኞች የደርሰን መረጃ አመለከተ::
የህወሀት ወታደራዊ ኮማንደሮች ክስተቱ ሆን ተብሎ የተቀናበረ ነው በሚል ድምዳሜ ማጣራት በማድረግ እንደተጠመዱ እና ከመመሪያ ግንኙነት እና ያልተጠና ትእዛዝ ሰጥተዋል በሚል የተጠረጠሩ መኮንኖች ድርጊቱ ድንገተኛና ከመከላከል አንፃር መወሰዱን አረጋግጠዋል::
ፍል ለኢትዬጵያ ህዝብ!!

የፌስ ቡክ ሰራዊት” ከቻይናው ” የ50ሳንቲም ሰራዊት” ጋር አንድና አንድ ነው




የፌስ ቡክ ሰራዊትና የ50ሳንቲም ሰራዊት

ሕወሓት በፍርሃት ያቋቋመው “የፌስ ቡክ ሰራዊት” ከቻይናው ” የ50ሳንቲም ሰራዊት” ጋር አንድና አንድ ነው. የቻይናው የ50ሳንቲም ሰራዊት ብዙ ሚሊዮን አባላት ያሉት የኮምኒስቶች ስብስብ ሲሆን አንድ ተቃዋሚን /አክቲቪስትን የሚያጥላላ ፖስት ለለጠፈ፣ኮሜንት የሰጠ የቻይና 50 ሳንቲም ማበረታቻ ይታሰብለታል. በዚህ አይነት በወር ጠቀም ያለ ጉርሻ በለጠፉት ፖስት መጠን ይገኛል.
በ200 የፌስ ቡክ መሪዎችና በ3000 ጀሌዎች በአቶ ሬድዋን ሁሴን የኮምዩኒኬሽን ሚኒስትርነት ዘመን ተመርቆ ስራ የጀመረው የሕወሓት የፌስ ቡክ ሰራዊት ዋና ዋና ሃላፊነቶች ተሰጥተውት በቻይና ሞዴል መስራት እየጀመረ ነው.የተቀበላቸውን የስራ ዝርዝሮች እንደሚከተለው እናቀርባለን


1. የሐሰት አካውንት መፍጠር - የፌስ ቡክ ሰራዊት ኮምፑዩተርና ኔትወርክ በየመስሪያ ቤቶች ቢሮዎች ተሰጥቷቸው በኦሮሞ፣በአማራ፣በትግራይ፣በሙስሊም፣በክርስቲያን ስም የሀሰት አካውንት በመፍጠር በየ ፔጁና በየ ተቃዋሚዎች ዌብ ሳይቶች እየገቡ ፖስት ይለጥፋሉ ኮሜንት ይጽፋሉ

2. የተሳሳተ መረጃ ማስተላለፍ -የፌስ ቡክ ሰራዊት የግንቦት ሰባት-የኦ.ፌ.ኮ ና የሌሎችም ፓርቲዎች አባል በመምሰል የተሳሳተ መረጃ ይሰጣሉ-ተቃራኒ ሃሳብ ያነሳሉ-ከፋፋይ ሃሳብ ያንሸራሽራሉ. አማራ በመምሰል ኦሮሞን ይሰድባሉ-ኦሮሞ በመምሰል አማራን ያዋርዳሉ -ሙስሊም በመምሰል ክርስቲያንን ክርስቲያን በመምሰል ሙስሊምን ያሰድባሉ.

3. የአክቲቪስቶች ስም ፌክ አካውንት መጠቀም - የታወቁ የፌስ ቡክ አክቲቪስቶችን ስምና ፕሮፋይል ፎቶ በመጠቀም ያደናግራሉ. በአክቲቪስቶች ስም ተቃራኒ ሃሳብ በመለጠፍ እምነት እንዲያጡ ያደርጋሉ.

4. የተቃዋሚ አመራሮችን ስም ያጠፋሉ -የተቃዋሚ አመራሮችን ስም እየጠቀሱ ሃሰተኛ ታሪክ እየፈጠሩና በፎቶ እያስደገፉ ተአማኒ እንዳይሆን ጥላሸት ይቀባሉ

5. ትግልን ማቃለል -የፌስ ቡክ ሰራዊት የህዝብን ትግል ያቃልላል. የጎንደር ገበሬን፣የግንቦት ሰባትን፣የኦሮሞ ህዝብን ትግል ያሳንሳል.የጥቂት ግለሰቦች የስልጣን ትግል እንደሆነ በማቃለል ይለጥፋል.የወጣቱ ጥያቄ የዲሞክራሲና የሃብት ፍትሃዊነት መሆኑን በማስተባበል የጥቂት ወጣቶች ስራ የማጣት እንደሆነ ያስተጋባሉ.

በህዝብ ትግል ላይ ወደሁዋላ የሚመልስ ሃሳብ ከተመለከታችሁ እሱ የህወሃት ቅጥረኛ የፌስ ቡክ ሰራዊት ነው. መከፋፈል፣ግጭት፣ልዩነት ለማንሳት የሚሞክር ሃሳብ ከፌስቡክ ሰራዊት ነው. ሁላችንም እነዚህን ከፋፋዮች አፍ ማዘጋት ይጠበቅብናል. ከፌስ ቡክ መረጃ መውሰድና መስጠት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት.

ናትናኤል መኮንን

በጐንደር ክፍለ ሀገር ከወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!!


በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ ወራሪውና ደም ጠጭው የህወሃት ፀረ-ሕዝብ ቡድን ጀግኖችን እያሳደዱ መግደል ማሰደድና ሀብታቸውን መዝረፍ የጀመረው ከዛሬ 40 ዓመት በፊት ቢሆንም የሚፈፀምባቸውን ግፍ በልባቸው አምቀው በመያዝ ጊዜና የሕግ የበላይነት ሲሰፍን በሕግ እንፋረዳለን ብለው ዝምታን የመረጡ ቢሆንም ተስፋፊው የሕወሃት ቡድን ማንኛውንም ጉዳይ ለማስፈፀምም ሆነ ለመማር በትግርኛ ነው እናንተም ትግሬዎች ናችሁ ትግሬ አይደለንም የምትሉ አባይን ተሻግራችሁ ትሄዳላችሁ እንጅ አማራዎች ነን እያላችሁ በትግራይ ክልል መኖር አትችሉም በማለት አካባቢውን ያቀኑትን ተወላጆች አሳዶ ከአካባቢው እንዲጠፉ ማድረጉ ይታወቃል።በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ሀብት ንብረታቸውን ተዘርፈው ተወልደው ያደጉበትን አጥቢያቸውን ለቀው ሄደው ተሰደው ከሚኖሩበት የጐረቤት አካባቢ ሰላዮችን በመላክና አፋኞችን አሠማርቶ የግድያ ወንጀል ላይ ተሰማርቷል።በዚህ ባሳለፍናቸው ሁለት ቀናት ውስጥም ሮጠው ያልጠገቡ የጐልማሳነት ዘመናቸውን ተደብቀው ለማሳለፍ ወደ አርማጭሆ ሄደው ከሚኖሩበት ገዳይ ኃይል በማሠማራት አካባቢው በተማረ የሰው ኃይልም እንዲደኸይ ለማድረግ ባለው እቅድ መሠረት ሁለት ቀምበጥ የወልቃይ ወጣቶችን ገድሏል።
እነሱም 1/ ዘውዱ ገብረእግዚአብሔር ዓለማየሁ እና 2/ ሙላው ከበደ ውብነህ ሲሆኑ በህወሃት አረመኔ የአጋዚ ጦር ግፍ ተፈጽሞባቸዋል።የተገደሉት ወንጀል ፈጽመው ወይም ጥፋተኛ የሚያደርጋቸው ክስ ቀርቦባቸው ሳይሆን በትግርኛ አንማርም፤ጉዳያችን ለማስፈፀም ማመልከቻ በትግርኛ አንጽፍም፤አማራዎች ነን፤ድንበራችን ተከዜ ነው፤እናንተ መጣችሁብን እንጅ እኛ አልመጣንባችሁም በማለታቸው ብቻ ነው ይህን የመሰለ ዘግናኝ ግፍ የተፈፀመባቸው።እነዚህ ሁለት ወጣቶች ከልጅነታቸው ጀምሮ በሳል አርቀው የሚያስተውሉና በትምህርታቸው ጎበዞች፤ሳቂተኛዎች ቁምነገረኛና ታማኞች ነበሩ።
**ዘውዱ ገብረእግዚአብሔር ዓለማየሁ፦ወልቃይት ቃብትያ ሻሃሸም ሚካኤል በሚባል ተወልዶ ያደገ እድሜው በ30ዎቹ ገደማ ሲሆን እስከ ስድስተኛ ክፍል በዚሁ ቦታ የተማረ ገና የአራተኛ ክፍል ተማሪ እያለ እንግሊዘኛን አቀላጥፎ የሚነገረው ዘውዱ እኔ አማራ ነኝ በትግርኛ አልማርም በማለት እናት አባቱን ጥሎ ወደ ጎንደር በመሄድ ፋሲለደስ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ከ7ተኛ እስከ 12ተኛ ከተከታተለ በኋላ በተከታታይ በነበረበት ህመም ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ግብርና ገባ።ተወልዶ ባደገበት መሬት የሚያርሰው አጥቶ በትግሬ ተወሮ እስከ ሱዳን ድረስ ሄዶ መሬት በመከራየት የሰሊጥና ጥጥ ማሽላ ያመርት ነበር።ማንነቴ ይመለስልኝ እኔ ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ በማለቱ ነብሰ ገዳዩና ወራሪው ወያኔ ህወሃት ሊያስረው ሲሞክር ከእስራት አምልጦ ወደ ወገኖቹ አርማጭሆ ውስጥ ገብቶ ህወሃትን ሲፋለም የነበረ ጀግና ነበር።**እኛ ሞተን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ስቃይና መከራ እስራት ሞት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማብቃት አለበት በማለት እንደ ክርስቶስ ለወገኖቹ ውድ የሕይወት ዋጋ ከፍሎ አለፈ ቤዛ ሆነ**።
**ኢኮኖሚስቱ አደራ ተቀባዩ ፤ታማኙ የወገን አለኝታው ከኔ በፊት ለወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ያለው የትግል አጋሩ ሙላው ከበደ ውብነህ፦በዚሁ በቃብትያ የተወለደ ሲሆን እድሜው ገና በ30ዎቹ አካባቢ ሲሆን በ1998 ዓ/ም በባህርዳር ዩኒቨችሲቲ ፔዳጎጅ ካምፓስ በኢኮኖሚክስ የመጀመርያ ዲግሪውን ያገኘና ተወልዶ ባደገበት አካባቢ በሁመራ ከተማ ሲሰራ የነበረ አማራ ነኝ በማለቱ በወያኔ ከሥራ የተሰናበተ ሲሆን የአባቱን ፈለግ በመከተል ወደ እርሻና ንግድ ገባ።በመጨረሻ ግን ለምን አማራ ነን አላችሁ ተብለው ጓዶቹ እነ ኮ/ሎኔል ደመቀ ዘውዱ፤አታላይ ዛፌ፤ጌታቸው አደመ፤መብራቱ ጌታሁን፤አለነ ሻማ፤ነጋ ባንቲሁን፤አዲሱ ሰረበ፤ንግሥት ይርጋ፤ጎይቶም አማረ፤አሊጋዝ አየለ፤ባየው ካሴ፤ሞላ ኃይሉ፤ሰለሞን ግዛቴ;ሊላይ ብርሃኔ፤ሰጠኝ አረሮ፤መሀመድ ያሲን፤አዛውንቱ የ70 አመት ሽማግሌ መኮንን ደስታ፤ሰፊሁን አበበ፤ዳኘው አቸነፈ፤ተሻገር ወልደሚካኤል፤ዮሐንስ ጠጋ፤አባተ ነጋ፤ዘውዱ ነጋ፤ገብረመስቀል ማማይ፤ወረታው አዛናው እና እንዲሁም እጅግ በርካታ የጐንደርና አካባቢው፤የባህርዳርና ባህርዳር አካባቢ ወጣቶች ጐልማሳዎች ጭምር በወያኔ ማጐርያ በሲኦል እስር ቤት የሚገኙ ብዙ አማራዎች የመገኘታቸው ሁኔታ ሕሊናው ሊቀበለው ባለመቻሉ ቤት ንብረቱን ጥሎ በአጠቃላይ ከወያኔ የሚደርስበትን ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከልና አማራነቱን ለማስከበር ዱር ቤቴ ብሎ የወጣ ጀግና ከዘውዱ ጋር በመሆን ከወያኔ(ህወሃት)ወታደሮች ጋር ተፋልመው ታሪክ ሠርተው አለፉ።
ተወልደው ባደጉባት ቧርቀው ባልጠገቡባት ወልቃይት ልዩ ቦታ “”ቃብታያ ወልቃይት በክብር ፤በነፃነት የማልኖርብሽ መንደር ከሆንሽ ሞቼ በክብር አጽሜ የሚያርፍብሽ የክብር መቃብሬ ትሆኛለሽ””በማለት በ10/04/2009 ዓ/ም ከቀኑ7.00 ገደማ የቀብር ስነስራታቸው ተፈጽሟል።እነዚህ ሁለት ወጣት ጀግኖች የጀመሩትና የሕይወት ዋጋ የከፈሉበት ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ በቅርቡ ይመለሳል።የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ አማራ ነው፤የአማራ ማነነት በቅርቡ ይመለሳል፤ድንበራችን ተከዜ ነው!!
ታጋይ(ጀግና) ይሞታል ትግሉ ግን አይሞትም!!

Monday, December 26, 2016

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ነገ ፍርድ ቤት እንደማይቀርብ ታወቀ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በ2006ዓ.ም ዕንቁ መጽሔት በዋና አዘጋጅነትበሚሰራበት ወቅት የመጽሔቱ አምደኛ የሆነውን ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን ጽሑፍ በሆነው ‹‹የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉ ሃውልቶች የማንና ለማን ናቸው)›› በሚል ርዕሥ የተጻፈ ጽሑፍ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል ብጥብጥ ተነስቶ ወደ 40.000 ብር የሚገመት ንብረቶች ወድሟል›› ሲል የፌዴራል አቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ ምክንያት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች ይቀርባሉ፡፡አቃቤ ሕግ ‹‹ግዙፍ ባልሆነ የወንጀል ድርጊት የሀገሪቷን ህዝቦች አንድነት ለመለያየት በማሰብ›› የሚል ይዘት ያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳንና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን እያንዳንዳቸው የ20.000 ሺህ ብር ዋስትና ተጠይቆባቸው በወቅቱ የተጠየቀውን የዋስትና ማስያዝ ባለማቻላቸው ምክንያት ለአንድ ሳምንት ያህል በቂሊንጦ እስር ቤት ከታሰሩ በኋላ የዋስትና ማስያዟው በሰዎች ትብብር ተከፍሎ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን በቀጠሯቸው ቀን እየተገኙ በመከራከር ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍርድ ቤቱም የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ታኅሳስ 19 ቀን 2009ዓ.ም የቀጠረ ቢሆንም የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ፍርድ ቤት እንደማያቀርበው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በተለያዩ የግል ጋዜጦች ላይ የሰራ ሲሆን በ‹‹አውራምባ ታምይስ›› እና በ‹‹ፍትህ›› ጋዜጦች ላይ በከፍተኛ ሪፖርተርነት፣ በ‹‹ዕንቁ›› መጽሔት እና›› ‹‹በቀዳሚ ገጽ›› ጋዜጦች›› ‹‹በአዲስ ገጽ መጽሔት›› በዋና አዘጋጅነት የ‹‹ሚሊዮኖች ድምጽ›› ጋዜጣ በምክትል አዘጋጅነት የሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በኮማንድ ፖስቱ በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከአንድ ወር በላይ ታስሮ የሚገኝ ሲሆን ኮማንድ ፖስቱ ፍቃድ ካልሰጠ በስተቀር ነገ ፍርድ ቤት እንደማይቀርብም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ብሪታኒያ በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 400 ወታደሮችን የማሰማራት እቅድ እንዳላት ገለፀች።


የአገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጠቅሶ ሲሲቲቪ እንደዘገበው፥ አሁን የሚላኩት ወታደሮች በዚያ የሚገኘውን 12 ሺህ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ጦር ለማጠናከር ነው።
ወታደሮቹም በብዛት የህክምና እና ምህንድስና አገልግሎት የሚሰጡ እንደሚሆንም ነው የተመለከተው።
ደቡብ ሱዳን ከፈረንጆቹ 2013 ታህሳስ ወር ጀምሮ ጦርነት ላይ ትገኛለች።
ይህን ግጭት ለማስቆም በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና በተቀናቃኛቸው በኩል የሰላም ስምምንቶች ሲፈረሙ ቢቆዩም በተደጋጋሚ ሲፈርሱ ታይትዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተሰናባቹ ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፈጥኖ ለዚያች አገር ቀውስ ምላሽ ካልሰጠ የከፋ ጥፋት እንደሚደርስ አስጠንቅቀዋል።

በጎንደር በህዝብ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ 10 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

በጎንደር በህዝብ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ 10 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

 ኢሳት ዜና :- 15 ሰዎችን ጭኖ ከጎንደር  ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽካርካሪ ጠዳ ከተማ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ 10 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 4 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል።
የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ሲኖ ትራክ እየተባለ በሚጠራ የጭነት ተሽከርካሪ ተመትቶ ሳይገለበጥ እንዳልቀረ ወኪላችን ገልጿል።
አብዛኞቹ ሟቾች ነገ የሚከበረውን ወንቅሸት ገብርኤል ለማክበር በመጓዝ ላይ የነበሩ ናቸው።

“ወርቅነህ ገበየሁ ካይሮ የኦሮሞ ተቃዋሚ ኃይሎችን ትደግፋለች ማለታቸው የሁለቱን ሀገራት ወዳጃዊ ግንኙነት ይጎዳዋል” – ግብፅ


የግብፅና የኢትዮጵያ መንግስት ሌላ የውዝግብ ምዕራፍ |  የአዲስ አድማስ ዘገባ
– “የኢትዮጵያ መንግስት ግብፅን ያለማስረጃ ከመወንጀል ይቆጠብ” – ግብፅ
– “የግብፅ መንግስትን ይፋ ምላሽ እየጠበቅን ነው” – ኢትዮጵያ
አለማየሁ አንበሴ
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በማስረጃ ላይ ያልተመሰረተ ውንጀላ ከማቅረብ እንዲቆጠብ ያስጠነቀቁ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ ‹‹ላቀረብኩት ጥያቄ አሁንም ቢሆን ይፋ ምላሽ እየጠበቅሁ ነው›› ብሏል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኃላፊ በመግለጫቸው፤ “የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፣ ባለፈው ሰኞ ካይሮ የኦሮሞ ተቃዋሚ ኃይሎችን ትደግፋለች ማለታቸው የሁለቱን ሀገራት ወዳጃዊ ግንኙነት ይጎዳዋል” ብሏል፡፡
መቀመጫው በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ለሆነው “ዘ ሚድል ኢስት ሞኒተር” ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጡ የተባሉ ስማቸው በይፋ ያልተገለፀ አንድ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊ፤ “ሀገራቸው ተቃዋሚዎችን እንደምትደግፍና በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ መግባቷን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ማስረጃ እንደሌለው በመጠቆም፣ በግብፅ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችም በማናቸውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ የተጣለባቸውን የህግ ገደብ አክብረው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
“ግብፅ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የምትገባበት ምንም ምክንያት የላትም” ያሉት ባለስልጣኑ፤ በየጊዜው ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጉዳዮች የሚወዛገቡ ቢሆንም ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ሊካድ አይገባም ብለዋል – የኢትዮጵያ መንግስት መረጃ ላይ ካልተመሠረተ ውንጀላ እንዲታቀብ በማስጠንቀቅ፡፡
ባለስልጣኑ ሰጡ በተባለው መግለጫ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሰሩ፤ ‹‹የሽብር ቡድኖችንና ፀረ-ሠላም ሃይሎችን አንዳንድ የግብፅ ተቋማት እንደሚደግፉ ከተለያዩ ማስረጃዎች ለማወቅ መቻሉን ጠቁመው፣ ከኢትዮጵያ ጋር በመልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ የሚገኘው የግብፅ መንግስት ይፋዊ ማብራሪያ እንዲሰጥ መጠየቁንና እስካሁንም ይፋዊ ምላሽ አለመገኘቱን አስታውቀዋል፡፡
በሁለቱ ሃገራት መካከል ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳ በውይይትና በድርድር ሊፈታ ይገባል የሚል ፅኑ አቋም የኢትዮጶያ መንግስት እንዳለው የጠቀሱት አቶ ተወልደ በአባይ ጉዳይ ግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በመልካም የስምምነት ሂደት ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሃገሪቱ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን እንደምትረዳ ለቀረበባት መረጃ ምላሽ እንዲሠጠው ላቀረበው ጥያቄ አሁንም የግብፅ መንግስት ይፋዊ ምላሽ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል፡፡

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 125 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ በምርመራ እያጣራ መሆኑን የፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

የአርበኛ ጎቤ መልኬ ጦር የወያኔን ጦር ዳግም ቀጣ – የወያኔ ጦር በ6 መኪና ተጭኖ ከሁመራ ወደ መተማ አቅጣጫ እያመራ ነው




(ዘ-ሐበሻ) በአርበኛ ጎቤ መልኬ የሚመራው ጦር በትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ መቀጠሉ ተሰማ::
ከትናንት በስቲያ በሕወሓት ወታደሮች ተከቦ የነበረው የአርበኛ ጎቤ ጦር በሕወሓት ወታደሮች ላይ የበላይነቱን ወስዶ ከከባበው ከወጣ በኋላ ትናንትናም የሕወሓት ጦር ኃይሉን አጠናክሮ ወደ የጎቤን የሕዝብ ጦር ሊያጠቃ ሞክሮ በድጋሚ ሽንፈትን ተከናንቦ ተመልሷል::

በዛሬው ዕለትም እንዲሁ የሕወሓት ጦር በጎቤ ኃይል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቢሞክርም እንደገና መቀጣቱን እና የጎቤም ጦር በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የተሰራጨው መረጃ አመልክቷል::

በሌላ በኩል አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሐንስ “በዛሬው እለት ከሁመራ የተነሱ በ6 መኪና የሞሉ የወያኔ ወታደር ወደመተማ አቅጣጫ እያመሩ ነው። ስናር ላይ መድረሳቸው ታውቋልና በመተማ ቋራና አካባቢው ዝግጅት እንዲደረግ መልእክት ይተላለፍ” ሲል ጥሪውን አቅርቧል::

አክቲቭስቱ ጨምሮም “ጎንደር ላይ በየአቅጣጫው የተወጠረው ወያኔ ያለ እረፍት የወታደር እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። የመኸር ስራውን በጥድፊያ የተያያዘውን ገበሬ እጅግ የፈራው ወያኔ የተደገሰለትን ለማደናቀፍ ሲል አስቀድሞ በየቦታው ጦርነት እያስነሳ ይገኛል። ወያኔ የፈራውን እንደማያመልጠው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት በሙሉ ልብ ይናገራሉ።” ሲል ያለውን መረጃ ለሕዝብ አካፍሏል::

Sunday, December 25, 2016

በምስራቅ አፍሪካ ለምግብ እርዳታ ከተጋለጡት ግማሽ ያህሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ተመድ ገለጸ


ኢሳት 
ኢትዮጵያን ጨምሮ በጎረቤት ሶማሊያና ኬንያ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ከተጋለጡ ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ።
በቀጣዮቹ ሁለትና ሶስት ወራቶች በሃገሪቱ ያለው የድርቅ አደጋ እየተባባሰ ሊሄድ የሚችል በመሆኑን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባው ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው አዲስ ሪፖርት አስፍሯል።
በተለይ በኢትዮጵያ ከአንድ አመት በፊት ተከስቶ የነበረው የድርቅ አደጋ ዕልባት ሳያገኝ በቅርቡ ያጋጠመው አዲስ የድርቅ ክስተት በሃገሪቱ ያለውን ችግር የከፋ ሊያደርገው እንደሚችል ተሰግቷል።
በሶስት ሃገራት ያለው ይኸው የድርቅ አደጋ የምግብ ዋጋ ንረትን ያስከትላል ተብሎ የተገመተ ሲሆን በአደጋው በሺዎች የሚቆጠሩ የቤት እንስሳትም እንደሚሞቱ የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ መምሪያ አመልክቷል።
በአለም ምግብ ፕሮግራም የአስቸኳይ ጊዜ ማቋቋሚያ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶሚኒክ በርገን በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና፣ ኬንያ ያጋጠመው የዝናብ እጥረት ለደርቁ አደጋ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ለችግሩ ተጋልጠው የሚገኙ ወደ ስድስት ሚሊዮን ሰዎችን ለመደገፍ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ የሚያስፈልግ ሲሆን ከ20 የሚበልጡ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን ለመደገፍ ጥረት እየደረጉ መሆኑ ታውቋል።
በሶማሊ፣ አፋር፣ ኦሮሚያና፣ የደቡብ ክልሎች ስር የሚገኙ በርካታ ዞኖች አዲስ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ የመለክታል።
የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ድርቁ እየተባባሰ እንዳይሄድ አፋጣኝ ርብርብ ካላደረጉ የተረጂዎች ቁጥር በቀጣዮቹ ሶስት ወራቶች ውስጥ ሊጨምር ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
መንግስት በበኩሉ አደጋው ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ባለፈው አመት በስድስት ክልሎች ተከስቶ የነበረው ተመሳሳይ የድርቅ አደጋ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንዲጋለጡ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።
ችግሩ ዕልባት ባለማግኘቱ 9.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የቅርብ ክትትል የሚፈልጉ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

Petition condemning the vicious and malicious attack against EMP Ana Maria Gomes by Surrogates of the brutal regime in Ethiopia.

Task Force for Human Rights and Justice in Ethiopia – Europe
Petition condemning the vicious and malicious attack against EMP Ana Maria Gomes by Surrogates of the brutal regime in Ethiopia.
Following a litany of gross violation of human rights and political repression for over 25 years, Ethiopians have been protesting since November 2015 for their human dignity, constitutional rights and against economic and political marginalisation. The brutal repressive regime responded using brute force killing thousands and sent over 11, 000 innocent citizens to various prisons around the country[1].
On October 9th 2016 the regime, which has lost its legitimacy to rule, declared a six-month country wide state of emergency to inculcate fear among citizens. The state of emergency has effectively put the country under TPLF military rule have shut down mobile Internet service, blocked social media and prohibited public gatherings. The despised minority regime keeps committing crimes against humanity as it fights for its survival.
On December 1st,   2016 Dr. Merara Gudina, Chairman of the Oromo Federalist Congress (OFC) was arrested upon his return to Ethiopia from Brussels after attending a hearing on the political situation in Ethiopia. Ms Ana Maria Gomes wrote to Federica Mogherini, High Representative of the Union for Foreign Affairs and Vice President of the Commission[2], to take strong measures against the Ethiopian government which has absolute disregard for the respect of human rights, namely freedom of speech.
In an absolute travesty of events, the brutal regime has mobilized its surrogates who were granted political asylum under false pretence of fleeing from persecution in Ethiopia and living in Europe in freedom; to launch a petition campaign against the European Parliament and Ms. Ana Maria Gomes for demanding that Ethiopia respect international human rights norms that it is bound to uphold under the Cotonou Agreement.
We the undersigned and the European Task Force for Human Rights and Justice in Ethiopia fully support the request of Ms Ana Maria Gomes, calling for the European Parliament to take a strong action against the repressive regime in Ethiopia and demanding the immediate and unconditional release of Dr. Merara Gudina.
We strongly condemn the malicious smear campaign against a highly respected member of an EU Parliamentarian by the brutal minority regime of Ethiopia. Ms Ana Maria Gomes is an ardent defender of human rights, freedom and democracy speaking against repression and injustice in Ethiopia. As the distinguished statesman Edmund Burke once said, “All tyranny needs to gain a foothold is for people of good conscience to remain silent”.

“በልጄ የልደት ቀን ተገኙ” የሚል ግብዣን በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጩት አባት በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን ለማስተናገድ ተገደዋል


 በሜክሲኮ ላ ጆያ ማህበረሰብ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ አንድ ልማድ አለ፤ ሴቶች ከተወለዱ 15 ዓመት ሲሆናቸው የልደት ቀናቸውን በልዩ ዝግጅት ማክበር፡፡
ይህ ባህል “የኩዊን ሴናሪአ” በዓል ይባላል።
በዓሉ ሴቶች ከልጅነት ወደ ኮረዳነት የሚሸጋገሩበት የ15ኛ ዓመት የልደት በዓል ማክበርን ለመግለፅ ያገለግላል።
የሩቢ ኢብራ ጋርሺያ ቤተሰቦችም "ክቡራት እና ክቡራን እንዴት ናችሁ፤ በታህሳስ 26 የፈረንጆች 2016 ዓመት በልጃችን ሩቢ ኢብራ ጋርሺያ 15ኛ ዓመት የልደት በዓል እንድትገኙልን እና የደስታችን ተካፋይ እንድትሆኑ ስንል በአክብሮት ጠርተንዎታል" የሚል መልዕክት በቪዲዮ ቀርፀው በማህበራዊ ትስስር ገፆች የታደሙልን ግብዣ ያስተላልፋሉ።
ይህን ግብዣ ተከትሎም በሩቢ ልደት ላይ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ሰዎች እንደሚገኙ ያሳውቃሉ።
የሩቢ ቤተሰቦች በማህበራዊ ትስስር ገፆች ያስተላለፉት የቪዲዮ መዕዕክት ከ800 ሺህ በላይ ጊዜ የተጋራ ሲሆን፥ ለቁጥር የሚያዳግት አስተያየትንም አስተናግዷል። ይህ ለምን ሆነ የሚለው መልስ የለውም።
የሜክሲኮ አየር መንገድም ተጓዦችን ወደ ሩቢ 15ኛ ዓመት የልደት በዓል ከሆነ የሚጓዙት የ30 በመቶ የቲኬት ዋጋ ቅናሽ አድርጋለሁ ማለቱም አነጋጋሪ ነበር።
ግብዣውን በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ከተመለከቱ እና እንገኛለን ካሉት ውስጥም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በልደቷ ላይ ለመገኘት በቅተዋል፤ ይህም በሩቢ ቤተሰቦች ላይ አግራሞትን ፈጥሯል::
በሺህ ሰው መሃል ከልጃቸው ጋር የተገኙት የሩቢ አባት አቶ ኢብራ ጋርሺያም ለተሰበሰበው ሰው "ጥሪውን ያከናወነው ለጎረቤቶቻችን እና ለጓደኞቿ ቢሆንም በልጃችን የ15ኛ ዓመት የልደት በዓል ላይ ለመታደም የመጣችሁ ሁላችሁም ለበዓሉ የተሰናዳውን ድግስ እንድትበሉ፣ እንድትጠጡ በፈረስ እሽቅድምድም እና በሙዚቃ ባንድ ጨዋታዎች እንድትዝናኑ እጠይቃለሁ” አሉ።
በእለተ ሰኞም በሩቢ የልደት በዓል ለታደሙት ሁሉ የተለያዩ የምግብ እና መጠጥ አይነቶች በየጠረጴዛቸው ቀረበ፤ ከድግሱ በኋላም ሩቢ በተሰበሰበው ህዝብ መሃል በወላጆቿ "እደጊ" ተብላ ተመረቀች።
በሺህዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችም ሩቢን "መጪው ዘመንሽ የተባረከ ይሁን" በማለት የማስታወሻ ፎቶ ለማንሳት የስልክ ካሜራቸውን አነጣጠሩባት።me_cameera.jpg
የሩቢ 15 ዓመት የልደት ቀን በዚህ መልኩ ሲከበር አባቷ አቶ ጋርሺያ በፈረስ እሽቅድምድም ተሳትፎ ያሸነፈ ሰው 10 ሺህ የሀገሪቱ ፔሶ ወይም 490 የአሜሪካ ዶላር እንደሚሸልሙ መናገራቸውን ተከትሎ ብዙዎች በውድድሩ ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም የሩቢ አባት አቶ ኢብራ ጋርሺያ “በዚህ እለት እኛ ጋር ሆናችሁ የልጃችን 15ኛ ዓመት የኩዊን ሴናሪአ በዓል ታድማችሁ፣ ለልጃችን መልካም የተመኛችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን” ብለዋል።
በቴሌቪዥን ቀርበው ስለሁኔታው ሲጠየቁም “ያልጠበቅነው ግን ደስ የሚል ነገር ነው ያጋጠመን” ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የበርሊኑ ጥቃት፤ የገና በዓል፤ የኢትዮጵያዉያን አስተያየት


በሳምንቱ መጀመርያ በጀርመን መዲና በርሊን በተዘረጋዉ የጀርመናዊ ባህላዊ የገና ገባያ ላይ ጥቃት ከደረሰ ወዲህ ፤ በሃገሪቱ በየዓመቱ በሚጠበቀዉ የጀርመናዉያኑ የገና በዓል አከባበር ላይ የሃዘን ጥላ ያንዣበበበት ይመስላል። በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን የጀርመናዉያኑን ገና እንዴት ይሆን የሚያከብሩት? ኢትዮያዉያንን አስተያየት አሰባስናል።


አውዲዮውን ያዳምጡ።15:07

ኢትዮጵያዉያን የጀርመናዉያኑን ገና እንዱት ያከብሩታል?

    
በጀርመናዉያኑ ዘንድ በደማቅ ሥርዓት የሚከበረዉ የገና በዓል በገና ዛፍ ማለት ጥዱን አሽቆጥቁጦ፤ በገና ገበያ በቅርንፉድ ቀረፋ የተፈላዉን ወይን ይዞ፤ የገና አባት የተባለዉን ባለነጭ ሪዛም ሽማግሌን ስጦታ አሸክሞ፤ ቤተሰብን አሰባስቦ በመምጣቱ በጉጉት ይጠበቃል። በሳምንቱ መጀመርያ ታኅሳስ 10 ቀን ሰኞ ምሽት በበርሊን ከተማ በተዘረጋዉ በባህላዊዉ የገና ገበያ ላይ የደረሰዉ ጥቃት በርግጥ በጉጉት የሚጠበቀዉን ይህን በዓል ጥላ ሳያጠላበት አልቀረም። እንድያም ቢሆን በርካታ ጀርመናዉያን በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች በሚሰጡት አስተያየት ጥቃቱ የፈሪ ነዉ ፤ ለፈሪ ደግሞ ባህላችን እና አኗኗራችንን አንቀይርም ሲሉ ይናገራሉ።
Deutschland Nach Anschlag auf Berliner Weihnachtsmarkt (picture-alliance/dpa/B. Pedersen)
የበርሊን ነዋሪዎች ቦታዉ ላይ በመገኘት ኃዘናቸዉን እየገለጹ ነዉ
ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የጀርመናዉያንን ገናን በዓል እንዴት ያከብሩታል፤ በበርሊን የደረሰዉ ጥቃት የአከባበር እቅዳቸዉን ቀይሮት ይሆን?።
በጀርመን የገና በዓል  በየዓመቱ በጎርጎረሳዉያኑ ታህሳስ 24 ማለት ምሽት ጀምሮ መከበር ይጀምራል። በጎርጎረሳዉያኑ ታሕሳስ 24 ማለት ዲሴምበር 24 ምሽት ፤ እየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቅዱስ ምሽት፤ በነጋታዉ ታህሳስ 25 ቀዳማዊ ገና፤ ታህሳስ 26 ቀን ደግሞ ዳግማዊ ገና ሲሉ ጀርመናዉያን በተከታታይ ቀናት ከቤተሰብ ጋር በእርጋታ ያከብሩታል።
ጀርመናዉያን በገና በዓል አከባበር ከሌሎች አዉሮጳዉያን የሚለዩት ደግሞ፤ ያዉ ከአራት ሳምንታት ጀምሮ በዓሉ እስከሚከበርበት ድረስ፤ በሚዘረጉት በገና ገበያቸዉ እና፤ በቀረፋ ቅርንፉድ በተቀመመዉና በተፈላዉ በወይን መጠጣቸዉ ነዉ። የገና በዓል ሊከበር አራት ሳምንት ሲቀረዉ ጀምሮ በየእሁዱ አንዳንድ ሻማን ያበራሉ፤ የበዓሉን መምጣት ይጠባበቃሉ። በየከተማዉ መሃል የሚዘረጋዉም ባህላዊዉ የገና ገበያም ቢሆን የገና በዓል ሊከበር አራት ሳምንት ሲቀረዉ ነዉ የሚዘረጋዉ። በዚህ ገበያ  የሕጻናት የአዋቂዎች መጫወቻና መዝናኛ ቦታዎች ይገኛል፤ ምግብ መጠጡም ቢሆን በገፍ የሚቀርብበት ቦታም ነዉ። በርግጥም የጀርመናዉያን ዋንኛ ባህላዊ እንቅስቃሴ የሚታይበት ቦታ ነዉ። ባለፈዉ ሰኞ ታኅሳስ 10 በበርሊን እንብርት ላይ በተዘረጋዉ የገና ገበያ ላይ ጥቃት ደርሶ ሰዎች በመገደላቸዉ በርግጥ በዓሉ ላይ የሃዘን ጥላ ያጠላበት ይሆን ? በጀርመን ሲኖሩ ከ 20 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩትና በበርሊን ይኸዉ አደጋ ከደረሰበት ብዙም ሳይርቅ የሚኖሩት አቶ ደረጀ መንገሻ ድርጊቱ እንዳሳዘናቸዉ ይናገራሉ። 
Deutschland Berlin Kaiser-Wilhelm-Gedächtnis-Kirche (Getty Images/A. Rentz)
በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በሶቭየት ኅብረት ቦንብ የተመታዉ በርሊን እንብርት ላይ የሚገኘዉ ቤተ-ክርስትያን

«በጣም በጣም የሚያሳዝን ነዉ። ባለፉት ዓመታት በሌሎች ሃገራት ላይ የደረሱትን የሽብር ጥቃቶች ታዝበናል። በጀርመን ሃገር አንጻራዊ ሰላም ነበር። እንደሚታወቀዉ በጀርመን ገና በዓል፤ በከተማ መሃል በሚዘረጋዉ የገና ገበያ ቦታ ቤተሰቦች ሕጻናት ልጆቻቸዉን ዘመዶቻቸዉን ጓደኞቻቸዉን ይዘዉ ነዉ የሚሄዱት። ገበያዉ ቦታ ልዩ ልዩ መጫወቻ ቦታዎች አሉ፤ መዝናኛ ቦታዎች ተዘጋጅተዉ ይገኛሉ። ቤተሰብ ሁሉ የሚሰባሰብበት ቦታም ነዉ ።እና ይህ ጥቃት ሰዉ የሆነን ሰዉ ሁሉን የሚያሳዝን ልብ የሚሰብር ድርጊት ነዉ። በዚህም ወቅቱ የሃዘን ድባብ ያጠላበት ሆንዋል። እርግጥ ይህን ነገር በሃዘን ብቻ ማለፍ ሳይሆን፤ ይበልጥ ሽብርተኝነትን ለመታገል ሕዝቡ የበለጠ ቆርጦ መነሳት እንዳለበት የሚያመላክትም ነዉ ብዬ ነዉ የማስበዉ።»    
በበርሊን እንብርት ላይ የሚገኘዉ የጀርመን ባህላዊ የገና ገበያ የተዘረጋዉ ታሪካዊ ቦታ ነዉ ያሉን አቶ ደረጀ፤ ገበያዉ የተዘረጋበት አደባባይ ላይ የሚገኘዉ ቤተ-ክርስትያን ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በከፊል የተረፈ ነዉ።
« ቤተ-ክርስትያኑ በሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት ጊዜ በቦምብ የተመታ ነዉ። የቤተ-ክርስትያኑ ጉማጅ አሁንም እዝያዉ ቦታ ይገኛል በርግጥ አሻሽለዉታል፤ ቤተ-ክርስትያኑ አሁንም ፀሎት ይካሄድበታል፤ አላፊ አግዳሚዉ፤ የሃገር ጎብኝዉ ሁሉ የሚመጣበት ቦታ ነዉ። ድሮ ምዕራብና ምስራቅ ጀርመን በነበረበት ጊዜ የምዕራብ በርሊን ማዕከላዊ የሚባል ቦታ ነበር። ሰዉ ሁሉ የሚገኛኝበት ቦታ ነበር፤ አሁን በርሊን ከተማ ስለሰፋ ብዙ  ማዕከላዊ የሚባል ቦታ ተፈጥሮአል። ድሮ ግን ይህ ቤተ-ክርስትያን የሚገኝበት ቦታ ሰዉ የሚገናኝበት ማዕከላዊ የታወቀ ቦታ ነበር፤ ልክ እኛ ሃገር ፒያሳ እንደሚባለዉ ቦታ ማለት ነዉ። »
Deutschland Nach Anschlag auf Berliner Weihnachtsmarkt (picture-alliance/dpa/B. Pedersen)
የበርሊን ነዋሪዎች ቦታዉ ላይ በመገኘት ኃዘናቸዉን እየገለጹ ነዉ
በጀርመን ብሎም በአዉሮጳ የገና በዓል በድምቀት ይከበራል ያሉን በጀርመን ሲኖሩ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት ወ/ሮ ባዩሽ አበበ በበኩላቸዉ
« አዉሮጳዉያን በብዛት የክርስትና እምነት ተከታዮች ናቸዉ። የገና በዓል ደግሞ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የሚከበር ትልቅ በዓል ነዉ። አብዛኞቹ ነዋሪዎች ከጥንት ከብዙ ሺህ ዘመን ጀምሮ የክርስትና እምነት ተከታዮች ናቸዉ ፤ ስለዚህ የገና በዓል ከፋሲካም ከማንኛዉም በዓል በላይ በድምቀት ይከበራል፤ ቤተሰብም ከተለያየ ቦታ የሚሰባሰብበት በዓል ነዉ»
ወ/ሮ ባዩሽ በመቀጠል እንደተናገሩት በርሊን ጀርመን ላይ የተከሰተዉ ጥቃት ቢያሳዝንም ጀርመናዉያን ችግሩን ለመፍታት ወደፊት ስልሚያዩ  በገና በዓል አከባበር ላይ ለዉጥ አያመጣም።
« እነዚህ ነገሮች እኮ በዓለም ላይ አሁን እየተደጋገመ የምናየዉ ነዉ፤ በተለያዩ  የዓለም ሃገራት ማለቴ ነዉ። ስለዚህ ጀርመናዉያን ጠንካሮች ናቸዉ ብዙ ያለፉ ናቸዉ። በርግጥ ጥቃቱ ቤተሰብን የጎዳ ቢሆንም አካባቢዉን የጎዳ ቢሆንም፤ እንዲሁም ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ይህ ጥቃት ስለተፈፀመ ያሳዝናል እንጂ ፤ በገና በዓላቸዉ ላይ ያንን ያክል ተጽኖ የሚያመጣ አይሆንም። ጀርመናዉያን ብዜ ጊዜ ወደፊት ነዉ የሚመለከቱት፤ አንድ ችግር ላይ ቆመዉ አይቆዩም »
በጀርመን ኢትዮጵያዉያን በመሰባሰብ በተለያዩ ማኅበራትና ስፖርታዊ ዝግጅቶችና ኢትዮጵያዊ ባህላዊ ክንዉኖች ከሚታዩባቸዉ ከተሞች በተለይ ኑረምበርግ ከተማ የሚገኙት ኢትዮጵያዉያን ልቀዉ ይገኛሉ። በኑረምበርግ ከተማ የሚገኘዉ የገና ገበያ በጀርመን ከሚገኙት የገና ገበያዎች ሁሉ የላቀ መሆኑ ይነገርለታል። በኑረምበርግ የኢትዮጵያዉያን ማኅበር ዉስጥ በመሥራታቸዉ የሚታወቁት የኑረምበርግ ነዋሪ አቶ ካሱ ለገሰ ፤ እንደሚሉት በጀርመን የደረሰዉ ጥቃት በጣም የሚያሳዝን ነዉ የገና ስሜትን ረብሽዋል፤
Fahndungsfoto Anis Amri (picture-alliance/dpa/Bundeskriminalamt)
ጥቃት አድራሹ ተጠርጣሪ የቱኒዚያ ተወላጅ አኒስ አምሪ እየታደነ ነዉ
« ይህ አይነቱ ሁኔታ በተለያዩ አዉሮጳ ሃገራት እየተከሰተ ነዉ ። በጀርመን ላይም ሊከሰት ይችላል ተብሎ ጥበቃ ቢደረግም ያዉ በርሊን ላይ ጥቃት ሊጣል ችሎአል። በርግጥ እንዲህ አይነቱ ጥቃት እንዴትና የት ሊከሰት እንደሚችል መገመቱ አስቸጋሪ ነዉ። እኔ በምኖርበት በኑረንበርግ ከተማ የገና ገባያ በታም ታዋቂ ነዉ ጥበቃዉ በጣም ጠንካራ ነዉ። በበርሊን ጥቃት ከደረሰ በኋላ ጥበቃዉ ይበልጥ ተጠናክሮ አይቻለሁ። እናም በዚህ ዓመት ብቻ በኒዛ፤ በቤልጄም፤ በጀርመንም ቢሆን በተለያየ ሁኔታ ጥቃትን አይተናል፤ የአሁኑ የበርሊኑ ጥቃት በጣም የሚያሳዝን ነዉ የገና ስሜትን ረብሽዋል፤ በጣም የሚሳዝን ነዉ፤ እንግዲህ ከእንዲህ አይነቶች ጋር አብሮ መኖር ነዉ። »
በጀርመን ስኖር ወደ 27 ዓመት እንደሆናቸዉ የነገሩን ዶክተር ለማ የጀርመናዉያኑን ገና እንደ ማኅበረሰቡ ሁሉ እንደሚያከብሩ ነግረዉናል።  በዝግጅቱ ቃለ ምልልስ የሰጡን ለጀርመናዉያኑ መልካም የገና በዓልን ተመኝተዋል። የፈረንጆቹን ገና በዓልን ለምታከብሩ የዶይቼ ቬለ ተከታታዮች በሙሉ መልካም የልደት በዓል እያልን ቃለ ምልልስ የሰጡንን በማመስገን ሙሉ ቅንብሩን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን!  
አዜብ ታደሰ
ነኃሽ መሃመድ

wanted officials