Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, December 23, 2016

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በእሳት እየነደደ ነው


(ዘ-ሐበሻ) በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ደብርንርሃን ከተማ ውስጥ የሚገኘው የደብረብርሃን ዩኒቭርሲቲ ውስጥ የ እሳት ቃጠሎ መነሳቱ ተሰማ:: ቃጠሎው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳለ ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ የለም::
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተነሳው ቃጠሎ ምንነት እስካሁን ያልታወቀ ቢሆንም እሳቱ እንደተነሳ ለ እሳት አደጋ ቢደወልም የ እሳት አደጋ ሰራተኞች ቶሎ እንዳልመጡና ቀድምው የአጋዚ ወታደሮች ዩኒቨርሲቲውን እንደከበቡት ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
እንደምንጮች ገለጻ ከሆነ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እሳት አደጋውን ለማጥፋት ቢረባረቡም በአንዳንድ ተማሪዎች ላይ የአጋዚ ወታደሮች ካለምንም ምክንያት ድብደባ ፈጽመዋል::
ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድረገጽ ላይ ዘ-ሐበሻ ካገኘችው መረጃ መረዳት እንደተቻለው በዚህ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከአስር ሺህ ያላነሱ ተማሪዎች ይማራሉ::

No comments:

Post a Comment

wanted officials