አንዳንዴ ግርም ይለኛል፤ የተሻለች ሀገር ትኖረን ዘንድ፤ ህዝብ ላይ ወያኔ የጫነውን የመከራ ቀንበር ለመጣል ሲሉ ለትግሉ ዋጋ የከፈሉትን ለመርሳት የተቻኮሉትን ሳይ፤ ዋጋ የከፈሉት እየከፈሉ ያሉት ተዘንግተው መድረኩን የሞሉትን ዝና ፈላጊ ተንጠልጣዮችን ሳስብ፤ እድሜያቸውን ሙሉ ያለስስት ላመኑበት የከፈሉ፤ የሞቀ ትዳር ቤተሰብ ልጄ ሳይሉ ግዜ ገንዘብ እውቀታቸውን ላመኑበት የትግል ስልት የለገሱ፤ ይዘውት ለተነሱት ትልቅ ህልም እታች ድረስ ወርደው የሰሩት ተዘንግተው የድል አጥቢያ አርበኞች ሲሞገሱ ባይ [ትግሉ ተጠናቀ፣ መስመሩን ይዟል አለማለቴ ይታሰብልኝ። ሀሳባቸውን ብቻ በመግልፃቸው በወያኔ ማጎሪያ የተሰቃዩ ታስረው ሲፈቱም ከህዝብ ጎን የቆሙ የማከብራቸውን አይመለከትም፤ ሁሉም አሁን ትግል ላይ ያሉትን አለማለቴም ይያዝልኝ “አንዳንዶች” ናቸው]
ግፍን ተቀብለው መከራን እያዩ ስላሉት አለመናገር ስለከፈሉት አለመወሳቱን እያሰብኩ መታዘቤን ብቀጥል ለትግሉ መሰርትን ለመጣል ደፋ ቀና ያሉ ሲታሰብ እንኳን የሚዘገንን ግፍ የተቀበሉ ተዝንግተው “ሲነጋ” የደረሱት ሲወደሱ ባይ ግርምቴ ሁሉ ገረመኝ አንዳች ሳይሰሩ ዋጋ በከፈሉ በሰው ጥላ ተጠልለው የዝና ካባን መደረብ በሚሹ መሀል መሆኔን ለካ ዘንግቼው ነበር፤ ጀሌ አንጋሾቻቸውም የነገሯቸውን እንደበቀቀን የሚደግሙ ታሪክን መለስ ብለው ማየት የማይሹ ተላላኪዎች እንደሆኑ።
አልተነገረላቸው ተረሱ ብዬ እኔ ባስብም፤ እነሱ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ በቆራጥነትና በጀግንነት አርገው ውጤቱን ሊያዩ ጥቂት ሲቀራቸው አብረናቹህ ነን ባሉ ታሪክ ተሻሚ እንዝህላሎች ውስጣቸው ያሉትን ካህዲዎች እንኳን በማያቁ ከንቱዎች የልፋታቸውን ውጤት ሳያዩ ቀርተዋል። ውጤቱን ሊያዩ ከአንድ እጅ መዳፋ የጣት ቁጥር ያነሰ ቀን እየቀራቸው፤ የነሱ መልክተኛ በሆኖ ሆዳሞች ተላልፈው ለወንበዴ ተሰጥተዋል። እስታሁንም እንዴት ይህንን ሁሉ አጠገባችን ሆነው ሰሩ በሚል የወያኔ መተረማመስና ለከት ያጣ ብስጭት የዛን ሰሞን ትውስታች ነው። የሀላፊነት ግዴታ ሆኖበት ስለተፈጠረው ነገር ለሚዲያ በሰጠው መግለጫ በግዜው የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ዴታ የነበረው ለዛሬ ስደት ምክንያቱ እንደሆነውም አይረሳንም። [ስለ ጉዳዩ እሱ ዝምታን ቢመርጥም]
መንግስት ነን ባይ ሰው በላዎች እጅ ሲወድቁ የሰው ልጅ በሰው ላይ ያረገዋል ተብሎ የማይተመንን ግፍ ከተያዙበት እለት እስከ ማዕከላዊ ድረስ ቢፈፀምባቸው አቋማቸውን ያልቀየሩትና እስታሁንም መቼ ቅስማቸው የማይሰበረውን ዛሬም በመንፈስ ከፍታ ላይ ያሉትን ስለኛ ነፃነት መከራ ገፊዎቻችንን አቋም አቃለሁ አከብራለሁ፤ ጠንካራና ብርቱ ናቸው ዝና ለነሱ ምንም ነው አላማቸውን ብቻ ማሳካት ነበር ግባቸው። ማልቀስ ማዘን የሚገባው ለአንዳዶች ነው እንጂ አንዳች ሳያዋጡ በቸብቸብ የዝና ከፍት ይገባናል በሚል እራሳቸውን ሰማያ ሰማያት ላደረሱት፤ ዛሬ ላይ ቆመው ለትግሉ እዚህ መድረስ የለፉትን ማስታወስ ለተሳናቸው ወጪት ሰባሪዎች ነው፤ ዘመን ፈቅዶ በሜዳችን እስትንነጋገር እንታዘባለን!!
እርግጥ የኔዋን የልብ እምነቷን በደንብ አቀዋለሁ እምነቷ ቀድማ እራሷን ነፃ ለማውጥት ቀጥሎ ህዝብን ነበርና የራሷን ነፃነት ለማግኘት ጨርቄን ማቄን ሳትል ለትግሉ እራሷን ሰታለች። አምናበት ለከፈለችው እየከፈለች ላለውም ከማንም መታወስን አትሻም በራሷ መንፈስ ከፍታ ላይ ነች። ስለሷ አለመነገሩ እሷን አያስገርማትም። ሌሎች ጓዶቿም ተመሳሳይ እምነት ያላቸው ይመስለኛል።
ሁላቹህም የህሊና እስረኞች ስለከፈላችሁት ዋጋ አከብራቹሀለው!!
No comments:
Post a Comment