Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 19, 2016

የትግራይ ነፃ አውጭው አየር ሀይል አብራሪዎች ለግመዋል ስለተባለ ሊታፈኑ ነው




የህወሀት ኮማንድ ፓስት የሰሜኑ አየር ሀይል ማዘዣ ና አብራሪዎች ላይ ያነጣጠረ ድንገተኛ አፈና ሊያካሄድ እንደሆነ ታማኝ የመረጃ ምንጮች አሳዉቀዋል።
መረጃዋች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በሰሜን ጎንደር አካባቢ እየተካሄደ በሚገኘው ጀግና የአማራ ገበሬዎችና የ አርበኞች ግንቦት 7 ኃይሎች በተሰባጠረ መልኩ የከፈቱትን የህወሃት በቃን ዘመቻን ለመመከት እንዲሁም ለማጥቃት በተለይም ለእግረኛ የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮች ቅኝት እና ሽፋን ለመስጠትና ብሎም ጭራሹን የተባበሩትን የነፃነት ኃይሎችን የመደምሰስ ግዳጅ ተሰጥቶአቸው ግዳጃቸውን በብቃት አልተወጡም፤  ሆን ብለው ለግመዋል፤ እና እንዲሁም ለህዝባዊ ነበልባሉ ወግነዋል  የተባሉ የአየር ኃይል አባላቶች እንዲታፈኑ ኮማንድ ፓስቱ ዛሬ ትእዛዝ አዉጥቶአል።
ይህ መረጃ እጅግ በሚስጥር የተወሰነ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials