Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, December 1, 2016

ሰሜን ጎንደር ግንባር…የድል ዜና! የድጋፍ ጥሪ!



ሕዝባችን ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ነው
ድጋፋችንን ባፋጣኝ ይፈልጋል!
1
፨የቆላማው ወገራ ውጊያ አምስተኛ ቀን ሞላው። በታጣቂው ገበሬ የተከበበው የአጋዚ ሃይል ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። ለጊዜው ቁጥሩ በወል ያልታወቀ የወያኔ ወታደር ሙትና ቁስለኛ ከቅርብ እርቀት እንደሚታይ ከቦታው ተነግሮኛል።
፨ይህ ሕዝባዊ ቁጣ ያርበደበደው ወያኔ የተከበበትን አጋዚ ሃይል ለማስለቀቅ ከደጋማው ወገራ አካባቢ አምስት መኪና የሞላ ሰራዊት ቢልክም እንቆቆው ቆለኛ በነቂስ ግልብጥ ብሎ በጥይት ቆልቶ ገቶታል። ከቄሶች እስከ ሴቶች ድረስ ማሃላውን ጠብቀው አኩሪ የደጀንነት ስራ እየሰሩ ነው። ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው።
፨በተመሳሳይ መልኩ በዚሁ ደጋ ወገራ ገደብየ ከተማ ውጥረት እያስተናገደች ነው። አንድ ጀግና ገበሬ መሳሪያ ሊያስወርዱት የሄዱትን ሁለት ወታደሮች በመግደል እንዳመለጠ መረጃ ደርሶኛል ገደብየ ከወገራ በመጡ የወያኔ ወታደር ተከባለች፡፡
፨ሁኔታውን እየተከታተልኩ አቀርባለሁ። ውጊያ የሚደረግባቸውን ልዩ ቦታወች ለደህንነታቸው ስል አልጠቅሰውም። በምስልም አላስደግፍም። ይህ የገበሬ ሃይል በወያኔ የተከፋ እስካሁን ድረስ በራሱ ህዝብ ብቻ የሚታገዝ እንደሆነ መታወቅ አለበት። አንዳንድ ሚዲያወች የከሌ ድርጅት ውጊያ ብለው የሚዘግቡት ትክክል አይደለም።
©ከጎበዝ አለቆቹ እንደተረዳሁት እኛ የተከፋን የተገፋን ህልውናችንን ለማስጠበቅ የተደራጀን ነን። የብዙ ወረዳ ተወካዮች በተገኙበት ታላቅ ጉባኤ አድርገናል። መጠሪያችንንም ለህዝብ በቅርብ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

No comments:

Post a Comment

wanted officials