Ethiopiazare.com – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በፓልቶክ ክፍል ቀርቦ የኦሮሞ ተወላጅ መሆኑን አስረግጦ ተናግሯል። ካፈርኩ አይመልሰኝ ነገር።
አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ከዚህ ዘር ነኝ የማለት የተጠበቀ ነው። የዘር ቆጠራን ያመጡት ራሳቸው ሥልጣን ላይ ያሉት ዘረኞች ናቸው እንጂ እኛ አይደለንም። ዛሬ የራሳቸው ቃል እስረኛ የሆኑ ይመስላል። ጥያቄው ዘሩን በገዛ ፈቃዱ የመቀየር ጉዳይ አይደለም። ተቃውሞው ሹመቱ ላይም አይደለም። በዘር ያመጡት የሥልጣን ኮታ ዘሩ ባልሆነ ግለሰብ ሲደለደል – ጉዳዩን ለሚያውቁት ንቀት እና ስድብ ይሆናል።
ወርቅነህ የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት በሚፈቅደው ”ጉዲፈቻ” እና ”ሞጋሳ” ባህል መሰረት ወደ ኦሮሞነት ተቀይሮ ከሆነ ግልጽ ይሁን። ካልሆነ ግን የእሱን ማንነት የሚገልጸው ዶክመንት ተመልክቶ ፍርድ መስጠቱ ይበጃል።
ለስድስት ዓመታት በድህንነት ሲሠራ በርካታ ንጹሃን ዜጎችን አሳፍኗል – ከዚያም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆኖ ሲሠራ በተለይ በምርጫ 97 በነበረው ጭፍጨፋ ለ200 ዜጎች ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ ነው።


ማስረጃ ፪፣ የምርጫ ቦርድ ውጤት ላይ የዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የአያት ስም ነጋዎ (የኦሮሞ ስም) ኹኑዋል

ማስረጃ ፫፣ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን አስመልክቶ ፕ/ር መረራ ጉዲና በመጽሐፋቸው ላይ ካሰፈሩት የተወሰደ።
No comments:
Post a Comment