Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 13, 2016

ሐይማኖት ሴቶችና ስፖርት በሶማሊያ በዳዊት ሰሎሞን



ሐይማኖት ሴቶችና ስፖርት በሶማሊያ  በዳዊት ሰሎሞን
======================
Image may contain: 2 people, people standing
የሶማሊያ ታላላቅ የሐይማኖት መምህራን የቅርጫት ኳስ የሚጫወቱ ሴት ስፖርተኞችን በማስጠንቀቅ ስፖርቱ እስላማዊ አለመሆኑንና ሐይማኖታቸውን እንደሚፈታተን ተናግረዋል፡፡
የሶማሊያ ሐይማኖታዊ ምክር ቤት ሐሙስ ዕለት መግለጫ ያወጣው በፑንትላንድ ዋና ከተማ ጋሮው እንደሚካሄድ ቀጠሮ ለተያዘለት የሴቶች አገር አቀፍ ቅርጫት ኳስ ውድድር ዝግጅቱ እየተጧጧፈ በሚገኝበት ወቅት ነው፡፡
‹‹የሴቶች የቅርጫት ኳስ እስላማዊ ህግን፣ባህላችንና ሞራልን እንደሚጻረር አስጠንቅቀናል፡፡ሴቶች በቀላሉ ሊታለሉበት የሚችሉበት ቦታ እንደሆነም እናምናለን››የሚሉት የምክር ቤቱ ሊቀመንበር ሼህ ባሺር አህመድ ናቸው፡፡
በቀጣይ የሚደረገው ውድድር በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያው የሴቶች የቅርጫት ኳስ ውድድር በመሆን ይመዘገባል፡፡ሞቃዲሾን ጨምሮ አራት የፌደራሉ ክልሎች በውድድሩ ለመሳተፍ ተዘጋጅተዋል፡፡
‹‹እስላማዊ ደንቦቻችንን የመጠበቅ መብት አለን፡፡እነዚህ ደንቦቻችን ሴቶች ስስ ልብሶችን በመልበስ ወንዶች ሊያዩዋቸው በሚችሉ ቦታዎች መታየት እንደሌለባቸው የሚደነግጉ ናቸው፡፡ይህ ማንንም ለማጥቃት የተደረገ አይደለም››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ሊቀመንበሩ እንዲህ አይነት ነገሮች የወጣት ሙስሊሞችን አእምሮ ለመቀየር ሙስሊም ላልሆኑ ሰዎች ዕድል እንደሚፈጥር ይናገራሉ፡፡
‹‹ሴቶች የእስልምና ጠላቶች ዋነኛ ኢላማ መሆናቸውን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡በተለይም ወጣቶች ሐይማኖታቸውን ለማስቀየር የሚፈልጉ ኃይሎች የመጀመሪያ ታርጌት መሆናቸውን ሊያውቁ ይገባል››ይላሉ፡፡
ለቪኦኤ የሶማሊኛ ክፍል አስተያየት የሰጠችው ሳራ መሐመድ ‹‹የምጫወተው ሂጃቤን በማድረግና የሐይማኖቴን የትኛውንም ህግጋት እንዳልጣስኩ በማረጋገጥ እስከሆነ ድረስ የምወደውን ስፖርት የመጫወት መብት አለኝ፡፡ስፖርትን ሰላምን እንደሚገነባና የሶማሊያን ህዝብ በአንድነት እንደሚያቆም ትልቅ መሳሪያ ነው››ብላለች፡፡
በ2006 የኢስላሚክ ኮርትስ ዩኒየን የአገሪቱን ደቡባዊና ማዕከላዊ ግዛቶች ጨምሮ ሞቃዲሾን ይቆጣጠር በነበረበት ወቅት ሴቶችን ከስፖርት ውድድሮች አግዶ ነበር፡፡ዩኒየኑ በተለይም የቅርጫት ኳስ ስፖርትን እስላማዊ ህግጋትን የሚጻረር ‹‹ሰይጣዊ ድርጊት››በማለት ፈርጆት ነበር፡፡
የሶማሊያ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ቡድን ስካይ ብሉ ይሰኛል፡፡ቡድኑ በ2011 የአረብ ጌምስ በመካፈል በሶስት ሽንፈትን አስተናግዶ ሁለት ጨዋታዎችን በማሸነፍ የስፖርቱን ተከታዩች ትኩረት አግኝቶ ነበር፡፡የውድድሩ አዘጋጅ የነበረችውን ኳታርንና ኩዌትን መርታታቸውም ተመዝግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials