Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, December 15, 2016

በጃዊ እና አካባቢዋ የተነሳው የሕዝብ አመጽ እንደቀጠለ መሆኑ ታወቀ



ወያኔ የአማራ እና የቤኒ ሻንጉል ክልል ብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚዋሰነው የጃዊ ስኳር ፋቭሪካ አቅራቢያ ፈንድቃ ከተማና አካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ላይ መሆኑን የአካባቢው ኗሪዎች ተናግረዋል።
     የጃዊ የስኳር ፋቭሪካ 75%ቱ ለቱርክ ባለሃብቶች መሸጡን ተከትሎ ፕሮጀክቱ ለወሰደባቸው መሬት ተተኪ ቦታ ያላገኙና ምንም አይነት ካሳ ያልተከፈላቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች እያነሱት ያለው ቅሬታ ሳይበርድ የከተማው ወታደራዊ ባለስልጣናት በግላቸው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በአደረጉት እንቅስቃሴ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረትና የደም መፋሰስ እንደተከሰተ የአካባቢው ኗሪዎች ተናግረዋል።
     ከጃዊ ዋና ከተማ  ፈንድቃ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የገጠር ከተማ ለረጂም ዓመት በአሸዋ ንግድ ተደራጅተው የሚተዳደሩትን የአካባቢውን አርሶ አደሮች ስራ የጃዊ አካባቢ  ባለሥልጣናት የአሸዋ ንግዱን በመቀማት ለራሳቸው ለመስራት በማሰባቸው የተነሳው ግጭት ከእለት ወደእለት እየተባባሰ መሄዱ ታውቋል።
     የአሸዋ ማቅረቡን ስራ በመስራት ላይ ያሉት የህወሃት ባለስልጣናት ስራውን ከተነጠቁት የአካባቢው አርሶ አደሮች ሊደርስባቸው ከሚችለው ጥቃት ለመከላከል አሸዋ ለመጫን ለሚሄዱ መኪናዎች ጥበቃ የሚአደርጉ የመከላከያ ሰራዊት ዓባላትን መመደባቸው ተገልጿል።
     ጃዊ ውስጥ ያልተፈለገ ስራ በመስራት ላይ ከነበሩት አርሶ አደሮች ስራውን ነጥቀው በመስራት ተጠቃሚ በመሆን ላይ የነበሩት ባለሥልጣናት ያሰማሯቸው የጥበቃ ወታደሮች ከአርሶ አደሮቹ ጋር በተነሳው ግጭት ህይዎታቸው በማለፉ በታንክ የታገዙ የመከላከያ ሰራዊት በመላክ ግጭቱን ማባባሳቸውን የዐይን እማኞች ገልፀዋል።በወታደሮቹ እና በአካባቢው አርሶ አደሮች በተከሰተው ግጭት እስከ አሁን ድረስ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወታደሮች በተኩሱ ልውውጥ ወቅት ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
ወታደሩ ሕዝብን እና አገርን ከመከላከል ይልቅ የወታደሮቹን አለቃ ንብረት ጠባቂ የሆነባት አገር!

No comments:

Post a Comment

wanted officials