Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, December 11, 2016

በኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ለሚገኘው ሕዝባዊ ኣመጽ ጠቃሚ የሆኑ የሽምቅ ውጊያ መሰረታዊ መርሆችና ስልቶች

በኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ለሚገኘው ሕዝባዊ ኣመጽ ጠቃሚ የሆኑ የሽምቅ ውጊያ መሰረታዊ መርሆችና ስልቶች
ከኣርበኞች ግንቦት 7 የጥናትና የምርምር ዘርፍ የተዘጋጀ
ኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የበላይነት ስር ከሚገኘው ፋሽስታዊና ኣምባገነናዊ ሥርዓት ጋር የሚደርገውን ትግል ከዳር አስከዳር ለማቀጣጠልና የኣገዛዙን የመጨቆኛ ተቋማት ኣሽመድምዶ ለማንበርከክ በርካታ የትግል ስልቶችን መጠቀም፣ ማጠናከርና ተግባራዊ ማደረግ የግድ ይላል። ከእነዚህም የህዛባዊ ተቃውሞ የትግል ስልቶች መካከል ዋናዎቹ - ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ሕዝባዊ አመጽ፣ ሕዝባዊ ኣሻጥር፣ ሕዝባዊ ስለላና፣ ሕዝባዊ የስነ-ልቦና ጦርነትና ፕሮፖጋንዳ ይገኙበታል።
ዛሬ በሰሜን ጎንደርና በሌሎች ኣካባቢዎች የተጠናክረውን የፀረ-ወያኔ ሕዝባዊ ኣመጽ ማጠናከርና አጣዳፊ የሆኑ በርካታ የትግል ተግባራትን በየደረጃው መከወን ጊዜ የማይሰጠው ነው። ከነዚህም ኣንዱ የኣርበኝነት ትግል በማድረግ ላይ የሚገኙ የነፃነት ኃይሎች ሕዝባዊ አመጹን ዳር ለማድረስ ይውል ዘንድ ጠቃሚ ያልናቸውን መሠረታዊ የጎሪላ/ሽምቅ ውጊያ መርሆዎችና ስልቶች በመጭመቅ በዚህ ጥናት ተካተዋል። ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ በየአካባቢው ለተደራጁና ወደፊትም ለሚደራጁ የሕዝባዊ አመጽ ኃይሎች በህቡዕም በይፋም በማሰራጨት፡ አመጹ ዘመን ያልሻራቸው መርሆዎችና ስልቶችን በጥቅም ላይ በማዋል ትግሉን ለማጠናከር ግባኣት በመሆን ኣስተዋጾ ያደርጋል የሚል እምነት ኣለን። የጥናት ቡድኑ በሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ በሕዝባዊ ኣሻጥር፣ በሕዝባዊ ስለላና ፣በሕዝባዊ የሰነ ልቦና ጦርነትና ፕሮፖጋንዳ የትግል ስልቶች ዙሪያ ተከታታይ ጥናቶችን በማቅረብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ሥርዓት ጋር ለሚያደርገው ሁለገብ ትግል ማጠናከሪያ የግንዛቤ ግባት አንዲሆኑ ተመሳሳይና ተከታታይ ጥናቶችን በህቡዕና በይፋ ለተድራጁ ታጋይ ኃይሎችና ለሕዝቡ ያሰራጫል።
የጎሬላ/የሽምቅ ውጊያ
የጐሬላ ውጊያ ስልት በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ትጥቅ አደረጃጀቱ ከፍተኛ ጉልበት ያለውን የጠላት ኃይል መምቻና ማዳከሚያ መሣሪያና ጥበብ ነው። የጐሬላ ውጊያ ያለ ፖለቲካዊ ግብ ዋጋ የለውም፤ ፖለቲካዊ ዓላማዎቹም የሕዝብን ፍላጐትና ምኞት የተከተለ ካልሆነ የሕዝብን ትብብርና ድጋፍ ማግኘት አይቻልም። የጐሬላ ውጊያ በሕዝብና ለሕዝብ የቆመ ነው። ስለዚህ አንድ የጎሬላ ተዋጊ ኃይል ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ የሕዝቡን ድጋፍ ማግኘት ይኖርበታል። ከሕዝብ ጋር የተጣላ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ ብሎ የተነሳ ድርጅት ህልውናውን አስጠብቆ ለመዝለቅ ያለው እድል በጣም ጠባብ ነው። በመሆኑም ለአንድ ድርጅት የማኅበረሰቡ ድጋፍ መኖር የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጉዳይ ነው።
ስለዚህ የማኅበረሰቡን ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ተግቶ ለመሥራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሮ ለተግባራዊነት መንቀሳቀስ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ድርጅት ዋነኛው የቤት ሥራው ነው።
በጐሬላ/የሽምቅ ውጊያ የሚወሰዱ ስልቶች፦
1. ዋነኛ የጎሬላ ስልት ድንገተኛ በሆነ መንገድ ጠላትን መትቶ መሰወር ላይ የተመረኮዘ ነው።
2. ጠላት ባላሰበበትና በማይጠብቅበት ቦታ መርጦ ማጥቃት
3. የጠላት ጥንካሬ ያለበትን ቦታ ማስወገድ
4. የጠላትን ክፍተት (ቀዳዳ) በማጥናት ማጥቃት
5. ጠላትን በፍጥነት አጥቅቶ መሰወር
6. የጠላትን ስስ ጎኖች መርጦ ማጥቃት
7. የጠላትን አነስተኛ የሆኑ ተነጣይ ክፍሎችን መርጦ ማጥቃት
8. አንድ የጐሬላ ተዋጊ ኃይል ከጠላት ጋር ፊት ለፊት የሚደረግን ውጊያ አያካሄድም።
9. አነስተኛ የጠላትን ኃይል እየመረጡ መተንኮስና መምታት
10. ጠላት ድካም ወይም ዝለት በሚሰማው ጊዜ አድብቶ መምታት
11. ጠላት በሚደርስበት ጥቃት ሲያፈገፍግ ወይም ሊያመልጥ ሲሞክር ተከታትሎና ተረባርቦ መደምሰስ። በእንደዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ ወቅት በጠላት ወጥመድ ውስጥ እንዳንገባ መጠንቀቅ ይኖርብናል።
12. በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ አነስተኛ ጥቃቶችን በመፍጠር የጠላትን ኃይል መበታተን። የተበተነውን የጠላት ኃይል አነስተኛውን እየመረጡ በተናጥል ማጥቃት። በአብዛኛው ጊዜ ጥቃት የሚሰነዘረው በጠላት ጀርባ ወይም ጎን በኩል ብዙም ጥበቃ በማይደረግበት የሳሳ ቦታን ፈልጎ የሚደረግ ነው። የጠላትን ጥንካሬውን ማስወገድና ደካማ ጐኖቹን ማጥቃት (ጠላት በጣም በደከመበት ቦታ ላይ መምታት)፣
13. ጠላት ወደ ምንፈልገው የውጊያ ቅርፅ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ መደምሰስ። ማንኛውንም ውጊያ ስናካሄድ እኛ በፈለግነው መንገድ እንጂ ጠላት በሚፈልገው መንገድ መሆን የለበትም። በመሆኑም ጠላት እኛ ባዘጋጀነው የውጊያ ወጥመድ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ መምታት ይቻላል።
የጐሬላ ተዋጊ ኃይሎች የሚወስዱት እርምጃ አይነት፦
1. በመላው ኢትዮጵያ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በዞን፣ በክልል የሚገኙና በሕዝብ ላይ ግፍ የሚፍጽሙ የወያኔን የኣስተዳደርና የደህንነት የፖሊስ ጣቢያዎች፡ የሚሊሽያ መዋቅሮችን ማጥቃት ፣ መበጣጠስ፣ በሕዝብ ላይ ግፍና ጥቃት የሚፈጽሙትን ግለሰቦች መምታት፣ ማሰወገድ፣
2. ስለጠላትና አካባቢ ሁኔታ የሚገልጽ ማንኛውም መረጃ መሰብሰብ፣
3. የወያኔ ሠራዊት የተነጣይ አነስተኛ ክፍሎችን በወራራና ኣድብቶና አጥንቶ በደፈጣ ማጥቃት፣ መደምሰስ፣
4. የወያኔን የግንኙነት መስመሮችን በደፈጣና በድንገተኛ ወረራ ማጥቃት፣
5. የወያኔን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሸምቆና አድፍጦ መምታት፣ ማውደም፡ ስንቅና ትጥቅ መማረክ፣
6. በዋና መንገድ ላይ የሚጓዙ የወያኔ መሆናቸው የተረጋገጠ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን በሽመቃና በደፈጣ ማቃጠል፣
7. የወያኔ ኣገዛዝ ንብረት መሆናቸው የተረጋገጡ ተቋማት ማቃጠል፣ ማውደም፣
8. በታቀደ መንገድ ከወያኔ ወታደራዊ ኃይሎች ግምዣ ቤቶች ላይ መሳሪያ ለመግፈፍ የሚያስችል ተግባራትን መፈጸም፣
9. ወያኔ የሚጠቀምበትን መሰረተ ልማቶች ማውደም፣
10. ለወያኔ ኣገዛዝ እንቅስቃሴ የሚረዱ ዒላማዎችን ማቃጠል፡ ከጥቅም ውጭ ማድረግ፣ ማውደም፣
11. ለጠላት የኢኮኖሚ ዋልታ የሆኑ ዒላማዎችን ማቃጠል፣ ማውደም፣
የወያኔን የሕዝብ መጨቆኛ ኃይሎችን ለማስተጓጐል፣ ለማሰናከል፣ ለመበታተንና ለማውደም የምንችለው የእኛን ኃይሎች በአነስተኛ ቡድን እያደራጀን በተለያዩ ቦታዎች ማንቀሳቀስ ስንችል ነው።
የጐሬላ ውጊያ እንደዚህ በተለያዩ ቦታዎች የተደራጁ ኃይሎች በሚወስዱት እርምጃ የጠላትን ኃይል የመበታተን አቅምን ይፈጥራል።
የጠላት የተበታተን ኃይል በተናጥል ለማጥቃት እንዲያመች በአነስተኛ ቡድን መንቀሳቀስ የሚችሉና በርካታ ቦታዎችን የሚሸፍኑ የጎሬላ ተዋጊዎችን ማደራጀት ያስፈልጋል። እነዚህ ኃይሎች በተለያዩ ቦታዎች የሚንቀሳቀሱትን የጠላት ኃይል በተናጥል በመምታት ጠላት የማዳከም ተግባራትን ይፈጽማሉ።
አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች የሚንቀሳቀሱ የጎሬላ ተዋጊዎች አንድ ላይ በማሰባሰብ ሰፋ ያለ ግዳጆችን እንዲወጡ በማድረግ ተመልሰው ወደነበሩበት የእንቅስቃሴ ሂደት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ይቻላል። የጎሬላ ተዋጊዎች እራሳቸውን ከአካባቢው ሁኔታ ጋር እያዋሃዱና የጠላት እንቅስቃሴ መሠረት አድርገው ነው ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሚያደርጉት። ጠላት ፈጽሞ የጎሬላ ተዋጊዎች የት እንደሆኑ ማወቅ የለበትም።
የጎሬላ ተዋጊዎች ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ስለሚንቀሳቀሱ ጠላት የነሱን ዱካ ለማግኘት ያስቸግረዋል።
በመሆኑም የጎሬላ ተዋጊዎች ሁልጊዜ እራሳቸውን በእንቅስቃሴ ውስጥ ማግኘት ይኖርባቸዋል። ጠላት እዚህ ጋር ናቸው ብሎ ሊገምት በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ መገኘት ይኖርባቸዋል።
የጐሬላ ውጊያ በባህሪው የጠላትን ኃይል መቶ በመሮጥ /Hit and Run/ ላይ የተመሰረተ ነው። እንደ መርህ የጐሬላ ተዋጊው ኃይል ወደ ጠላትም ሆነ ወደ ኋላ ወረዳ ወይም ነፃ መሬት በሚንቀሳቀስበት ጊዜ በሄደበት መንገድ አይመለስም፣ በተመለሰበት መንገድም እንደገና አይሄድም፤በዋለበት ቦታም አያድርም፣ባደረበት ቦታም አይውልም።
ይሄም ጠላት ጨርሶ የጎሬላ ተዋጊውን ዱካ እንዳያገኝ ያደርገዋል። የጎሬላ ተዋጊውም እራሱ ከጠላት እይታ በሚገባ እንዲሰውር ያደርገዋል።
የጎሬላ ውጊያ በምናካሄድበት ጊዜ መጨበጥ የሚገባን አስተምህሮ
መረጃ
ወደ ውጊያ ከመግባታችን በፊት በቅድሚያ ሶስት ነገሮችን በቅድሚያ በጥልቀት ማወቅ (Foreknowledege) ይኖርብናል እነሱም፦
1. ስለ ወገን (የራስህን የአጐራባች ክፍሎችን ጥንካሬዎችና ድክመቶች) ማወቅ፣
2. ስለጠላት (የጠላትን ጠንካራና ደካማ ጐኖች) ማወቅ እና
3. ስለ መሬት (አካባቢያዊ ሁኔታዎችን፦ስለመሬትና አየር ሁኔታ) ማወቅ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱትን 3 ነገሮች በጥልቀት የምንረዳበት ሁኔታ መፍጠር ከቻልን የምናደርገውን ውጊያ በብቃት ማሸነፍ የምንችልበትን ሁኔታ መፍጠር እንችላለን።
ስለራሳችን አቅም፣ ጥንካሬና ድክመት ማወቅ ከቻልን ባለን አቅም ልክ ምን መሥራት እንደምንችል ስለምንረዳ ከአቅማችን በላይ ከሆነ ኃይል ጋር በግብታዊነት ወይም በስሜት በመነሳት ውጊያ ውስጥ እንዳንገባ ያደርገናል።
ሁልጊዜ እንቅስቃሴዎችን ወይም ግዳጆችን መፈጸም የሚኖርብን ባለን አቅም ልክ ላይ ተመስርተን መሆን ይገባዋል። ይሄም በመጀመሪያ ያለን እውነተኛ አቅም ምንድነው ብለን በመጠየቅ ጥንካሬያችንና ድክመቶቻችን በመለየት ድክመቶቻችንን በመቅረፍ ጠንካራ ሆነን እንድንወጣ ያደርገናል።
ስለ ጠላት በቂ የሆነ መረጃ ማግኘት የምንፈጽማቸውን ግዳጆች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን ይረዳናል። በመሆኑም መረጃዎችን የሚያቀርቡልን ሰዎች በማሰማራት ስለጠላት በቂ የሆነ መረጃዎችና ግንዛቤዎች እንዲኖሩን ማድረግ ያስፈልጋል። ካለ መረጃ የሚደረግ ምንም አይነት እንቅስቃሴ መኖር የለበትም። ስለዚህ የጠላትን መረጃዎች ማግኘት የሚያስችል ተግባራትን መፈጸም ያስፈልጋል።
አካባቢን እንዲሁ በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል። ግዳጆችን ለመፈጸም የአካባቢው ሁኔታ አመችነትን ለመረዳት ቀድመን ስለ አካባቢው በቂ ግንዛቤ እንዲኖረን ማድረግ ያስፈልጋል። የውሃ ነጥቦች የት እንደሆኑ፤ ለመደበቂያ አመቺ የሆኑ ቦታዎች የትኞቹ መሆናቸውን፤ የተለያዩ እንቅስቃሴ ለማድረግ አመቺ የሆኑ አካባቢዎችንና ለደፈጣ አመቺ የሆኑ ቦታዎችን ለመለየት አካባቢን መልካ ምድርን የኣካባቢዊንን ወንዞች ተራሮችና ሚዳዎች አንደ እጃችን መዳፍ ማወቅ ያስፈልጋል።
ድንገተኝነት
በጠላት ላይ ድንገተኝነትን የምንወስደው በማንኛውም ጊዜ ጠላት ሳያስበው በድንገት ቅድሚያ የምንወስዳቸውን ርምጃዎች ሁሉ ያጠቃልላል። ድንገተኛ ማጥቃት ማለት ጠላት ሳያውቅና ለአፀፋ ምላሽ ጊዜ ሳንሰጠው የውጊያ የበላይነት ለማግኘት የሚደረግበት ሂደት ነው።
በውጊያ የበላይነት ለማግኘት ድንገተኛ ምት በጠላት ላይ ማሳረፍ ጠላት የመልሶ ማጥቃት ርምጃ እንዳይወስድብን ያደርገዋዋል። ጠላት የመልስ ምት ሊያደርግ የሚችልበትን እድል አለመስጠት የድንገተኛ ማጥቃት ዋና ጠቃሚ ጉዳይ ነው። በዚህ አይነት የማጥቃት ሂደት ጊዜ ከፍተኛ የምት ኃይልና ፍጥነት ወሳኙን ድርሻ ይይዛሉ።
በፍጥነት መንቀሳቀስ ወይም ፈጣን መነቃነቅን መፍጠር ጠላትን ለማሸነፍ ከሚረዱ ቁልፍ መገለጫዎች አንዱ ነው። የጠላት ዝግጁ
አለመሆንን ለእኛ ጥቅም በሚሰጥ መንገድ ለማዋልና ለመጠቀም ወደ ጠላት አቅጣጫ ባልተጠበቀ የጉዞ መንገዶች ተጓጉዞና ጠላት ጥንቃቄ ባላደረገባቸው የውጊያ ቀጠናዎች ላይ በድንገት ደርሶ ለመምታት የሚያስችል የተዋጊው ኃይል ፈጣን ተነቃናቂነትን መፍጠር ያስፈልጋል።
አቅርቦት (supply)
ማንኛውንም አይነት ስኬታማ ውጊያ ለማድረግ ከተፈለገ የሎጀስቲክ አቅርቦትን በሚገባው ቦታ ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ያለ ስንቅና ትጥቅ ዝግጅት አንድን ውጊያ ማከናወን አይቻልም። እንደ አንድ የጎሬላ ተዋጊ የትጥቅ አቅርቦትን በዘለቄታዊ ሁኔታ ማሟላት የሚችለው ከጠላት ላይ በመግፈፍ ነው።
ግንኙነት
ግንኙነትቶች በአጠቃላይ በሁለት ወይም ከእዛ በላይ በሆኑ ሰዎች ወይም አካሎች መሀል የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦችን የሚያመለክት ነው።መረጃው የግድ መተላለፍና መቀበል ወይም መረዳትን የሚጠይቅ ነው። በአንድ ተዋጊ ኃይል ውስጥ የሚደረግ ግንኙነት ማለት ማንኛውንም አይነት መንገድና ዘዴ በመጠቀም ከአንድ ሰው ወይም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ወይም ወሬዎችን ለሚመለከተው ሰው ወይም አካል ማሰራጨት ማለትነው። ይህ ግንኙነት ምስጥራዊነትን የተላበሰ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል።
ደፈጣ
ደፈጣ ማለት አንድ የጎሬላ ተዋጊ በአንድ ለማጥቃት አመቺ በሆነ ቦታ ላይ እራሱና ደብቆ የጠላት ኃይል በሚመጣበት ጊዜ ድንገተኛ በሆነ መንገድ የተኩስ ውርጅብኝ በመፈጸም የሚያኬድ የጥቃት አይነት ነው። በዚህ የጥቃት ሂደት የጠላትን ኃይል ወይም ንብረት የሆነውን ማንኛውንም ነገሮች ደምስሶ ወይም አውድሞ በፍጥነትና ቅልጥፍና መሰወር ነው።
በደፈጣ የሚደረግ ማጥቃት ጠላትን ለከፍተኛ ውዥንብር ስለሚዳርገው የጠላትን የመልሶ ማጥቃት አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ይሰብረዋል። በዚህም የወገን ኃይል ከፍተኛ የሆነ ድልን የሚጎናጸፍበት እድል ይፈጥርለታል።
ደፈጣ በምናካሄድበት ጊዜ መውሰድ የሚገባን ግንዛቤ
1. የወገን ሀይሎች ተስማሚ የቦታ አያያዝ፦
ውጤታማ ደፈጣ ለማከናወን የጎሬላ ተዋጊዎች ጥሩ የተኩስ ሽፋን ሊሰጡ የሚችሉበትና ጥሩ መደበቂያ ያለበትን ቦታ መርጠው መያዝ ይኖርባቸዋል። ይህም ጠላት በቀላሉ ውጤታማ የሆነ መልሶ ማጥቃት እንዳያደርግ ያግደዋል።
2. የመግደያ ወረዳ አቀማመጥ፦
የመግደያ መሬት ማለት ደፈጣው በሚደረግበት ቦታ ላይ አጠቃላይ ተኩሱ ትኩረት የሚያደርግበት አካባቢ ወይም ቦታ ነው። የተመረጠው የመግደያ መሬት ጠላት ከጎሬላው ተዋጊ የሚሰነዘርበትን ጥቃት ሊከልል ወይም ሊመክት ወይም ሊደብቃቸው የማይችልባቸው ቦታዎች መሆን ይኖርበታል። ጠላት ከሚደርስበት ጥቃት ማምለጥ የማይችልበት የመሬት አቀማመጥ ያለበት “የሞት ወረዳ” /DEAD ZONES/” ነው። የመግደያ ወረዳ በወገን የተኩስ መስመሮች በሚገባ የተሸፈነ ሊሆን ይገባል። የወገን ኃይል የያዛቸውን ቦታዎች ከመልቀቁ በፊት ማንኛውም ጠላት አቅም ስለሚኖረው ለያዘው አቅም ሁሉ በተኩስ ቁጥጥር ስር ሊሆንና ሊተኰስበት ይገባል። በእንደዚህ ዓይነት ቦታዎች የገባን ጠላት ሙሉ በሙሉ ከመደምሰስ ውጪ ሌላ አማራጭ ሊኖር ይገባል።
3. የተኩስ ትክክለኛ ወይም ተገቢ ጊዜ ላይ አጀማመር፦
የደፈጣውን ተኩስ ለመጀመር ከአዛዡ የሚወርድ ትእዛዝ ይጠበቃል። ደፈጣው ሊጀመር አካባቢ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፣ስለእዚህ እያንዳንዱ ሰው በዒላማው ላይ ያነጣጥርና ለመተኮስ ዝግጁ ይሆናል፤ ትእዛዝ አንዴ ከተሰጠ በኋላ ሁሉም ሰው ከፍተኛ ሁኔታ ወደ መግደያ ወረዳ ይተኩሳል፤ ሁሉም የጠላት ሀይሎች-ተሽከርካሪዎችና ሠራዊት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ እስኪረጋገጥ ድረስ ወይም አዛዡ ተኩስ እንዲቆም ወይም የተኩሱ አቅጣጫ እንዲለወጥ ትእዛዝ እስኪሰጥ ድረስ በጠላት ላይ መተኮሱ ይቀጥላል። ጠላት ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ወይንም ከባድ ጉዳት ደርሶበት መሽመድመዱ እንደተረጋገጠ በፍጥነትና ቅልጥፍና በተሞላው መንገድ የጎሬላ ተዋጊዎቹ ከአካባቢው መሰወር ይኖርባቸዋል።
ጥብቅ ስነ ስርአት/ ዲሲፕሊን መኖር
የጎሬላ ውጊያ ውጤታማነት በጥብቅ ስነ ስርዓት መታነጽ ላይ ይወሰናል። ስለዚህ አባላቱ ምንም አይነት የስነ ስርዓት ግድፈት ሊታይባቸው አይገባም። በስነ ስርዓት ያልታነጸ ሰው እራሱ እና ድርጅቱ ላይ አደጋ የመጋበዙ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ችላ የሚባል ተግባር አይደለም።
የጎሬላ ውጊያ እና ይህን ተግባራት የሚወጡ አባላት የሚኖራቸው ጥብቅ የሆነ ስነ ስርዓት ተነጣጥለው የሚታዩ አይደሉም። የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። በመሆኑም አባላት ከፍተኛ ዲሲፕሊን ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።
ቅድሚያ የመውሰድ ተነሳሽነት
አንድ ለነጻነት የሚታገል ኃይል ቅድሚያ የመውሰድ ተነሳሺነቱን ካጣ የሚፈልገውን የሚያደርግበት ወይም እንቅስቃሴውን የሚመራበት ነፃነት ያጣል ማለት ነው።
ይሄም እንቅስቃሴውን ደካማ ወይም የተጓተተ እንዲሆን ያደርገዋል። በመጨረሻም ለውድቀትና ለሽንፈት የሚዳረግበት ሁኔታ አይቀሬ ያደርገዋል። ጨርሶውኑም እንዲጠፋ ምክንያት ይሆናል።
ጠላትህን በሚገባ ማወቅ አለብህ። መረጃ ለማግኘት የመጀመሪያ ሁን፤ ውሳኔ ለመውሰድ የመጀመሪያ ሁን፤ እርምጃ ለመውሰድ የመጀመሪያ ሁን። ጠላት ላይ የበላይነትን ለመጎናጸፍ የሚቻለው ከላይ የተቀመጡትን ተግባራት ለመወጣት የሚያስችል አቅም ሲፈጠር ነው። ጠላትን በመከላከል ተግባር ላይ ብቻ ተወስኖ እንዲቀርና በኋላም እንዲደመስስ ማድረግ የሚቻለው የወገን ኃይል ቅድሚያ የመውሰድ ተነሳሽነቱ ከፍተኛ መሆን ላይ ባለው ጥንካሬ ነው።
ቅድሚያ የመውሰድ ተነሳሽነት ያለው ኃይል በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እራሱን ያገኛል። ይህም የጠላት እንቅስቃሴ በወገን የማድረግ አቅም ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ያደርገዋል።
የጠላት/የወያኔ ሠራዊት ኣደረጃጀትን ዶክትሪን
የወያኔ ሠራዊት ኣደረጃጀት በከፊል መደበኛ በከፊል ፀረ ሽምቅ ስልጠና የወሰደ የፀረ ሽምቅ የጦር ስልቶችን የሚጠቀም ነው።
 ወያኔ የሚከተለው የፀረ ጎሬላ/ሽምቅ መሰረታዊ ዶርክትሪን/መርሆ/ፍልስፍና ኣለው።
ይህም፥ ኣንድ ሽምቅ ተዋጊ ኃይል - በኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ኣለበት የሚል ነው። የተወሰደ ጊዜ ተስወዶ፣ የፈለገው ኃይል ወስዶ፣ መስዋዕትነት ተደርጎ፣ በየትኛውም አካባቡው የሚገኝ የሽምቅ ኃይል መደምስ ወይንም መማረክ አለበት የሚል ነው። በአንጭጩ ኣስቀረው፤ አስኪያድግ ጊዜና ፋታ ኣትስጠው የሚል ነው።
 ኣንድ የሽምቅ ተዋጊ ህይል ባለበት ቦታ ሁሉ ፀረ-ሽምቅ ኃይል በኣካባቢው ይመደባል፤ ሥራው ሸማቂውን ማሳደድ ፥ ፋታ ማሳጣት፣ መምታት፣ መደምሰስ ወይንም መማረክ ኣለበት የሚል ነው። ኣንድም ሸማቂ ፣ የቆሰለ ሸማቂም ቢሆን በሕይወት መኖር የለበትም፤ መደምሰስ ወይንም መማረክ ኣለበት በሚል የወያኔ ዶክትሪን ያስቀምጠዋል። ወያኔ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ 10,000, 20,000 ሠራዊት ለሞትና ለምርኮ ቢዳርግ ከቁብም ኣይቆጥረውም። ሠራዊቱን የእሳት ራት ከማድረግ ምንም ኣያግደውም።
ስለዚህ የሕዝባዊ ኣመጹ ኣካል የሆኑ የነጻነት ኃይሎች መከተል የሚገባቸው ዶክትሪን/መርሆዎች
1. ከምንም በላይ ራስን መጠበቅ፡ ህልውናን መጠበቅ (survival) ላይ የተመሰረተ መሆን ያለበት- ባልታሰበ የጠላት ከበባ ላለመያዝ ከፍተኛ ጥንቃቄ አንደ ብረት የጠነከረ ዲስፕሊና ከፍተኛ የመረጃ ብቃት አንዲኖርው ማድረግ የግድ ይላል። አካባቢውን በአይነ ቁራኛ መጠበቅ፤ ቅኝት ማድረግ፣ ንቁ ሆኖ ራስን ከጠላት ጥቃት መጠበቅ፣ አካባቢህን አንደ እጅህ መዳፍ ማወቅ የግድ ይላል። ከጠላት ጋር የሚደረጉ ፍልሚያዎች ከጀብደኘት የራቁ ብልሀትን፣ ስልትን፣ መርጃን ከደፋርነትና ጀግነነት ጋር ያጣመሩ መሆን ኣለባቸው። ከግዙፍ የጠላት ኃይል ጋር ፊት ለፊት ኣለመግጠም። በኣቅምና በብዛት ካኣንተ በላይ የሆነ ጠላት መሸሽ ብልሀት አንጂ ፍርሃት ኣይደለም።
2. የአቅም ቁጠባ - ብዙ ዒላማዎች ላይ ከመሯሯጥ ወሳኝ በሆኑ ጥቂት ዒላማዎች ላይ ማነጣጠርና ማጥቃት።
3. ድንገተኛ ጥቃት - ጠላት ባልጠበቀው ቦታና ሰዓት በሰውም ሆነ በጦር መሣሪያ ንብረት ላይ ጥቃት ማድረስ
4. እልህና ቁርጠኝነት - አርበኛው የሚወስዳቸው ማናቸውም አይነት ጥቃቶች ጠላትን ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎ መደቆስ
5. የአላማ ጽናት - ጠላት ምንም አይነት የአጸፋ እርምጃ ቢወስድም አርበኛው ሳይዘናጋና ልቡ ሳይከፈል ተልዕኮውን መፈጸም
ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
• በሕዝብ የታቀፈና የተደገፈ የአርበኞች ትግል አሸናፊነቱ ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ነው። ይህን ዕውነት በተመለከተ ኢትዮጲያ ብዙ ታሪክ አላት። በተለይም በአምስት ዓመቱ የፋሺስት ኢጣሊያ ዘመን አርበኞቻችን ያሳዩት ተጋድሎና ፅናት፣ የሃገር ፍቅርና የሕዝብ ድጋፍ ትልቁ ምሳሌ ነው። ራስ ኣበበ ኣረጋይ በሸዋ፣ ራስ ኣሞራው ውብነህ በጎንደር፣ ፊታውራሪ በላይ ዘለቀ በጎጃም፣ ደጃዝማች በቀለ ወያ እና ደጃዝማችህ ግረሱ ዱኪ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ኮ/ል ኣብዲሳ ኣጋ፣ ልጅ ሀይለማርያም ማሞ፣ ጀ/ል ጃጋማ ኬሎ ፣ ራስ መስፍን ስለሺ፡ ቢትወደድ ኣዳነ፣ ከሴቶች አነ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ፡ በፋሽስት ጣልያን የወራራ ዘመን የኣርበኝነት የሽምቅ ውጊያ የኣርበኝነት ተጋድሎ ካደረጉ ኣርበኞች ጥቂቶቹ ናቸው።
• በከባድ መሳሪያና በጦር ኃይል ብዛት የታገዘን ጠላት ፊት ለፊት መጋፈጥ የእሳት እራት መሆን ነው፤ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ነው።
• የሽምቅ ተዋጊው ሁልጊዜም ቢሆን ራሱ በሚመቸውና በሚወስነው ቦታና ሰአት ብቻ መዋጋት ይኖርበታል። መቼ ማጥቃትና መቼ ማፈግፈግ እንዳለበት የሚወስነው እሱ ብቻ ነው።
• ስለ ጠላት እንቅስቃሴ በቂ መረጃ አስቀድሞ መሰብሰብ የግድ ይላል። የጠላት የሰው ኃይል ብዛት፣ የመሳሪያ አይነት፣ የቅድመ ዝግጅትና እቅድ መረጃዎች በጁ ካሉ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች እጅግ ጠቃሚዎች ናቸው።
• በስርአት የታነጸና ጥሩ ልምምድ ያለው ትንሽ የሽምቅ ጦር ብዛት ያለውን የጠላት ጦር ማሸነፍ እንደሚችል ታሪክ በተደጋጋሚ አሳይቷል። በቻይና በጃፓን ኢምፔሪያሊስም ላይ፤ በኣፍጋንሲታን በሩስያ ላይ፤ በቪየትናም በኣሜሪካ ላይ በሕዝብ የተደገፉ በብዛትም በመሳሪያ ብዛትናኣ ጥራት ኣናሳ የሆኑ ሽምቅ ተዋጊዎች ድል ኣድርገዋል።
• የአላማ ግልጽነት፤ የመንፈስና የሞራል ጽናት፣ አንዲሁም ስትራቴጂካዊ ብልሀትና ብልጠት ለድል ኣድራጊነት ትልቅና ወሳኝ ድርሻ ኣላቸው።
• በቂ የውጊያ ልምምድና በራሳቸው መቆም የሚችሉ ተዋጊዎች ጽናት፣ ቆራጥነትና በመረጃና በእቅድ የሚሰሩ ጠንካራ መሪዎች መኖራቸው ሌላው ውስኝ ግብዓቶች ናቸው።
• የሽምቅ ውጊያ ከመደበኛ ጦርነት የሚለየው በመሳሪያም ሆነ በሠራዊት ብዛት ታግዞ ጠላት ላይ አንድ ትልቅ ጥቃት ማድረስ ሳይሆን አሳቻ ጊዜና ቦታ እየመረጠ ተደጋጋሚና ትንንሽ የደፈጣ የወረራ ጥቃቶች ማድረሱ ላይ ነው።
• ጠላትን ድንገት ማጥቃት፣ ማቁሰልና ማዳከም አይነተኛ ባህሪዎቹ ናቸው። ኣንድ ሽምቅ ተዋጊ ድንገት ያጠቃል፣ ያፈገፍጋል፣ ይበተናል ደግሞ ተመልሶ ተደራጅቶ ያጠቃል።
• የሽምቅ ተዋጊ አርበኛ አወቃቀር እንደልብ የሚደራጅና ሲያስፈልግም የሚበተን መሆን አለበት።
• ከተማን መቆጣጠርና ትላልቅ የኢኮኖሚ አውታሮችን መያዝ ወይንም ገዢ መሬቶችን መቆጣጠር፣ ተቶጣጥሮም አነዚህን መከላከል የሱ ሥራ አይደለም።
የሽምቅ አርበኛው ዋና አላማዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
1. ተከታታይነት ያላቸው ትናንሽ ጥቃቶች በበርካታ ኣካባቢዎች ማካሄድ፣ ጠላትን እንቅልፍ መንሳት፣ ማበሳጨትና ሞራሉን ማዳከም፡
2. ጥቃቱን ተደጋጋሚና በሁሉም አቅጣጫ ማድረግ፡ ጠላት ሁሉንም ኣቅጣጫ ለመከላከል፡ የሠራዊት ክምችቱ እንዲበታተን፣ አንዲለጠጥ፣ ኣንዱ የጠላት ኃይል ለሌላው የጠላት ኃይል አንዳይደርስ፣ ኣቅሙና ጉልበቱ አንዲበታተን፣ እንዲከፋፈል ማስገደድ፤
3. ቀልጣፋ የሆነ የማፈግፈግ ስልት መጠቀም፣ እንደገናም ደግሞ ማጥቃትና እሱ ራሱ የሸማቂው ቡድን የወጠነው ዕቅድ ካልሆነ በቀር የጠላትን ጦር ቀጠና መልቀቅ።
4. በፍጹም በጀብደኝነት አለመጋፈጥ፤ መረጃን፣ የጎሬላ ስልቶችን፣ ጥበብን፣ ብልጠትና ብልሀትን መሠረት ኣድርጎ መንቀሳቀስ።
• በማያቋርጥ ተለማጭና ተለዋዋጭ እንቅስቃሴ ላይ በመሆኑ የሽምቅ ተዋጊው በቀላሉ የጠላት ኢላማ ውስጥ አይወድቅም። አስፈላጊውን ጥቃት ከፈጸመ በኋላ ይሰወራል።
• አርበኛው ሊፈጽመው ያሰበው ጥቃት ግልጽ የሆነ ሌሎች አርበኛ ባልደረቦቹ የተረዱትና በሚገባ የተዘጋጁበት መሆኑ በጣም ኣሰፈጊና መሰረታዊ ነው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ በቂ የሆነ መረጃ ሊኖር ይገባል።
• አርበኛው ስለጠላት ሊኖረው የሚገባው ሁለንተናዊ መረጃ እጅግ ወሳኝ ነው።
• በጥሩ መረጃና በጥሩ ሞራል የሚንቀሳቀስ አርበኛ ግዳጁን ከመፈጸም የሚያግደው ምንም አይነት ኃይል አይኖርም።
• ይህ ትግል ረዥምና የሚያስከፍለውም መስዕዋትነት ከፍተኛ ቢሆንም እንኳ በዓላማ ጽናትና በመንፈስ ብርታት የታነፀን አርበኛ ካለመው ግብ ከመድረስ አያግደውም፤ ያሸንፋል እንጂ በፍጹም አይሸነፍም።
• በየቀኑ የሚቀዳጀቸውን ትናንሽ ድሎች እያበረከተ ከፍ ወዳለ ደረጃ ማድረስና የሕዝቡንም ንቃትና ድጋፍ ማሳደግ የሽምቅ ተዋጊው ዋነኛ አላማ መሆን ይኖርበታል።የአርበኛውና የሕዝቡ መደጋገፍ ወደ ማያጠራጥር የድል ጎዳና ያደርሳል።
• የጠላትን ጦር እንቅስቃሴና ግንኙነት በመግታት ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ብቻ አፍኖ ይዞ በገጠሩና ትናንሽ ቀበሌዎች ውስጥ አርበኛው የራሱን የተቀውሞ ጎራ ማጠናከርና ብሎም በየፊናቸው የሚንቀሳቀሱትን ሌሎች አርበኞች ወደ አንድ ስብስብ ማምጣት ይኖርበታል።
• የአርበኛው ቀዳሚ ስትራቴጂ ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ ጠላት ባላሰበው ሰአትና ቦታ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ነው። ይህን ሲያደርግም የጠላት ጦር መልሶ ለማጥቃት የሚችልበትን አቅም ሙሉ በሙሉ በማሳጣት መሆን ይኖርበታል።
ማጠቃለያ
ኣርበኞች የራሳቸውን ህልውና ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ፡ በመረጃና በአቅድ ላይ ተመስርተው የሚከተሉትን መተግበር፦
1. በመላው ኢትዮጵያ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በዞን፣ በክልል የሚገኙና በሕዝብ ላይ ግፍ የሚፍጽሙ የወያኔን የኣስተዳድርና የደህንነት የፖሊስ ጣቢያዎች፡ የሚሊሽያ መዋቅሮችን ማጥቃት ፣ መበጣጠስ፣ በሕዝብ ላይ ግፍና ጥቃት የሚፈጽሙትን ግለሰቦች መምታት፣ ማሰወገድ፣
2. በመላው ኢትዮጵያ በጠላት ስስና ደካማ ጎኖች፤ በትናንሽ ተነጣይ የጠላት የጦር ክፍሎች ላይ የደፈጣና የወረራ ጥቃቶች፡
3. በኣራቱም የኢትዮጵያ ማእዘናትና ለወያኔ ግኙነትና ኣቅርቦት የሚያገልግሉና ዋና ዋና መንገደች ላይ በሚንቀሳቅሱ የጠላት መሆናችቸው በተረጋገጡ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ዲፖ መኪናዎች ላይ በመረጃናላይ የተመሰረቱ የደፈጣ ጥቃቶች መሰንዘር፡
4. የጠላት ወይንም የወያኔ ኢኮኖሚያዊ ተቋማት መሆናቸው በተረጋገጡ ላይ የማቃጠል፣ የማውደም አርምጃዎችን መውሰድ፡
5. በኣናሳ የጠላት የጦር ሰፈሮችና የፖሊስ ጣቢያዎች ላይ፣ ወዘተ የደፈጣና የወረራ ድንገተኛ ጥቃቶችን ተግባሪዊ ማደረግ፡
6. በጠላት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ሁሉ ኣርበኛው በመረጣቸው ጊዜ፡ ቦታና ሁኔታዎች ተመስርቶ ጥቃቶችን በብዛትና በስፋት በበርካታ ኣካባቢዎች ማድረግ፡
7. አነዚህ በተደረጉ መጠን የወያኔ ሠራዊት ሞራል ይብሱኑ አየተዳከመ ይሄዳል፣ ክመዳከምም ኣልፎ ሞራሉ ይላሽቃል፣ ይሰላቻል። የሚከዳው፣ የሕዝቡን ትግል የሚቀላቀለው፤ አንዲሁም በወያኔ ኣዛዦቹ ላይ የሚያምፀው ሠራዊት ቁጥር ይጨምራል።
8. በተለይም በሁሉም ቦታዎች፣ ኣካባቢዎችና ዋና ዋና የግንኙነትና የኣቅርቦት መንገዶች ላይ የሚደረጉ ወረራና ደፈጣዎች ሲበራከቱ፣ የወያኔ ጦር ኃይሉን በየቦታው ለመበታተን ይገደዳል፣ ወይንም ጥቂት ዋና ዋና ከተሞች ላይ ኃይልኑን ኣከማችቶ አነዚህን ከሸማቂ ኣርበኞች ለመከላከል ይገደዳል።
9. የጠላት ጠንካራ ጎኖቹ መሳሳት መመናመን ሲጀምሩ የጠላት መሪዎች በከፍተኛ ደረጃ ይሸበራሉ፤ ለማቀድ ለማሰብ ኣስቦ ለመንቅሳቅስ የማይችሉበት የሞራልና የስነልቦና ሁኔታ ውስጥ የሚገቡበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይህ ደግሞ ሕዝብን የሚስቆጣ ትግሉን የሚያግዙና የሚያጠናክሩ በርካታ ትልልቅ ስህተቶች እንዲፈጽሙ ያደርጋቸዋል፡፡
10. በዋና ዋና መንገዶች ላይ የጠላት የኣቅርቦትና የግንኑነት መንገዶችና መስመሮች ላይ የሚንቀሳቅሱ ተሽከርካሪዎች ከደፈጣ ጥቃቶች ለመከላከል ጠላት ኮንቮይ ወንም አጃባ ይጀምራል። ይህ ደግሞ በሠራዊቱ ላይ ብቻ ሳይሆን በወያኔ የኢኮኖሚያዊ ተቁዋሞች ላይ ከፍተኛ ውጥረትና አጥረት ይፈጥራል፡
11. የጠላት የገንዝብ ኣቅሙ ሰራዊቱን ለመቀለብና ለማስታጠቅ ያለው ኣቅም ይመናመናሉ። በሁለንተናዊ መልኩ የጠላት ጠንካራ ጎንኖቹ ሁሉ መሳሳት፣ መዳከም፣ መመናመንና መፍረክረክም ይጀምራሉ። በ100 ቦታ ላይ በስለት ተወግቶ ደሙ ያለማቋረጥ እንደሚፈስና ለሞት እንደሚጋለጥ ሰው ይሆናል።
12. ለሸማቂው ኣርበኛ የተመናመኑና የተበታተኑን አነዚህን የጠላት ሠራዊት ክፍሎች በብዛት ኣድቅቆ ለመምታት ለመደምሰስ ለማውደም የሚያስችለው ኣዳዲስ ሁኔታዎችን ይፈጠርለታል።
13. በዚህ ሂደት የሽምቅ ተዋጊ ኣርበኞች ሞራልና የውጊያ ልምድ በከፍተኛ ደረጃ መዳበር ይጀምራል። የሕዝብ ወገኖች በራስ የመተማመን፣ ሥርዓቱን በድፍረት የመታገል፤ ሕዝብም ለኣርበኛው የሚሰጠው ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል። ኣርበኛውን የሚቀላቀለው ኢትዮጵያዊ በከፍተኛ ቁጥርና በስፋት ማግኘት ይጀምራል፣ ኃይሉ ይጠናከራል፤ ከሽምቅ ተዋጊነት ወደ ሞባይል ጦርነት/ማለት አንደ መደበኛ ጦር የመዋጋት ደረጃ የሚሸጋገርበት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ለድል መቃረብን የሚመልክት ኣንዱና ትልቁ መለኪያ ይሆናል ማለት ነው።
ኣንብበው ያስተላልፉ
(Via Neamin Zelek)

No comments:

Post a Comment

wanted officials