Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, December 25, 2016

“በልጄ የልደት ቀን ተገኙ” የሚል ግብዣን በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጩት አባት በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን ለማስተናገድ ተገደዋል


 በሜክሲኮ ላ ጆያ ማህበረሰብ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ አንድ ልማድ አለ፤ ሴቶች ከተወለዱ 15 ዓመት ሲሆናቸው የልደት ቀናቸውን በልዩ ዝግጅት ማክበር፡፡
ይህ ባህል “የኩዊን ሴናሪአ” በዓል ይባላል።
በዓሉ ሴቶች ከልጅነት ወደ ኮረዳነት የሚሸጋገሩበት የ15ኛ ዓመት የልደት በዓል ማክበርን ለመግለፅ ያገለግላል።
የሩቢ ኢብራ ጋርሺያ ቤተሰቦችም "ክቡራት እና ክቡራን እንዴት ናችሁ፤ በታህሳስ 26 የፈረንጆች 2016 ዓመት በልጃችን ሩቢ ኢብራ ጋርሺያ 15ኛ ዓመት የልደት በዓል እንድትገኙልን እና የደስታችን ተካፋይ እንድትሆኑ ስንል በአክብሮት ጠርተንዎታል" የሚል መልዕክት በቪዲዮ ቀርፀው በማህበራዊ ትስስር ገፆች የታደሙልን ግብዣ ያስተላልፋሉ።
ይህን ግብዣ ተከትሎም በሩቢ ልደት ላይ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ሰዎች እንደሚገኙ ያሳውቃሉ።
የሩቢ ቤተሰቦች በማህበራዊ ትስስር ገፆች ያስተላለፉት የቪዲዮ መዕዕክት ከ800 ሺህ በላይ ጊዜ የተጋራ ሲሆን፥ ለቁጥር የሚያዳግት አስተያየትንም አስተናግዷል። ይህ ለምን ሆነ የሚለው መልስ የለውም።
የሜክሲኮ አየር መንገድም ተጓዦችን ወደ ሩቢ 15ኛ ዓመት የልደት በዓል ከሆነ የሚጓዙት የ30 በመቶ የቲኬት ዋጋ ቅናሽ አድርጋለሁ ማለቱም አነጋጋሪ ነበር።
ግብዣውን በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ከተመለከቱ እና እንገኛለን ካሉት ውስጥም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በልደቷ ላይ ለመገኘት በቅተዋል፤ ይህም በሩቢ ቤተሰቦች ላይ አግራሞትን ፈጥሯል::
በሺህ ሰው መሃል ከልጃቸው ጋር የተገኙት የሩቢ አባት አቶ ኢብራ ጋርሺያም ለተሰበሰበው ሰው "ጥሪውን ያከናወነው ለጎረቤቶቻችን እና ለጓደኞቿ ቢሆንም በልጃችን የ15ኛ ዓመት የልደት በዓል ላይ ለመታደም የመጣችሁ ሁላችሁም ለበዓሉ የተሰናዳውን ድግስ እንድትበሉ፣ እንድትጠጡ በፈረስ እሽቅድምድም እና በሙዚቃ ባንድ ጨዋታዎች እንድትዝናኑ እጠይቃለሁ” አሉ።
በእለተ ሰኞም በሩቢ የልደት በዓል ለታደሙት ሁሉ የተለያዩ የምግብ እና መጠጥ አይነቶች በየጠረጴዛቸው ቀረበ፤ ከድግሱ በኋላም ሩቢ በተሰበሰበው ህዝብ መሃል በወላጆቿ "እደጊ" ተብላ ተመረቀች።
በሺህዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችም ሩቢን "መጪው ዘመንሽ የተባረከ ይሁን" በማለት የማስታወሻ ፎቶ ለማንሳት የስልክ ካሜራቸውን አነጣጠሩባት።me_cameera.jpg
የሩቢ 15 ዓመት የልደት ቀን በዚህ መልኩ ሲከበር አባቷ አቶ ጋርሺያ በፈረስ እሽቅድምድም ተሳትፎ ያሸነፈ ሰው 10 ሺህ የሀገሪቱ ፔሶ ወይም 490 የአሜሪካ ዶላር እንደሚሸልሙ መናገራቸውን ተከትሎ ብዙዎች በውድድሩ ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም የሩቢ አባት አቶ ኢብራ ጋርሺያ “በዚህ እለት እኛ ጋር ሆናችሁ የልጃችን 15ኛ ዓመት የኩዊን ሴናሪአ በዓል ታድማችሁ፣ ለልጃችን መልካም የተመኛችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን” ብለዋል።
በቴሌቪዥን ቀርበው ስለሁኔታው ሲጠየቁም “ያልጠበቅነው ግን ደስ የሚል ነገር ነው ያጋጠመን” ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials