የወያኔ ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ ሲሄዱ የሚ ያሳቅቃቸው የ ዲሲ ታስክ ፎርስ መሪ ቴዎድሮስ ካብትይመር ፍርድ ቤ ት ቀረበ
በኢትዮጵያ ፓርላማ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ድርጅቶች ከግንቦት ሰባት እና ኦነግ ጋር በትብብር በመስራት በኢትዮጵያ መንግስትና ባለስልጣናት ላይ የሽብር ተግባር በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ በአሜሪካ የቨርጂንያ ግዛት መንግስት ክስ በመመስረት ፍርድ ቤት ማቅረብ ጀመረ፡፡
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ ጉብኝት በሚያደርጉበት በተለያዩ ጊዜያት ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር የአሜሪካን ሰላምና ፀጥታ ባደፈረሱ የግንቦት ሰባት እና ኦነግ አባላት ግለሰቦች ላይ ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የቨርጂንያ ግዛት መንግስት ወደ ፍርድ ቤት ማቅረቡ ታውቋል፡፡ በዚህም ራሳቸውን የዋሽንግተን ዲሲ ግብረ ኃይል ብለው ለሚጠሩ የግንቦት 7 ሽብር ቡድን መሪ የሆነውን ቴዎድሮስ ካብትይመር የተባለውን ግለሰብ የቨርጂኒያ መንግስት ክስ በመመስረት ወደ ፍርድ ቤት ማቅረቡ ታውቋል፡፡ ክሶቹም፡-
1. የአከባቢውን ሠላምና ፀጥታን በማደፍረስ ወንጀል
2. በግለሰቦች ላይ ጥቃት በማድረስና
3. ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በመቃወም በህዝቡ ላይ ፍርሃትና ድንጋጤ በመፍጠር ወንጀል መሆኑ ታውቋል፡፡
The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia
https://www.youtube.com/watch?v=yCHXAmoLLdI
No comments:
Post a Comment