ሰዎች የሞት አፋፍ ላይ ሲሆኑ ምን ያወራሉ…?
ሰዎች በሞት አፋፍ ላይ ሲሆኑ አጠገባቸው ላሉ ሰዎች ምን ያወራሉ የሚለው በርካቶችን ሊያነጋገርር ይችላል።
የስነ መለከቶት ተማሪ የነበረው እና በኋላ ላይ በሆስፒታል ውስጥ በማይድን በሽታ የተያዙ ሰዎችን የሚያማክር ቄስ የሆነው "የOn Living" መጽሃፍ ደራሲው ኬሪ ኤጋን ህይወታቸው ለማለፍ ከጫፍ ላይ የደረሱትን ሰዎች በማናገር በኩል ብዙ ልምድ አለው።
ኬሪ ኤጋን በዚህ ዘርፍ ላይ ከተማሪነት አንስቶ ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ ሲሆን፥ ከዚህ በመነሳትም የረጅም ጊዜ ልምዱን አካፍሏል።
ኬሪ ይናገራል፥ “ከ13 ዓመት በፊት ገና ተማሪ እያለሁም ይሁን አሁን ከሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎችን ሆስፒታል፣ መኖሪያ ቤት አልያም እንክብካቤ በሚደረግላቸው ቦታ በመሄድ አናግራለቸዋለሁ፤ ሰዎች ሊሞቱ ሲሉ ስለምን ማውራት ይፈልጋሉ ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እችላለው”።
“በርካቶቻችሁ ሰዎች ለመሞት ከጫፍ በሚደርሱበት ጊዜ ስለ ፈጣሪያቸው አልያም ንሰሃ ስለ መግባት ብቻ ነው የሚያወሩት ብላችሁ ልትገምቱ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አይደለም” ይለናል።
“ሰዎች ሰዎች የሞት አፋፍ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ በብዛት የሚያወሩት ስለ ቤተሰባቸው ነው፤ ስለ እናታቸው፣ አባታቸው፣ እህታቸው፣ ወንድማቸው፣ ልጆቻቸው፣ ስለ ትዳር አጋራቸው ነው የሚያወሩት” ሲልም ኬሪ ተናግሯል።
“በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎች በውስጣቸው ስላለ ፍቅር፣ ለሰዎች ስለሰጡት ፍቅር፣ ከሰዎች ስላጡት ፍቅር፣ በቅጡ ሳይጠቀሙበት ስለቀሩት ፍቅር፣ በጣም ከመጠን በላይ ስላፈቀሩት ሰው እና የመሳሰሉትን ማውራትም ምርጫቸው ነው” ሲል ኬሪ ይናገራል።
“ሰዎች ለመሞት የመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ ሲሆኑ ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዴት እንደተማሩ ማውራትን ይመርጣሉ” ያለው ኬሪ፥ ለመሞት በመጨረሻዋ ደቂቃ ምራቃቸውን አፋቸውን ሞልቶ ነገሮች አልታያቸው ሲል እንኳ እጃቸውን እያወራጩ እማማ፣ አባቴ፣ እናቴ እያሉ ቤተሰቦቻቸውን ይጣራሉ” ይላል።
“ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ያልገባኝ እና አሁን የተገለጸልኝ ነገር፤ ሰዎች ለመሞት ከጫፍ ላይ ሲደርሱ ስለ ፈጣሪ ሳይሆን ስለቤተሰቦቻቸው ነው ለቄሶች የሚናገሩት፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ሰዎች ስለ ፈጣሪያቸው በዚህ መልኩ ስለሚናገሩ ነው፤ ይህ ደግሞ የህይወትን ትርጉም የምንገልጽበት መንገድ ነው፤ የሰው ልጆች ስለመኖራቸው በሀይማኖታዊ መንገድ ለሚቀርበው ጥያቄም ምላሽ የሚሰጥ ነው” ሲልም ኬሪ ያብራራል።
“በስነ መለኮት እና እና በሌሎች ፅንሰ ሀሳቦች ላይ እንደተቀመጠው ኑሮን የምንኖረው በጭንቅላታችን ውስጥ አይደለም” የሚለው ኬሪ፥ “ኑሮን በተወለድንበት ቤተሰብ፣ በፈጠርነው ቤተሰብ፣ ጓደኞቻችን እንዲሆኑ ከመረጥናቸው ጓደኞቻችን ጋር በመሰረትነው ቤሰብ ውስጥ ነው የምንኖረው” ይላል።
“ይህ ቦታ ኑሮን የምንመሰርትበት ስፍራ ነው፣ ይህ የኑሮን ትርጉም የምናገኝበት ስፍራ ነው፣ ይህ ቦታ የምንኖርበት ምክንያት ግልጽ የሚሆንበት ስፍራ ነው” በመናለትም ኬሪ ስለቤተሰብ ያብራራል።
“ቤተሰብ ማለት ስለፍቅር መጀመሪያ ልምድ የምናገኝበት፣ ለጀመሪያ ጊዜ በሆነ ሰው የምንጎዳበት እንዲሁም ሁሉምን መገፋቶች ፍቅር እንደሚያሸንፍ የምንማርበት ነው፤ ይህ ፍቅርን የምንማርበት ስፍራ ሀይማኖታዊ ጥያቄዎችን ማቅረብ የምንጀምርበት ስፍራም ነው” ይላል ኬሪ።
“ሰዎች በመጨረሻዋ ሰዓት ቤተሰባዊ ፍቅራቸውን በተግባር ሲገልጹ አይቻለው” የሚለው ኬሪ፤ ባል ምንም የመኖር ተስፋ የሌላትን ሚስቱን ፊት በውሃ የራሰ ፎጣ በመጠቀም ሲጸዳዳ፣ ለረጅም ዓመታት በህመም ምክንያት በእናቷ የተረሳች ልጅ በእናቷ አፍ ላይ ተከድና ፍቅሯ ስታካፍል” ተመልክቻለው።
“ሚስት ከሞተው ባሏ ጭንቅላት ስር አንሶላ ስታስተካክል ከመመልከት በላይ ሰዎች ፍቅርን ሲገላለፁ ማየት የትም አይገኝም” ሲልም ኬሪ ይናገራል።
“የመኖርን ትርጉም በመወያየት ማግኘት እልችልም፤ የመኖርን ትርጉም ከመፅሀፍት፣ ከቤተክርስቲያን፣ ከመስጊድ አልያም ከተለያየ የአምልኮ ስፍራ ማግኘት አንችለም” ይላል ኬሪ።
“ፈጣሪ ፍቅር ነው ካልን እና እውነት መሆኑን ካመንበት፤ ስለ ፈጣሪ የምናውቀው ስለ ፍቅር ስናውቅ ነው፤ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው የፍቅር ትምህር ቤት ደግሞ ቤተሰብ ነው” ሲልም ኬሪ ያብራራል።
“አንዳንዴ ሁሉም የቤተሰብ ፍቅር ሙሉ ላይሆን ይችላል፣ ቤተሰብ በተለያዩ ምክንያቶች ተቃርኖ ውስጥ ገብተው ሊጋጩ ይችላሉ፣ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያሳለፉ ሰዎችንም ቢሆን አናግሬያለው” የሚለው ኬሪ፥ በቤተሰባቸው ውስጥ ፍቅርን የማያውቁ ሰዎች እንኳ ፍቅር ማግኘት እንደነበረባቸው ያውቃሉ ብሏል።
“እነዚህሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ምን እንደጎደለ እና ከልጅነታቸው አንስቶ ፍቅርን ማግኘት እንደበረባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ” ብሏል።
“ፍቅር ሙሉ በማይሆንበት ጊዜ ቤተሰብ ይበጣበጣል፤ በዚህ ጊዜም አንድ ነገር መለመድ አለበት የሚለው ኬሪ “ይህም ይቅርታ ማድረግ ነው” ሰዎች በእምነታቸው ውስጥ ይቅርታ ማድረግን መልመድ አለባቸው ሲልም ይናገራል።
“እኛ ለሞት ከተቃረቡ ሰዎች ጋር ስናወራ ስለ ፈጣሪ ለማውራት የሚያግዘንን ስነ መለኮታዊ ቃል አንጠቀምም” ያለው ኬሪ፥ “በሚሞቱበት ጊዜ እርስ በእርስ በመዋደድ እና ይቅርታ በመደራረግ ልጆቻቸውን ስለ ፈጣሪ ካስተማሩት ሰዎች መማር አልብን” ይላል።
ምንጭ፦ cnn.com/health
በሙለታ መንገሻ
No comments:
Post a Comment