Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, December 16, 2016

የሳውዲው ባለሥልጣን የአባይን ግድብ መጎብኘት ውዝግብ አስነሳ





ባለፈው ሳምንት ማጠናቀቂያ ላይ አንድ የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ ባለሥልጣን የኢትዮጵያን አባይ ግድብ ከጎበኙ በኋላ ግብጽና ሳውዲ እየተቆራቆሱ ነው።

አህመድ ካህቲብ የተባሉት የሳውዲ የነገሥታትቱ ፍርድ ቤት አማካሪና የሳውዲ ፈንድ ቦርድ አባል ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ያለችውን አጨቃጫቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መጎብኘታቸው ለግብጽ የተለየ መልዕክት እንዳለው ነው የግብጽ የመገናኛ ሚዲያዎች በመናገር ላይ ያሉት።

ግብጽና ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል ስምምነት በግድቡ ዙሪያ ያላደረጉ ሲሆን ካይሮ ዛሬም ድረስ አይኖቿን ከፍታ እየተከታተለችው እንደሆነና በማንኛውም ሰአት እርምጃ ልትወስድ ትችላለች ነው የሚባለው።

ከጥቂት ወራት ወዲህ በግብጽና በሳውዲ አረቢያ መካከል ከፍተኛ ቅራኔ የተቀሰቀሰ ሲሆን በዚህም ሳቢያ ሁለቱ ሀገራት በርካታ የንግድ ልውውጦቻቸውን ማስቆማቸው ይታወቃል።

አሁን የሳውዲ ባለስልጣናት ወደ ኢትዮጵያ እግር ማብዛታቸው ደግሞ ግብጽን ያስቆጣ ሲሆን በምላሹ ግብጽ በአረብ ሊግ ውስጥ ባለኝ ሚና የሳውዲን መንግስት ፖሊሲዎች ውድቅ አደርጋቸዋለሁ በማለት ዝታለች።

ከዚህም ባሻገር ሳውዲ የግብጽን ሰላም በሚፈታተን መልኩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ጣልቃ ለመግባት የምትሞክር ከሆነ የእጇን ታገኛለች ሲሉ አንድ በካይሮ የሚገኝ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ምሁር ተናግረዋል።

“የአባይ ግድብ ጉዳይ ያለቀ አይደለም። በድንገት ልክ እንደ እሳተ ገሞራ ሊፈነዳ ይችላል።” በማለት የግብጽ ባለሥልጣናት ከረር ያለ ንግግር እየተናገሩ መሆኑን ነው ዘገባዎች የሚያመለክቱት።

No comments:

Post a Comment

wanted officials